TIKVAH-ETHIOPIA
#Udpate በጂንካና አካባቢው ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ ግለሰቦች 22 ሲፈቱ ቀሪዎቹ ላይ ምርመራ መቀጠሉ ተሰምቷል። ዞኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የተከሰተው ችግር በቁጥጥር ስር ውሎ ማኅበረሰቡም ወደ ቀደመው የኑሮ ሁኔታ እየተመለሰ ነው ብሏል። የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የሰላም እና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ደሞ በዛብህ ፤ ከፀጥታው ችግር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ካሉበት…
" ደቡብ ኦሞ ዞን "
ከሰሞኑን በደቡብ ኦሞ ዞን በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከቤታቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።
ተፈናቃይ ወገኖቻችን ተፈናቅለው ከተጠለሉበት አንዱ ሜፀር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሲሆን በአሁን ወቅት አስቸጋሪ ኑሮ እየመሩ እንደሆነ ገልፀዋል ፤ መንግስት ፈጥኖ መልሶ እንዲያቋቁማቸው እና የዕለት ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።
ትላንት የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጉዳቱ በደረሰባቸው አካባቢዎች በመገኘት ችግሩን ተመልክተዋል፤ ተፈናቃይ ወገኖችንም አግኝተዋል።
ጉዳት የደረሰባቸውን አካላትን መልሶ ለማቋቋም እንደሚሰራ አሳወቀዋል።
በሌላ በኩል ከሰሞኑን በተፈፀመው ክስተት ዙሪያ ጉዳዩን የሚመረምሩ አካላት ከክልል ወደ ዞኑ መግባታቸውን ከዞኑ ኮሚኬሽን የወጣው መረጃ ያመለክታል።
@tikvahethiopia

#AddisAbaba🏍
በአዲስ አበባ ባለሞተሮች ከራሳቸው ውጭ ሌላ ተደራቢ ሰው እንዳይጭኑ #እገዳ ተጣለባቸው።
ሞተር ሳይክልን በተመለከተ በትራንስፖርት ቢሮ በኩል አዲሱ ጥናት ተጠናቆ ይወርዳል ተብሏል።
ይህ ጥናት እስኪወርድ መጪው የፋሲካ በዓል በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ስለሚኖር፣ ግርግር እና ስርቆት እንዳይፈጠር ላልተወሰነ ጊዜ የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ከሞተር ብስክሌት አሽከርካሪ ውጭ ሌላ ተደራቢ ተሳፋሪ እንዳያጭኑ ቁጥጥር እንዲደረግ እና እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ መተላለፉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።
የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች ከነገ ሚያዝያ 7 ጀምሮ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ መመሪያ መሰጠቱም ታውቋል።

#Tigray የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የህክምና፣ ምግብ እና የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችን ያካተተ ድጋፍ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ትግራይ ክልል ደርሷል፡፡ ይህም እ.ኤ.አ ከመስከረም 2021 በኋላ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ክልሉ የደረሰ የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ድጋፍ ነው፡፡ https://www.icrc.org/en/document/ethiopia-icrc-resumes-aid…
#Tigray , #Mekelle📍
የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በዚህ ወር ለሁለተኛ ጊዜ ፦
👉 የህክምና ቁሳቁሶችን ፣
👉 አስቸኳይ የምግብ ድጋፎችን ፣
👉 የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችን እና አስፈላጊ የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን የያዘ ቡድን ዛሬ ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ገብቷል።
በተጨማሪም ድጋፉ ለአካል ተሃድሶ ማዕከል አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው።
#ICRC

#AmharaBank
አማራ ባንክ ስራውን ለመጀመር ከጫፍ መድረሱን አስታውቋል።
ባንኩ ትላንት በላከልን መግለጫ ፤ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና ለባንክ ኢንዱስትሪው እድገት ተጨማሪ ጉልበት ለመፍጠር በሚያስችል ደረጃ ስራው ለመጀመር ጫፍ መድረሱን ገልጿል።
ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ " የባንክ ስራ ፍቃድ " (Banking Business License) ካገኘ በኃላ ለተለያዩ የባንኩ የስራ ክፍሎች እንዲሁም ቅርንጫፎች ብቃት ያላቸውን ሰራተኞችን በመመደብ የቅድመ ስራ ጅማሮ ተግባራትን ማከናወኑን ገልጿል።
በተጨማሪ የባንክ አገልግሎቱን በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ የቅርንጫፍ ቦታ መረጣ ተግባራትን አጠናክሮ መቀጠሉን አሳውቋል።
ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የኮር-ባንኪንግ ቴክኖሎጂ በዘርፉ ስመ-ጥር እና ታዋቂ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ጋር ውል በማሰር የቴክኖሎጂ ኩባንያው ወደ ስራ መግባቱን ገልጿል።
አማራ ባንክ ፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋርም ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማዕከል አገልግሎት ስምምነት ከቀናት በፊት መፈራረሙን አሳውቋል።
ባንኩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተቀላጠፈ እና እጅግ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር አብስሯል።
የአማራ ባንክ አ.ማ ከ190,000 በላይ በሆኑ ባለአክሲዮኖች የተመሰረተ ፤ ከፍተኛ መነሻ ካፒታል ማሰባሰብ የቻለና በአንጋፋነት የተመሰረተ ባንክ መሆኑን በተላከልን መግለጫ ላይ ተገልጿል።

#Update የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን ፈተና የሚያጣራ ቡድን ወደ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አግልግሎት መላኩን ዛሬ አስታወቀ። የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች የውጤት ችግር መግጠሙን ተከትሎ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል ብሏል። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ችግሩን ለመፍታት በርካታ ተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱን ገልጾ በአሁን ሰዓት ፦ 👉 ከክልሉ ትምህርት…
የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሂደት ላይ የቀረቡ ቅሬታዎችን እንዲያጣራ ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላከው ኮሚቴ ምንድነው ያለው ?
የ2013 የትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት አስመልክቶ የአማራ ክልል ትምህርት ባቀረባቸው ቅሬታዎች ላይ የተደረሰበት ሂደት ኮሚቴው ለህዝብ አሳውቋል።
በዚህም መሰረት ፤ በጦርነት አውድ ውስጥ ቆይተው ፈተና እንዲወስዱ የተደረጉ በክልሉ የሁሉም ዞን ተማሪዎች በውጤታቸው ላይ የተለየ ተፅዕኖ የተፈጠረ መሆኑ እና ጉዳዩ በልዩ ሁኔታ መታየት እንዳለበት #ከትምህርት_ሚኒስቴር ጋር አስፈላጊው መግባባት መፈጠሩን ገልጿል።
በትምህርት ቢሮው በኩል በጦርነት ተጽዕኖ ምክንያት ውጤታቸው የቀነሰባቸው ተማሪዎች ዝርዝር መረጃ እና አስፈላጊ ማስረጃዎች ሁሉ ለትምህርት ሚኒስቴር መቅረቡን ገልጿል።
የትምህርት ሚኒስቴርም በቀረበለት መረጃ እና ማስረጃ መሰረት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እያየው እንደሆነና ውሳኔውን #በቅርብ_ቀናት የሚያሳውቅ መሆኑን ኮሚቴው ለህዝብ አሳውቋል።
ሌላው ኮሚቴው የተለያዩ መረጃዎችን አደራጅቶ ወደ ፈተናዎች ኤጀንሲ በመሄድ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምርመራ ያደረገ ሲሆን የደረሰበትን በዝርዝር አሳውቋል ፤ (በዚህ ያንብቡ https://telegra.ph/Amhara-Education-Bureau-04-15)
ተማሪዎች ፣ ወላጆች እና መላው ማህበረሰብ የትምህርት ሚኒስቴርን የመፍትሄ ሃሳብ በትግስት እንዲጠብቅ ኮሚቴው ጥሪውን አቀርቧል፡፡
በሌላ በኩል ፤ የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በተፈጠረው ችግር ሳይዘናጉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲዘጋጁ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጥሪውን አቅርቧል።

#DawroZone 📍
በዳውሮ ዞን ባጋጠመ የዝናብ እጥረት እና የአየር መዛባት ምክንያት ወገኖቻችን ለከፍተኛ የምግብ እጥረት እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል።
በ5 ወረዳዎች በተከሰተ የምግብ እጥረት እናቶች እና ህፃናት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።
በተለይ በዛባ ገዞ ወረዳ፤ ሰዎች እየተራቡ የቤት እንስሳትም እየሞቱባቸው መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ከቤት እንስሳት በተጨማሪ በጫካ ውስጥ የሚኖሩ እንስሳት ጭምር በምግብ እጥረት እንደሞቱ ገልጸዋል።
አንድ የአካባቢው ነዋሪ " የተለያየ ነገር እንተክላለን ነገር ግን ዝናብ የለም፤ ዝናብ ቢዘንብ እንኳን በቀበሌ ደረጃ ብንቆጠር 4 የሚሆን ጥማድ በሬ ማግኘት አንችልም። በመኖር እና በመሞት መካከል ነው የምንገኘው " ብለዋል።
የምግብ ጥረቱ በመማር ማስተማር ላይም ተፅእኖ ያሳደረ ሲሆን በርካታ ተማሪዎች ትምህርት አቋርጠዋል።
የዳውሮ ዞን ግብርና መምሪያ የአደጋ ፅህፈት ቤት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው የምስክ ምልከታ 112 ሺ በላይ ወገኖቻችን ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አረጋግጧል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በበኩሉ አሁን በከፋ ሁኔታ ላይ የሚገኙና አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችን 44 ሺ ሲሆኑ የቀሩት በሴፍቲኔትና በምግባ ይካተታሉ ብሏል፤ በችግር ላይ ለወደቁ ወገኖች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን መግለፁን የጀርመን ሬድዮ ዘግቧል።
በሌላ መረጃ ፤ በዳውሮ ዞን በቆላማ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን የተለያዩ አካላት ድጋፍ እያደረጉ ሲሆን፤ የቤንች ሸኮ ዞን ፣ ካፋ ዞን፣ ኮንታ ዞን ፣ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣ የቦንጋ መምህራን ኮሌጅ፣ ቀይ መስቀል፣ የክልል ቢሮዎች ሌሎችም ድጋፍ አድርገዋል።

#IFTAR
ዛሬ በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ይካሄዳል።
ለዚህም ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ።
ከደሴ ከተማ ኮሚኬሽን ቢሮ ባገኘነው መረጃ ዛሬ አርብ የሚካሄደው ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት እንደ አምናው " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ሲሆን ለደሴ ከተማ የክርስትና እምነት የተከታዮችም " ኑ በጋራ እናፍጥር " ውብ የሆነውን የወሎን እሴት እናስቀጥል የሚል ጥሪ ቀርቧል።
በሌላ መረጃ ነገ ቅዳሜ ረመዳን 15 (ሚያዚያ 8) በድሬዳዋ ከተማ " የአብሮነት ኢፍጣር በድሬዳዋ " በሚል በምድር ባቡር ለገሃር አደባባይ ይካሄዳል፤ በዕለቱ በአብሮነት ከማፍጠር ባለፈ የቁርዓን እጥረት ላለባቸው ከተሞች ቁርዓን የሚሰበሰብ ሲሆን እስከ 1000 ቁርዓን ለማሰባሰብ ታቅዷል።
