TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ምርጫ ፦ የመጀመሪያው ዙር ውጤት : 👉 ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ➡️ 65 👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 59 👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 52 👉 ሀሰን አሊ ኻይሬ ➡️ 47 ⬇️ 👉 ሸሪፍ ሼክ አህመድ ➡️ 39 👉 አብዲራህማን ዋርሳሜ ➡️ 15 👉 አብዱልቃድር ኦሶብል ➡️ 12 👉 አዶው አሊ ጊስ ➡️ 8 328 የፓርላማ አባላት ድምጽ የሰጡ ሲሆን 4 ከፍተኛ…
#Update

በጎረቤታችን ሶማሊያ እየተካሄደ በሚገኘው ምርጫ የ2ኛው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ሂደት አብቅቷል ፤ ይህን ተከትሎ የድምጽ ቆጠራው ይካሄዳል።

#ማስታወሻ ፦ የመጀመሪያው ዙር ውጤት ፦

👉 ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ➡️ 65
👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 59
👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 52
👉 ሀሰን አሊ ኻይሬ ➡️ 47

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በጎረቤታችን ሶማሊያ እየተካሄደ በሚገኘው ምርጫ የ2ኛው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ሂደት አብቅቷል ፤ ይህን ተከትሎ የድምጽ ቆጠራው ይካሄዳል። #ማስታወሻ ፦ የመጀመሪያው ዙር ውጤት ፦ 👉 ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ➡️ 65 👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 59 👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 52 👉 ሀሰን አሊ ኻይሬ ➡️ 47 @tikvahethiopia
#ሶማሊያ

እጅግ ከባድ ፉክክር እየታየበት በሚገኘው የሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ የሁለተኛው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ተጠናቆ የድምፅ ቆጠራው እየተካሄደ ይገኛል።

የ2ኛው ዙር የምርጫ ውጤትን እንዲሁም አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየተከታተል እንልክላችኃለን።

ቀጣዩ የጎረቤታችን ሶማሊያ ፕሬዜዳንት ማን ይሆን ? አብረን የምናየው ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሶማሊያ እጅግ ከባድ ፉክክር እየታየበት በሚገኘው የሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ የሁለተኛው ዙር ድምፅ አሰጣጥ ተጠናቆ የድምፅ ቆጠራው እየተካሄደ ይገኛል። የ2ኛው ዙር የምርጫ ውጤትን እንዲሁም አጠቃላይ የምርጫውን ሂደት ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየተከታተል እንልክላችኃለን። ቀጣዩ የጎረቤታችን ሶማሊያ ፕሬዜዳንት ማን ይሆን ? አብረን የምናየው ይሆናል። @tikvahethiopia
#Update

የሶማሊያ ምርጫ ሁለተኛው ዙር ውጤት ፦

በሁለተኛው ዙር የቀድሞ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ አንደኛ አሁን ሶማሊያን በፕሬዜዳንትነት እየመሩ ያሉት ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል።

እንዲሁም ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ሶስተኛ ፤ ሀሰን አሊ ኻይሬ አራተኛ ሆነው የ2ኛውን ዙር የምርጫ ፉክክር አጠናቀዋል።

የምርጫው ውጤት በቁጥር ፦

👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 110

👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 83

👉 ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ➡️ 68

👉 ሀሰን አሊ ኻይሬ ➡️ 63

በፋርማጆ እና ሀሰን ሼክ መካከል ሶስተኛውና የመጨረሻው ዙር የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ፉክክር ይካሄዳል።

የምርጫውን ሂደት ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሶማሊያ ምርጫ ሁለተኛው ዙር ውጤት ፦ በሁለተኛው ዙር የቀድሞ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ አንደኛ አሁን ሶማሊያን በፕሬዜዳንትነት እየመሩ ያሉት ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል። እንዲሁም ሰዒድ አብዱላሂ ዴኒ ሶስተኛ ፤ ሀሰን አሊ ኻይሬ አራተኛ ሆነው የ2ኛውን ዙር የምርጫ ፉክክር አጠናቀዋል። የምርጫው ውጤት በቁጥር ፦ 👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 110 👉 ሞሀመድ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ በሞቃዲሾ ካራን እና አብዲአዚዝ አካባቢዎች በደስታ ተኩስ እሩምታ እየተናጡ ናቸው።

አካባቢዎቹን በተኩስ እሩምታ እየናጡ የሚገኙት በሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለ3ኛውና የመጨረሻ ዙር የደረሱት የሀሰን ሼክ ሞሐመድ ደጋፊዎች ናቸው ተብሏል።

