TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጭሮ የ ' አጥንት ካንሰር ታማሚ ' በመምሰል በተሽከርካሪ ላይ እየተዘዋወረች ስትለምን የነበረችውን ወጣት ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጭሮ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ወጣቷ ከሰባት (7) ግብረ አበሮቿ ጋር የአጥንት ካንሰር ታማሚ መስላ በተለያዩ ከተሞች እየተዘዋወረች  ስትለምን መቆየቷን በምርመራ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል። የጭሮ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ምርመራ ወጣቷ ግብረ…
#AddisAbaba

በመዲናችን አዲስ አበባ የ10 ዓመት ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታውቋል።

የሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት በህፃኑ ስም ገንዘብ ሲያሰባስቡ ተገኝተው በቁጥጥር ስር የዋሉት 11 ግለሰቦች (9 ሴቶች እና 2 ወንዶች) ሲሆኑ አሁን ላይ ምርመራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት በ3 ክፍለ/ከተሞች ስም የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነድ እንዲሁም የሃኪም ማስረጃዎችን ከሚለምኑባቸው 2 ሚኒባስ መኪኖች (ታርጋ ቁጥር 58456 እና 79169 ኮድ 3 ኦሮሚያ) ጋር በህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማና በፀጥታ ኃይሎች ክትትል ነው ተብሏል።

አሁን ላይ በከተማዋ የተለያዩ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማዘጋጀትና ያልታመመ ሰውን ታሟል በማለት የሚመለከተው የህክምና ተቋም ማረጋገጫ ሳይሠጥ በህገ-ወጥ መንገድ የሚካሄዱ ልመናዎች በዝተወልና ህብረተሰቡ ከአጭበርባሪ ወንጀለኞች ራሱንና ንብረቱን ይጠብቅ ተብሏል።

ከዙህ ቀደም (የካቲት ወር ላይ) በጭሮ ከተማ የ ' አጥንት ካንሰር ታማሚ ' በመምሰል በተሽከርካሪ ላይ እየተዘዋወረች ስትለምን የነበረችውን ወጣት በፖሊስ መያዟ ይታወሳል (ለማስታወስ ይኸው ሊንኩ t.iss.one/tikvahethiopia/67710 )

እንዲህ ያሉ ድርጊቶች በእርግጥም ታመው እና አቅም አንሷቸው በህምመም ለሚሰቃዩ ወገኖቻን በሚደረገው ድጋፍ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል፤ ሰዎች ድጋፋቸውን ለማድረግ እንዲጠራጠሩም ይሆናል፤ በዚህም ምክንያት በእኛ የ10 ብር እና 20 ብር ድጋፍ ተሰባብሶ ሊተርፉ የሚችሉ ወገኖቻችን እናጣቸዋለን።

ምን ቢደረግ የተሻለ ነው ? ሃሳባችሁን አካፍሉ ፤ ተነጋገሩት👇

@tikvahethiopiaBOT
#SIDAMA

ዘንድሮ " ፊቼ ጫምባላላ " በአደባባይ በድምቀት ይከበራል።

ላለፉት ለሁለት ዓመታት የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በጉዱማሌ አለመከበሩ (ህዝቡ በየቤቱ እንዳከበረ) ይታወቃል።

ዘንድሮ ግን በአደባባይ በ " ጉዱማሌ " ለማክበር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ በተጨማሪ በሀገር ደረጃ (በሌሎችም የሀገራችን ከተሞች) ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተሰምቷል።

የፊቼ ጫምባላላ በዓል ኢትዮጵያ በዓለም ቅርስነት በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰስ ቅርስ አንዱ እንደመሆኑ በዓሉን ለመታደም ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ እንድግዶችን ፣ ቱሪስቶች እና ለባለድርሻ አካላት ለማስተናገድ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።

መረጃውን ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል ፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WFP #UN #Ethiopia #TigrayRegion ዛሬ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ አልሚ ምግብን ጨምሮ ህይወት አድን ፍጆታዎችን የጫኑ 47 ተሸከርካሪዎች ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸውን አሳውቋል። ከ47ቱ ተሽከርካሪዎቹ በተጨማሪ ለመሰረታዊ አገልግሎቶች የሚውል ነዳጅ የጫኑ 3 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ። ከሁሉም ባለስልጣናት በተደረገው ድጋፍ እስካሁን ጉዞው የተሳካ እና መልካም የሚባል…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

#Tigray, #Mekelle 📍

ትላንትና በጉዞ ላይ እንደነበሩ የተነገረላቸው አስፈላጊ የሆኑ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶችን የጫኑት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሸከርካሪዎች የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ደርሰዋል።

ሁሉም (50ውም) ተሸከርካሪዎች በሰላም ነው መቐለ የደረሱት።

ምን ይዘዋል ?

