TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#USA

በአሜሪካ ሀገር ካሊፎርኒያ ግዛት ሳክራሜንቶ ከተማ በተከፈተ ተኩስ በትንሹ 6 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ድንገተኛው የተኩስ እሩምታ መጠጥ ቤቶች እና ምግብ ቤቶች በሚበዙበት አካባቢ የተከፈተ ሲሆን ሰዎችም እራሳቸውን ለማዳን በየጎዳናዎቹ ሲሯሯጡ እና የድረሱልን ጥሪያቸውን ሲያሰሙ ነበር ተብሏል።

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ በቦታው ሲደርስ በርካታ ሰዎች በአካባቢው ተሰብስበው እንደነበር የገለፀ ሲሆን እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር እንዳልዋለ አመልክቷል።

የሟቾች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰውም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ተገምቷል።

የከተማዋ አስተዳዳሪ የሆኑት ዴረል ሰቲንበርክ በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈና ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር ማሰብ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸዋል።

አክለውም ፤ " በጦር መሳሪያ የሚፈጸሙ ጥቃቶች የከተማችን፣ የግዛታችን እንዲሁም የአገራችን ስጋት ነው። ይህንን ለመቀነስ የሚደረጉ ማንኛውም አይነት እርምጃዎችን እደግፋለው " ማለታቸውን ቢቢሲ በደረገፁ አስነብቧል።

እንደ Gun Violence Archive ድረገፅ መረጃ በአሜሪካ ሀገር ከጦር መሳሪያዎች ጋር በተያያዘ በየዓመቱ #አርባ_ሺህ (40,000) ሰዎች የሚሞቱ ሲሆን ይህ ደግሞ በመሳሪያዎች እራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎችን ያካታታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም ተግባራዊ መሆን ይጀምራል። ከዚህ ፈተና ጋር በተያያዘ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የተናገሩት ፦ " የመውጫ ፈተና ስትራተጂ የማዘጋጀት ስራ ተጠናቋል። ስትራቴጂውን ማስተግበሪያ መመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል። ዝርዝር እቅድ ይህ የመውጫ ፈተና እንዴት ? ፤ መቼ ? ፤ በማን ? እንደሚሰጥ…
#MoE

ከሚቀጥለው ዓመት 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው የዩኒቨርሲቲ " መውጫ ፈተና " የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ አቅማቸው እስኪጎለብት፣ አካዳሚክ እና ተቋማዊ ነጻነታቸው ሙሉ በሙሉ እስኪረጋገጥ ድረሰ ፈተናው #በጊዜየዊነት በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ይህ የተገለፀው በአሁን ሰዓት የትምህርት ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች ጋር በመውጫ ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ አውደ ጥናት እያካሄደ በሚገኝበት መድረክ ነው።

በአውደጥናቱ ላይ የመውጫ ፈተናን አስመልክቶ በተለያዩ ምሁራን ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከመጪው ዓመት ጀምሮ እንዲሰጥ ለማድረግ ተገቢው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ ላይ መገለፁን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
#ዘይት

ዛሬ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በዘይት አምራች ፋብሪካዎች የመስክ ጉብኝት አድርገው ፤ ከባለሃብቶች ጋርም ውይይት አድርገው ነበር።

ጉብኝቱ የተገደረገው በፊቤላ ዘይት ማምረቻ ኢንዱስትሪ እና በደብሊው ኤ (WA) ዘይት ፋብሪካ ነው።

በዚህም ወቅት በቀን 1 ሚሊዮን 500 ሺ ሊትር ዘይት የማምረት አቅም ያለው ፊቤላ የዘይት ፋብሪካ ፦ በግብዓት አቅርቦት ችግር እና በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ካለው የማምረት አቅም ከ40 በመቶ በታች እያመረተ መሆኑን አሳውቋል።

ፊቤላ ዘይት ፋብሪካ ስራ ከጀመረ አንድ አመት ያስቆጠረ ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከ70 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት በማምረት ለህብረተሰቡ እንዳሰራጨ ገልጿል።

በተመሳሳይ የደብሊው ኤ (WA) ዘይት ፋብሪካ በግብዓት አቅርቦት እና በካፒታል እጥረት ምክንያት ካለው የማምረት አቅም እስከ 30 በመቶ ብቻ እያመረተ እንደሆነ አሳውቋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በፋብሪካው በአካል በመገኘታቸው የችግሮችን ጥልቀት መረዳታቸውን ገልፀዋል።

