#Repost
የደም እጥረት ተከስቷል።
አሁን ወቅቱ የፆም በመሆኑ አዲስ አበባ ከተማ ጨምሮ በሁሉም የደም ባንኮች የሚሰበሰበው የደም መጠን በመቀነሱ የደም እጥረት አጋጥሟል።
የብሔራዊ ደም ባንክ በላከልን መልዕክት ህብረተሰቡ ደም እንዲለግስ ጥሪ አቅርቧል።
#ይህንን_መልዕክት_ያጋሩ !!
@tikvahethiopia

#ኩርሙክ 📍
ትላንት ምሽት 3:00 ገደማ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፣ ኩርሙክ ወረዳ ድንገት በተነሳ አውሎ ነፋስ በመኖሪያ ቤቶች እና በተቋማት ላይ ጉዳት ደረሰ።
ድንገተኛው አውሎ ነፋስ በወረዳው 7 ቀበሌዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።
አውሎ ነፋሱ በወረዳው ፦
👉 አሸሽሬ፣
👉 ዱልሆደ፣
👉 አደንግዝ፣
👉 ቤለሁጅብላ፣
👉 ዱልሸታሎ፣
👉 ኦገንዱ፣
👉 አቀንደዩና ሳሊማ ቀበሌዎች በሰዎች፣ በመኖሪያ ቤቶች፣ በመንግስት ት/ቤቶች፣ በመብራት ፖሎች፣ በእንስሳት ጤና ኬላዎች፣ በንግድ ሱቆች፣ የሀይማኖት ተቋማትና በቤት እንስሳት ላይ ሙሉ ለሙሉና በከፊል ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ የደረሰው የጉዳት መጠን በወረዳ ደረጃ በተቋቋመ አጣሪ ኮሚቴ እየተጣራ ነው ተብሏል።
መረጃው የኩርሙክ ወረዳ ነው።

#ETHIOPIA
የ2021 የዓለም የረሃብ ተጋላጭነት ደረጃ (Global Hunger Index) ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ተደርጓል።
በ2021 በዓለም የረሃብ ተጋላጭነት ልኬት ደረጃ ውስጥ ሙሉ መረጃ ማቅረብ የቻሉ 116 ሀገራት የተካተቱ ሲሆን ኢትዮጵያ 90ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በዓለም የረሃብ ተጋላጭነት ደረጃ 4 መስፈርቶች በልኬትነት የተቀመጡ ሲሆን እነዚህም ፦
- በይዘቱ ያልተመጣጠነ አመጋገብ፤
- ስር የሰደደ የህፃናት የተመጣጠነ የምግብ እጥረት (ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት፤ ከቁመታቸው ጋር የማይመጣጠን ክብደት ላይ መገኘት)፤
- ከአምስት ዓመት በታች ህፃናት ከእድሜያቸው በታች ክብደት ላይ መገኘት፤
- ከ5 ዓመት በታች ህፃናት ሞት ናቸው።
በዚህ ልኬት ኢትዮጵያ ከ116 ሀገራት 90ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
የሀገራቱ ደረጃ በተለያየ መለኪያ የተቀመጠ ሲሆን ከፍተኛው የልኬት መጠን 0 ሲሆን ዝቅተኛ እጅግ አስከፊ የተባለው 100 ሆኖ ተቀምጧል፤ ኢትዮጵያ 24.1 ነጥብ ተሰጥቷል።
ሀገራቱ ዝቅተኛ ፣ መካከለኛ ፣ አሳሳቢ ፣ አደገኛ ፣ እጅግ በጣም አሰገኛ ደረጃ ላይ ያሉ ተብሎ የተለየ ሲሆን ኢትዮጵያ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ናት።
የኢትዮጵያ የምግብ እጥረት ደረጃ ከሱማሊያ፣ ማዳጋስካር፣ ሞዛምቢክ፣ ጅቡቲ፣ ሩዋንዳ፣ ከሱደን እና ታንዛኒያ የተሻለች ስትሆን ከኬንያ ፣ ማላዊ ፣ ሞሪሺየስ በታች ናት።
በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ በድርቅ፣ በትግራይ ፣ አፋር እና አማራ በጦርነት በመጪው አመት የሚኖረው የሰብዓዊ ድጋፍ ጥያቄ ያሻቅባል ተብሏል።
የኢትዮጵያ 25 % ስንዴ ከዩክሬን የምታስገባ በመሆኑ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት በኢትዮጵያ ላይ ተፅእኖ ይኖረዋል መባሉን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።
ፎቶ ፦ እስራኤል ኃይሉ

የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፦
" ከዓለም ህዝብ ሩብ ያህሉ (2 ቢሊዮን ህዝብ) በጦርነት ቀጠና ውስጥ እየኖረ ነው።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ሁከትን የፈጠሩ ከፍተኛ ግጭቶች አሁን ላይ ተስተውለዋል።
በየመን፣ በሶሪያ፣ በሚያንማር፣ በሱዳን፣ ሄይቲና ሳህል ቀጠና ያሉ ጦርነቶች እንዲሁም የቅርብ ጊዜው የዩክሬኑ ጦርነት ዓለም የተገነባበትን ስርዓት የሚሸረሽሩ ናቸው።
እነዚህ ጦርነቶች #በምግብ፣ #በነዳጅ እና #በማዳበሪያ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንዲኖር ምክንያት ሆነዋል።
ባለፈው ዓመት ብቻ 84 ሚሊየን ሰዎች ጦርነት በፈጠረው ሁከትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ቤታቸውን ለቀው ተሰደዋል።
በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተደረገው ጦርነትም 4 ሚሊዮን ዜጎችን ከዩክሬን ሲያስወጣ በሀገሪቱ ውስጥ ደግሞ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሆኑት እንዲፈናቀሉ አድርጓል።
በዚህ ዓመት ብቻ 274 ሚሊየን ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 17 በመቶ ጨምሯል "
#AlAIN

TIKVAH-ETHIOPIA
📩 ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የምግብ ዘይት ዋጋ ከሳምንታት በፊት ከነበረበት ምን አይነት ለውጥ እየተመለከታችሁ ነው ? አቅርቦቱስ እንደልብ አለ ? ከተማችሁን በመግለፅ በ @tikvahethiopiaBOT መልዕክታችሁን አስቀምጡልን። @tikvahethiopia
#TikvahFamily🍛
" በሚዲያው ላይ የሚነገረው እና በመሬት ላይ ያለው ሁኔታ አይገናኝም " - የቲክቫህ አባላት
ከዘይት ዋጋ ጋር በተያያዘ ከሳምንታት በፊት ከነበረው ምን የተቀየረ ነገር አለ ? አቅርቦትስ እንደልብ እየተገኘ ነው ? የሚል ጥያቄ ለቤተሰቦቻችን ቀርቦ ነበር።
በሁሉም አቅጣጫዎች የሚገኙ የቤተሰብ አባላቶች መልዕክታቸውን በመላክ ሁኔታው አስረድተዋል። ያለውን ችግር እና ምሬት ገልፀዋል፤ መፍትሄ ይፈለግ ዘንድም ጠይቀዋል።
በአንዳንድ ቦታዎች አቅርቦቶች ቢኖርም በዋጋው ላይ አንዳች ግን ለውጥ እንዳላዩ የገለፁት አባላቶቻችን በአንዳንድ ቦታ ደግሞ አቅርቦት ማነስ ምክንያት በሚባለው ዋጋ ለመግዛት እራሱ ማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀዋል።
በተለይ ከውጭ የሚገባው የፈሳሽ ዘይት ዋጋ አምስት ሊትሩ አሁንም ከ880 - 1000 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው ፤ እንዲህ ያሉ መለማመዶች ተገቢ እንዳልሆነ አንስተዋል።
ዋጋውን እንዲህ በየቀኑ እያለማመዱን በዚሁ ተሰቅሎ እንዳይቀር ያሰጋናልም ብለዋል።
መወደዱን የተቀበልን በድህነት ውስጥ ያለን ዜጎች መከራ ላይ ነን፤ ለመኖርም እየሰጋን ነው ሲሉ ያሉበትን የከፋ ሁኔታ አስረድተዋል።
የነዋሪው ገቢ አይጨምርም ዘይት ሆነ ሌላው ሁሌም ዋጋው እንደናረ ነው ፤ ዓለም አቀፍ ሁኔታው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለመረዳት ባያስቸግርም እዚሁ ሀገር ውስጥ ያለው የከፋ አሻጥር፣ ሙስና፣ የአስተዳደር ጉድለት ችግሩን እያባባሰው ነው ብለዋል።
ከተለያዩ ከተሞች በ @tikvahethiopiaBot የተላኩ መልዕክቶችን በጥቂቱ ከታች ያንብቧቸው።
(በተጨማሪ ቤተሰቦቻችን በብዙ ሺዎች የሚቆጠረውን የናተን አስተያየት በአንድ ለመሰብሰብ የሚከብድ ስለሆነ ከታች ባለው አስተያየት መስጫ ላይ ተጨማሪ ማስቀመጥ ትችላላችሁ)
NB. ውድ ቤተሰቦቻችን እንደሁል ጊዜው ማንኛውም የጥላቻ ንግግር ሆነ ሃሳብ፣ ስድብ፣ ሰውን ማንቋሸሽና ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ መልዕክት ማስፈር በቀጥታ እስከመጨረሻው ከቤተሰባችን ጋር እንደሚያለያይ ይታወቅ።
https://telegra.ph/Tikvah-Family-04-05

Telegraph
Tikvah Family
#የምግብ_ዘይት ከሳምንታት በፊት ከነበረው የዘይት ዋጋ አሁን የታየ ለውጥ አለ ? ዘይትስ እንደልብ ይገኛል ? ከአዲስ አበባ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፦ • " የዘይት ዋጋ : 950 ብር አድራሻ : አዲስ አበባ ቂርቆስ " - Breket (ከአዲስ አበባ) • " አረ ለውጥ የለውም አሁንም ኮተቤ 02 አካባቢዎች የሚሸጠው 910/890 ብር ነው ምንም ለውጥ የለም " - Serawit (ከአ/አ) • " የዘይት ዋጋ…
#ነዳጅ
ኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተቀራራቢ ለማድረግ እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የዋጋ ተመን ለማውጣት መታቀዱ ታውቋል። የመንግስት ድጎማም ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ብቻ እንዲሆን ታስቧል።
አቶ ገብረመስቀል ጫላ (የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር) ለህ/ተ/ም/ቤት የሚኒስቴሩን የ8 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የተናገሩት ፦
" ነዳጅ እኛ ድሃ ሀገር ሆነን ስናበቃ ፥ ከውጭ ሀገር በዶላር ነው ፤ ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው ለነዳጅ የምናወጣው የምናስገባውን ነዳጅ የምንሸጠው ደግሞ ከዋጋው 50 % ወይም ከዛ በላይ ሰብረን ነዳጅ ለኢኮኖሚ ፣ ለምርታማነት ያለውን ፋይዳ በመረዳት የኢትዮጵያ መንግስት እዳውን ለራሱ ተሸክሞ ከዋጋው 50 % ሰብሮ ሲሸጥ ይሄ ነዳጅ ግን ከአካባቢ ሀገሮች ዋጋ ጋር ተመሳሳይ ስላልሆነ እኛ ጋር 30 ብር የሚሸጥ ናፍጣ ጅቡቲ 100 ብር ስለሚሸጥ ከጅቡቲ አምጥተን ስናበቃ ከጅቡቲ የጫነው ቦቴ ተመልሶ ጅቡቲ እያራገፈ ስለሆነ ወይም ሶማሌላንድ እያራገፈ ስለሆነ ዋናው ጉዳይ የነዳጅን ዋጋ ወደ ዓለም ዋጋ ማስተካከል ነው፤ አለዚያ ሁል ጊዜ እኛ በዶላር እየገዛን ነዳጅ ዋጋው ከፍ ወዳለው ሀገር ለሊት እንዲሁም በኮንትሮባንድ እየወጣ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። "

