TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#BenishangulGumuz📍

በኢትዮጵያ በተለያየ አቅጣጫ በጦርነት እና በግጭት ምክንያት እጅግ በርካታ ወገኖቻችን ተፈናቅለው ይገኛሉ።

በርካታ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ከሚገኙባቸው አካባቢዎች አንዱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ነው።

በክልሉ በተለያየ ጊዜ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው እርዳታ የሚጠባበቁ ወገኖቻችን ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ከክልሉ የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን እንደተገኘው መረጃ አሁን በክልሉ ከ400 ሺህ በላይ ተፈናቅይ ይገኛል።

ከመኖሪያቸው ከተፈናቀሉ ጀምሮ በርካታ ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ የሚናገሩት ተፈናቃይ ወገኖቻችን ዝናብ እና ፀሃይ እየተፈራረቀባቸው መሆኑን እና የሚደረግላቸው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ አስረድተዋል።

ከተፈናቃዮቹ ብዛት ያላቸው ሴቶች፣ ህፃናት ፣ ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን በእድሜ የገፉ አረጋዊያን በመጦሪያ እድሜያቸው ተፈናቅለው እየተንገላቱ ናቸው።

እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ የሚገልፁት ተፈናቃዮች ግን በቂ እንዳልሆነ ምግብ፣ የህክምና፣ አልባሳት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል።

ክልሉን የሚያስተዳድሩት አቶ አሻድሊ ሀሰን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል፤ በክልሉ ከደረሰው ጉዳት እና ካለው ተፈናቃይ ቁጥር አንፃር የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀው ለመንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ አጋር አካላት ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

እየቀረበ ካለው ጥሪ ጋር በተያያዘ ፤ Action for Social Development and Environmental Protection Organization (ASDEPO) የተባለ ድርጅት ከ100 ሺህ በላይ ሰዎችን ለመድረስ 40 ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘለት ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን የማረሚያ ቤት አዛዥ ተወካይን ጨምሮ 3 የጸጥታ አካላት እንደታገቱበት ገለፀ።

እገታው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን መፈፀሙን ገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ ፥ በአሁን ሰዓት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ የኦሮሚያና የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ጥረት መጀመራቸውን አሳውቋል።

ፖሊስ እንደሚለው በማረሚያ ቤት ኃላፊዎቹ ላይ እገታው የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ መጋቢት 22/2014 ዓ.ም ከአሶሳ ከተማ ወደ ካማሺ ዞን እየሄዱ ባሉበት ወቅት መንገድ ላይ ነው።

ታጋቾቹ የት እንዳሉ እና በምን ምክንያት እንደታገቱ ሙሉ መረጃ ባይኖርም እስከ ትላንት በስቲያ ድረስ በሕይወት እንዳሉ መረጃ እንዳለው ፖሊስ ገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ምስጋናው እንጅፈታ ፥ ታጋቾቹ " በሌላ ስልክ አስደውለው በሕይወት እንዳሉና "አታስቡ" የሚል መልዕክት ለቤተሰብ ማስተላለፋቸውን ገልፀዋል።

ክልሉ፥ ከኦሮሚያ ክልል ጋር እየተነጋገረ ሲሆን የክልሉ አባ ገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ግለሰቦቹን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረጉ መሆኑን ተገልጿል።

በካማሺ ዞን በኩል የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ወደ ስፍራው አምርተው ቀጥታ ግንኙነት በማድረግ በውይይት ሰዎቹ እንዲለቀቁ ለማድረግ እቅድ ያለ ሲሆን እኚሁ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ስፍራው ያመራሉ ተብሏል።

የአጋቾቹ ማንነት በተመለከተ ም/ ኮሚሽነር ምስጋናው በሰጡ ቃል እስካሁን በግልፅ የተደረሰበት ነገር እንደሌለ ፤ ነገር ግን በመረጃ ደረጃ በአካባቢው የ " ኦነግ ሸኔ " ኃይል በስፋት እንደሚንቀሳቀስ ገልፀው እገታውን የፈፀመው " ኦነግ ሸኔ " ነው የሚል ጥርጣሬ አለን ማለታቸውን #ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Update

የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በ108 ዶላር እየተሸጠ ነው።

ዛሬ የ1 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 108 ዶላር እየተሸጠ የሚገኝ ሲሆን በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት 1 በርሜል ነዳጅ 104.4 ዶላር በሆነ ዋጋ እየተሸጠ ነው።

ሩስያና ዩክሬን የገቡበት ጦርነት መፍትሄ አለናግኘቱን ተከትሎ አሁንም በነዳጅ ዋጋ ላይ እያሳደረ የሚገኘው ተፅእኖ እጅጉን በርትቷል።

#OilPrice

@tikvahethiopia
የአውሮፓ ሀገራት የሩስያ ዲፕሎማቶችን ከሀገራቸው እያባረሩ ነው።

በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ የለየለት መካረር ውስጥ የገቡ የአውሮፓ ሀገራት የሩስያን ዲፕሎማቶችን እያባረሩ ይገኛሉ።

ዴንማርክ 15 የሩስያ ዲፕሎማቶች፣ ጣልያን ከደህንነት ጋር በተያያዘ 30 የሩስያ ዲፕሎማቶችን፣ ስውዲን 3 የሩስያ ዲፕሎማቶችን፣ ስፔን ወደ 25 የሚደርሱ የሩስያ ዲፕሎማቶችን ፣ ፈረንሳይ 35 ዲፕሎማቶችን፣ ጀርመንም ቁጥራቸው ያልታወቀ ዲፕሎማቶችን አባረዋል።

ሉታኒያ ደግሞ የሩሲያ አምባሳደር ከሀገሪቱ ለቀው እንዲወጡ አዛለች።

ሩያስ ሀገራቱ እየወሰዱ ያሉትን በብዛት ዲፕሎማቶችን የማባረር ድርጊት " አጭር እይታ ያለው እርምጃ ነው " ፥ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን እድሎች የሚያጠብ እና ግንኙነቶችን የሚያወሳስብ ስትል ኮንናዋለች።

@tikvahethiopia
#Repost

የደም እጥረት ተከስቷል።

አሁን ወቅቱ የፆም በመሆኑ አዲስ አበባ ከተማ ጨምሮ በሁሉም የደም ባንኮች የሚሰበሰበው የደም መጠን በመቀነሱ የደም እጥረት አጋጥሟል።

የብሔራዊ ደም ባንክ በላከልን መልዕክት ህብረተሰቡ ደም እንዲለግስ ጥሪ አቅርቧል።

#ይህንን_መልዕክት_ያጋሩ !!

@tikvahethiopia
#ኩርሙክ 📍

ትላንት ምሽት 3:00 ገደማ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፣ ኩርሙክ ወረዳ ድንገት በተነሳ አውሎ ነፋስ በመኖሪያ ቤቶች እና በተቋማት ላይ ጉዳት ደረሰ።

ድንገተኛው አውሎ ነፋስ በወረዳው 7 ቀበሌዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።

አውሎ ነፋሱ በወረዳው ፦
👉 አሸሽሬ፣
👉 ዱልሆደ፣
👉 አደንግዝ፣
👉 ቤለሁጅብላ፣
👉 ዱልሸታሎ፣
👉 ኦገንዱ፣
👉 አቀንደዩና ሳሊማ ቀበሌዎች በሰዎች፣ በመኖሪያ ቤቶች፣ በመንግስት ት/ቤቶች፣ በመብራት ፖሎች፣ በእንስሳት ጤና ኬላዎች፣ በንግድ ሱቆች፣ የሀይማኖት ተቋማትና በቤት እንስሳት ላይ ሙሉ ለሙሉና በከፊል ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ የደረሰው የጉዳት መጠን በወረዳ ደረጃ በተቋቋመ አጣሪ ኮሚቴ እየተጣራ ነው ተብሏል።

መረጃው የኩርሙክ ወረዳ ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የ2021 የዓለም የረሃብ ተጋላጭነት ደረጃ (Global Hunger Index) ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ ተደርጓል።

በ2021 በዓለም የረሃብ ተጋላጭነት ልኬት ደረጃ ውስጥ ሙሉ መረጃ ማቅረብ የቻሉ 116 ሀገራት የተካተቱ ሲሆን ኢትዮጵያ 90ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በዓለም የረሃብ ተጋላጭነት ደረጃ 4 መስፈርቶች በልኬትነት የተቀመጡ ሲሆን እነዚህም ፦

- በይዘቱ ያልተመጣጠነ አመጋገብ፤
- ስር የሰደደ የህፃናት የተመጣጠነ የምግብ እጥረት (ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት፤ ከቁመታቸው ጋር የማይመጣጠን ክብደት ላይ መገኘት)፤
- ከአምስት ዓመት በታች ህፃናት ከእድሜያቸው በታች ክብደት ላይ መገኘት፤
- ከ5 ዓመት በታች ህፃናት ሞት ናቸው።

በዚህ ልኬት ኢትዮጵያ ከ116 ሀገራት 90ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የሀገራቱ ደረጃ በተለያየ መለኪያ የተቀመጠ ሲሆን ከፍተኛው የልኬት መጠን 0 ሲሆን ዝቅተኛ እጅግ አስከፊ የተባለው 100 ሆኖ ተቀምጧል፤ ኢትዮጵያ 24.1 ነጥብ ተሰጥቷል።

ሀገራቱ ዝቅተኛ ፣ መካከለኛ ፣ አሳሳቢ ፣ አደገኛ ፣ እጅግ በጣም አሰገኛ ደረጃ ላይ ያሉ ተብሎ የተለየ ሲሆን ኢትዮጵያ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ናት።

የኢትዮጵያ የምግብ እጥረት ደረጃ ከሱማሊያ፣ ማዳጋስካር፣ ሞዛምቢክ፣ ጅቡቲ፣ ሩዋንዳ፣ ከሱደን እና ታንዛኒያ የተሻለች ስትሆን ከኬንያ ፣ ማላዊ ፣ ሞሪሺየስ በታች ናት።

በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ በድርቅ፣ በትግራይ ፣ አፋር እና አማራ በጦርነት በመጪው አመት የሚኖረው የሰብዓዊ ድጋፍ ጥያቄ ያሻቅባል ተብሏል።

የኢትዮጵያ 25 % ስንዴ ከዩክሬን የምታስገባ በመሆኑ የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት በኢትዮጵያ ላይ ተፅእኖ ይኖረዋል መባሉን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ እስራኤል ኃይሉ

@tikvahethiopia
የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፦

" ከዓለም ህዝብ ሩብ ያህሉ (2 ቢሊዮን ህዝብ) በጦርነት ቀጠና ውስጥ እየኖረ ነው።

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ሁከትን የፈጠሩ ከፍተኛ ግጭቶች አሁን ላይ ተስተውለዋል።

በየመን፣ በሶሪያ፣ በሚያንማር፣ በሱዳን፣ ሄይቲና ሳህል ቀጠና ያሉ ጦርነቶች እንዲሁም የቅርብ ጊዜው የዩክሬኑ ጦርነት ዓለም የተገነባበትን ስርዓት የሚሸረሽሩ ናቸው።

እነዚህ ጦርነቶች #በምግብ#በነዳጅ እና #በማዳበሪያ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንዲኖር ምክንያት ሆነዋል።

ባለፈው ዓመት ብቻ 84 ሚሊየን ሰዎች ጦርነት በፈጠረው ሁከትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ቤታቸውን ለቀው ተሰደዋል።

በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የተደረገው ጦርነትም 4 ሚሊዮን ዜጎችን ከዩክሬን ሲያስወጣ በሀገሪቱ ውስጥ ደግሞ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚሆኑት እንዲፈናቀሉ አድርጓል።

በዚህ ዓመት ብቻ 274 ሚሊየን ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ 17 በመቶ ጨምሯል "

#AlAIN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
📩 ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የምግብ ዘይት ዋጋ ከሳምንታት በፊት ከነበረበት ምን አይነት ለውጥ እየተመለከታችሁ ነው ? አቅርቦቱስ እንደልብ አለ ? ከተማችሁን በመግለፅ በ @tikvahethiopiaBOT መልዕክታችሁን አስቀምጡልን። @tikvahethiopia
#TikvahFamily🍛

" በሚዲያው ላይ የሚነገረው እና በመሬት ላይ ያለው ሁኔታ አይገናኝም " - የቲክቫህ አባላት

ከዘይት ዋጋ ጋር በተያያዘ ከሳምንታት በፊት ከነበረው ምን የተቀየረ ነገር አለ ? አቅርቦትስ እንደልብ እየተገኘ ነው ? የሚል ጥያቄ ለቤተሰቦቻችን ቀርቦ ነበር።

በሁሉም አቅጣጫዎች የሚገኙ የቤተሰብ አባላቶች መልዕክታቸውን በመላክ ሁኔታው አስረድተዋል። ያለውን ችግር እና ምሬት ገልፀዋል፤ መፍትሄ ይፈለግ ዘንድም ጠይቀዋል።

በአንዳንድ ቦታዎች አቅርቦቶች ቢኖርም በዋጋው ላይ አንዳች ግን ለውጥ እንዳላዩ የገለፁት አባላቶቻችን በአንዳንድ ቦታ ደግሞ አቅርቦት ማነስ ምክንያት በሚባለው ዋጋ ለመግዛት እራሱ ማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀዋል።

በተለይ ከውጭ የሚገባው የፈሳሽ ዘይት ዋጋ አምስት ሊትሩ አሁንም ከ880 - 1000 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው ፤ እንዲህ ያሉ መለማመዶች ተገቢ እንዳልሆነ አንስተዋል።

ዋጋውን እንዲህ በየቀኑ እያለማመዱን በዚሁ ተሰቅሎ እንዳይቀር ያሰጋናልም ብለዋል።

መወደዱን የተቀበልን በድህነት ውስጥ ያለን ዜጎች መከራ ላይ ነን፤ ለመኖርም እየሰጋን ነው ሲሉ ያሉበትን የከፋ ሁኔታ አስረድተዋል።

የነዋሪው ገቢ አይጨምርም ዘይት ሆነ ሌላው ሁሌም ዋጋው እንደናረ ነው ፤ ዓለም አቀፍ ሁኔታው ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለመረዳት ባያስቸግርም እዚሁ ሀገር ውስጥ ያለው የከፋ አሻጥር፣ ሙስና፣ የአስተዳደር ጉድለት ችግሩን እያባባሰው ነው ብለዋል።

ከተለያዩ ከተሞች በ @tikvahethiopiaBot የተላኩ መልዕክቶችን በጥቂቱ ከታች ያንብቧቸው።

(በተጨማሪ ቤተሰቦቻችን በብዙ ሺዎች የሚቆጠረውን የናተን አስተያየት በአንድ ለመሰብሰብ የሚከብድ ስለሆነ ከታች ባለው አስተያየት መስጫ ላይ ተጨማሪ ማስቀመጥ ትችላላችሁ)

NB. ውድ ቤተሰቦቻችን እንደሁል ጊዜው ማንኛውም የጥላቻ ንግግር ሆነ ሃሳብ፣ ስድብ፣ ሰውን ማንቋሸሽና ከጉዳዩ ጋር የማይገናኝ መልዕክት ማስፈር በቀጥታ እስከመጨረሻው ከቤተሰባችን ጋር እንደሚያለያይ ይታወቅ።

https://telegra.ph/Tikvah-Family-04-05
#ነዳጅ

ኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተቀራራቢ ለማድረግ እና ከጎረቤት ሀገራት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የዋጋ ተመን ለማውጣት መታቀዱ ታውቋል። የመንግስት ድጎማም ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ብቻ እንዲሆን ታስቧል።

አቶ ገብረመስቀል ጫላ (የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር) ለህ/ተ/ም/ቤት የሚኒስቴሩን የ8 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የተናገሩት ፦

" ነዳጅ እኛ ድሃ ሀገር ሆነን ስናበቃ ፥ ከውጭ ሀገር በዶላር ነው ፤ ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው ለነዳጅ የምናወጣው የምናስገባውን ነዳጅ የምንሸጠው ደግሞ ከዋጋው 50 % ወይም ከዛ በላይ ሰብረን ነዳጅ ለኢኮኖሚ ፣ ለምርታማነት ያለውን ፋይዳ በመረዳት የኢትዮጵያ መንግስት እዳውን ለራሱ ተሸክሞ ከዋጋው 50 % ሰብሮ ሲሸጥ ይሄ ነዳጅ ግን ከአካባቢ ሀገሮች ዋጋ ጋር ተመሳሳይ ስላልሆነ እኛ ጋር 30 ብር የሚሸጥ ናፍጣ ጅቡቲ 100 ብር ስለሚሸጥ ከጅቡቲ አምጥተን ስናበቃ ከጅቡቲ የጫነው ቦቴ ተመልሶ ጅቡቲ እያራገፈ ስለሆነ ወይም ሶማሌላንድ እያራገፈ ስለሆነ ዋናው ጉዳይ የነዳጅን ዋጋ ወደ ዓለም ዋጋ ማስተካከል ነው፤ አለዚያ ሁል ጊዜ እኛ በዶላር እየገዛን ነዳጅ ዋጋው ከፍ ወዳለው ሀገር ለሊት እንዲሁም በኮንትሮባንድ እየወጣ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። "

@tikvahethiopia
በሩስያ ኤምባሲ ላይ ፊታቸውን ያዞሩ ነዳጅ አቅራቢዎች⛽️

በዓለም ላይ ሁለተኛዋ ሀብታም የነዳጅ አምራች ሀገር ሩስያ አይርላንድ ሀገር ደብሊን የሚገኘው ኤምባሲዋ በነዳጅ እጥረት ምክንያት ልመና ገብቷል።

ነገሩ ደግሞ የዩክሬን ጦርነት ነው ፤ አይርላንድ ያሉ ነዳጅ አቅራቢዎች ሩስያ በዩክሬን ላይ " ወራራ ፈፅመሻል " በሚል አገልግሎት አናቀርብም ብለው አድመዋል።

ይህንን ተከትሎ የሩስያ ኤምባሲ የአይርላንድ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ እየጠየቀ ነው። ኤምባሲው ድርጊቱን አድሏዊ ያለው ሲሆን የአይርላንድ መንግስት ጣልቃ እንዲገባ በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።

ኤምባሲው አሁን ላይ ነዳጅ እየጨረሰ ሲሆን በእጁ ላይ ያለው የሚቆይለት ይህ ሳምንት እስኪያበቃ ድረስ መሆኑን የአይሪሽ ኒውስ ዘገባ ያሳያል።

ይህ መረጃ ይፋ ከተደረገ በኃላ የነዳጅ አቅራቢዎቹ ድርጊት በርካታ ሩስያውያን አስቆጥቷል።

ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ በሩስያና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት መካከል ያለው መቃቃር በየዕለቱ እየጨመረ ሲሆን በርካታ ሀገራት የሩስያን ዲፕሎማቶችን ከሀገራቸው እያባረሩ ናቸው።

@tikvahethiopia