TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" አባታዊ የሰላም ጥሪ "

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበር ተክለሃይማኖት ሰሞኑን በተለይ በጎንደርና አካባቢው ፤ በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን አካባቢ በተፈጠረው አለመረጋጋት እና የሰው ህይወት መውደቅ እጅግ ማዘናቸውን ገልፀዋል።

አባታዊ የሰላም ጥሪም አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም ፦

" ከእልቂት የሚያተርፈው ፀላዔ ሠናያት የሆነው ዲያብሎስ ብቻ ነው።

እሳትን በእሳት ማጥፋት አይቻልምና ስንናገር ስንራመድ ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲኖረን በብርቱ እማፀናለሁ።

ይህም ጠብና እልቂት የሞራል ውድቀት ፣ የኃጢያት አውራ ተብሎ ከመመዝገብ ውጭ ስምና ታሪክ አይሆነንምና ሁላችንም ለሰላም እንድንቆም እለምናለሁ።

የእኛን ድጋፍ የሚፈልጉ በሰሜን ፣ በምስራቅ ፣ በምዕራብ ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ብዙ ወገኖች ሳሉ ሌላ ችግር በመጨመር አገርን ወደ አዘቅት መስደድ ፍፁም የተወገዘ ግብር ነው።

በሞቱት ወገኖች እጅግ አዝናለሁ።

አብያተ እምነትም የሰው ልጆች የምስጋና የነፍስ መማፀኛ ናቸው እንጂ የእሳት ግብር የሚሰጣቸው አይደሉምና ይህንን ድርጊት ተገቢ አለመሆኑን እገልፃለሁ።

እርስ በእርስ በመጣላት ላይ ሀገርም እያፈረስን ነው። ተጣልቶ ለመታረቅም ሀገር ያስፈልገናልና ሀገራችንን ልንሳሳላት ይገባናል።

ሁላችንም #ለሰላም_እንድንቆም ፤ መንግስትም ከሰው እና ከእግዚአብሔር የተቀበለውን አደራ ፈጥኖ እንዲያስፈፅም ፣ የሃይማኖት አባቶችም ትውልድን የማነጽ ተግባራቸውን በርትተው እንዲቀጥሉ አደራ ጭምር ጠይቃለሁ። " ብለዋል።

(ተጨማሪ ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
#AddisAbaba 🪪

" ላልተወሰነ ጊዜ አዲስ መታወቂያ መስጠት አቁመናል " - የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ

የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ላልተወሰነ ጊዜ " አዲስ መታወቂያ " የመስጠት አገልግሎት ማቆሙን አስታውቋል።

ኤጀንሲው የመታወቂያ ፣ የልደት ፣ የጋብቻና የሞት ማስረጃዎችን ይመዘግባል ፤ ዜጎች በሚፈልጉበት ወቅትም አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡

በአገልግሎት አሰጣቱ ውስጥ በተለይ የመታወቂያ አገልግሎቱ ላይ በተቋሙ ውስጥ እና ከተቋሙ ውጭ ባሉ ሃሰተኛ ማስረጃን በሚያድሉ ግለሰቦች የተነሳ ለማይገባቸው ሰዎች መታወቂያ አላግባብ እየተሰጠ መሆኑን ኤጀንሲው ገልጿል።

ይህን ህገ ወጥ የሆነ ድርጊት ሲፈጽሙ የተያዙ ግለሰቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል።

የነዋሪነት መታወቂያ ለማግኘት ሲባል ህገወጥነት እየተባባሰ በመምጣቱ ችግሩን በሚገባ ለማጥራት እንዲቻል በከተማ አስተዳደሩ ደረጃ በተላለፈ ውሳኔ መሰረት አዲስ መታወቂያ እንዳይሰጥ ላልተወሰነ ጊዜ መታገዱን ኤጀንሲው ገልጿል።

የመታወቂያ እድሳትም ሆነ ሌሎች የወሳኝ ኩነት አገልግሎቶች ባሉበት ይቀጥላሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ቲቪ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ዛሬ ሁለተኛው " ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር " ስነስርዓት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ስነስዓቱ ላይ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ምእመን ተገኝቶ ነበር። @tikvahethiopia
ሼህ ሱልጣን አማን ፦

" እስላም ሰላም ነው ፤ እስላም ሰላም ነው ፤ እስላም ሰላም ነው ፤ እስላም ስርዓት ነው።

እኛ ሙስሊሞች ነን ፤ ሰላም ፈላጊዎች ነን፤ ሀገራችን ሰላም ፣ ህዝባችን ሰላም ሁሉም ሰላም እንዲሆን እንፈልጋለን።

ሰላማችንን የሚያደፈርስ አካል በህግ እንቃወማለን፣ ማንም ከማንም አይበልጥም፤ ሁላችን እኩል ነን፤ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ለዚህች ሀገር ዜጋ ነው። ሁላችንም እኩል መብት አለን።

የተሰውት ወንድሞቻችን ፤ በጎንደር በደባርቅ አላህ ይማራቸው፤ ለጀነት አላህ ያርጋቸው፤ የታመሙትን አላህ ያሽራቸው።

እኛ ይሄን በወንድሞቻችን ላይ ያደረሰው አክራሪ ቡድን ላይ ከመንግስት ግልፅ የሆነ፣ ፍትሃዊ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድልን እንጠይቃለን።

እኛ ለወንድሞቻችን፣ ተቃውሞ ወይም ድምፃችንን ስናሰማ በስርዓት መሆን አለበት። ሌላውን እንዳንጎዳ ዲናችን ያዘናል። ሌላውም በእነሱ ወንጀል መንካት የለብንም። እራሳችንን መጉዳት የለብንም፤ የሀገራችንን ሰላም መጠበቅ አለብን የኛ ግዴታ ነው።

ዛሬ በዚህ ባማረ መልኩ እንደጨረስን ሁሉ ለኢዳችን አላህ በሰላም እንዲያደርሰን እና በሰላም እንድንጨርስ ወንድሞቼ ፣ እህቶቼ አደራ እላችኃለሁ "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ኡስታዝ ከሚል ሸምሱ ፦

" ውድ ወንድሞች እና እህቶች እኛ እንደ ሙስሊሞች በቁርአን ፣ በሀዲስ ነው የምንመራው።

አላህ ሱብሀነ ወተአላ በራሳችን ፣ በስሜታችን ፣ በነብስያችን እንድንመራ አልፈቀደልንም። የመልካም ስራዎች ተምሳሌት ፤ የመልካም ተግባራት አርአያዎች እንጂ እኛ ከሌሎች ሰዎች መጥፎ ነገሮችን የምንኮርጅ ፤ መጥፎ ነገርን በመጥፎ የምንመልስ ሰዎች አይደለንም።

አላህ በቁርአን " ክፉ ነገርን በመልካም መልስ ያ ነው በአንተ እና በሌሎች መካከል ያለን ትስስር ፤ ግንኙነት የሚያስተካክለው " ስለሚለን በስሜት ውስጥ ሆነን የምንራመድ ህዝቦች አይደለንም።

ውድ ወንድሞች ፤ እህቶች እዚህ እንዳማረብን ቀጣዩ ኢዳችንን የተሳካ ኢድ እንዲሆን ፤ የታሳቡ ነገሮች ሁላ ከሽፎ ፤ ለሀገራችን ሰላም ፣ ለሀገራችን አንድነት ፣ የሀገሪቷ ባለቤቶች መሆናችንን በተግባር የምናሳይበት ኢዳችንን በጉጉት እየጠበቅን ባለንበት ሁሉ #ሰላምን መስበክ ፣ በሰላም መኖር ፀረ ሰላም የሆኑ ሰዎችን ደግሞ እነሱ በሚፈልጉት መስመር ውስጥ ሳንገባ መሄድ አለብን።

አላህ ኢዱን የሰላም ኢድ አድርግልን፤ ኢዱን የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የክብር እና የእኩልነት ኢድ ያድርግልን። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ዛሬ ሁለተኛው " ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር " ስነስርዓት በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ስነስዓቱ ላይ ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ምእመን ተገኝቶ ነበር። @tikvahethiopia
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፦

" ... ሰሞኑን ልባችን ተሰብሯል፣ አንጋታችን ተደፍቷል፤ ውስጣችን አዝኗል። መሆን የማይገባቸው ነገሮች ሆነዋል።

እንደ ሀገር ፣ እንደ ማህበረሰብ ሁላችንም በመከባበር ፣ እውቅና በመሰጣጣት ፣ በመተሳሰብ ስንኖርባት ነው ይህች ሀገር ነገ የተሻለ ሆነ ለትውልድ የምታልፈው።

በየትኛውም ጊዜ ነውረኛ ተግባር የሚፈፅሙ አካላት ፣ምንም ይሁን ማንነታቸው ወንጀለኞች ናቸው በህግ እና ለስርዓት ሊዳኙ ይገባል።

መንግስት ይህን የማስከበር ስራ እየሰራ ስላለ አሁንም ከመንግስትና ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን በሰላም ጉዳዮቻችን መፍትሄ እንዲያገኙ ፣ ያዘንባቸው እንዲታከሙ ሁላችንም በሰላም የምንታወቅበት ባህሪ አለን ያን መስመር ይዘን እንድንሄድ ነው አደራ የምንለው።

ከዛ ባለፈ እንደ ሀገር አሁንም የምንቀጥለው ጥፋት የሚያጠፋ አካል ሲያጠፋ ጥፋትን በመድገም አይደለም ውጤት የሚመጣው ፤ ነውርን በነውር አናክመውም ፤ ጥፋትን በጥፋት አናድነውም።

እስልምናችን እንደሚያዘን የራሳችን የሆነ መለያ ማንነት አለን ያንን መሰረት ተከትለን ነው የምንሄደው።

...በዛሬው ኢፍጣር ፕሮግራም መድረክ ከተለያዩ ቤተ እምነቶች የተወከሉ የሃይማኖት አባቶች ፣ ፓስተሮች ፣ ቀሳውስቶች ጥሬያችንን አክብረው ከጎናችን ቆመዋል እኛ የሚያምርብን እንደ ኡትዮጵያዊነት የሚገልፀን ይሄ ነው።

ተከባብረን ፣ እውቅና ተሰጣጥተን ስንኖር ፤ ይሄንን እናስቀጥላለን ፤ ጥፋቱን እንቃወማለን ፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን በሰላም ፣ በአንድነት ሀገራችንን እናስቀጥላለን "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዋግኽምራ 📍 የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በፋሲካ ዋዜማ በአማራ ክልል ፤ ዋግ ኽምራ ዞን የሰቆጣ ከተማ ማእከላዊ እዝ እና ማህበረሰቡን መጎብኘታቸውን ፅ/ቤታቸው አስታውቋል። ዶ/ር ዐቢይ ፤ ከማህበረሰቡ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት የአገው ሕዝብን የኪነ-ህንፃ ልህቀት እና ፍልስፍናዊ መሰረት አድንቀው እነዚህን እሴቶች የመጠቀም እና ፈተናዎችን ለማሸነፍ አንድነትን ማስጠበቅ ያለውን ጠቀሜታ…
#Woldia📍

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የዒድ አል ፈጥርን ዋዜማ ከወልድያ ከተማ ሕዝብና በአካባቢው ካለው ሠራዊት ጋር ማክበራቸውም ገለፀዋል።

በዚህም የተሰማቸድን ደስታ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " ጀግናው ሠራዊታችን የሕዝቡን ደኅንነት እና ልማት በደሙ ለማስከበር ወትሮ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል። " ያሉ ሲሆን " ይሄንን ሕዝብና ሠራዊት በዓላማ አንድነት ያጸናውን ግንብ፣ እንኳን ሊደፍሩት ሊጠጉት አስፈሪ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት በትንሳኤ በዓል ዋዜማ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ተገኝንተው ከማእከላዊ እዝ እና ከማህበረሰቡ ጋር ተገናኝተው እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopia
የአሠልጣኞች ሥልጠና ጥሪ

የተሳትፎ መመዝገቢያ ቅፅ: ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት መምህራን መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ፅንሰ-ሐሳቦች ላይ ያተኮረ የአሠልጣኞች ሥልጠና

የመብቶች ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD) በአዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ ፣ አዳማ፣ ደብረብርሀን፣ ድሬዳዋ፣ ሀዋሳና ሀረሪ ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የስነዜጋና ስነምግባር ትምህርት መምህራን የሰብዓዊ መብቶች ፅንሰ-ሐሳቦች ላይ ያተኮረ የአሠልጣኞች ሥልጠና ለመስጠት አቅዷል።

ሥልጠናው “የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዲስ ትውልድ’’ የተባለውና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሠራው ፕሮጀክት አንዱ አካል ነው መሆኑን ገልጿል።

ከስልጠናው በኋላ ተቋሙ በተጠቀሱት አካባቢዎች በቀጣይነት ለሚኖረው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ስልጠና ሂደቶችን በማስተባበር ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ለማድረግ አቅዷል።

ለመመዝገብ https://bit.ly/3vu4rZK