በሩስያ ኤምባሲ ላይ ፊታቸውን ያዞሩ ነዳጅ አቅራቢዎች⛽️
በዓለም ላይ ሁለተኛዋ ሀብታም የነዳጅ አምራች ሀገር ሩስያ አይርላንድ ሀገር ደብሊን የሚገኘው ኤምባሲዋ በነዳጅ እጥረት ምክንያት ልመና ገብቷል።
ነገሩ ደግሞ የዩክሬን ጦርነት ነው ፤ አይርላንድ ያሉ ነዳጅ አቅራቢዎች ሩስያ በዩክሬን ላይ " ወራራ ፈፅመሻል " በሚል አገልግሎት አናቀርብም ብለው አድመዋል።
ይህንን ተከትሎ የሩስያ ኤምባሲ የአይርላንድ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ እየጠየቀ ነው። ኤምባሲው ድርጊቱን አድሏዊ ያለው ሲሆን የአይርላንድ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።
ኤምባሲው አሁን ላይ ነዳጅ እየጨረሰ ሲሆን በእጁ ላይ ያለው የሚቆይለት ይህ ሳምንት እስኪያበቃ ድረስ መሆኑን የአይሪሽ ኒውስ ዘገባ ያሳያል።
ይህ መረጃ ይፋ ከተደረገ በኃላ የነዳጅ አቅራቢዎቹ ድርጊት በርካታ ሩስያውያን አስቆጥቷል።
ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ በሩስያና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት መካከል ያለው መቃቃር በየዕለቱ እየጨመረ ሲሆን በርካታ ሀገራት የሩስያን ዲፕሎማቶችን ከሀገራቸው እያባረሩ ናቸው።

#GreyImport
ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ?
ሙሉ ከወገብ በላይ (ቦዲ) - 950ብር
የቦርጭ ብቻ -650 ብር
ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚቀንስ እና ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ስልክ፦ 0913979706 ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ?
ሙሉ ከወገብ በላይ (ቦዲ) - 950ብር
የቦርጭ ብቻ -650 ብር
ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚቀንስ እና ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ስልክ፦ 0913979706 ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሮበርት ሜንዴዝ የቀረበው S.3199 ረቂቅ ህግ ዛሬ ማለፉ ተሰምቷል። ኮሚቴው ፤ "በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማበረታታ " በሚል ርዕስ የቀረበው S.3199 ላይ ተወያይቶ ማማሻያ ካደረገ በኃላ ነው ማሳለፉ የታወቀው። የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ ተመልክቶ ያሳለፈው S.3199 ረቂቅ ህግ…
#USA
የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ማዕቀቦችን ይጭናል የተባለውን ረቂቅ ህግ ለማዘግየት መስማማታቸውን ዘ አፍሪካን ሪፖርት ዘግቧል።
እንደ ዘ አፍሪካን ሪፖርት ዘገባ ይህ ውሳኔ የመጣው ከሳምንታት በፊት በሰብዓዊነት ላይ የተሰመሰረት ግጭት የማቆም ውሳኔ ላይ ተንተርሶ ሲሆን የተደረሰው ስምምነት ተግባር ላይ እስከዋለ ድረስ የኮንግረሱ አባላት ረቂቅ ህጎችን ለማዘግየት ተስማምተዋል።
ጦርነቱ የሚያገረሽ ከሆነ ግን እንዲዘገዩ የተደረጉት ረቂቅ ሕጎች እንደገና እንደሚንቀሳቀሱ ተሰምቷል።
አሁን ኮንግረሱ ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ ረቂቅ ህጉ እንዲዘገይ የተስማማውን ውሳኔ በተመለከተ የኮሚቴው ህግ አውጪዎች ጉዳዩ ለኢትዮጵያ መንግስት፣ ለኤርትራ መንግስት፣ እና ለትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ግልፅ መልዕክት ያስተላለፈ ነው ፤ ረቂቅ ህጉ ለመጨረሻ ድምጽ አሰጣጥ ከቀረበ በፍጥነት ለማለፍ በቂ ድምጾች አሉ ብለዋል።
የአሜሪካ ኮንግረስንና ሴኔትን እንዲሁም የረቂቅ ሕጎችን ሂደት የሚከታተለው የGovTrack.us H.R. 6600 እና S.3199 ረቂቅ ህጎችን ስለመዘግየታቸው የሚገልጽ መረጃ ይፋ አላደረገም።
እ.ኤ.አ መጋቢት 29 የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ባለፈው አመት ህዳር ወር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቀውን S.3199 ረቂቅ ህግ (በኢትዮጵያ ሰላም እና ዴሞክራሲ ለማበረታታ) እንዳሳለፈው ይታወሳል።
NB : እንዲዘገይ ተደረገ ከተባለው ረቂቅ ህግ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ሚዲያዎች " ተቋረጠ " ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን በኢትዮጵያ የመረጃ አጣሪው ድረገፅ ኢትዮጵያ ቼክ አሳውቋል።

