የኢትዮጵያን የፋይናንስ ስርዓት ያግዛል የተባለ ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ የተባለ ተቋም ሥራውን በይፋ ጀምሯል።
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ማስፋፊያ (FSD Ethiopia) ለመንግሥት እና ለግሉ ፋይናንስ ዘርፍ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፎችን ይሰጣል ተብሏል።
ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ ተደራሽነት ያላቸው፣ አካታች እና ዘላቂ የሆኑ የፋይናንስ ገበያዎችን በማሳደግ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት የሚሠራ የልማት ኤጀንሲ ነው፡፡
አዲሱ ተቋሙ መንግሥት የአገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት አካታች መሆኑን ለማረጋገጥ እና የዕድገት ግቦችን ለማስተባር የሚያደርጋቸውን ጥረቶች የሚደግፍ ወሳኝ አጋር መሆኑን የኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ ገልጸዋል፡፡
ተቋሙ ለኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ሽግግር አስተዋጽኦ ይኖረዋል ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ፤ መንግስት ቅድሚያ በሚሰጣቸው የፋይናንስ አካታችነት፣ የካፒታል ገበያ ዕድገት እና የተቋማት አቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ በጥምረት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ የተጋረጡ ችግሮችን ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽንና በእንግሊዙ የውጭ የጋራ ብልጽግና አገሮች የልማት ቢሮ በገንዘብ የሚደገፈው ኤፍኤስዲ ኢትዮጵያ፤ የገበያ ሥርዓት ዘዴዎችን በመጠቀም የአገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ለማጠናከር እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡
@tikvahethiopia

#ጥንቃቄ
' ሴንሆን የማር ምርቶች ' እና ' ሮም የገበታ ጨው ' የጤና ብቃት ማረጋገጫ ባለማግኘታቸው ከገበያ እየተሰበሰቡ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን አሳውቋል።
ባለስልጣኑ ፦
➡️ ሮም የገበታ ጨው
➡️ ሴንሆን ማር በሚል ስም የተገለፁ የምርት ውጤቶች ተገቢውን የጤና ብቃት ማረጋገጫ ሳያወጡ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ በመስራታቸውና የምርቶቹ ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ሲመረመር መስፈርቱን የማያሟላና #ለጤና_ጉዳት የሚያመጣ ሆኖ በመገኘቱ ከገበያ እንዲሰበሰቡ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ምርቱን የሚያመርቱት የድርጅት ባለቤቶችም በምርቶቹ ላይ የተሰጣቸው የእርምጃ ውሳኔ ተገቢ መሆኑን አምነው በቀጣይ ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርት አሟልተው አዲስ ምርት አምርተው ወደ ገበያ እንደሚገቡ ከባለስልጣኑ ጋር መግባባት ላይ ደርሰዋል ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን (ኤፍ ቢሲ)

TIKVAH-ETHIOPIA
የብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ጠበቃ አቶ ሸጋው አለበል ምን አሉ ? (ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ከሰጡት ቃል) ፦ " ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች የመኪና መንገድ ዘግተው ከከበቧቸው በኋላ በርከት ብለው አስገድደው ተሽከርካሪ ውስጥ እንዳስገቧቸው ነግረውኛል። ተሽከርካሪ ውስጥ ግባ አልገባም በሚል ኃይል እንደተጠቀሙና መጠነኛ ቢሆንም የእጅ ነገር እንዳረፈባቸውም…
#Update #ችሎት
ፍርድ ቤት በብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለግንቦት 22 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።
የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አመልካች የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍና በተጠሪ ብርጋዴል ጄኔራል ተፈራ ማሞ መካከል በነበረው የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ሀሳብ አዳምጧል።
ፍርድ ቤቱም ፤ ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ውስጥ 10 ቀን በመፍቀድ ለግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ከአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጠበቃ አቶ ሸጋው አለበል ብርጋዴር ጀነራሉ " ህገ መንገስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል " በሚል ፍርድ ቤት መቅረባቸውን አሳውቀዋል።