ሀገር በቀል የሆነ ዘይት እንዲመረት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንሚያደርግ ተናግረው ፤ የተነሱትን የመብራት፣ የካፒታል እጥረት እና የግብዓት አቅርቦት ችግሮች በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥረት እንደሚደረግ አሰረድተዋል፡፡

አሁን እየተስተዋለ ያለውን የዘይት እጥረት ለመቅረፍ መንግስት በልማት ድርጅቶች በቀጥታ ተገዝቶ እንዲቀርብ እያደረገ እና 322 ባለሀብቶች በፍራንኮ ቫሉታ ያለቀለት የምግብ ዘይት እንዲያስገቡ እየተደረገ መሆኑንና ፍትሀዊ ስርጭት እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
የደም እጥረት ተከስቷል።

አሁን ወቅቱ የፆም በመሆኑ አዲስ አበባ ከተማ ጨምሮ በሁሉም የደም ባንኮች የሚሰበሰበው የደም መጠን በመቀነሱ የደም እጥረት አጋጥሟል።

የብሔራዊ ደም ባንክ በላከልን መልዕክት ህብረተሰቡ ደም እንዲለግስ ጥሪ አቅርቧል።

#ይህንን_መልዕክት_ያጋሩ !!

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል። መንግስት የነዳጅ ዋጋ ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማስታወቁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ውሳኔው ከቀላል ጥቁር ናፍጣ፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ከአይሮኘላን ነዳጅ በስተቀር በሌሎች የነዳጅ ዓይነቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑም ነው የተገለፀው።…
#ሚያዚያ

የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፥ የሚያዚያ ወር የቤንዚን እና የናፍጣ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመጋቢት ወር ላይ ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የአውሮፕላን ነዳጅ ፣ የከባድ ጥቁር ናፍጣ እና የቀላል ጥቁር ናፍጣ የመሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ የመጣው ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ZOnlineShopping

የጀርባና የወገብ ችግር አለቦት?
ሙሉ የጀርባ አና የወገብ ቀበቶ  950 ብር
የትከሻ ቀበቶ  650 ብር
የመቀመጫ  (Cushion)   850 ብር
የጀርባ መደገፊያ (Pillow)  750 ብር
የጀርባ መጉበጥ ችግርን ፣ የጀርባ ዲስክ መንሸራተት በእድሜ መግፋት የሚመጡ የጀርባ ችግሮች የሚከላከልና ቀጥያል እና ማራኪ ቁመና የሚያላብስ
ስልክ ፦ 0989055551 ፡ ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን።
አድራሻ ፦ ቦሌ አቢሲንያ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
#ShegerDerby🇪🇹

ተጠባቂው የሸገር ደርቢ ዛሬ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሚካሄድ ይሆናል ።

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ለ 44ኛ ጊዜ የሚካሄደው የ ቡናማዎቹ እና ፈረሰኞቹ ጨዋታ ከወዲሁ በጉጉት ይጠበቃል ።

ከሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ መከላከያ ከ ሰበታ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት መርሐ ግብራቸውን ያከናውናሉ ።

Join : @tikvahethsport
'' ... በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የኛ ሙዚቃዎች አይሰሙም ይህ የሚያስቆጭ፣ የሚያሳፍርም ነው '' - አቶ ተሾመ ወንድሙ

ሰላም ኢትዮጵያ ከ25 ዓመት በፊት በስዊዲን የተመሰረተ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ከተቋቋመ 17 ዓመታት አስቆጥሯል። አሁን ላይ በ9 ክልሎች ውስጥ ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ድርጅቱ በቅርቡ " ሙዚቃዊ " የተሰኘ በአዲስ አበባ እና በስዊድን-ስቶክሆልም ውስጥ የሚሰራና በአደረጃጀቱ ሪከርድ ሌብል ፣ የሙዚቃ ህትመት፣ ዘመናዊ ስቱዲዮ፣ አርቲስት ማኔጅመንት እንዲሁም ኤቨንት ማስተባበርን የያዘ መዋቅር ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ሙሉውን ያንብቡ https://telegra.ph/Muzikawi-04-03
#Bale📍

የረመዷን ፆም ባለፈው ቅዳሜ ተጀምሯል። ይህን ታላቅ ወር ህዝበ ሙስሊሙ በጾም በዱአ እያሳለፈ ይገኛል።

በባሌ ዞን በድርቅ ውስጥ ያሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ግን " የሚጠጣ ና የሚበላ ስላሌለን ለዘንድሮ ለረመዳን ፆም ሰግተናል " ሲሉ ያለውን ችግር ያስረዳሉ።

የራይቱ ገልቢ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ሀጂ አሊዪ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ "እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ አይተን አናውቅም። ባሌ የጥጋብ ሀገር ፣ ሌሎችን የምትቀልብ ሀገር ነበረች። አሁን የሚበላ እና የሚጠጣ የለንም። ድጋፍ የማይደርስልን ከሆነ ለመፆም እንቸገራለን" ብለዋል።

አባታችን ሃጂ አሊዪ የረመዳን ወር ውስጥ እንደዚህ አይነት ችግር ገጥሞን አያውቅም ያሉ ሲሆን "የኛ ህዝብ ረመዳንን በደስታ ለመቀበል ይጠብቁ ነበር፣ አሁን ግን በስጋት የተሞላ ነው" ብለዋል።

ሌላኛው የዚሁ አከባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብዱራህማን ሃጅ አሊዪ፥ "ፈጣሪ በተዓምራቱ መፍትሔ ከበጀልን እንጂ፣ በዚህ እጥረት ውስጥ ሆነን እንፆማለን ለማለት እንደ ራይቱ ይከብዳል" ሲሉ ያስረዳሉ።

በደርቅ በተጎዳችው በባሌ ዞን በምትገኘው የራይቱ ወረዳ ወደ 60 ሺ ከሚገመቱ ከብቶች ከግማሽ በላይ እንዳለቁ እና ሌላው ደግሞ መሰደዱን ከዞኑ አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በአጠቃላይ ድርቁ በተከሰተባቸው የኦሮሚያ አከባቢዎች እስካሁን 800 ሺ የሚጠጉ ከብቶች የሞቱ ሲሆን 300 ሺ የሚሆኑ ከብቶች ደግሞ መድከማቸውን የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ከድር ተናግረዌ።

ሀጂ አሊዪ ከሰሞኑ የተወሰነ ዝናብ መዝነቡን ጠቁመው ዝናቡ ቀጥሎ ቢዘንብ የምንዘራው ዘር ፣ የምናርስበት ከብት ፤ የምንቆፍርበት ጉልበት የለንም ሲሉ የሚመለከተው አካል እንዲተባበራቸው ጠይቀዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/BALE-04-05

@tikvahethiopia
#AddisAbaba 📍

ፍሬን የበጠሰ ታክሲ ባደረሰው አደጋ ህፃናት ተማሪዎችን ጨምሮ የ6 ሰዎችን ህይወት ቀጠፈ።

በጉለሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

የትራፊክ አደጋው የደረሰው ኮድ 3 A02166 አዲስ አበባ የሆነ ሚኒባስ ታክሲ ፍሬን በመበጠሱ ሲሆን ባደረሰው ጉዳት ህጻናት ተማሪዎችን ጨምሮ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ታክሲው ከቁስቋም ሽሮ ሜዳ በመጓዝ ላይ ነበረ።

ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አጠቃላይ በ6 ሰዎች ላይ የሞት አደጋ እንዲሁም ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ እና ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል፡፡

በአደጋው የደረሰው የጉዳት መጠንና መንስኤውን ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ፖሊስ አሳውቋል ሲል የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።

More : @tikvahethmagazine
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን እና በሲዳማ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ እሁድ ምሽት በተቀሰቀሰ ግጭት ቢያንስ 5 ሰዎች ተገደሉ።

የሲዳማ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ፥ ግጭት የተቀሰቀሰው በሲዳማ ክልል፣ ጪሪ ወረዳ፣ ሀሌላ ቀበሌ ነዋሪዎች ዘንድ ታዋቂ የሆኑ የሀገር ሽማግሌ መገደላቸውን ተከትሎ ነው ብለዋል።