#Qatar2022
" ለኳታሩ 2022 የዓለም ዋንጫ በዳኝነት እንዳጫውት በፊፋ መመረጤን አላውቅም " - ባምላክ ተሰማ (ለቢቢሲ)
ዓለም አቀፍ ዳኛ ባምላክ ተሰማ "ለኳታሩ 2022 የዓለም ዋንጫ በዳኝነት እንዳጫውት በፊፋ መመረጤን አላውቅም" ሲል ተናግሯል።
ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፥ " ምንም ነገር አላውቅም። በይፋ የደረሰኝ ነገር የለም " ብሏል።
ባምላክ ተሰማ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ እንዲዳኙ በFIFI ከተመረጡ 8 አፍሪካውያን ዳኞች መካከል አንዱ መሆኑን የምዕራብ አፍሪካ ድረ-ገጾች እና በሀገራችን የተለያዩ ሚዲያዎች ሲዘግቡ ነበር።
" እንደዚህ ዓይነት መረጃ ከየት እንደሚመጣ አላውቅም" ያለው ኢንተርናሽናል አልቢትር ባምላክ ተሰማ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ በፊፋ ስለመመረጡ የወጡ ዘገባዎችን መመልከቱን ግን ተናግሯል።
የተለያዩ ሚዲያዎች ባምላክ ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ መመረጡን የዘገቡት ፊፋን ዋቢ አድርገው ሲሆን በፊፋ ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ የተባለ ነገር የለም።
ባምላክ ፊፋ የዓለም ዋንጫን የሚመሩ ዳኞችን ማንነት ይፋ ለማድረግ ጊዜው የፈጠነ ነው ብሎ እንደሚያስብም ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ገልጿል።

Photo
#Update
እስር ላይ ከነበሩ ጋዜጠኞች መካከል እስካሁን ስይፈታ የቆየው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ዛሬ ረቡዕ ከእስር መፈታቱ ተገልጿል። [ https://t.iss.one/tikvahethiopia/65538 ]
" ተራራ ኔትዎርክ " የተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ አቋቁሞ ሲሰራ በነበረበት ወቅት ታህሳስ 1 ቀን የታሰረው ጋዜጠኛ ታምራት ከ118 ቀናት እስር በኃላ መፈታቱን የሚሰራበት ሚዲያ አሳውቋል።
ጋዜጠኛ ታምራት ከታሰረ በኃላ በተደጋጋሚ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን በ50 ሺህ ብር ዋስ ነው ከእስር የተፈታው።
ከዚህ ቀደም ጋዜጠኛ መአዛ መሃመድ፣ ጋዜጠኛ እና አክቲቪስት ኢያስፔድ ተስፋዬ ፣ ጋዜጠኛ ክብሮም ወርቁ ፣ የአሶሴትድ ፕረስ (AP) ጋዜጠኛ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ ከእስር መፈታታቸው ይታወቃል።

#ZOnlineShopping
የጀርባና የወገብ ችግር አለቦት?
ሙሉ የጀርባ አና የወገብ ቀበቶ 950 ብር
የትከሻ ቀበቶ 650 ብር
የመቀመጫ (Cushion) 850 ብር
የጀርባ መደገፊያ (Pillow) 750 ብር
የጀርባ መጉበጥ ችግርን ፣ የጀርባ ዲስክ መንሸራተት በእድሜ መግፋት የሚመጡ የጀርባ ችግሮች የሚከላከልና ቀጥያል እና ማራኪ ቁመና የሚያላብስ
ስልክ ፦ 0989055551 ፡ ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን።
አድራሻ ፦ ቦሌ አቢሲንያ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