TIKVAH-ETHIOPIA
የትምህርት ሚኒስቴርና የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ! ከብሄራዊ ፈተና አስተዳደር ጋር በተያያዘ ባለፉት አመታት የታዩ ችግሮች ለመቅረፍ ከፈተና ዝግጅት ጀምሮ እስከ ውጤት ማሳወቅ ያሉትን ተግባራት በጥቃቄ እንዲከናወኑ ፦ 1ኛ. ፈተናዎችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተደግፎ መስጠት የሚቻልበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ፤ ይህ እውን እስኪሆን ድረስ የሚሰጡ…
#MoE
ከ2013 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ የተነሳውን ቅሬታ ሲከታተል የቆየው የህ/ተ/ም/ቤት የሰው ሀብት ልማት ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የትምህርት ሚኒስቴርን ውሳኔ " አደንቃለሁ " ብሏል።
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ፤ ቋሚ ኮሚቴው ከህብረተሰቡ ዘንድ ሲነሱ የነበሩትን ጥያቄዎች በመያዝ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ተደጋጋሚ ውይይት ሲያደርግ እንደነበር ገልጸዋል።
ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ " ይሄ የትውልድ ጉዳይ ነው ፤ ግልፀኝነት መፈጠር አለበት በተለይም ተቋማት ላይ ዜጎች እምነት ሊኖራቸው ይገባል። " ያሉ ሲሆን " ጉዳዩን ለመፍታት በተሄደበት ርቀት እና አሁን ለተደረሰው ደረጃ ቋሚ ኮሚቴው የራሱን አበርክቶ አድርጓል " ብለዋል።
" ትምህርት ሚኒስቴር ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ እና የህብረተሰቡን ጥያቄ አድምጦ ያሳለፈውን ውሳኔ በበጎ መልኩ ነው የምናየው ፤ ቋሚ ኮሚቴው ውሳኔውን ያደንቃል " ሲሉ ተናግረዋል።
ሌላው ጉዳዩን የሚከታተለው የህዝብ ዕንባ ጠበቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ኃይሌ የትምህርት ሚኒስቴርን ውሳኔ አንድ እርምጃ ወደፊት የተባለበት ነው ሲሉ ገልፀውታል።
" አንድ ውሳኔ ሲወሰን ሁሉንም ላያስደስት ይችላል " ያሉት ዶ/ር እንዳለ " በፊት ከነበረው አሁን የተሻለ ውሳኔ ተወሰኗል የሚል እምነት አለን " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ተናግረዋል።
@tikvahethiopia

" ከ4 ክልሎች ተጨማሪ 8,080 ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ "
የትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ይፋ ካደረገው ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ ካላቸው 152,014 ተማሪዎች በተጨማሪ 8 ሺህ 80 የሚሆኑ ተማሪዎችን ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደሚመድብ አሳውቋል።
ምንም እንኳን ጦርነት ሁሉንም ክልሎች በተወሰነ ደረጃ ተፅእኖ ቢያሳድርባቸውም ነገር ግን በተለየ ሁኔታ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የነበረው ሁኔታ በልዩነት እንዲታይ ተደርጓል።
የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአራቱ ክልሎች ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ ፥ " የጦርነት ስሜት የፈጠረው ነገር ተማሪዎችን ጎድቷቸው እንደሆነ አስተያየት የሚደረግበት መንገድ እንፈልግ በሚል የክልል ትምህርት ቢሮዎች ተስማምተው ለትምህርት ሚኒስቴር የሰጡት ስራ አስተያየት የሚደረግበት ሁኔታ ካለ እንዲፈለግ " የሚል እንደነበር አስረድተዋል።
በዚህም በፊት ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ከተቆረጠው ቁጥር 152 ሺ ተጨማሪ የሚገኝ ቁጥር ካለ ታይቷል ሲሉ ገልፀዋል።
በተለይም ከትግራይ ክልል መጥተው አራተኛ ዓመት ጨርሰው የሚወጡ ተማሪዎች ስለሚኖሩ የቅበላ ቦታዎችን ማግኘት ይቻላል በሚል ስራ ላይ ያሉት 43 ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን አቅም አሟጠው ወደ 8,080 ተማሪዎች የቅበላ ቦታ እንዳሳወቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
4ቱ ክልሎችም ተማሪዎችን ለይተው እንዳሳወቁ ገልፀዋል።
የተገኘውን የተማሪ ቅበላ አቅም በፍትሃዊነት ለ4ቱ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት በተጎዱ ተፈታኞች መጠን እንዲከፋፈል መወሰኑን አሳውቀዋል።
ምንም እንኳን የተገኘው የቅበላ ቦታ ለ4ቱ ክልሎች ይከፋፈላል ቢባልም ክልሎቹ በምን አግባብ እና መንገድ ተማሪዎቹን እንደለዩ እስካሁን በግልፅ የተብራራ ሆነ የታወቀ ነገር የለም።

#JudyMobile
📲ኦሪጅናል ስልኮች እና ኤሌክትሮኒክሶች በ ተመጣጣኝ ዋጋ ከ ሙሉ ዋስትና ጋር ከ ኧኛ ይሸምቱ!
💥 Iphone💥 Samsung💥Huawei
For more info join our telegram channel https://t.iss.one/judymobile
📍አድራሻ :ቦሌ መድሃኒያለም ከ ሬድዋን ህንፃ ጐን ሳዉዝጌት ፕላዛ #5 ያገኙናል።
Call +251913574171 or +251914213555

#ATTENTION📣 በአማራ ክልል ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ ቦታዎች ከትላንት ጀምሮ የፀጥታ ችግር መፈጠሩን ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች በርካቶች ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ሲሆኑ በዙሪያቸው የሚገኙ ቦታዎች ላይም ጭንቀት እና ውጥረት ፈጥሯል። በተለይ ደግሞ አጣዬ እና በዙሪያዋ ከዚህ በፊት ተደጋጋሚ ችግር ስለደረሰባት የአካባቢው ነዋሪ በከፍተኛ…
#Update
የሰሜን ሸዋ ዞን ፤ በኤፍራታና ግድም ወረዳ እና በቀወት ወረዳ እንዲሁም በኦሮም ብሄረሰብ ዞን አዋሳኝ አካባቢ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የፌድራል መንገድ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ክፍት ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ አሳውቋል።
መንገዱ ወደ አገልግሎት የተመለሰው በሰሜን ሸዋ ዞን አመራሮችና በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን አመራሮች ፣ በፀጥታ አካላቶች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች በተሰሩ ስራዎች ነው ብሏል።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በበኩሉ ከደሴ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ወይም ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚወስደው መንገድ ክፍት ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ ነው ብሏል።
ወረዳው ፤ ሰሞኑን ተፈጥሮ በነበረው የአካባቢ ግጭት የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡ አስታውሷል።
በአሁኑ ሰአት አካባቢው ሰላም በመሆኑ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ወይም ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚያስኬደው መንገድ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ሲል አሳውቃል።
ወደ ደሴ እየሄዳችሁ ያላችሁ አልያም ደግሞ ከደሴ ወደ አ/አ እየሄዳችሁ ያላችሁ እንደተባለው መንገድ ክፍት መሆኑን በተመለከተ መልዕክታችሁን @tikvahethiopiaBOT መላክ ትችላላችሁ።
ከሰሞኑን በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞንና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ አካባቢዎች ያገረሸው የፀጥታ ችግር ነዋሪዎችን ለከፋ የደህንነት ስጋት የጣለ ፤ ጉዳትም የተመዘገበበት ነው።
ፎቶ ፦ ፋይል

