TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Soufflet

60 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ ተደርጎበት የተገነባው " ሱፍሌት ማልት ኢትዮጵያ " የተሰኘ ብቅል አምራች ፋብሪካ ዛሬ ተመረቀ።

የብቅል ፋብሪካው የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ስር በሚተዳደረው በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ነው የተገነባው።

በዛሬው የምረቃ ስነስርዓት ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፤ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዶካን ደበበ ፤ የፋብሪካው አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ፋብሪካው 10 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በአመት 60 ሺህ ቶን ብቅል የማምረት አቅም አለው ተብሏል።

በግብርና ላይ የሚሰራ " ኢንቪቮ ግሩፕ " በተባለ የፈረንሳይ 🇫🇷 ኩባንያ ስር የሚገኘው ሱፍሌት ማልት በ38 ሀገራት የተለያዩ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ፤ 90 የኢንዱስትሪ መንደሮች እና 13 ሺህ ሰራተኞች አሉት።

ኢንቪቮ ግሩፕ በተለያዩ ሀገሪት በገነባቸው 28 የብቅል ማምረቻዎች አማካኝነት በየአመቱ 2.6 ሚሊዮን ቶን ብቅል ለአለም ገበያ እያቀረበ ይገኛል።

መረጃው የኢትዮ ንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለን እንጠብቃለን " - የNATO ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶለተንበርግ ከሩስያ ጋር 1300 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር የምትጋራው ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል የአባልነት ጥያቄዋን የፊታችን እሁድ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። ስውዲንም የአባልነት ጥያቄዋን በተመሳሳይ ቀን ታቀርባለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው።…
#Update

የዩክሬን እና የፊንላንድ ፕሬዜዳንቶች በስልክ ተነጋገሩ።

በዋነኝነት NATOን ለመቀላቀል ባሳየችው ፍላጎት ሳቢያ ከሩስያ ጋር ዛሬም ድረስ መፍትሄ ያላገኘ አስከፊ ጦርነት ውስጥ የገባቸው #ዩክሬን እና NATOን ለመቀላቀል ጥያቄ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ የምትገኘው #ፊንላንድ ፕሬዜዳንቶች በስልክ ተነጋግረዋል።

የፊንላዱ ፕሬዜዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ፤ ከፕሬዜዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ ጋር በነበራቸው ውይይት ሀገራቸው ለዩክሬን ያላትን ፅኑ ድጋፍ በድጋሜ እንዳረጋገጡላቸው ገልፀዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፊንላንድ የNATO አባል ለመሆን እየሄደችበት ስላለው ሂደት እንዳሳወቋቸው ገልፀው የዩክሬኑ ፕሬዜዳንትም ያላቸውን ድጋፍ እንደገለፁለቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

የዩክሬን ፕሬዜዳንት ዜሌንስኪ በበኩላቸው ከፊንላዱ ፕሬዜዳንት ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት ፊንላንድ ለNATO አባልነት ለማመልከት ያላትን ዝግጁነት አድንቀው አመስግነዋል ፤ በተጨማሪ ስለ ዩክሬን የአውሮፓ ውህደት በተመለከተ መነጋገራቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
#GERD🇪🇹

" የታላቁ ህዳሴ ግድብ 3ኛውን የውሃ ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ ነው ፤ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ በትኩረት እየተሰራ ነው " - ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ ፥ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው የምትገኘው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከናወን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሌ/ጀኔራል ደስታ " ሠራዊቱ የተሠጠውን ተልኮ ሌት ተቀን በቁርጠኝነት መፈፀም በመቻሉ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውሉ ግብአቶች በሰላም ተጓጉዘው እንዲደርሱ እና ሰራተኞችም ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ማድረግ ተችሏል " ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ #3ኛውን_የውሃ_ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት ሌ/ጀኔራሉ " የግድቡ ግንባታ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ በትኩረት እየሰራ ነው " ብለዋል።

አክለውም " የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ ዕድገታችንን ለማደናቀፍ #ከሱዳን ሰርገው የሚገቡ ኃይሎችን እየተከታተለ ሴራቸውን እያከሽፈው ይገኛል ፤ በቀጣይም ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ሲቪል አመራሮች ጋር ተቀናጅቶ ግዳጁን በአስተማማኝ ለመወጣት ዝግጁነቱ የላቀ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

#FDRE_Defense_Force🇪🇹

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ከሁለትና ሶስት ወር በላይ ውል አልታደሰልንም፤ ተገቢውም ክፍያ አልተከፈለንም " ያሉ በአዲስ አበባ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ስራ ካቆሙ ቀናት አልፈዋል። እነዚህ አውቶብሶች በከተማይቱ ያለውን የትራንስፖርት ችግር እንዲያቀሉ ድጋፍ እንዲሰጡ ተመድበው ከአመት በላይ አገልግሎት የሰጡ ሲሆን ካለፈው ሚያዚያ 30 ጀምሮ ግን " ከሁለት እና ሶስት ወር በላይ ውል አልታደሰልንም፤ ተገቢ…
#አዲስ_አበባ