በመጨረሻውና ሶስተኛው ዙር የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ከወቅቱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ጋር ይፎካከራሉ።

የመጨረሻው የምርጫ ውጤት በሶማሊያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ቀንድ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።

በሶስተኛው ዙር ከሁለት አንዱ 165 ድምፅ ያገኘው ምርጫውን በድል ያጠናቅቃል፤ ቀጣዩ የሶማሊያ ፕሬዜዳንትነትም ይሆናል።

ፈርማጆ አልያም ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ ማን ቀጣዩ የጎረቤት ሀገር ፕሬዝዳንት ይሆናል ? የሶስተኛው ዙር ምርጫ ምላሽ ይሰጠናል።

Credit : Morad

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ ፦ በሞቃዲሾ ካራን እና አብዲአዚዝ አካባቢዎች በደስታ ተኩስ እሩምታ እየተናጡ ናቸው። አካባቢዎቹን በተኩስ እሩምታ እየናጡ የሚገኙት በሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለ3ኛውና የመጨረሻ ዙር የደረሱት የሀሰን ሼክ ሞሐመድ ደጋፊዎች ናቸው ተብሏል። በመጨረሻውና ሶስተኛው ዙር የፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ከወቅቱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ጋር ይፎካከራሉ። የመጨረሻው የምርጫ…
#Update

በሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ የመጨረሻው ዙር የድምፅ አሰጣጥ ተጠናቋል።

በቀጣይ የድምፅ ቆጠራው ይካሄዳል።

በመጨረሻው ዙር ምርጫ ፈርማጆ አልያም ደግሞ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፉክክሩን በድል ያጠናቅቃሉ።

ፈርማጆ ካሸነፉ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሆነው ዳግም ይመረጣሉ ፤ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ካሸነፉ ከፈርማጆ በፊት የነበሩበትን የፕሬዜዳንትነት መንበር በመረከብ ሀገራቸውን ዳግም የመምራት እድልን ያገኛሉ።

#ማስታወሻ ፦ የሁለተኛው ዙር ውጤት ፦

👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 110

👉 ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 83

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በሶማሊያ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ የመጨረሻው ዙር የድምፅ አሰጣጥ ተጠናቋል። በቀጣይ የድምፅ ቆጠራው ይካሄዳል። በመጨረሻው ዙር ምርጫ ፈርማጆ አልያም ደግሞ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፉክክሩን በድል ያጠናቅቃሉ። ፈርማጆ ካሸነፉ የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ሆነው ዳግም ይመረጣሉ ፤ ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ካሸነፉ ከፈርማጆ በፊት የነበሩበትን የፕሬዜዳንትነት መንበር በመረከብ ሀገራቸውን ዳግም የመምራት እድልን ያገኛሉ።…
#ሰበር_ዜና

የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ በድጋሚ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሆነው ተመረጡ።

ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የአሁኑን የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብድላሂ ፈርማጆን እጅግ ፉክክር በተሞላበት ሶስት ዙር የምርጫ ሂደት አሸንፈዋቸዋል።

የመጨረሻ ውጤት ፦

👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 214 ድምፅ
👉 ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 110 ድምፅ

3 ድምፅ ዋጋ ቢስ ሆኗል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰበር_ዜና የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ በድጋሚ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሆነው ተመረጡ። ሀሰን ሼክ ሞሐመድ የአሁኑን የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብድላሂ ፈርማጆን እጅግ ፉክክር በተሞላበት ሶስት ዙር የምርጫ ሂደት አሸንፈዋቸዋል። የመጨረሻ ውጤት ፦ 👉 ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ➡️ 214 ድምፅ 👉 ሞሐመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ➡️ 110 ድምፅ 3 ድምፅ ዋጋ ቢስ ሆኗል። @tikvahethiopia
#BREAKING

የሶማሊያ ፌደራል ፓርላማ ሀሰን ሼክ ሞሀመድን የሀገሪቱ 10ኛ ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።

አዲሱ ፕሬዜዳንት እ.ኤ.አ. ከመስከረም 2012 እስከ የካቲት 16 / 2017 ድረስ በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል።

ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ተሰናባቹን ፕሬዝዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆን በማሸነፍ በሶማሊያ ታሪክ ለሁለት ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡ የመጀመሪያው ሰው መሆን ችለዋል።

ምንጭ፦ የሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የሶማሊያ ፌደራል ፓርላማ ሀሰን ሼክ ሞሀመድን የሀገሪቱ 10ኛ ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል። አዲሱ ፕሬዜዳንት እ.ኤ.አ. ከመስከረም 2012 እስከ የካቲት 16 / 2017 ድረስ በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል። ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ተሰናባቹን ፕሬዝዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆን በማሸነፍ በሶማሊያ ታሪክ ለሁለት ጊዜ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡ የመጀመሪያው ሰው መሆን ችለዋል። ምንጭ፦ የሶማሊያ…
#SOOMAALIYA 🇸🇴

አጫጭር ጉዳዮች ፦

➡️ አዲሱ ሶማሊያ ፕዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ዳግም ፈርማጆን አሸንፈው ፕሬዜዳንት ሆነው ከተመረጡ በኃላ ሀገራቸው ሰላም የሰፈነባትና ከዓለም ጋር ሰላም ያላት ሀገር አደርጋታለሁ ሲሉ ቃል ገብተዋል።

➡️ የቀድሞ ፕሬዜዳንት መሃመድ አብድላሂ ፈርማጆ ለአዲሱ ፕሬዜዳንት እንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል። ፈርማጆ " ወንድሜ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ 10ኛው የሀገራችን ፕሬዜዳንት ሆነው በመመረጦ እንኳን ደስ ያልዎት " ያሉ ሲሆን መላው ሶማሊያውያን ለአዲሱ ፕሬዜዳንት ድጋፋቸውን እንዲሰጡና ለስኬታቸው እንዲፀልዩ ጥሪ አቅርበዋል። ምርጫው በሰላም እንዲጠነቀቅ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

➡️ ለአዲሱ ፕሬዜዳንት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛል። መልዕክታቸው ካስተላለፉት አንዱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ዐቢይ አህመድ ሲሆኑ " ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ በድጋሚ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጥዎ እንኳን ደስ ያለዎት ለማለት እወዳለሁ " ብለዋል። አክለውም " የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራርበን እንደምንሠራ እምነቴ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

➡️ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት አስተላልፏል።

➡️ በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት እንኳን ደስ ያልዎት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በስልጣን ዘመናቸው ስኬትን ተመኝተዋል። በሌላ በኩል የቀድሞው ፕሬዜዳንት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለውን የወንድማማችነት ግንኙነት እንዲጠናከር ላደረጉት አስተዋፆ አመስግነዋቸዋል።

@tikvahethiopia
#Amhara #BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን እና በአማራ ክልል ወረዳዎች እንደቀድሞው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር መግባባት ላይ መደረሱ ተገለፀ።

አራት ዓመታትን ያስቆጠረው የመተከል ዞን የሰላም መደፍረስ ወደ ፍፁም ሰላም እንዲመለስ በመተከል እና በአማራ ክልል አጎራባች ወረዳዎች በትናንትናው ዕለት የምክክር መድረክ ተካሂዷል ።

የጓንጓ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ በሰጡት ቃል የትላንቱን የምክክር መድረክ " ከሁሉም የመተከል ዞን ወረዳዎች እና የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ወረዳዎች የተውጣጡ የእምነት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ አመራሮች እና በአጠቃላይ ከ500 በላይ እንግዶች ተሳትፈውበታል " ብለዋል።

ኃላፊው ፥ ወረዳዎቹ ከዚህ በፊት ብዙ ተፈናቃዮችን ያስተናግዱ እንደነበር እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የችግሩ ገፈጥ ቀማሽ እንደነበሩ ገልፀው ፤ አሁን ላይ የነበረውን ግጭት ወደ ጎን ትተው #ለእርቅ መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ከሁለቱም ወገን እንደቀድሞው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር መግባባት ላይ መደረሱ የተነገረ ሲሆን በቦታው ያሉ ልዩ ሀይሎች፣ መከላከያን ጨምሮ እንዲሁም ጥምር የፌዴራል ፖሊስ ሃይል ሀላፊነት እንዳለባቸው ተነስቷል።

ከዚህ በፊት ሸፍተው በጫካ የነበሩ የጉሙዝ ብሔረሰብ ተወላጆች እጃቸውን በመስጠት ትጥቅ ፈትተው፤ በባህላቸው መሠረት ዕርቅ ፈፅመው ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀላቸውን የጓንጓ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ መኮንን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

Credit : Ethio FM 107.8

@tikvahethiopia