TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EOTC

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓመት ሁለት ጊዜያት ከሚካሄዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያት አንዱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የፊታችን ረቡዕ ግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ/ም ከጧቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

ይህ ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ካሉ አህጉረ ስብከት በሚመጡ ብፁዓን አበው ሊቀነ ጳጳሳት ተሰብሳቢነት የሚከናወን እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ሮሮና የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ መልስ !

➡️ " ነዳጅ ጨምሯል በሚል ከታሪፍ ውጪ በቀን ከ10 ብር እስከ 15 ብር ምሽት ላይ ደግሞ 20 ብር ድረስ ጭማሪ እየተደረገብን ነው " - የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች

➡️ " ችግሩን በ90 ቀናት (በ3 ወር) ውስጥ ለመቅረፍ እየሰራሁ ነው " - የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ

ኢፕድ ፡ https://telegra.ph/EPA-05-16

@tikvahethiopia
#USA

መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች በርካቶች በሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ከሰሞኑን ተፈፅመው በነበሩ ጥቃቶች ሰዎች ተገድለዋል ፤ ቆስለዋል።

ሰሞኑን በኒው ዮርክ ግዛት በፋሎ ከተማ አንድ ነጭ ታጣቂ ጥቁሮች የሚበረክቱበት መገበያያ ሥፍራ ገብቶ ጥቃት ፈፅሞ 10 ሰዎችን ገድሏል።

ይኸው ተጠርጣሪ 18 ዓመቱ ሱሆን ፔይተን ጌንድሮን ይባላል ጥቃቱን 320 ኪሎ ሜትር ተጉዞ መጥቶ መፈፀሙን ፖሊስ ገልጿል።

አሜሪካዊው ታጣቂ ጥቁሮችን ብቻ ነጥሎ ጥቃት መፈፀሙ ተነግሯል።

ጥቃቱ #በዘረኝነት መንፈስ የተፈፀመ ሊሆን ይችላል በሚልም ምርመራ እየተደረገበት ነው።

የበፋሎ ከተማ ከንቲባ ባይረን ብራውን ተጠርጣሪው "የቻለውን ያክል #የጥቁር_ነፍስ ለማጥፋት ነው የመጣው" ብለዋል።

ግለሰቡ ከጥቃቱ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን ጥቃቱን አልፈፀምኩም ሲል ቃሉን ሰጥቷል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ምንም እንኳ ምርመራው ባይጠናቀቅም " ይህን ዘረኛ ጥቃት እቃወማለሁ " ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ትላንት እሁድ አንድ የታጠቀ ሰው በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ቤተክርስትያን ውስጥ ተኩስ ከፍቶ አንድ ሰው ገድሎ 5 ሰዎችን አቁስሏል። 4ቱ ሰዎች በፅኑ የቆሰሉ ናቸው።

ተጠርጣሪው እድሜው በስልሳዎቹ ሲሆን አሁን ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኛል።

እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ይህ ደግሞ በመሳሪያዎች እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ያካታታል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

በአቢሲንያ የኢ-ኮሜርስ ክፍያ መንገድ ንግድዎን ያቀላጥፉ!

የድርጅትዎን ድህረ ገፅ ወይም መተግበሪያ ከባንካችን የኢ-ኮሜርስ ክፍያ መንገድ ጋር በማሳለጥ ከመላው ዓለም ክፍያ በቪዛ እና ማስተር ካርድ በቀላሉ መቀበል ይችላሉ::
የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
#Ethiopia

በጦርነት ሳቢያ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ከዓለም ባንክ ጋር መፈፀሙን የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች ማቋቋሚያና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ይውላል የተባለው ይኸው የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የደቡብ ሱዳንና የኤርትራ ካንትሪ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን እና በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ተፈርሟል።

ፕሮጀክቱ በአማራ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚተገበር ሲሆን በጦርነት የተፈናቀሉ ማሕበረሰቦችን ለማቋቋም፣ መሰረታዊ አገልግሎታቸው የተናጋባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ቀጥታና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚስችል ነው፡፡

በተመረጡና በጦርነትና ግጭት ምክንያት በተጎዱ ክልሎች፣ ወረዳዎች በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋልም ተብሏል።

መረጃው የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር / ኢፕድ ነው።

@tikvahethiopia
#DireDawa

#ማሻሻያ

በድሬዳዋ አስተዳደር እሁድ ጠዋት ለትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ እንዲሆን የተወሰነው ውሳኔ ላይ ማሻሻዮች ተደርጎበታል።

በድሬዳዋ አስተዳደር በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ላይ ከጠዋት 12 ሰአት እስከ 4 ሰአት ድረስ በከተማዋ ላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል ።

በዚሁም ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ ከሀይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል ።