በተጨማሪ የፊታችን እሁድ ሚያዚያ 9 በኮምቦልቻ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት መዘጋጀቱ ተሰምቷል።
እንዲሁም በሀረር ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሚያዚያ 9 ከራስ ሆቴል እስከ ጁምዓ መስጂድ ድረስ ይካሄዳል ተብሏል።
በሌሎችም የሀገራችን ከተሞች ላይ ተመሳሳይ ስነ ሥዓቶችን ተከታትለን እናሳውቃለን።
ፎቶ ፦ ደሴ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ነዋሪዎችን ያማረሩት ጫኝ እና አውራጆች ፦
ከቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፦
" ... በአዲስ አበባ ከተማ ላይ በሁሉም ሰፈር ማለት ይቻላል በህገወጥ ጫኝና አውራጆች በሚጠየቅ የተጋነነ ክፍያ ምክንያት ዕቃ መኪና ላይ መጫንም ሆነ ማውረድ አዳጋች ሆኗል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ እነዚህ ህገ ወጦች ላይ እርምጃ በመውሰድ ህብረተሰቡን ሊታደግ ይገባል።
ሰው ተሰቃይቷል ፤ ህዝቡ ተበሳጭቷል ፤ ጉረቤትህ እና ልጆችህ እንኳ ተባብረው ሊያራግፉልህ እድል አይሰጡም።
እነዚህ ወጣቶች ሌላው በመቶ ብር ሚያራግፈውን እነሱ ቢያንስ እስከ 3 ሺ ብር ይጠይቃሉ። "
ከሰሞኑን ከዚህ ነዋሪዎችን እያማረረ ካለው ህገወጥ ድርጊት ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ለሸገር FM 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል አሳውቋል።
በአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ፥
" ብዙ ችግር ነው ያለው። ለምሳሌ ፦
👉 ቁሳቁሱን እኛ ብቻ ነን የምናወርደው ፤ የምንጭነው ብለው እራሳቸው ይወስናሉ በሰው ንብረት።
👉 ተመጣጣኝ ክፍያ አይጠይቁም።
👉 እርስ በእርስም የሚጣሉበት ሁኔታ አለ፤ በዚህም ንብረት ይወድማል አካል ጉዳት ይደርሳል። ምንም በማያገባው እዛ ባለው ግለሰብ ንብረት ላይ ጭምር ጉዳት ይደርሳል።
👉 ግለሰቦችን ማጨነቅ አለ እኛ ካላወረድነው እናወድመዋልን የሚሉም አሉ።
ይሄ እጅግ በጣም ከባድ ነገር ነው። ስለዚህ ይሄን ስራ የሚሰሩ ሰዎች ተለይተው ህብረተሰቡ ለፖሊስ መረጃ በመስጠት አደብ እንዲገዙ መደረግ መቻል አለበት ካለበለዚያ ከባድ ስጋት ነው የሚሆኑት። " ብለዋል።
ፖሊስም የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት በህገወጥ ጫኝ እና አውራጆች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ምክትል ኮማንደር ማርቆስ አሳውቀዋል።
ም/ኮማንደር ማርቆስ ፦
" በለሚኩራ ክ/ከተማ በ6 ወር በ21 መዝገቦች 80 ተከሳሾች ይዘን ምርመራ እያጣራን ነው። በተመሳሳይ በ12 መዝገቦች 45 ተጠርጣሪዎች ማረሚያ ቤት ወርደው ጉዳያቸውን በህግ እንዲከታተሉ እየተደረገ ነው።
በቦሌ ክ/ከተማ በ10 መዝገቦች 63 ተከሳሾች ላይ ክስ ተመስርቷል። 62ቱ ተይዘዋል። እነዚህም ምርመራ እየተጣራባቸው ነው።
ንፋስስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ሰፈራ የሚባል አካባቢ ባለፈው ወር የተሰራ ስራ በቀን 21/7/2014 ዓ/ም በአንድ መዝገብ 10 ተከሳሾች ይዘን ምርመራ እያጣራን ነው።
በለቡ ፖሊስ ጣቢያ ፤ ሆፕ ዩኒቨርሲቲ የሚባል አለ እዛ አፓርታማ ቤቶች አሉ እዛ የሚገቡ ሰዎች ላይ ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ በአንድ መዝገብ 13 ተጠርጣሪዎች ተይዘው በ4ቱ ላክ ሁለት ሁለት ወር እንዲወሰንባቸው ተደርጓል " ሲሉ አስረድተዋል።
ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ " አንዳንድ ስራቸውን በአግባቡ የሚሰሩ ጫኝና አውራጆች አሉ፤ በቅርቡም ጥይቶች ተጭነው እስከማጋለጥ የደረሱ መኖራቸውን ተመልክተናል " ያሉ ሲሆን ያልተገባ ስራ የሚሰሩትን ፤ ወደ ህግ ከማቅረብ ይልቅ #ተስማሙ የሚሉ የፖሊስ አባላትን ህብረተሰቡ ሲመለከት በ 991 ነፃ የስልክ መስመር እና በ 0111110111 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ከሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት ጥሪ አቅርበዋል።