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድርስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት #በነባሩ_ክፍያ_ታሪፍ በሙሉ አቅም ሊሰሩ ይገባል ተብሏል።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም ተቋማት፣ የታክሲና ሀይገር ባለንብረቶች ማህበራትና ግለሰቦች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድረስ በነባሩ የክፍያ ታሪፍ መሰረት አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።

ከነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ጋር ተያይዞ አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ የማይሰጡና ህብረተሰቡን ለተለያዩ እንግልቶችና አላስፈላጊ ወጪዎች የሚዳርጉ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ወደ ስራ እንዲገቡ፤ በማይገቡትም ላይ ቢሮው አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ቢሮው ፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታና በህጋዊ መንገድ ለተቋሙ ሳያሳውቁ ከስራ ገበታቸው የወጡት የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡስ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት በገቡት ውል መሰረት መብታቸውን እየጠየቁ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስቧል።

የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ስራቸውን ካቆሙ ቀናት የተቆጠረ ሲሆን ባለንብረቶች በሰጡት ቃል ስራ ያቆሙት ከሁለትና ሶስት ወር በላይ ውል ስላልታደሰለቸው እና ተገቢ ክፍያ እየተከፈላቸው ስላልሆነ መሆኑን መግለፃቸው ይታወሳል።

https://t.iss.one/tikvahethiopia/70126?single

@tikvahethiopia
#UAE

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሼክ ኸሊፋ ቢን ዛይድ አል ናህያን በዛሬው ዕለት ነው በ73 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸው የተሰማው።

በፈረንጆቹ 1948 የተወለዱት ሼክ ኸሊፋ ከ2004 ጀምሮ ሀገራቸውን በፕሬዝዳንትነት በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የፕሬዝዳንቱን ሞት ተከትሎ ለቀጣዮቹ 40 ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ወስናለች፡፡

በቀጣዮቹ ሶስት ቀናት ስራ ዝግ እንደሚሆንም መገለፁን አል ዓይን ኒውስ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በነዳጅ ጭማሪ ምክንያት በአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ይህንን ተከትሎም የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር የተደረገውን የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ማስተካከያ መሠረት በማድረግ የአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንፖርት አገልግሎት ለሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ - አልያም ይህን ይጫኑ 👉https://telegra.ph/Ministry-of-Transport-and-Logistics-05-13

@tikvahethiopia
" አሁን ያለዉ መንግስት በስልጣን የመቀጠል ያለመቀጠል ዕጣ ፋንታዉ የሚወሰነዉ እየፈታ ባለዉ የህዝብ ችግሮች መጠን ነዉ " - የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

አሁን ያለዉ መንግስት በስልጣን የመቀጠል ያለመቀጠል ዕጣ ፋንታዉ የሚወሰነዉ እየፈታ ባለዉ የህዝብ ችግሮች መጠን ነዉ ሲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሃይሌ ተናግረዋል፡፡

መንግስት የመልካም አስተዳደር ችግሮች በሚፈጽሙ የመንግስት ሰራተኞችም ሆነ ሃላፊዎችን ተጠያቂ በማድረጉም ሆነ ባለማድረጉ ፣ ከህዝብ የበለጠ ተጎጂ ስለሆነ ተጥያቂነት ማንበር እንደሚገባው በአፅንኦት ተናግረዋል።

ሃላፊው ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ተገኝተው ለህግ ፣ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ 10 ወራት የስራ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት ፡፡

ዋና ዕንባ ጠባቂው ከቋሚ ኮሚቴ አባላት በኩል ከተጠያቂነት አንጻር ለተነሳላቸዉ ጥያቄ መንግስት በድጋሚ መመረጥ እና በስልጣን ላይ መቆየት የሚፈልግ ከሆነ ጥሰቶችን በሚፈጽሙ ሰራተኞች እና ሃላፊዎች ላይ እርምጃ መዉሰድ እንደሚገባውና ጠቀሜታው ለራሱ እንደሆነ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

በተያያዘም ዶ/ር እንዳለ " እኛ እንደ አንድ ዴሞክራሲ ተቋም እንዲሁም የተከበረዉ ምክርቤት ማድረግ የሚችለዉ ነገር ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል ህግ እና ደንብ እንዲሁም ስርዓት፣ መመሪያ ወይም አዋጆችን ማዉጣት ነዉ፤ ከዛ ባለፈ የወጡ አዋጆችን ወይም ደንቦችን የመፈጸም ሃላፊነት ያለበት ግን የመንግስት አስፈጻሚ አካል ነዉ "ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በነዚህ ምክረሃሳቦች ላይ መግባባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን በማንሳት መግባባት ከሌለ ግን ምክር ቤቱ ብዙ ህግ ቢያወጣ ፤ የዴሞክራሲ ተቋማት ምክረሃሳቦችን ቢሰጡ እና መፈጸም ባይችሉ ፤ መንግስት ተጎጂ እሆናለዉ ብሎ በማሰብ የበለጠ ቢሰራ የተሻለ መሆኑንም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ በወሰዱ ከ200 በላይ የህንፃ ስር ፓርኪን አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ፍተሻ ተካሄደ።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የህንፃ ስር ተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ስፍራውን ለታለመለት አላማ ማዋለቸውን ለመለየት በ214 ህንጻዎች ላይ ፍተሻ አድርጓል።

በተካሄደው ፍተሻ ከ214 ህንፃዎች ውስጥ ፦

👉 86 (40.2%) የህንፃ ስር ፓርኪንግ አገልግሎት ስፍራውን ለታለመለት አላማ ማዋላቸው ተረጋግጧል።

👉 74 (34.6) ህንፃዎች ከታለመለት ዓለማ ውጭ በከፊል ለሌሎች አገልግሎቶች ማዋላቸው ተረጋግጧል።

👉 54ቱ (25.2%) ህንፃዎች ለምን አላማ እንዳዋሉ ማወቅ አልተቻለም ተብሏል።

የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታውን በከፊል ለሌላ አገልግሎት የቀየሩት ፦

👉 ለውኃ ታንከርና ጀነሬተር ማስቀመጫ፣
👉 ለእቃ ማከማቻ፣
👉 ለቢሮ አገልግሎት፣
👉 ለንግድ ስራ፣
👉 ለቆሻሻ ማጠራቀሚያ እና ተረፈ ምርት ማከማቻ እና ለሌሎች ያልታወቁ አገልግሎት የዋሉ መሆናቸው ተረጋግጧል።

በ11ዱም ክ/ ከተማዎች የህንፃ ስር ፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷቸው ለሌላ አገልግሎት ያዋሉ ተቋማት ላ እርምጃ ለመውሰድ ኤጀንሲው እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለን እንጠብቃለን " - የNATO ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶለተንበርግ ከሩስያ ጋር 1300 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር የምትጋራው ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል የአባልነት ጥያቄዋን የፊታችን እሁድ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። ስውዲንም የአባልነት ጥያቄዋን በተመሳሳይ ቀን ታቀርባለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው።…
#NATO

ቱርክ ፤ የፊንላንድ እና ስውዲን NATOን መቀላቀል እንደማትደግፍ አስታወቀች።

የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ፤ ሀገራቸው ስዊድን እና ፊንላንድን NATOን በአባልነት የመቀላቀል እቅድ እንደማትደግፍ ገልፀዋል።

ምንም እንኳን ፕሬዝዳንቱ በግልፅ ባያብራሩም የኖርዲክ ሀገራት የብዙ አሸባሪ ድርጅቶች መገኛ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ዛሬ አንካራ ውስጥ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ኤርዶጋን ፥ " ስዊድን እና ፊንላንድን በሚመለከት ያለውን ሂደት እየተከታተልን ነው ፤ ነገር ግን በጉዳዩ ላይ አዎንታዊ አመለካከት የለንም " ብለዋል።

ከዚህ ቀደም NATO ግሪክን በአባልነት መቀበሉ ስህተት ነበር ሲሉም ተደምጠዋል። " እንደ ቱርክ ተመሳሳይ ስህተቶችን መድገም አንፈልግም " ሲሉ አክለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዝርዝር ባያብራሩም " የስካንዲኔቪያ አገሮች የአሸባሪ ድርጅቶች ማረፊያ ናቸው " ሲሉ የተደመጡት ፕሬዜዳንት ኤርዶጋን ፤ " እንደውም በአንዳንድ ሀገራት የፓርላማ አባላት ናቸው ፤ እኛ ደጋፊ መሆን አንችልም (NATOን የመቀላቀል ጉዳይ) " ብለዋል።

ቱርክ ስውዲንን እና ሌሎች የምዕራብ አውሮፓ ሀገራትን አሸባሪ ስትል የፈረጀቻቸውን እንደ ኩርዲሽ ሚሊሻ ቡድን PKK እና YPG ፤ እንዲሁም በአሜሪካ መቀመጫቸውን ያደረጉትን የፈቱላህ ጉለንን ተከታዮች ይደግፋሉ/ያስተናግዳሉ ስትል በተደጋጋሚ ስትወቅስ ይደመጣል።

አንካራ ጉሌኒስቶች እ.ኤ.አ. በ2016 መፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል ስትል የምትከስ ሲሆን ጉለን እና ደጋፊዎቹ ክሱን አይቀበሉትም።

@tikvahethiopia
#ውበት

ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ?
0911607446
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!              
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 950ብር
የቦርጭ ብቻ(ጉርድ) -650  ብር

ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚቀንስ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።

ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ @wibet1
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ ቤዛ ህንፃ 2nd floor # webet