➡️ 1,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ እና ጥራጥሬ ፤
➡️ 700 ሜትሪክ ቶን የጤና ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና WASH (ውሃ፣ የአካባቢ እና የግል ንፅህና መጠበቂያ እቃዎች) + 115,000 ሊትር ነዳጅ ይዘው ነው መቐለ የደረሱት።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም መቐለ የደረሱትን እነዚህን ምግብ / አልሚ ምግቦች በዚህ ሳምንት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ማከፋፈል እንደሚጀምር አሳውቋል።

በዚህም ድርጅቱ 43,000 አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች እንዲሁም ተጋላጭ ለሆኑ 24,000 እናቶች እና ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ ለመድረስ ማቀዱን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IFTAR ዛሬ በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ይካሄዳል። ለዚህም ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ። ከደሴ ከተማ ኮሚኬሽን ቢሮ ባገኘነው መረጃ ዛሬ አርብ የሚካሄደው ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት እንደ አምናው " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ሲሆን ለደሴ ከተማ የክርስትና እምነት የተከታዮችም " ኑ በጋራ እናፍጥር " ውብ የሆነውን የወሎን እሴት እናስቀጥል የሚል ጥሪ ቀርቧል። በሌላ መረጃ ነገ ቅዳሜ ረመዳን…
#IFTAR

በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሄደ።

በደሴ ከተማ ዛሬ ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ተካሂዷል።

የኢፍጣር ስነስርዓቱ ከ " ፒያሳ እስከ መናኸሪያ " ባለው ጎዳና ላይ የተካሄደ ሲሆን እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የደሴ ከተማ ነዋሪ ታድሟል።

በሌላ በኩል ደሴ የረመዳንን በዓል አስመልክቶ " ከኢድ እስከ ኢድ " በተሰኘው መርሃ ግብር ደሴ የሚገቡ እንግዶችን ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ትገኛለች።

ፎቶ፦ ሶሻል ሚዲያ የተሰባሰበ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የታሰሩበት 33 አባላቱ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን አስታወቀ። ከ33ቱ መካከል ሁለቱ ለለ14 ቀን ሲቀጠሩ ቀሪዎቹ 31 አባላቱ ለሀሙስ መጋቢት 1 ተቀጥረዋል ብሏል። ተከሳሾቹ ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡት ለሁለት ቡድን ተከፍለው ሲሆን 31ዱ እስረኞች ከልደታ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው የቀረቡት። ሁለቱ ደግሞ ጊዮርጊስ የሚገኘው…
#Balderas

ከዓድዋ እና ካራማራ ድል መታሰቢያ በዓላት ጋር በተያያዘ ታስረው የቆዩ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት ሁሉም ከእርስ ተለቀዋል።

ከእስር የተለቀቁት በዋስትና ነው።

ፖሊስ ወጣቶቹ በእስር ላይ በነበሩ ሰዓት ለፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ ከዓድዋ እና ካራማር በዓላት ጋር በተያያዘ ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት ፣ ህዝብን በመንግስት ላይ እንዲያምፅ የመንግስት ባለስልጥናትን በአደባባይ በመስደብ ተግባር ላይ አግኝቻቸዋለሁኝ ብሏል።

የፓርቲው ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ ክሱን በተመለከተ " ወጣቶቹ ትግላችን ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ነው፤ ሁለቱም አደጋ ላይ ናቸው ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን " ሲሉ መመለሳቸውን ገልፀዋል።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ ለ41 ቀናት መታሰራቸውን ገልፆ ትላንት እና ዛሬ በዋስ ከእስር መፈታታቸውን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" እጅግ ነውር ተግባር ነው "

ከ2 ዓመት በፊት የቀረበን ሪፖርት በቀጥታ ገልብጦ ያቀረበው የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር” እጅግ ነውር ተግባር” ፈጽሟል ሲል የዉሃ ፣ መስኖ ፣ ቆላማ አከባቢ እና አከባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ።

ቋሚ ኮሚቴው የዉሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ9 ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት እንዲያቀርብ በተገኘበት መድረክ ምንም ዓይነት የሪፖርት ማሻሻያ ሳያደርግ በቀጥታ #እየገለበጠ እንደሚያስተላልፍ ደርሼበታለዉ ብሏል።

ዛሬ ቋሚ ኮሚቴው የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የአፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል።

በዚህም ወቅት ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፖርቶችን በቀጥታ ገልብጦ ከማምጣቱም ባሻገር የተቋሙ የበላይ ሃላፊዎች #የማያዉቁት እና #ያልተገመገመ ሪፖርት ለምክርቤት መላኩ " እጅግ ነዉር ነዉ " ሲል ወቅሷል፡፡