አዴ ሎኬ ዮኔ የተባሉት እኚሁ አባት እሁድ ምሽት 4 ሰዓት ገደማ የተገደሉት " ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ነው " ብለዋል። 

ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ በሀሌላ ቀበሌ የተቀሰቀሰው ግጭት ወደ አጎራባች ቀበሌዎች ተስፋፍቶ በሲዳማ ክልል ጪሪ ወረዳ ሱጫ ቀበሌን እና በኦሮሚያ ክልል ሻምበልና ውሮ ቀበሌዎችን አዳርሷል።

በግጭቱ እስካሁን ከሲዳማ በኩል የሀገር ሽማግሌውን ጨምሮ ቢያንስ 2 ሰዎች ሲገደሉ፤ በኦሮሚያ በኩል የ3 ሰዎች ህይወት እንዳለፈ ገልጸዋል።

ከቦናና በዳዬ ሆስፒታል በተገኘው መረጃ 15 ሰዎች በጥይት ቆስለዋል። ቦና ከገቡ 7 ሰዎች 3ቱ በብርቱ የቆሰሉ ናቸው። በዳዬ ደግሞ 9 ሰዎች ቆስለው የገቡ ሲሆን አንዱ ህክምና እርዳታ ላይ እያለ ህይወቱ አልፏል።

ሰው ላይ ከደረሰ ጉዳት ባለፈ በርካታ ቤቶች ወድመዋል።

የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ግጭቱን ለማርገብ እርምጃዎች መውሰዳቸውን የተገለፀ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የሁለቱ ክልል ኃላፊዎች፣ በአባ ገዳዎች እና በሲዳማ ሀገር ሽማግሌዎች የታገዘ ምክክር በማድረግ ግጭቱ እንዲቆም ማድረጋቸውን አቶ አለማየሁ ገልፀዋል።

የጥቃቱን ፈጻሚዎች ማንነት በተመለከተ ታጣቂዎቹን ለመለየት ማጣራት እየተደረገ ነው ሆኖም ግን "በኦሮሚያ ክልል ታጥቀው የሚዞሩ ታጣቂዎች ሊሆኑ ይችላሉ" ብለዋል።

ለጊዜው ከኦሮሚያ በኩል አስተያየት ሊገኝ እንዳልተቻለ ዘገባውን ያሰራጨው 👉ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ገልጿል።

@tikvahethiopia
#BenishangulGumuz📍

በኢትዮጵያ በተለያየ አቅጣጫ በጦርነት እና በግጭት ምክንያት እጅግ በርካታ ወገኖቻችን ተፈናቅለው ይገኛሉ።

በርካታ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ከሚገኙባቸው አካባቢዎች አንዱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ነው።

በክልሉ በተለያየ ጊዜ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው እርዳታ የሚጠባበቁ ወገኖቻችን ቁጥር እየጨመረ ሲሆን ከክልሉ የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን እንደተገኘው መረጃ አሁን በክልሉ ከ400 ሺህ በላይ ተፈናቅይ ይገኛል።

ከመኖሪያቸው ከተፈናቀሉ ጀምሮ በርካታ ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ የሚናገሩት ተፈናቃይ ወገኖቻችን ዝናብ እና ፀሃይ እየተፈራረቀባቸው መሆኑን እና የሚደረግላቸው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነ አስረድተዋል።

ከተፈናቃዮቹ ብዛት ያላቸው ሴቶች፣ ህፃናት ፣ ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን በእድሜ የገፉ አረጋዊያን በመጦሪያ እድሜያቸው ተፈናቅለው እየተንገላቱ ናቸው።

እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ የሚገልፁት ተፈናቃዮች ግን በቂ እንዳልሆነ ምግብ፣ የህክምና፣ አልባሳት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀዋል።

ክልሉን የሚያስተዳድሩት አቶ አሻድሊ ሀሰን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል፤ በክልሉ ከደረሰው ጉዳት እና ካለው ተፈናቃይ ቁጥር አንፃር የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀው ለመንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ አጋር አካላት ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል።

እየቀረበ ካለው ጥሪ ጋር በተያያዘ ፤ Action for Social Development and Environmental Protection Organization (ASDEPO) የተባለ ድርጅት ከ100 ሺህ በላይ ሰዎችን ለመድረስ 40 ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘለት ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን ከብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia