TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አብን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ከድርጅት ህገ-ደንብ እና አሰራር ውጭ በመሆን አፍራሽ ድርጊቶችንና የዲሲፕሊን ጥሰቶችን ፈፅመዋል ባላቸው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ላይ የእርምት ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል። የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ29/8/2014 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ነው በፓርቲው መዋቅር የተለያዩ የሃላፊነት እርከኖች ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ የዲሲፕሊን እና ድርጅታዊ መርህ ጥሰቶችን…
" ...መሰል ውሳኔዎችን ለመወሰን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሥልጣን የለውም " - አቶ ክርስቲያን ታደለ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ከድርጅት ህገደንብ እና አሰራር ውጭ በመሆን አፍራሽ ድርጊቶችን እና የዲሲፕሊን ጥሰቶችን ፈፅመዋል ባላቸው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ላይ የእርምት ውሳኔ ማስለፉ ይታወቃል።

ፓርቲው ይህን የእርምት ውሳኔ ማሳለፉን የሚገልፅ ደብዳቤም በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አሰራጭቷል።

ውሳኔ ከተላለፈባቸው አመራሮች አንዱ የንቅናቄው ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ ሲሆኑ ፓርቲው " የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ " እንዲሰጣቸው ውሳኔ አሳልፏል አቶ ክርስቲያን ይህን የተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ክርስቲያን ፤ " በአብን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስም የወጣውን መግለጫ ያየሁት ዘግይቼ ነው " ያሉ ሲሆን " ፍሬ ነገሩ ልክ ይሁንም፥ አይሁንም መሰል ውሳኔዎችን ለመወሰን ግን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሥልጣን የሌለው መሆኑን ለንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊዎች መግለጽ እፈልጋለሁ " ብለዋል።

አክለውም " ንቅናቄው የተመሰረተባቸውን ሕዝባዊና አገራዊ ጥያቄዎች ከግብ እንዲያደርስ ሁላችንም በጎ ሚና እንድንጫዎት አደራ ማለት እፈልጋለሁ " ሲሉ ገልፀዋል።

አብን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ዛሬ ይፋ ባደረገው የእርምት ውሳኔ ለአቶ ክርስቲያን ታደለ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከመስጠት ባለፈ 10 የመካከለኛ አመራሮች እና አባላትን ከድርጅቱ አግዷል፤ ለሁለት የቋሚ ኮሚቴዎች አባላት ደግሞ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትምህርት ሚኒስቴርና የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ! ከብሄራዊ ፈተና አስተዳደር ጋር በተያያዘ ባለፉት አመታት የታዩ ችግሮች ለመቅረፍ ከፈተና ዝግጅት ጀምሮ እስከ ውጤት ማሳወቅ ያሉትን ተግባራት በጥቃቄ እንዲከናወኑ ፦ 1ኛ. ፈተናዎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደግፎ መስጠት የሚቻልበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ፤ ይህ እውን እስኪሆን ድረስ የሚሰጡ…
" ተማሪዎቹ በድጋሚ እንዲፈተኑ ተወስኗል "

በኮንሶ ዞን በፀጥታ ችግር የ2013 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በድጋሜ እንዲፈተኑ መወሰኑን የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታውቋል።

መምሪያው ይህን ያሳወቀው የክልሉን ትምህርት ቢሮ ዋቢ በማድረግ ነው።

ተማሪዎቹ ድጋሜ እንዲፈተኑ ውሳኔ የተላለፈው ለኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በቀረበ ቅሬታ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች ከወዲሁ ለፈተናው እንዲዘጋጁ ጥሪ ቀርቧል።

በኮንሶ ዞን አከባቢ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በፀጥታ ችግር ምክንያት ተማሪዎች በሙሉ ቀልባቸው አልተማሩም።

የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተፈተኑ 824 ተማሪዎች መካከል 51 ተማሪዎች ብቻ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ሲሆን፤ 773ቱ ወደ ዩኒቨርሲቲ ማለፍ አልቻሉም።

እኚሁ 773 ተማሪዎች ናቸው በድጋሜ የ12ኛ ክፍል ፈተና እንዲወስዱ ዕድል የተመቻቸላቸው።

ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ ክልሎች በፀጥታ ችግር ውስጥ ሆነው ፈተና ተፈትነው ውጤት ያልመጣላቸው ተማሪዎች ከ2014 ተፈታኞች ጋር በድጋሜ እንዲፈቱን ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 20/2015 ዓ.ም በኃላ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃውን ከኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በጋምቤላ ክልል የስራ ሰዓት ወደነበረበት ተመልሷል።

በክልሉ የሙቀት መጠኑ እየቀነሰ መምጣቱን ተከትሎ የመንግስት የስራ ሰዓት ወደ መደበኛ የስራ ሰዓት መቀየሩን የክልሉ መንግስት ዛሬ አሳውቋል።

ባለፉት 3 ወራት ፦

👉 ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ከ30 የነበረው ከ1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ከ30

👉 ከሰዓት በኋላ ከ10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት ከ30 የነበረው ከ9 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ከ30 ሆኖ በቀድሞው የመደበኛ የስራ ሰዓት ተቀይቅሯል።

የመንግስት ሰራተኞች በተጠቀሰው ጊዜ ወደ ቢሮ በመግባት የተለመደ ሥራችሁን አከናውኑ ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ5G ኔትዎርክ በኢትዮጵያ ፦ ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) ኔትወርክን በሃገር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙከራ አገልግሎት ለማስጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ካፒታል ጋዜጣ በድረገፁ አስነብቧል። የሙከራ አገልግሎቱ በመጪው ሳምንት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው ያስረዳል። ኩባንያው ፕሮጀክቱን ከቻይናው የሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በተገኘ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ነው ተግባራዊ እንደሚያደርግ የተነገረው።…
#AddisAbaba📍

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛው ትውልድ(5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት መጀመሩን ዛሬ አስታውቋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ኩባንያው ላለፉት ወራት ያደረገውን ሙከራ አጠናቆ የ5ኛ ትውልድ ሞባይል ኔትዎርክ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡

አገልግሎቱን በመዲናችን ውስን ቦታዎች ማግኘት እንደሚቻልም አሳውቀዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎቱን ማብሰሪያ መድረክ ያከናውነው በሸራተን ሲሆን ፤ በዚሁ በሸራተን አካባቢ በአሁኑ ሰዓት 5G አገልግሎት በይፋ ጀምሯል።

በተጨማሪ በዩኒቲ ፓርክ፣ አንድነት ፓርክ፣ ቸርችል ጎዳና እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም መስሪያ ቤት አካባቢዎች የ5G አገልግሎት ተግባራዊ ሆኗል።

ኔትዎርኩ በቻይናው ሑዋዌ ኩባንያ አማከኝነት ነው የተዘረጋው።

እጅግ ፈጣን የሚባለውን የ5ኛ ትውልድ የኔትወርክ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ደንበኞች ከአገልግሎቱ ጋር የተስማማ የእጅ ስልክ እና የ5G ኔትወርክን የሚያቀርብ መሠረተ-ልማት ያስፈልጋቸዋል።

መረጀው ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢዜአ፣ ከኢትዮ ኤፍ ኤም እና ከጀርመን ሬድዮ የተውጣጣ ነው።

@tikvahethiopia
#EthioTelecom

በአሁን ሰዓት ከኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ጋር ከተገናኙ 75.8 ሚሊዮን ኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች መካከል 110 ሺህ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ በውስን ቦታዎች የተጀመረውን 5G አገልግሎት ማስጠቀም የሚያስችሉት።

13 ሚሊዮን የሚሆኑት LTE መጠቀም የሚያስችሉ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዛሬ ምሽት ወደ ቤቱ ተመለሰ።

ጋዜጠኛው ባለፉት ቀናት የት እንዳለ ሳይታወቅ መቆየቱ ቤተሰቦቹን ጭንቀት ላይ ጥሎ እንደነበር እንዲሁም የተለያዩ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችም ሁኔታው እንደሚያሳባቸው ሲገልፁ እንደነበር ይታወሳል።

በርካቶችም በጋዜጠኛው አድራሻ መጥፋት ሀሳብ ላይ ነበሩ።

ዛሬ ምሽት ጋዜጠኛው በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ አጭር መልዕክት ፅፏል።

በዚህም ከኢድ አልፈጥር አንድ ቀን ቀደም ብሎ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት በአጥር ዘለው አፍነው እንደወሰዱት ፅፏል።

አክሎም " ዛሬ ከምሽቱ 3:00 ላይ አይዬን በጨርቅ አስረው ቤቴ በር ላይ ጥለውኝ ሄደዋል " ብሏል።

ጋዜጠኛው እስከ ዛሬ የት እንዳቆየ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የገለፀ ሲሆን በጤናው ላይ አንዳች የደረሰ ነገር እንደሌለ አሳውቋል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዛሬ ወደ ቤት መመለሱን ተከትሎ ባሰራጨው መልዕክት አፍነው ወስደውት እንደነበር ስለገለፃቸው አካላት ተቋማቱ የሚሰጡት ማብራሪያ ካለ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።

@tikvahethiopia
#Repost

ግንቦት እና ኢትዮጵያ !

በቀረበኝ ኖሮ ለምን በላሁት
አያበቅለው የለ ሰኔና ግንቦት
የግንቦቱ ባሰ አረም በዝቶበት

ግንቦት ወር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ብዙ ክስተቶችን ያስተናገደች ታሪካዊ ወር ናት።

ኢትዮጵያ በዚህ ግንቦት ወር ታዋቂ ልጆቿን ወልዳለች ፤ ወደማይቀረው ዓለምም ሸኝታለች ፤ መሪዎቿን ወደ ስልጣን አምጥታለች ፤ ከስልጣናቸው ሽራለች፤ አስከፊ ጦርነቶችን አስተናግዳለች፤ ከእነዚህ ታሪካዊ ክስተቶች በተጨማሪ ግንቦት ያልተለመዱ ክስተቶች የተስተናገዱበት ወርም ነው።

አሁን አሁን ላይ እየቀረ መጥቶ ነው እንጂ በዚህ ወር ከተፈጠሩ መጥፎ አጋጣሚዎች ጋር በማያያዝ ወሩን በገደቢስነት በመፈረጅ በተለይ በመሃል ሃገር ጋብቻ አይፈፀምም ነበር።

በግንቦት ወር የተመዘገቡ አብየት ክስተቶች እጅግ በጥቂቱ ፦

➨ የታላቋ አክሱም ንጉስ አፄ ካሌብ ያረፉት በግንቦት ወር ነው። አፄ ካሌብ ከአክሱም እና አካባቢው አልፈው ቀይ ባህር ተሻግረው የደ/ አረቢያ ህዝቦችን ያስገበሩ ንጉስ ነበሩ።

➨ እቴጌ ምንትዋብ ያረፉት በግንቦት ወር ነው። እቴጌ ምንትዋብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሳ እንስቶች መካከል አንዷ ነበሩ።

➨ የውጫሌ ውል የተፈረመው በግንቦት ወር ነው።

➨ ለንግስና ያልበቁት ልጅ እያሱ ምኒልክ የተሾሙት በዚህ ወር ነው።

➨ ልዑል መኮንን ኃይለስላሴ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ህይወታቸው ያለፈው ግንቦት 1949 ነበር።

➨ ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ህይወታቸው ያለፈው ግንቦት 29/1984 ነበር።

➨ ሀገራችን በታርክ በግንቦት ወር አስከፊ ጦርነቶችን አስተናግዳለች።

➨ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የተወለዱት ግንቦት 19 ነው።

➨ በቀድሞ ፕሬዜዳንት ኮ/ል መንግስቱ ኃለማርያም ላይ መፈንቅለ መንግስት የተሞከረው ግንቦት 8 ነበር።

➨ በኮ/ሌ መንግስቱ ኃ/ማርያም ላይ የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት በአዲስ አበባ ግንቦት 8 ከሸፈ፥አስመራ ላይ ግንቦት 9/1981 ከሸፈ።

➨ በኮ/ሌ መንግስቱ ኃይለማርያም ላይ በተሞከረው መፈንቅለ መንግስት አ/አ ላይ ሙከራውን ያደረጉት ጄነራሎች ራሳቸውን ገደሉ፣ ተገደሉ፣ ታሰሩ። አስመራ ላይ ግንቦት 9 የ102ኛ አየር ወለድ ክ/ጦር በምስራቅ እና በሰሜን የገጠማትን ጦርነት ሲመሩ የኖሩት ጄነራሎች ተገደሉ።

➨ ኮ/ሌ መንግስቱ ሀገር ጥለው የወጡት ግንቦት 13/1983 ነበር።

➨ 12 ከፍተኛ ጄነራሎች የተገደሉት ግንቦት 11/1982 ነበር።

➨ ኢህአዴግ አዲስ አበባን የተቆጣጠረው ግንቦት 20/1983 ነው።

➨ የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የተወለዱት ግንቦት 1 ነው።

➨ በኢትዮጵያ ታሪካዊ ነው የተባለው ምርጫ የተካሄደው ግንቦት 7 ቀን 1997 ነው። በዚህ መነሻ በርካታ ወጣቶች በአደባባይ ተረሽነዋል ፥ ሺዎች ታስረዋል ፤ የተቃዋሚ አመራሮች ዘብጥያ ተጥለዋል።

➨ የደረግ ከፍተኛ አመራሮች ሞት የተፈረደባቸው ግንቦት 18 ቀን 1999 ነው።

➨ ሞት የተፈረደባቸው የደርግ አመራሮች ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ የተቀየረላቸው ግንቦት 2003 ነው።

ምንጭ ፦ ሌተናል ኮሎኔል ፍስሃ ደስታ (አብዮቱና ትዝታዬ)፣ ታሪከ ነገስት-በደሴ ቀለብ ፣ፀሀፊ ተክለፃዲቅ መኩሪያ፣ ኢፕድ ድረገፅ፣ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#iጤና

• በስትሮክ፣ በአደጋ፣ እና በሌሎች በሽታዎች ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለተፈጠረ አለመንቀሳቀስ (Paralysis)
• እድሜ በመግፋት ለሚፈጠሩ ጉድለቶች እንደ አልዛይመርስ፤ ዲሜንሻ
• ከተለያዩ ቀዶ ጥገናዎች ለማገገም
• በሙሉ (Coma) ወይም በከፊል የንቃተ ህሊና መቀነስ ላላቸው ታካሚዎች እንክብካቤ
• ለካንሰር እና ተከታታይ የህክምና ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች

👉 በ0901222233 ይደውሉልን
Telegram | FB | IG | Twitter 🌍
🏥 አድራሻችን ጀሞ ከ ጀሞ ሞል 200m ገባ ብሎ፡፡
" ነዳጅ ማደያዎች በኃላፊነት እና በስነ ምግባር ሊሰሩ ይገባል "

ዜጎች ነዳጅ ፍለጋ በየቀኑ ረጅም ሰዓታት በሰልፍ እያሳለፉ ይገኛሉ ችግሩ በአዲስ አበባ ከተማ እና በሌሌችም ከተሞች ይታያል ፤ ላለፉት ወራትም ሲታይ ቆይቷል።

ነዳጅ ለመቅዳት ሰዉ አምስት ወይም ከዚያ በላይ ሰዓታት ወረፋ እየጠበቀ በጎን ሌሎች ስራዎች በትውውቅ እና በገንዘብ እንደሚሰሩ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል።

ይህ እጅግ ያልተገባ እና እርስ በእርስ መተዛዘንና መተሳሰብን እየጎዳ ያለ ድርጊት ከመሆኑም በላይ ሰዎችን ክፉኛ እየተስተጓጎለ በስራቸውም ላይም ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ ይገኛል።

ነዳጅ ማደያዎች እና ነዳጅ ማደያ ቦታዎች የሚሰሩ ሁሉ ስራቸውን በአግባቡ ኃላፊነት እና ስነምግባር በተሞላበት መልኩ ሊያከናውኑ እንደሚገባ ችግሩን የተመለከቱ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል።

@tikvahethiopiaBOT
#ጥቆማ

ለሰሜን ወሎ ዞንና አጎራባች ማህበረሰብ ክፍሎች ፦

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሀረር ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር እንዲሁም ከአንገት በላይ እባጭ ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች #በነፃ_የህክምና አገልግሎት ለመስጠት አቅዷል።

በሆስፒታሉ ቢሮ ቁጥር 12 ላይ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ 0333311680 / 0920218203 በመደወል ከ1/09/2014 ዓ/ም ጀምሮ በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ መሆን ይቻላል።

(ላልሰሙትም አሰሙ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Shell ሼል ከሩስያ ድፍድፍ ነዳጅ አልገዛም አለ። ሼል በሳምንቱ መገባደጃ ላይ ከሩስያ በርካሽ ድፍድፍ ነዳጅ ገዝቶ የነበረ ሲሆን ለዚህም ይቅርታ በመጠየቅ ፤ ከሩሲያ ነዳጅ እና ጋዝ መግዛቱን ለማቆም ቃል ገብቷል ተብሏል። በተጨማሪ ሼል በሀገሪቱ ያሉትን ሁሉንም የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚዘጋና በሀገሪቱ ውስጥ አሁን ላይ እየሰራ ያላቸውን ሁሉንም ስራዎች እንደሚያቆም አሳውቋል። ሼል በሳምንቱ…
#የሼል_ትርፍ

በዓለማችን የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ ጣራ በነካበት በዚህ ወቅት " ሼል " የተሰኘው ግዙፉ የኢነርጂ ኩባንያ ከፍተኛ የሆነ ትርፍ ማስመዝገቡ ተሰምቷል።

ሼል በዓመቱ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት 9.13 ቢሊዮን ዶላር ያገኘ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ካገኘው 3.2 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ በሦስት እጥፍ ገደማ ያደገ ነው።

ነገር ግን ድርጅቱ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከሩሲያ የነዳጅ እና ጋዝ ገበያ መውጣቱ 3.9 ቢሊዮን ዶላር እንዲያጣ እንዳደረገው አሳውቋል።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ተዳክሞ የነበረው የዓለም ኢኮኖሚ ማንሰራራት ሲጀምር የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ እየጨመረ ቢመጣም የቅርቡ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት የነዳጅ እና ጋዝ ዋጋ ጣራ እንዲነካ አድርጎታል።

የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋ መጨመር ለኢነርጂ ኩባንያዎች ከፍተኛ ትርፍ እንዲያገኙ እያደረጋቸው ይገኛል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተማሪዎቹ በድጋሚ እንዲፈተኑ ተወስኗል " በኮንሶ ዞን በፀጥታ ችግር የ2013 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በድጋሜ እንዲፈተኑ መወሰኑን የኮንሶ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታውቋል። መምሪያው ይህን ያሳወቀው የክልሉን ትምህርት ቢሮ ዋቢ በማድረግ ነው። ተማሪዎቹ ድጋሜ እንዲፈተኑ ውሳኔ የተላለፈው ለኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በቀረበ ቅሬታ ሲሆን…
#Konso #Ale #Amaro

2023 ተማሪዎች የድጋሜ ፈተና ይወስዳሉ።

በኮንሶ ዞን ፣ በአማሮ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ኧሌ ልዩ ወረዳ በፀጥታ ችግር ውስጥ ሆነው የ2013 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ውጤት ያልመጣላቸው ተማሪዎች ከ2014 ተፈታኞች ጋር ድጋሚ ፈተና እንዲወስዱ ተወስኖላቸዋል።

ትላንትና የኮንሶ ዞን 773 ተማሪዎች ከ5 ትምህርት ቤቶች የድጋሜ ፈተና እንዲወስዱ መወሰኑን መግለፁን የሚመለከት መረጃ ልከንላችሁ ነበር።

ከኮንሶ ዞን ባለፈ በአማሮ ልዩ ወረዳ 7 ትምህርት ቤቶች 1171 ተማሪዎች በኧሌ ልዩ ወረዳ በ3 ትምህርት ቤቶች 79 ተማሪዎች የድጋሜ ፈተና እንዲወስዱ ተወስኖላቸዋል።

በአጠቃላይ በአንድ ዞን እና ሁለት ልዩ ወረዳዎች የድጋሜ ፈተናውን የሚወስዱት 2,023 ተማሪዎች ናቸው።

እነዚህ ተማሪዎች በአካባቢያቸው ላይ የፀጥታ ችግር በተደጋጋሚ እየተከሰተ ከፍተኛ በሆነ የስነ ልቦና ጫና ውስጥ ሆነው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የተፈተኑ ሲሆን ነገር ግን ወደ ዩኒቨርሲቲ ሊያስገባቸው የሚችል ውጤት ሊያመጡ አልቻሉም።

@tikvahethiopia
#Huawei #AAU

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና ሁዋዌ ሃንድሼኪንግ ፎረም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ትናንት ተከፍቷል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያዘጋጀው የምርምርና ፌር ሳምንት Research and Fairs Week በትናትናው ዕለት ተጀምሯል።

በዚህ። የተለያዩ ኤግዚቢሽኖች ተከፍተው ፤ በአዲስ ዩኒቨርስቲ በምርምር ዘርፍ የተሰሩ የምርምር ስራዎች ለእይታ ቀርበው ተጎብኝተዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በአይሲቲ መሰረተልማት እና ስማርት መጠቀሚያዎችን በማምረት ቀዳሚ የሆነው ሁዋዌ በዩኒቨርስቲው በመገኘት የ Handshaking Forum ጆብ ፌር ከፍቷል ፥ ይህ ዛሬ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ሁዋዌ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር Handshaking Forum በሚል የተመራቂ ተማሪዎችን ሲቪ ሲያሰባስብ ለ2ኛ ጊዜው ሲሆን በዚህ ፎረም አቅም ያላቸው ተመራቂ ተማሪዎችን ከአሰሪዎች ጋር ለማገናኘት ይሰራል።

ከሁዋዌ ባገኘነው መረጃ መሰረት ሁዋዌ አዲስ ለተመረቁ ምሩቃን ያዘጋጀው የኢንተርንሺፕ ፕሮግራም ሲኖረው በዚህም ለ3 ወራት በሁዋዌ ኢትዮጵያ ቢሮ እንዲሰለጥኑ ካደረገ በኃላ የተሻለ አፈጻጸም ያሰስመዘገቡትን ይቀጥራል።

ባለፈው ዓመት ለ250 ተማሪዎች የኢንተርንሺፕ እድል የፈጠረ ሲሆን ከነዚያም መካከል 200 ያህሉ በድርጅቱ ተቀጥረዋል። በዚህ ዓመት 300 ያህል የመቀበል እቅድ ሲኖረው እስካሁን ከ90 በላይ ተቀብሏል።

@tikvahethiopia