ሪፖርቱ ከ2012 ጀምሮ እስካለንበት 2014 የግማሽ ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርቶች #በቀጥታ ተገልብጠዉ የተላለፉ ናቸዉ።

ለማሳያነትም ፤ በስነምግባር እና በጸረ ሙስና ብልሹ አሰራሮች ናቸዉ ተብለዉ ከቀረቡት 16 ጥቆማዎች መሀል 13ቱ ተጣርተዉ መልስ የተሰጣቸዉ ሲሆኑ 3 ጥቆማዎች በሂደት ላይ የሚገኙ ናቸዉ " የሚለዉ አፈጻጸም ከ2012 የ9 ወር ሪፖርት ቃል በቃል ምንም ለዉጥ ሳይደረግበት ተገልብጦ የመጣ መሆኑን በግልጽ ያሳያል ሲሉ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የሆኑት ፈትያ አህመድ ገልፀዋል።

ሰብሳቢዋ ይህንን ሀሰት ነዉ የሚል አካል ካለ በርካታ ተጨባጭ የሰነድ ማሳያዎች ማቅረብ እንችላለን ሲሉ ተናግዋል።

በሚኒስቴር ዲዔታ ማዕረግ የሚኒስቴሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ በሪፖርቱ ላይ የቀረበዉ ትችት ትክክል እንደሆነ አምነዋል።

የሪፖርት ጥራትና ወቅታዊነት ጉዳይ ፍጹም ለጥያቄም ቢሆን የሚቀርብ ጉዳይ እንዳልሆነ አንስተዋል። ይህም መስተካከል እንዳለበት እንደሚያምኑ እና የተለያዩ መ/ቤቶች አንድ ላይ መዋሃድ ይህንን ክፍተት መፍጠሩን እንደምክንያት አንስተዋል።

በቀጣይ ይህንን አስተካክለዉ እንደሚቀርቡ ገልጸዉ ቋሚ ኮሚቴዉን ይቅርታ መጠየቃቸውን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ... እንዲህ ብሎ መናገር ከባድ ነው ግን ዓለም መባላትን መርጧል። " - ፖፕ ፍራንሲስ

በጎርጎራውያኑ ዘመን አቆጣጠር የክርስትና እምነት ተከታዮች የእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓልን አከብረዋል።

በዓሉ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ የተከበረ ሲሆን በአውሮፓ ሀገራት፤ በዩክሬንና ሩስያ ጦርነት ሳቢያ በዓሉ ተቀዛቅዞ ነው የተከበረው።

በዓሉን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ " ዘመኑ ከፍቷል " ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ፦

" ይህ ጦርነት (የዩክሬን እና ሩስያ) እዚህ አውሮፓ የሚደረገው ጦርነት እየመታን ነው።

ራቅ አድርገን እንመልከት ዓለም ጦርነት ላይ ናት። በየስፍራው ጦርነት ነው ፤ እንዲህ ብሎ መናገር ከባድ ነው ግን ዓለም መባላትን መርጧል።

ጦርነት እርስ በእርስ የመባላት ስርዓት ማለት ነው፤ ወንድም ወንድሙን መግደል " ሲሉ ተደምጠዋል።

በዓለም ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የካቶሊካዊ ክርስቲያን መንፈሳዊ አባት የሆኑት ፖፕ ፍራንሲስ የእየሱስ ክርስቶስን አብነት ለመዘከር በየዓመቱ እንደሚያደርጉት ትላንትም የ12 እስረኞችን እግር አጥበው ስመዋል።

መረጃው የዶቼቨለ ሲሆን የፎቶው ባለቤት ሮይተርስ ነው።

@tikvahethiopia
" ሀሰተኛ የሆኑ መረጃዎችን ካላጠፋችሁ ቅጣት ይጠብቃችኃል " - ሩስያ

ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ጎግል (Google) እና ዊኪፒዲያን (Wikipedia) እቀጣለሁ ስትል ሩስያ ዝታለች።

የሩስያ ፍርድ ቤት የአሜሪካው ግዙፉ የኢንተርኔት ኩባንያ ጎግል እና የዊኪፔዲያ ባለቤት ዊኪሚዲያ ፋውንዴሽን ስለ ዩክሬን ግጭት "ሀሰተኛ" ያላቸውን መረጃዎች ካልሰረዙ/ካላጠፉ የቅጣት በትሩን እንደሚያሳርፍባቸው አሳውቋል።

ኢንተርፋክስ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ፤ የሩስያ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ተቆጣጣሪ በተለይም ጎግል ፤ በዩትዩብ (YouTube) ቪድዮ ማጋሪያ ላይ የተጫኑ ሩስያ ህገወጥ ነው የምትላቸውን ቪድዮዎች ካላጠፋ ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቀው አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia