TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ከአሜሪካ ኤምባሲ በኩል ይፋ በሆነ መረጃ ውይይቱ ፥ በአሜሪካ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም በሀገራቱ መካከል ስላለው ወሳኝ ኢኮኖሚያዊ እና የንግድ ግንኙነት ላይ ትኩረት ያደረገ…
#US

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ ትሬሲ አን ጃኮብሰን ከሰሞኑ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነርና ምክትል ዋና ኮሚሽነር ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ይታወሳል።

በኃላም ከገንዘብ ሚኒስትር ጋር በኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መክረው ነበር።

ትላንት ከኢትዮጵያ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ጋር በገለልተኛ የዳኝነት ስርዓት እንዲሁም የሰብአዊ መብት አያያዝ አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል።

በዛሬው ዕለት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጋር ተገናኝተዋል።

ሰላም እና እርቅ እንዲፈጠር እንዲሁም ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እርዳታ እንዲደርስ ያላቸውን ተስፋ መጋራታቸውን ከአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ባገኘነው መረጃ ደግሞ ፥ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የአሜሪካን ተጠባባቂ አምባሳደር ጃኮብሰንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ይገልፃል።

አምባሳደር ኣን ጃኮብሰን ፤ ከቅዱስነታቸው ቡራኬ ለመቀበል እና ይፋዊ የሥራ ትውውቅ ለማድረግ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የተገኙ መሆናቸውን መረጃው ይገልፃል።

ቅዱስነታቸው ከአምባሳደሯ ጋር በነበራቸው ቆይታ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት በማስተላለፍ በኢትዮጵያ የሚቆዩበት ጊዜ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን የሚችሉበት ይሆን ዘንድ አባታዊ ተምኔታቸውን ገልጸው በቡራኬ ሸኝተዋቸዋል።

@tikvahethiopia
#Afar

ህወሓት ኃይሎቹን ከአፋር ክልል፤ " ኤሬብቲ " ማስወጣቱን በመግለፅ መግለጫ አውጥቷል።

ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ የሚገኘው ህወሓት ኃይሎቹን ከአፋር ክልል ኤሬብቲ ያስወጣው ሰብዓዊ እርዳታ የማድረስ ስራን ለማገዝን ነው ብሏል።

የሰብዓዊ እርዳታ ወደክልሉ እንዲገባና ችግር ላይ ላሉ ዜጎች እንዲደረስ ከዚህ ቀደም ለሰብዓዊነት ተብሎ የተደረሰው ስምምነት ለማክበር ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቋል።

ኃይሎቹን ከኤሬብቲ ማስወጣቱን የገለፀው ህወሓት በሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት ላይ አፋጣኝ ለውጥ እንደሚጠብቅ ገልጿል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲደርስና ሁሉም አስፈላጊ አገልግሎቶች ወደነበሩበት እንዲመለሱ ለማድረግ የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት በኩል የወጣውን መግለጫ "የተሳሳተ" ብሎታል።

ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ለዶቼ ቨለ በሰጡት ቃል፤ አሁንም አፋር ውስጥ ወረዳዎችን እንደያዙ ነው ብለዋል።

አቶ ከበደ፥ "እንደዚህ አይነት ነገር ሰማን (ወጡ የሚል) ትርጉም ያለው መልቀቅ አይደለም፤ የተያዙ ቦታዎች አሉ ለቀቁ የሚል እምነት የለንም በኛ በኩል። ሰብዓዊ እርዳታው በአግባቡ እንዲደርስ በሚል ነው መንግስት ያለ ቅድመ ሁኔታ ስለፈቀደ ነው እንጂ አልተለቀቁም" ብለዋል።

ከዚህ ቀደ። የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ እርዳታው እንዲሳለጥ የህወሓት ኃይል ከአፋር ክልል ለቆ እንዲወጣ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግስት የህወሓት ኃይሎች በአፋር ክልል ዞን 2 በኃይል ይዘዋቸዋል ካላቸው ወረዳዎች መካከል አብአላ፣ መጋሌ፣ ኤሬብቲና በራህሌ ይገኙባቸዋል።

ለሰብዓዊት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ ከታወጀ በኃላ እስካሁን በአፋር በኩል ወደትግራይ የገባው 26 ተሽከርካሪ ነው።

@tikvahethiopia
#EthioTelecom #SafaricomEthiopia

ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሰረተ ልማት መጋራት እንዲሁም ትስስር ላይ ያደጉት ዘርፈ ብዙ ድርድሮች በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገልጿል።

በቅርቡ በኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም መካከል #ስምምነት_ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢትዮ ቴሌኮም የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በሌላ በኩል ፥ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሚያዚያ 1 /2014 አገልግሎት ለመጀመር እቅድ እንደነበረው ከዚህ በፊት መግለፁ ይታወሳል፤ ነገር ግን በተባለው ቀን አገልግሎት ያልጀመረ ሲሆን በቅርቡ አገልግሎት እንደሚጀምር ይጠበቃል።