#Russia #Ukraine ሰሞኑን አዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በር ላይ በርካታ " ኢትዮጵያዊያን ሩሲያን ወግነው ዩክሬንን ለመውጋት " ለመመዝገብ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው የሚል ምስል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ኢትዮጵያውያኑ በእጃቸው ላይ ዶክመት ይዘው ተሰልፈው ይታያል። የሩስያ ኤምባሲ ፕረስ አታቼ የሆኑት ማሪያ ቸርኑኪና ለአል ዐይን በሰጡት ቃል ፤ " ሩሲያ ለዩክሬን…
#Ukraine
በአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ ፥ " ሩሲያ ለዩክሬን ጦርነት ኢትዮጵያዊያንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አላወጣችም፣ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃም ሀሰተኛ ነው "፤ ኢትዮጵያውያኑ የተሰለፉት ድጋፍ ለመግለፅ ነው ማለቱ ይታወሳል።
የዩክሬን ኤምባሲ ግን ማስተባበያው እራሱ ሀሰተኛ ነው ብሏል።
ኤምባሲው፤ " በተለያዩ የማህበረሰብ ትስስር ገጾች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው " መባሉ " በራሱ ውሸት ነው " ሲል ገልጿል።
ሩሲያ አሁን ላይ ከኢትዮጵያ ወጣቶችን ለመመልመል ሙከራ እያደረገች ትገኛለች ብሏል።
የኤምባሲው የሚሽን ሃላፊ አሌክሳንደር ለአል ዓይን በሰጡት ቃል፥ ከሰሞኑ አንድ የሩሲያን ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሰ ሰው አዲስ አበባ ገብቷል ሲሉ ተናግረዋል።
የሰውዬው መግባት ከጉዳዩ ጋር ምን እንደሚያገናኘው ተጠይቀው " ዩኒፎርም የለበሰው ወታደር መቼም በግ ጠባቂ አይደለም፣ ወታደር እንጅ " ሲሉ መልሰዋል።
ሩሲያ "70 % የሚሆነው ጦሯ አልዋጋም ስላላት ኢትዮጵያውንን ለመመልመል ጥረት እያደረገች ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ግን ፈቃደኛ አልሆኑላትም" ሲሉም ተናግረዋል።
ሩስያ ምልመላ ለማድረግ እየሞከረች ነው ያለው የዩክሬን ኤምባሲ " የተለያዩ መደለያዎችን እሰጣለሁ " በማለት ነው ኢትዮጵያውያንን ለመመልመል ጥረት እያደረገች የምትገኘው ሲል ለአል ዓይን ኒውስ ገልጿል።
ምንም እንኳን ሩስያ "ለምልመላ ማስታወቂያ አላወጣሁም" ብትልም ዛሬም ሰዎች በተለይ ዶክመት የያዙ ወጣቶች ኤምባሲው በር ላይ ተሰልፈው እንደነበር ቢቢሲ ፅፏል።
በኤምባሲ በር ላይ ተሰልፎ የነበረ አንድ ወጣት በጥሩ ደመወዝ በወታደርነት ወይም በተገኘው ስራ ለመቀጠር እንደመጣ ተናግሮ " ሩሲያን እወዳታለሁ " ብሏል።
ስለጉዳዩ በኢትዮጵያ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

#ከፍተኛ_የደም_እጥረት_ተከስቷል !
በብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ዘርፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ተመሥገን አበጀ ፦
" በአገሪቱ ያሉት የሁለቱ ትላልቅ ሃይማኖቶች ተከታዮች ፆም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ በመላ አገሪቱ ከፍተኛ የደም እጥረት ተከስቷል።
በአገሪቱ ያለውም የመጠባበቂያ ደም ክምችት ከ5 ቀናት የማይበልጥ ነው።
በአገር ደረጃ ሲታይ ከፆም በፊት በዚህ ዓመት የነበረው የደም ክምችት አመርቂ የሆነበት ዓመት ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል።
የዐቢይና ረመዷን አፁዋማት ከገቡ በኋላ የመደበኛ ደም ለጋሾችም ሆነ ሌሎች ለጋሾች ቁጥር አሽቆልቁሏል።
ይህም የደም ክምችት ላይ ከፍተኛ እጥረት እንዲፈጠር አድርጓል።
በተለይ እንደ ፕላትሌት የደም ተዋፅዖ እና ‘ኦ’ የደም ዓይነት ክምችቶች እጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ፕላትሌት የሚባለው የደም ተዋፅዖ ለካንሰር ታማሚዎች እና የደም መፍሰስ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የሚሰጥ የደም ዓይነት ነው፤ ክምችቱ ለአንድ ቀን ብቻ ሲሆን ‘ኦ' የተባለው የደም ዓይነትም በዛ ቢባል ለ2 ቀናት የሚሆን ክምችት ነው ያለው "
ያንብቡ : https://telegra.ph/EPA-04-19-2
#EPA

" ከ4 ክልሎች ተጨማሪ 8,080 ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ " የትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ይፋ ካደረገው ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ ካላቸው 152,014 ተማሪዎች በተጨማሪ 8 ሺህ 80 የሚሆኑ ተማሪዎችን ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደሚመድብ አሳውቋል። ምንም እንኳን ጦርነት ሁሉንም ክልሎች በተወሰነ ደረጃ ተፅእኖ ቢያሳድርባቸውም ነገር ግን በተለየ ሁኔታ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል…
#Update
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ፤ ከክልሉ ተጨማሪ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ የተወሰነላቸው 4339 ተማሪዎች በምን አግባብ እና በምን ሂደት እንደሚመረጡ አሳውቋል።
4,339 ተማሪዎች 50 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ ካመጡ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች መካከል በውጤታቸው ቅደም ተከተል ይመረጣሉ ብሏል።
ይህ በዚህ እንዳለ ሌሎች 50 ፐርሰንት እና በላይ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባት ያልቻሉት ደግሞ በክልሉ መምህራን ኮሌጆቾ " በመደበኛው የዲግሪ ኘሮግራም " የመምህርነት ስልጠና እንዲጀምሩ ሰፋ ያለ ቁጥር ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ቢሮው አሳውቋል።
ሌላው የመግቢያ ነጥብ ያላመጡ ተማሪዎች በመደበኛ ተማሪነት በድጋሜ ፈተና ይወስዳሉ የተባለው ሁሉንም የክልሉን ተማሪዎች የሚያካትት ሲሆን ይህም በልዩ ሁኔታ ለአማራ ክልል ብቻ መሆኑ ተገልጿል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ወደ ዩኒቨርስቲዎች ሆነ ወደ መምህራን ኮሌጆቾ መግባት ያልቻሉት ተማሪዎች በቂ ዝግጅት አድርገው መፈተን እንዲችሉ የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል የፈተና ጊዜ እንዲራዘም ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቋል።
ትምህርት ሚኒስቴርም ቢሮው ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ከመስከረም 2015 ዓ/ም በፊት ፈተናው እንደማይሰጥ ትላንት መወሰኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
የክልሉ ተማሪዎች የ2014 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 20 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ጊዚያት ሊሰጥ እንደሚችል አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ቢሮው አሳስቧል።
መረጃውን ይፋ ያደረጉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ማተብ ታፈረ ናቸው።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#COVID19Ethiopia - Health Worker Training Platform
ኮቪድ-19 ሰልጠና ሰርተፍኬትዎን አሁኑኑ በሰልክዎ ባለው መተግበሪያ መውሰድ ይችላሉ።
የኮቪድ-19 ስልጠና ወስደው ሰርተፍኬትዎን መውሰድ እንዴት እንደሚችሉ ለማወቅ ከላይ ቪድዮውን ይመልከቱ።
https://bit.ly/3apv5J2 ይህንን ማስፈንጠርያ በመጫን አፕልኬሽኑን ያዘምኑ።

#Ukraine በአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ ፥ " ሩሲያ ለዩክሬን ጦርነት ኢትዮጵያዊያንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አላወጣችም፣ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃም ሀሰተኛ ነው "፤ ኢትዮጵያውያኑ የተሰለፉት ድጋፍ ለመግለፅ ነው ማለቱ ይታወሳል። የዩክሬን ኤምባሲ ግን ማስተባበያው እራሱ ሀሰተኛ ነው ብሏል። ኤምባሲው፤ " በተለያዩ የማህበረሰብ ትስስር ገጾች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው "…
" እያጣራን ነው "
ኢትዮጵያ ሩስያ ኤምባሲ በር ላይ ተሰልፈው ስለታዩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ እየተጣራ ነው ብላለች።
ከሰሞኑን በአ/አ የሩስያ ኤምባሲ በር ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ዶክመንት ይዘው ተሰልፈው መታየታቸው ይታወቃል።
አንዳንድ ቃላቸው የሰጡ፥ ባለው ኢኮኒኖሚያዊ ችግር እንዲሁም ለሩስያ ባላቸው ፍቅር ለሩስያ በመዝመት የተሻለ እድል ለማግኘት እንደሆነ ተናግረዋል።
የተሰለፉት "ለወታደራዊ ምልመላ" ነው ቢባልም ሩስያ" ሀሰት ነው፤ ሩስያ ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን የመመልመል እቅድ የላትም፤ የመጡት ድጋፋቸውን ለመግለፅ ነው" ስትል አስተባብላ ነበር።
ትላንትም ኤባሲው ባወጣው መግለጫ "ምንም አይነት የውትድርና ምልመላ ጥያቄዎችን አልቀበልም" ብሏል።
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ያለችውን ጦርነት የአገሪቱ ጦር በብቃት እንደሚወጣ ባለ ሙሉ እምነት መሆኑንም ገልጾ፤ እየቀረቡ ላሉ የአጋርነት ጥያቄዎች ክብር እንዳለው አሳውቋል።
ኤምባሲው በተመድ ሩሲያ በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሩሲያ ያሳየው ድጋፍ የሚደነቅ ነው ብሏል።
ኤምባሲው የ1961 የቬን ኮንቬሽን እንደሚያከብር ገልጾ፤ በዚህ ስምምነት መሠረት የውትድርና ምልመላ በሌላ አገር ማድረግ ተቀባይነት የለውም ብሏል።
ዩክሬን በበኩሏ፤ የሩስያ ኤምባሲ ኢትዮጵያውያንን ለውትድርና ለመመልመል ሲሞክር እየታየ ነው በሚል የሚሰጠውን ማስተባበያ ውሸት እንደሆነ ገልጿል።
በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግስት የማጣራት ስራ እየሰራ መሆን አሳውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፤ በሩስያ ኤምባሲ በር ላይ የታየው ሰልፍ ለምን ዓላማ እንደሆነ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም ያሉ ሲሆን ነገር ግን ሰዎቹ ለምን ጉዳይ እንደተሰለፉ እየተጣራ ነው ብለዋል።

#EthiopianAirlines #EthioTelecom
" የትም መሄድ ሳይጠበቅባችሁ እና ሳትንገላቱ የበረራ ትኬታችሁን በቴሌ ብር መግዛት ትችላላችሁ " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ / ኢትዮ ቴሌኮም
ከዚህ በኃላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች የበረራ ትኬታቸውን በ 'ቴሌ ብር ' አማካኝነት መግዛት ይችላሉ ተብሏል።
ዛሬ ኢትዮ-ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጋር ሊሰሩ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን የአየር መንገዱ ደምበኞች የበረራ ትኬት ክፍያ በቴሌ ብር አማካኝነት መፈፀም እንደሚችሉ ተገልጿል።
የተደረገው ስምምነት የአየር መንገዱ ደንበኞች የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው እና ሳይንገላቱ ባሉበት ሆነው በሞባይል ስልካቸው አማካኝነት ትኬት መግዛት እና ክፍያ ለመፈፀም እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፥ ለሀገር ውስጥ ሆነ ለውጭ ሀገር በረራ እስከ 30 ሺህ ብር የሚያወጡ የአየር መንገዱን ትኬቶች የትም መሄድ ሳያስፈልግ ካሉበት ሆኖ መግዛት ይቻላል ብሏል።

' የትምህር ቤት ክፍያ '
የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2015 የትምህርት ዘመንን የክፍያ ጭማሪ አስመልክቶ ከትምህርት ቤቶች ጋር ምክክር አድርጎ ነበር።
በዚህም ፥ በ2014 ዓ/ም ጭማሪ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ ተገልጿል።
ነገር ግን ላለፉት 2 እና 3 አመታት ጭማሪ ሳያደርጉ የቆዩ ትምህርት ቤቶች በሚያቀርቡት ፕሮፖዛል እና ከወላጅ ጋር በሚያደርጉት መግባባት መሰረት ጭማሪ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፎቻቸውን ጨምሮ 2 ሺህ ገደማ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ እነዚህ ትምህርት ቤቶች 400 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን ያስተናግዳሉ ፤ ይህም ከአጠቃላይ የአዲስ አበባ የተማሪ ሽፋን 43 በመቶውን ይይዛል፡፡
#AMN
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#UK
አሜሪካ #በጥብቅ የምትፈልገው የ " ዊኪሊክስ " መስራች ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ ተላፎ እንዲሰጥ የብሪታኒያ ፍርድ ቤት ዛሬ ወስኗል።
አሳንጅ ለአሜሪካ ፍርድ ቤት ተላልፎ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ የሚሆነው የብሪታኒያ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ሲያጸድቀው ነው ተብሏል።
አሳንጅ የአሜሪካን ወታደራዊ መረጃዎች አውጥቷል ፤ አትሟል ፤ ወታደራዊ ሚስጥሮችን የያዙ ሰነዶች ለውጭ ኃይሎች አሳለፎ ሰጥቷል በሚል እና በሌሎችም ጉዳዮች ነው አሜሪካ የምትፈልገው።
18 በሚሆኑ ክሶችም ዋና ተፈላጊ ሰው ነው።
የ50 ዓመቱ አሳንጅ በአሜሪካ የቀረበለትን ክስ ውድቅ ቢያደረግም፤ አድርጎታል ከተባለ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለ7 ዓመታት በለንደን በሚገኘው የኢኳዶር ኤምባሲ፤ እንዲሁም እንደፈረንጆቹ ከ2019 አንስቶ አስካሁን ድረስ በደቡብ ምስራቅ ለንደን በሚገኘው ቤልማርሽ እስር ቤት እንዲታሰር አድርጎታል።
መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።