በተለይም እድሜያቸው የገፍ እናት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እሁድ ወደ ቤተ-እምነቶች ለመሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በእጅጉ እየተቸገሩ ከመሆናቸው ባለፈ የጤና እክል ያለባቸው አካላትም ረጅም እርቀት በእግር ለመሄድ መቸገራቸውንም የሀይማኖት አባቶቹ በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

ስለሆነም ማሻሻያ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እሁድ ጠዋት በከተማዋ ላይ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዝግ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከነዋሪው ህብረተሰብ እንዲሁም ከሀይማኖት አባቶች የተነሱትን ጥያቄዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት እሁድ ጠዋት ሙሉ ከተማው ለትራንስፖርት ክፍት እንዲሆን መወሰኑን አሳውቀዋል።

ነገር ግን ከኮኔል ድልድይ አንስቶ ከዚራ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ለትራንስፖርት ዝግ እንደሚሆንም ከንቲባው ተናግረዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለሚገኙት መንጌ፣ ከማሽ፣ ፓዌና ወንበራ ሆስፒታሎች ጠቅላላ ሃኪም ይፈለጋል።

በአጠቃላይ በተጠቀሱት ሆስፒታሎች የሚፈለጉት የጠቅላላ ሀኪም ብዛት 11 ሲሆን ሁሉም በቋሚነት የቅጥር ሁኔታ ነው የሚፈለጉት።

ተፈላጊ ችሎታን በሚመለከት ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ በጠቅላላ ሀኪም የተመረቀ/ቀች መሆን ይጠበቅበታል/ታል ፤ የስራ ልምድ 0 አመት ሲሆን ደመወዝ 9,056 ብር ነው።

(ከላይ በተያያዙት ምስሎች ተጨማሪ መረጃ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
" በሰሜን ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ከፍተኛ ስጋት አድሮብኛል " - ነእፓ

ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሌላ ዙር ጦርነት እንይቀሰቀስ ከፍተኛ ስጋት ያደረበት መሆኑን ገለፀ።

ነእፓ ያንዣበበው የጦርነት አደጋ ተቀርፎ በሰሜኑ የሀራችን ክፍል አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም ይረጋጥ ዘንድ ለሚለከታቸው አካላት ሁሉ ጥሪውን አስተላልፏል።

ፓርቲው የተፈጠረውን የጦርነት ስጋት ማስወገድ ይቻል ዘንድ ሀሳቦችን አቅርቧል።

(ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በሰሜን ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ከፍተኛ ስጋት አድሮብኛል " - ነእፓ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ሌላ ዙር ጦርነት እንይቀሰቀስ ከፍተኛ ስጋት ያደረበት መሆኑን ገለፀ። ነእፓ ያንዣበበው የጦርነት አደጋ ተቀርፎ በሰሜኑ የሀራችን ክፍል አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም ይረጋጥ ዘንድ ለሚለከታቸው አካላት ሁሉ ጥሪውን አስተላልፏል። ፓርቲው የተፈጠረውን የጦርነት…
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ፦

(ለሚመለከተው ሁሉ የቀረበ ሀሳብ)

➢ ነእፓ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ክልሎች አንዱ ትግራይ መሆኑና በጦርነቱ የክልሉ ህዝብ ከፍተኛ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት እንደደረሰበት ገልጿል። በክልሉ እና በህዝቡ ላይ የደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ዘላቂ ሰላም በመፍጠር በአፋጣኝ ሊቀየር ይገባል ብሏል። በመሆኑም ትግራይን በማስተዳደር ላይ ያሉ ኃይሎች በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰውን ከፍተኛ ጉዳት ለመቀነስ እና በክልሉ ላይ ያንዣበበውን የጦርነት ስጋት ለመግታት ዳግም ወደ ጦርነት ከሚያመሩ ወታደራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና የሚዲያ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠቡ፣ በአንጻሩ ለሰላም መረጋገጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

➢ በጦርነቱ ምክንያት በትግራይ ከልል የተፈጠረውን ከፍተኛ የምግብ፣ የመድሀኒት እና ሌሎች ቁሳቁሶች ችግር ለመቅረፍ የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ወደ ክልሉ አንዲገባ መፍቀዱን አስታውሷል፤ በዚሁ መሰረት የፌዴራል መንግስቱ ምግብ፣ መድሀኒት እና ሌሎች ሰብአዊ ድጋፎች በበቂ ሁኔታ ወደ ክልሉ እንዲደርስ አስፈላጊውን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

➢ የፌዴራሉ መንግስት ፤ እንዲሁም የአማራ እና የአፋር ክልላዊ መስተዳድሮች እና የትግራይ ኃይሎች የተፈጠረውን ዳግም ወደ ጦርነት የመመለስ አደጋ ለማስወገድ እና ችግሩን በሰላማዊ መንድ ለመፍታት የሚጠበቅባቸውን እንዲያደርጉ ጠይቋል። የፌደራል መንግስት ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እና በድርድር አንዲያልቅ የድርድር ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ በአስቸኳይ ወደ ተግባራዊ እርምጃ አንዲገባም ጠይቋል።

➢ የሀገር ሸማግሌዎች ፤ የፖለቲካ ፓቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፤ ባለሃብቶች፣ የተፈጠረውን የግጭት ስጋት ለማስወድ የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ፤ የሚዲያ ተቋማት እና አክቲቪሰቶች ካለፈው ትምህት በመውሰድ ግጭት ቀስቃሸ የሆኑ መልእከቶችን ከማሰራጨት በመቆጠብ እና ሰላምን በማቀቀን ሀገራችን ዳግም ወደ ጦርነት እንዳትግባ ሙያዊ ግዴታቸውን ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ እንዲወጡ ጠይቋል።

➢ በማንኛውም ሁኔታ ለሚቀሰቀስ የእርስ በእርስ ጦርነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ትልቅ ዋጋ የሚከፍሉት ዜጎች ናቸው - ከአንድ አመት በላይ በሰሜኑ የሀገራችን ከፍል በተካሄደው ጦርነት ትልቅ ዋጋ የከፈሉትም መላው የሀገራችን ህዝቦች ናቸው። በመሆኑም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያንዣበበው የጦርነት ስጋት ተወግዶ ሰላም እንዲረገጥ መላው የሀገራችን ህዝቦች ጦርነትን በማውገዝ እና የሰላምን አርማ ከፍ አድርጎ በማውለብለብ ሰላም እንዲሰፍን የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

#ነእፓ #ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
#USA #Somalia

አሜሪካ ዳግም ወታደሮቿን በሶማሊያ ልታሰማራ ነው።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ወታደሮች እንደገና ወደ ጎረቤታችን ሶማሊያ እንዲሰማሩ ፈቃድ መስጠታቸው ተሰምቷል።

ይህ የጆ ባይደን ውሳኔ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 700 የሚጠጉ ሶማሊያ ውስጥ ሰፍረው የነበሩ ሁሉም ወታደሮቻቸው አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ያደረጉበትን እርምጃ የሚቀለብስ ነው።

አሁን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ምን ያህል ወታደሮች ወደ ሶማሊያ እንደሚያሰማሩ ባይታወቅም፣ ነገር ግን ወታደሮቹ የልዩ ተልዕኮ ኃይል አባላት እና እዚያው ሶማሊያ ውስጥ የሚሰፍሩ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ባይደን የአሜሪካ ሠራዊት አባላት ዳግም ሶማሊያ ውስጥ እንዲሰማሩ ከመፍቀዳቸው ባሻገር፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ተጠርጣሪ የአልሸባብ መሪዎችን ኢላማ ያደረገ ዕቅድ ማጽደቃቸው ተነግሯል።

ይህ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ አሜሪካ ሠራዊቷን ከአፍጋኒስታን ካስወጣች በኋላ ጥያቄ ውስጥ ገብቶ የነበረውን የፀረ ሽብርተኝነት ዘመቻን መልሶ እንዲያንሰራራ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

የአሜሪካ ሰራዊቷን ወደ ሶማሊያ እንደምታሰማራ የተሰማው ትላንት የሶማሊያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተካሂዶ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ማሸነፋቸው ከታወቀ በኃላ ነው።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
የስንዴ ዋጋ ንረት 📈

ከሰሞኑን ሕንድ በሀገሯ የምግብ አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በሚል የስንዴ ምርት ከሀገር እንዳይወጣ እገዳ ጥላለች።

ነገር ግን ይሄ እገዳ በሂደት ላይ የነበሩ የስንዴ ግብይቶችን አይመለከትም።

ሕንድ የስንዴ ምርት ወደ ውጭ እንዳይላክ ማገዷን ተከትሎ ከወዲሁ የስንዴ ዋጋ በአውሮፓ ሪከርድ በሆነ ሁኔታ ጭማሪ አሳይቷል።

የስንዴ ዋጋ ወደ 435 ዩሮ (453 ዶላር) በቶን ከፍ ማለቱ ተነግሯል። ባለፈው አርብ 422 ዩሮ ነበር።

የሰሞኑን የሕንድ ውሳኔ የተለያዩ ሀገራት የኮነኑት ሲሆን ውሳኔው በዓለም የስንዴ ገበያ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ብለዋል።

ሕንድ በስንዴ ሽያጭ ላይ እገዳ መጣሏ በተለይ በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የስንዴ አቅርቦት የተቋረጠባቸው የአፍሪካ እና እስያ ሀገራት ሕንድን እንደ አማራጭ ለመጠቀም አስበው ነበር።

ሕንድ በዓለም ሁለተኛዋ ከፍተኛ የስንዴ አምራች ሀገር ናት።

ሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ውስጥ ከገቡበት የካቲት ወር አንስቶ በተፈጠረው ስጋት ሳቢያ የዓለም የስንዴ ዋጋ 40 በመቶው ጨምሯል።

በዓለም የስንዴ ዋጋ መናር የማዳበሪያ እጥረትም እንደምክንያት ይነሳል።

@tikvahethiopia