ፎቶ ፦ ኢትዮ ቴሌኮም

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthioTelecom #SafaricomEthiopia ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ጋር በመሰረተ ልማት መጋራት እንዲሁም ትስስር ላይ ያደጉት ዘርፈ ብዙ ድርድሮች በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገልጿል። በቅርቡ በኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም መካከል #ስምምነት_ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢትዮ ቴሌኮም የተገኘው መረጃ ያመለክታል። በሌላ በኩል ፥ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ…
ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፦

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በላከልን መልዕክት በዛሬው ዕለት የመሰረተ ልማት መጋራት እና #በደንበኞች_መካከል_የግንኙነት_ልውውጥ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ ከበርካታ ዙር ውይይቶች በኋላ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጾልናል።

ውይይቶቹ በኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን የተመሩ መሆኑን የገለፀው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለሥልጣኑ ላሳየው ብቁ የአመራር ጥበብ ምስጋና አቅርቧል።

ስምምነቶቹን ለማጠናቀቅም ቀጣይ ሥራዎች የሚከወኑ እንደሆነም ገልጿል።

ስምምነቶቹ ከሳፋሪኮም ኢንቨስትመንት እና ከኔትዎርክ ዝርጋታ ጋር ተደምረው በዚህ ዓመት ለሚጀመረው አገልግሎት ጠንካራ መሠረት፣ ለቴሌኮም ሴክተሩ እድገት እንዲሁም ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ዲጂታል አካታችነት ዕቅድ መሳካት ወሳኝ ምዕራፍ ይሆናሉ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በከተማዋ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም የካዳስተር ምዝገባ እና እወጃ ሥራ እንደሚካሄድ አሳውቋል። ከዚህ ቀደም የመሬት ይዞታቸውን በካዳስተር ያላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መረጃዎቻቸውን ለሚቀጥሉት ተከታታይ 15 ቀናት ማዘጋጀት እንደሚችሉ ተነግሯል። ከተማ አስተዳደሩ ከ10 ዓመት በፊት ጀምሮ ሕጋዊ…
#AddisAbaba

" ... የመሬት አገልግሎት ከተመረጡ 25 ቀጠናዎች በስተቀር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ላይ መደበኛ አገልግሎት ይሰጣል " - ኤጀንሲው

የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ማምሻውን ለከተማው ኮሚኒኬሽን በሰጠው መረጃ ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት አገልግሎት ከተመረጡ 25 ቀጠናዎች በስተቀር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ላይ መደበኛ አገልግሎት ይሰጣል አለ።

መረጃውን ይፋ ባደረገው የከተማው ኮሚኒኬሽን ገፅ ላይ ፥ የተመረጡ 25 ቀጠናዎች ይባል እንጂ በዝርዝር የተገለፀ ነገር የለም።

ኤጀንሲው በተመረጡ 25 ቀጠናዎች ላይ የይዞታ ምዝገባ የሚያከናውን በመሆኑ ምዝገባውን በሚከናወንባቸው አካባቢዎች ብቻ እስከ ጳጉሜ 5 /2014 ዓ.ም አገልግሎት የሚቋረጥ መሆኑን ገልጿል።

ዛሬ " የመሬት አገልግሎት በሁሉም አካባቢዎች ላይ እንደማይሰጥ " የተሰራጨው መረጃ #ስህተት እንደሆነ ኤጀንሲው አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ይዞታቸውን በ " ዲጂታል ስርአት " ያስመዘገቡ ባለይዞታዎች አገልግሎት ማግኘት ይችላሉም ተብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ከፍተኛ ጫና እያሳደረብን ነው "

የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው ምደባ የሚጠባበቁ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ምደባው እንዲፋጠንለቸው በድጋሚ ጠይቀዋል።

የመጀመሪያውን ዙር ፈተና ተፈትነው እና ውጤታቸውን አውቀው ቤታቸው የተቀመጡ ተማሪዎች 6ኛ ወራቸውን ሊደፍኑ እየተቃረቡ ይገኛሉ።

እስካሁን ምደባ ይፋ የሚሆንበት ቀን ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ይህ ሁኔታ ተማሪዎችና ወላጆችን ጫና ውስጥ እየከተተ ነው።

መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል የሆኑ አንድ ወላጅ ልጃቸው ብሄራዊ ፈተና ወስዳ ወራት ቢቆጠሩም እስካሁን የምትማርበትን ተቋም ባለማወቋ ጫና እየደረሰባት፤ በግል እንኳን ለማስተማር ውሳኔ ላይ ለመድረስ እንደተቸገሩ፤ አመቱም እየተጠናቀቀ በመሆኑ ከእሷም አልፎ ቤተሰብ ላይ ጫናው እየበረታ መምጣቱን ገልፀዋል።