#ETHIOPIA
የፌዴራል መንግስት የዜጎች ሰላም፣ ደህንነት እና የሀገር ቀጣይነት የሚረጋገጠው የህግ የበላይነት ሲከበር ብቻ ነው ብሏል።
መንግስት ትላንትና ምሽት ባሰራጨው ወቅታዊ መግለጫ ፤ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ጨምሮ በሁሉም ክልሎች የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ኃይሎች ህግን የማስከበር እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን ገልጿል።
በኦሮሚያ እና አጎራባች ክልሎች በህ/ተ/ም/ቤት በአሸባሪነት በተፈረጀው 'ሸኔ' ላይ፣ በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች በ 'አልሸባብ' ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን በመግለፅ እርምጃው ውጤታማ ነው ብሏል።
ሰሞኑን ደግሞ በአማራ ክልል ፦
➙ በህገወጥ ጦር መሳሪያ እና ገንዘብ ዝውውር
➙ በቡድን ተደራጅቶ የግለሰቦችን ሀብትና ንብረት በመዝረፍ በማውደም ላይ የተሰማራ
➙ ነፍስ በማጥፋት ሚጠረጠሩ
➙ አንዱን ህዝብ ከሌላው ጋር በማጋጨት ክልሉ እንዳይረጋጋ በሚያደርጉ ቡድኖች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው ሲል አሳውቋል።
እርምጃው መጠነ ሰፊ ነው ሲልም ገልጿል።
እየተወሰደ ባለ እርምጃ በሁሉም ክልሎች በርካታ ግለሰቦችና ቡድኖች ከነትጥቆቻቸው፣ ከዘረፉት ንብረትና ቀጣይ ሊፈፅሙ ካቀዷቸው ጥፋቶች ካሰፈሩባቸው ሰነዶች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል። ጉዳያቸው በተገቢው ሂደት እየተጣራ መሆኑንና ለፍርድ እየቀረቡ እንደሚገኙ ገልጿል።
መንግስት እየወሰድኩ ነው ባለው እርምጃ ከፍተኛ ህዝብ ድጋፍ እንዳለው ገልፆ ህዝቡ የጥፋት ሰንሰለቶችን ከማጋለጥ አንስቶ አጀንዳውን ለሁከትና ብጥብጥ ማስፈፀሚያ የሚያደርጉትን እየታገለ ነው ብሏል።
በሌላ በኩል በህገወጥ ተግባር ላይ በመሳተፍ፤ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር ሆነ ብለው አቅደዉ በሚሰሩ አካላትና ግለሰቦች እንዲሁም የሚዲያና የጋዜጠኝነት ካባ በደረቡ አካላት ላይ የሚወሰደው የማያዳግም እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

#Sekota📍
በሰቆጣ ከተማ እንቅስቃሴ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ጥብቅ ውሳኔዎች ተላለፉ።
የሰቆጣ ከተማ የጸጥታ ም/ቤት ከከተማው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ውሳኔዎች ያሳለፈ ሲሆን ፤ ከውሳኔዎቹ መካከልም ፦
➡️ የትኛውም ተሽከርካሪ ከተፈቀደለት እና ስምሪት ከተሰጠው ውጭ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11:30 መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
➡️ ማንኛውም ግለሰብ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በኋላ እና ከንጋቱ 11:30 በፊት ከተፈቀደለት አካል ውጭ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
➡️ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ስምሪት ከተፈቀደለት የጸጥታ አካል ውጭ ማንኛውም ግለሰብ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።
➡️ የጸጥታ መዋቅሩ በሚያከናውኗቸው ህግን የማስከበር ስራዎች ተባባሪ የማይሆን ለማደናቀፍ የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል።
➡️ ከከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ አካላት ውጭ የመንግስትም ሆነ የግል ታጣቂዎች በከተማዋ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከልክሏል።
➡️ መጠጥ ቤቶች ፣ ግሮሰሪዎች የትኛውም የመዝናኛ ድርጅት ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በኋላ አገልግሎት መስጠት ተከልክሏል።
➡️ በከተማው በ4ቱ ቀበሌ በህገ ወጥ የመሬት ወረራየተሳተፉ እስከ 12/09/2014 ዓ/ም ድረስ እራሳቸው አፍርሰው እንዲቆዩ ይህን ካልሆነ የጸጥታ መዋቅሩ እርምጃ ይወስዳል።
➡️ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ሃሰተኛ መረጃ ማሰራጨት፣ የግለሰቦችን ሰብዕና የሚያጎድፍ እንዲሁም የጸጥታ መዋቅሩን ስም ማጠልሸት ተከልክለዋል ... የሚሉት ይገኙበታል።
(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

#MoH
#ጨረታው_ተሰርዟል !
30 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የወባ አጎበር ግዢ ጨረታ ተሰረዘ።
የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር 30 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት በኬሚካል የተነከረ የወባ መከላከያ አጎበር ግዢ በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት በኩል ግዢ እንዲፈጸም ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
በዚህም መሰረት ፤ ዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ ወጥቶ ተጫራቾች ቀርበው አሸናፊውን ቢለይም በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ መቅረቡን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ማጣራት በማድረግ ጨረታውን እንዲሰረዝ ማድረጉን አሳውቋል።
የጤና ሚኒስቴር በሌሎች ተቋማት የማጣራት ስራ መሰራቱን እንዲሁም ደግሞ በራሱ ባደረገው የማጣራት ስራ በጨረታ ሂደቱ ላክ የተፈጸመ ህገ-ወጥ ድርጊት እንዳላገኘ ገልጿል።
ነገር ግን " የብቃት ማረጋገጫ " እና " ምዝገባ " ጋር በተያያዘ በግብርና ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በህግ የተሰጠ ነገር ግን የስልጣን መደራረብ የነበረ መሆኑን እና የጨረታ መገምገሚያ መስፈርት ጋር በተያያዘ ቅሬታ ቀርቦ ባለበት ሁኔታ ሂደቱን ከማስቀጠል የፋይናንስ ድጋፍ በሚያደርገው ድርጅት አማካኝነት ግዢው እንዲፈጸም ማድረግ ለሚኒስቴሩ የተሻለ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በመገንዘብ ጨረታው እንዲሰረዝ ተደርጓል፡፡
(ተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ ተያይዟል)

#Mokeypox
ከሰሞኑ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ፖርቱጋል፣ ስፔን እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) ተከስቷል።
ለመሆኑ የበሽታው መገለጫዎች ምንድናቸው ?
የጦጣ ፈንጣጣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ቫይረሱን የሚሸከሙ እንስሳት ባሉበት ሞቃታማ የዝናብ ደኖች አቅራቢያ ይገኛሉ።
የጦጣ ፈንጣጣ የሚጀምረው ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የጡንቻ ሕመም ፣የንፍፊት እብጠት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ድካም ያሳያሉ።
ትኩሳት ከታየ ከ 1 እስከ 3 ቀናት ውስጥ (አንዳንዴ ረዘም ያለ ጊዜ) በሰዉነት ላይ ሽፍታ ይወጣል። ብዙውን ጊዜ ሽፍታዉ ፊት ላይ ጀምሮ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ይስፋፋል። በአጠቃላይ በሽታው ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ይቆያል።
የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) በተወሰነ መልኩ ከፈንጣጣ በሽታ ጋር ተመሳሳይነት አለዉ ። ነገር ግን በፈንጣጣ እና የጦጣ ፈንጣጣ ምልክቶች መካከል ያለው ዋነኛው ልዩነት የጦጣ ፈንጣጣ የንፍፊት እብጠት ሲያመጣ ፈንጣጣ አያመጣም።
ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው ስርጭት የተገደበ ቢሆንም ከሰውነት ፈሳሾች ጋር በመገናኘት ፣ በቆዳ ላይ ወይም በውስጣዊ ንጣፎች ላይ ለምሳሌ በአፍ ወይም በጉሮሮ፣ በመተንፈሻ አካላት ጠብታዎች እና በተበከሉ ነገሮች ላይ ሊተላለፍ ይችላል።
የቀድሞ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአፍሪካ የጦጣ ፈንጣጣ በበሽታው ከተያዙት ከ10 ሰዎች ውስጥ 1 ሰዉ ላይ ሞት እንደሚያደርስ ታይቷል።
(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