ከትምህርት እንዳትርቅ ጥረት እያደረጉ መሆኑ የገለፁት ወላጅ ፤ ነገር ግን ከመደበኛው ትምህርት ስርዓት ተማሪ መነጠሉ የሚያሳድረው ጫና ከባድ ነው ብለዋል።

መንግስት የሚስተካከሉ እና የቀረቡ ቅሬታዎች ካሉ በፍጥነት አስተካክሎ እና መፍትሄ ሰጥቶ ተማሪዎችን በፍጥነት ምደባቸውን እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል።

ሌሎች መልዕክታቸውን የላኩ የቤተሰቡ አባላት ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ውጭ ሆነው የሚያሳልፉት ጊዜ ከፍተኛ የስነልቦና ጫና ውስጥ እየጣላቸው በመሆን መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከጥቂት ቀናት በፊት ምደባን በተመለከተ ለቲክቫህ በላከው መልዕክት ትንሽ እንዲታገሱ መልዕክት ማስተላለፉ ይታወሳል።

የ2013 ዓ/ም ፈተና የመጀመሪያ ዙር #ከጥቅምት 28/2014 ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት የ2ኛው ዙር ፈተና #ከጥር 24 ጀምሮ ለተከታታይ 4 ቀን መሰጠቱትና ውጤትን ጨምሮ መቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሁለት ወር ተራዝሟል ! በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ላለፉት 6 ወራት ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ የማደራጀትና የማጥራት ስራ ሲሰሩ ነበር። በተለያዩ ምክንያቶች መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ ላልቻሉ ደንበኞች ተጨማሪ የ2 ወር ጊዜ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል። የባንክ ደንበኞች ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ከወዲሁ ወደ ባንክ በመሄድ መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። #CBE…
" ቀነ ገደቡ ሊጠናቀቅ ከ1 ወር ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል "

የባንክ ደንበኞች መረጃቸውን ወቅታዊ እንዲያደርጉ የተራዘመው የሁለት ወር ጊዜ ሊጠናቀቅ ከ1 ወር ያነሰ ጊዜ እንደቀረው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እኤአ በ27/08/2021 በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም ባንኮች የደንበኞችን መረጃ አጣርተው እንዲያደራጁ መመሪያ አውጦት ነበር።

በኃላም ስራው የብሄራዊ ባንክ ባስቀመጠው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ ለተጨማሪ 2 ወር መራዘሙ አይዘነጋም።

ይኸው የተራዘመ የ2 ወር ጊዜ ሊጠናቀቅ ከ1 ወር ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል።

መረጃቸውን ወቅታዊ ያላደረጉ የባንክ ደንበኞች አቅራቢያቸው ወዳለ የባንክ ቅርንጫፍ መታወቂያ ይዞ በመሄድ መረጃቸውን ወቅታዊ እንዲያደርጉ እና በመጨረሻ ቀን ላይ የሚፈጠር መጉላላት እና መጨናነቅ እንዲያስቀሩ ተጠይቋል።

#CBE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ... የመሬት አገልግሎት ከተመረጡ 25 ቀጠናዎች በስተቀር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ላይ መደበኛ አገልግሎት ይሰጣል " - ኤጀንሲው የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ማምሻውን ለከተማው ኮሚኒኬሽን በሰጠው መረጃ ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት አገልግሎት ከተመረጡ 25 ቀጠናዎች በስተቀር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ላይ መደበኛ አገልግሎት ይሰጣል አለ። መረጃውን…
#AddisAbaba

" ከ05/08/2014 ዓ.ም ጀምሮ በቀጣዮቹ አምስት ወራት በ25 ቀጠናዎች 21,000 አካባቢ የሚሆኑ ቁራሽ መሬቶች /parcels / ላይ ብቻ የማረጋገጥ እና ምዝገባ ስራ ይከናወናል።

እወጃ በሚደረግባቸው ቀጠናዎች ብቻ በማንኛውም ደረጃ ያለ የስም ዝውውር ይቆማል።

ነገር ግን የስም ዝውውር በሙሉ የከተማው ይዞታዎች ላይ ያልቆመና ያልታገደ መሆኑ እንገልፃለን " - የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ከ05/08/2014 ዓ.ም ጀምሮ በቀጣዮቹ አምስት ወራት በ25 ቀጠናዎች 21,000 አካባቢ የሚሆኑ ቁራሽ መሬቶች /parcels / ላይ ብቻ የማረጋገጥ እና ምዝገባ ስራ ይከናወናል። እወጃ በሚደረግባቸው ቀጠናዎች ብቻ በማንኛውም ደረጃ ያለ የስም ዝውውር ይቆማል። ነገር ግን የስም ዝውውር በሙሉ የከተማው ይዞታዎች ላይ ያልቆመና ያልታገደ መሆኑ እንገልፃለን " - የአዲስ አበባ ከተማ…
#Update

በአዲስ አበባ የመሬት ስም ዝውውርና የኮንዶሚኒየም ሽያጭ ስም ዝውውር የታገዱ ሰፈሮችን የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ይፋ አድርጓል።

በተለዩት ሰፈሮች የሚገኙ ይዞታዎች የኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶችንና ሌሎችንም ጨምሮ የስም ዝውውርና ሌላውም እስከ ጳጉሜ መታገዱ ተገልጿል።

ከእነዚህ ሰፈሮች ውስጥ ፦

👉 በአራዳ ክ/ከተማ ፦ ሐግቤስ አካባቢ ፣ ጅንአድ ራስ እምሩና አግአዚ ሰፈር ፤

👉 የካ ክፍለ ከተማ ፦ ኪዳነ ምህረት ሰፈር ዞን 03 ፣ ሲግናል ሲግናል አፓርትመንት እና ቡና ቦርድ ፤

👉 ኮልፌ ክ/ከተማ ፦ አርሴማ ሰፈር ፣ አየር ጤና ለማ ነጋገዎ ሰፈር ፣ እፎይታ አየር ጤና መሰናዶ አካባቢ ፣ ሞቢልና መሳለሚያና ሌሎችም፤

👉 በቦሌ ክፍለ ከተማ ፦ ጅማ ህንፃ ፣ 24 ቀበሌ ውሃ ልማት ወይም ቅርቦትና ሌሎችንም ሰፈሮች፤

👉 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፦ ቀጠና 2 ላይ ሰፈረ ሰላም ጭማድ ፣ ሰላሌ ሰልጤ ማርያም፣ መኮድ ጃቴ ኪዳነ ምህረትና ሌሎችም ፤

👉 በልደታ ክፍለ ከተማ ፦ ማዕድን ሚኒስቴር ድል ገበያ ሰባራ ድልድይ ፤

👉 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፦ ቃጤ ሰፈር ድላችን ኮንዶሚኒየም ፥

👉 በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፦ ላፍቶ ኢንዱስትሪ ሰፈር ፣ ላፍቶ መድሃኒያለም አካባቢ ፣ 54 ማዞሪያ አካባቢ ፣ ላፍቶ 1 ኮንዶሚኒየም በሙሉ የመሬት ሽያጭና ስም ማዛወር እስከ ጳጉሜ አምስት ድረስ ለ5 ወር ታግዶ ይቆያል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ / የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ገንዘብ በጣም አስፈለገዎት፣ ክፍት የሆነ ባንክ የለም፣ የ ኤ.ቲ.ኤም ካርድዎንም አልያዙም...አይጨነቁ የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግን ተጠቅመው በአቅራቢያዎ ከሚገኙት የ ኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች ያለ ካርድ ገንዘብዎን በቀላሉ ማውጣት ይችላሉ።

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
#WFP #UN #Ethiopia #TigrayRegion

ዛሬ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ አልሚ ምግብን ጨምሮ ህይወት አድን ፍጆታዎችን የጫኑ 47 ተሸከርካሪዎች ወደ ትግራይ ጉዞ መጀመራቸውን አሳውቋል።

ከ47ቱ ተሽከርካሪዎቹ በተጨማሪ ለመሰረታዊ አገልግሎቶች የሚውል ነዳጅ የጫኑ 3 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።

ከሁሉም ባለስልጣናት በተደረገው ድጋፍ እስካሁን ጉዞው የተሳካ እና መልካም የሚባል እንደሆነ ጠቁሟል።

ለሰብዓዊነት ተብሎ ግጭት የማቆም ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ እስካሁን ድረስ ወደ 26 ተሸከርካሪዎች ብቻ ናቸው ወደ ክልሉ የገቡት።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ በችግር ላይ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን የሰብዓዊ ፍላጎት ለማሟላት በየዕለቱ 100 ተሽከርካሪዎች ወደ ክልል መግባታ እንዳለባቸው ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል።

በሌላ መረጃ ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት በ “any other business” ስር ዛሬ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ በዝግ ይመክራል።

በስብሰባው ላይ የሰብአዊ ጉዳዮች ም/ ዋና ጸሃፊ ማርቲን ግሪፍትስ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የዛሬውን ስብሰባውን የጠየቁት የA3 የምክር ቤቱ አባላት (ጋቦን፣ ጋና እና ኬንያ) ናቸው። #በA3 ብቻ በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ስብሰባ ሲጠየቅ ይህ የመጀመሪያው መሆኑን ተመድን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን አስነብቧል።

@tikvahethiopia