#ProfessorSenaitFisseha ዛሬ የጤና ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞችን በቅጥር ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ፕሮጀክት ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች ጋር ተፈራርሟል። ፕሮጀክቱ ዘንድሮ ጀምሮ ለ3 ዓመት ይቆያል። በመጀመሪያ አመት 2,898 ሃኪሞች ወደስራ ለማስገባት ታቅዷል። ለዚሁ ለመጀመሪያው ዓመት ስራ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከፌዴራል እና ከልማት አጋር…
#MoH
➤ በአዲስ አበባ ለ161 ጠቅላላይ ሀኪሞች ቅጥር ወጥቶ ለመቀጠረ ያመለከቱት 2,300 ናቸው።
0⃣ በሶማሌ እና አፋር ክልል ለጠቅላላ ሀኪሞች የስራ ቅጥር ቢወጣም #ምንም አመልካች ጠቅላላ ሀኪም ለማግኘት አልተቻለም።
ጤና ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር 2,898 አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞችን በሃገር አቀፍ ደረጃ በመቅጠር ወደ ስራ ለማሰማራት ከሁሉም ክልል ጤና ቢሮዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በተደረገ ስምምነት ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም አንድ ፕሮጀክት በይፋ መጀመሩ ይታወሳል።
ይህ እኩል በእኩል መዋጮ ፕሮጀክት የሶስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን በመጀመሪያዉ የፕሮጀክት ዓመት ወደ ስራ ለማሰማራት ከታቀደው 2,898 ጠቅላላ ሐኪሞች እና በተጨማሪ ከፕሮጀክቱ በጀት ዉጪ በክልሎች ተጨማሪ በጀት ➙ 961 ሃኪሞች በድምሩ ➙ 3,701 አዳዲስ ምሩቃን ጠቅላላ ሀኪሞች ለመቅጠር ከወራት በፊት በሁሉም የከተማ አስተዳደር እና የክልል ጤና ቢሮዎች የቅጥር ማስታወቂያ ወጥቶ ነበር።
የቅጥር ማስታወቂያ ቢወጣም አመልካች ጠቅላላ ሀኪሞች በሁሉም የቅጥር ማስታወቂያ በወጣባቸው ቦታዎች ላይ #በወጥነት እንዳላመለከቱ በተደረገ ክትትል ታውቋል።
ለአብነት ያህል ፤ አዲስ አበባ ላይ ለ161 የቅጥር መደብ 2,300 ጠቅላላ ሀኪሞች ናቸው ለመቀጠር ያመለከቱት።
ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ በአንዳንድ ክልሎች ለቅጥር ማስታወቂያ ከወጣባቸዉ መደቦች በጣም ባነሰ ቁጥር ያመለከቱ ሲሆን በአንዳንድ ክልሎች ደግሞ ምንም አመልካች አልተገኘም።
ምንም አመልካች ጠቅላላ ሀኪም ያልተገኘው ሶማሌ እና አፋር ክልሎች ላይ ነው።
እስካሁን ድረስ በአጠቃላይ 1,309 ጠቅላላ ሃኪሞች ብቻ የተቀጠሩ ሲሆን ይህም ከሚጠበቅው የቅጥር ብዛት አንፃር 35% ላይ ይገኛል።
ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ጠቅላላ ሃኪሞች በተለይም አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞች የቅጥር ማስታወቂያ በወጣባችው ክልሎች ፦
➡️ አማራ ክልል፣
➡️ አፋር ክልል፣
➡️ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
➡️ ጋምቤላ ክልል፣
➡️ ኦሮሚያ ክልል፣
➡️ ሲዳማ ክልል፣
➡️ ደቡብ ክልል፣
➡️ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እና ሶማሌ ክልል ለ2,392 ጠቅላላ ሃኪሞች ክፍት የሆነ የቅጥር ቦታ እንዳለ አውቀው እድሉን እንዲጠቀሙ ጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል።

#WFP #Ethiopia
የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።
በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል።
ኤድሪያብ ቫን ደር ክናፕ (በዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ) ፥ " ፍጥነቱ አሁን እየጨመረ ስለሆነ በዚህ ወር መጨረሻ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ 30 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ እና የምግብ ሸቀጦች ወደ ትግራይ ይደርሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ። እቅዳችን በሰኔ ወር መጨረሻ 100 ሺህ ቶን ምግብ ለማድረስ ነው " ብለዋል።
በሌላ በኩል ፤ የረድኤት ድርጅቶች አፋርን ጨምሮ በአጎራባችን ክልሎች ቀውሶች እየተባባሱ በመሆናቸው እጅ እያጠራቸው ፤ የእርዳታ ክምችታቸውም እየተመናመነ መሆኑን ጠቁመዋል።
የዩክሬን ጦርነት እና ሌሎችም በዓለም ዙሪያ የታዩት ቀውሶች የለጋሾችን የረድዔት አቅም እየቀነሰው መሆኑ የታገለፀ ሲሆን WFP በሚቀጥለው 6 ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚያስፈልገው የእርዳታ አቅርቦት የ522 ሚሊዮን ዶላር እጥረት እንደሚያጋጥመው ገልጿል።
ከዚህ ውስጥ 220 ሚሊዮን ዶላር ትግራይን ጨምሮ በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል ለሚሰራው የረድኤት ስራ የሚውል ነው።
ኤድሪያብ ቫን ደር ክናፕ ፤ " ያለን ክምችት በጣም በፍጥነት እያለቀ ነው። ስለዚህ ስጋታችን ይህን አውንታዊ ድባብ ፈጥረን እነኚህን መተላለፊያዎች ከፍተን መልሰን ማቆም ሊኖርብን ነው እናም ሁሉ ነገር ከሚያዚያ በፊት ወደነበረው ስፍራ ሊመለስ ነው " ብለዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/VOA-05-21

#ገበያ
በድሮ ጊዜ ገበያ መሄድና እቃ መግዛት በጣም አድካሚ ሥራ ነበር። የሚፈልጉትን እቃ ለማግኘት ረዥም መንገድ መጓዝ፣ ዋጋና ጥራትን ለማወዳደር ከቦታ ወደ ቦታ መንቀሳቀስ፣ የሚፈልጉትን እቃ አለማግኘትና እቃውን ማጓጓዝ ከብዙዎቹ የግብይት ችግሮች ጥቂቶቹ ነበሩ።
ምስጋና ለTechnology ይግባና የKorojo መተግበሪያ ይህን ሁሉ ልፋት አስቀርቶ ካሉበት ቦታ ሆነው የሚፈልጉትን ነገር ሁሉ በስልክዎ ብቻ መገብየት አስችሏል።
የKorojo መተግበሪያን አውርደው በአቅራቢያዎ ለሽያጭ የቀረቡ እቃዎችን ይመልከቱ፣ ይሸምቱ። https://korojo.app/download

" የጦርነት ያክትም " እናታዊ ተማፅኖ
በኢትዮጵያ የእርስ በርስ ጦርነትና በየቦታው የሚነሱ የብሔር ግጭቶች በሴቶች፣ በወጣቶችና በሕፃናት ላይ ስቃይና ሰቆቃን አስከትለዋል፡፡
እናቶች እንባቸውን የሚያብስላቸው አጥተዋል፡፡ ሕፃናት ተሳቀዋል፡፡ ወጣቶች የጦርነት ሰለባ ሆነዋል፡፡
በየአካባቢው በሚነሱ ግጭቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሞተዋል፡፡ ሕፃናት ያለ ወላጅ ቀርተዋል፡፡ በተለይ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ከዓመት በፊት የተነሳው ጦርነት ዛሬም አልሻረም፡፡
የብዙዎችን ሕይወት ነጥቆ፣ አካል ጉዳተኛ አድርጎ፣ ሥነ ልቦና ሰልቦ በተለይም የአካባቢውን ነዋሪዎች ለሰቆቃና ሰቀቀን ዳርጓል፡፡
ዛሬም የጦርነት ነጋሪት እየተጎሰመ ነው፡፡ ይፋዊ ጦርነት ዳግም ይጀመር ይሆን? የሚለው የበርካቶች ሥጋት ሆኗል፡፡ በተለይ የእናቶችን ልብ አርዷል፡፡ በእንባ እንዲታጠቡ ምክንያት ሆኗል፡፡
በጦርነትና ግጭት ምክንያት ለዓመታት ያፈሩት ንብረቶች የወደመባቸው፣ ልጆቻቸውንና ባሎቻቸውን በጦርነት ያጡና ግራ የተጋቡ እናቶች በአግባቡ እንኳን እግዚአብሔር ያፅናችሁ ሳይባሉ፣ የሚገርፋቸው ረሃብና ጉስቁልና ከትከሻቸው ሳይወርድ ሌላ የጦርነት ፍዳ ከፊታቸው ተደቅኗል፡፡
ሆኖም የእናቶችን እንባ የሚያብስ ጠፍቷል፡፡ የታሰረ አንጀታቸውን የሚፈታም ናፍቋቸዋል፡፡ በመሆኑም በኢትዮጵያ የተከሰተው አሰቃቂና አሳዛኝ ምዕራፍ እንዲዘጋ ምኞታቸውና ፍላጎታቸው ነው፡፡
ይህ እንዲሳካ ደግሞ በጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ወገኖች ሁሉ ጆሮ እንዲሰጧቸው፣ ልባቸውን ከፍተው ችግራቸውን እንዲያዳምጧቸው ይማፀናሉ፡፡
ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-05-22-2
Credit : ሪፖርተር

#Mokeypox ከሰሞኑ በዩናይትድ ኪንግደም፣ ፖርቱጋል፣ ስፔን እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) ተከስቷል። ለመሆኑ የበሽታው መገለጫዎች ምንድናቸው ? የጦጣ ፈንጣጣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ቫይረሱን የሚሸከሙ እንስሳት ባሉበት ሞቃታማ የዝናብ ደኖች አቅራቢያ ይገኛሉ። የጦጣ ፈንጣጣ የሚጀምረው ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የጡንቻ ሕመም ፣የንፍፊት…
#update
በትላንትናው እለት እስራኤል እና ስዊዘርላንድ የመጀመሪያዉን የጦጣ ፈንጣጣ (Monkeypox) በሽታ ሪፖርት አድርገዋል።
ባለፉት ሳምንታት በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን፣ በቤልጂየም፣ በጣሊያን፣ በፖርቹጋል፣ በስፔን እና በስዊድን እንዲሁም በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በአውስትራሊያ ከ100 በላይ የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ(Monkeypox) መገኘቱን ተከትሎ ቫይረሱ ሊስፋፋ ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።
ሳይንቲስቶች እንደሚሉት ቫይረሱ በሌለባቸው አገሮች ውስጥ ያለው ወረርሽኝ ያልተለመደ እንዲሁም የአሁኑ የጦጣ ፈንጣጣ(Monkeypox) ዝርያ የሚለየዉ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች ሊሆን እንደሚችል እየተገለፀ ይገኛል።
የዓለም ጤና ድርጅት በበሽታው ከተጠቁ ሀገራት እና ከሌሎች ጋር በመሆን የበሽታ ክትትልን በማስፋት የተጠቁ ሰዎችን ለማግኘት እና ለመደገፍ እንዲሁም በሽታውን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል መመሪያ ለመስጠት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።
የዝንጀሮ በሽታ ከኮቪድ-19 በተለየ ሁኔታ ይተላለፋል። ሆኖም ግን በንክኪ ከሰዉ ወደ ሰዉ ሊተላለፍ ስለሚችል ጥንቃቄ ይሻል ።
እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ገለፃ በሚቀጥሉት ሳምንታት ከተለያዩ የአዉሮፓ ሀገራት የጦጣ ፈንጣጣ በሽታ ሪፖርት ሊኖር እንደሚችል ገልጿል።