TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ጋዜጠኞቹ በዋስትና እንዲፈቱ ተወሰነ። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሶሴትድ ፕሬስ (AP) ዘጋቢ አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያ ቶማስ እንግዳ እያንዳንዳቸው በ60 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተለቅቀው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኖላቸዋል። ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኞቹ ከአገር እንዳይወጡ የጉዞ እገዳም አስተላልፎባቸዋል። ጋዜጠኞቹ በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብለ የተፈረጀውን "ሸኔ"…
ጋዜጠኞቹ ከእስር ተፈተዋል።

የአሶሴትድ ፕረስ (AP) ጋዜጠኛው አሚር አማን እና የካሜራ ባለሙያው ቶማስ እንግዳ ከእስር መፈታታቸው መረጋገጡን ኢትዮ ኒውስ ፍላሽ ዘግቧል።

ከህዳር 19 ጀምሮ ፤ " የአሸባሪውን ሸኔ ቡድንን በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ ስራ ሲሰሩ ነበር " በሚል ጥርጣሬ ተይዘው የነበሩት ጋዜጠኞች ትላንትና በዋስ እንደተለቀቁ ተረጋግጧል።

ከቀናት በፊት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በ60 ሺህ ብር ዋስትና (እያንዳንዳቸው) ከእስር ተለቅቀው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ወስኖላቸው እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Bichena📍 2 ታዳጊዎችን አግተው ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። በምስራቅ ጎጃም ዞን ብቸና ከተማ ቀበሌ 03 ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሀሊማ ሀሰን በቀን 19/07/2014 ዓ/ም ወደ ብቸና ከተማ ፖሊስ ፅ/ቤት ቀርበው የማያውቁት ሰው ስልክ እየደወለ " ልጅሽን አግተነዋልና ዛሬውኑ 400,000 ብር ካላመጣሽ እንገለዋለን " እያለኝ ነው የሚል መረጃ ለፖሊስ ይሰጣሉ።…
#ተፈርዶባቸዋል

ከቀናት በፊት መጋቢት 19 ላይ በብቸና ከተማ 2 ታዳጊዎችን አግተው ከቤተሰቦቻቸው 400 ሺ ብር የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንና የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑን መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም።

[ https://t.iss.one/tikvahethiopia/69002?single ]

ከከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ በተገኘው መረጀ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል።

የእነማይ ወረዳ ፍርድ ቤት በተጠርጣሪዎች ላይ የተጣራውን ምርመራ መዝገብ የተመለከተ ሲሆን 2ቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ መሆናቸውን በቀረቡ ማስረጃዎች አረጋግጧል።

መጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎትም 1ኛ ተከሳሽ ተሾመ ሀብቴ በ7 ዓመት ከ6 ወር ፤ 2ኛ ተከሳሽ በሀይሉ ይዘንጋው በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

መረጃው የብቸና ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ነው።

@tikvahethiopia
#Alert

የጤና ሚኒስቴር የትዊተር አካውንት ተጠለፈ።

ከ204 ሺ በላይ ተከታዮች ያሉት የሚኒስቴሩ የትዊተር አካውንት ተጠልፏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጤና ሚኒስቴር ይፋዊ የትዊተር አካውንቱ #FMoHealth ዛሬ መጋቢት 24 መጠለፉን (ሃክ መደረጉን) አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ በትዊተር ገጹ ላይ የሚለቀቁ ማንኛውም መረጃዎች እንደማይወክሉት ገልጿል።

@tikvahethiopia
#DireDawa

1443 ኛው የረመዳን ፆም ወር የአፍጢር መርሀ-ግብር በአሁን ሰአት በለገሀር አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ የአፍጢር መርሀ-ግብር ላይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ፣ የሀይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

ፎቶ ፦ የድሬዳዋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 13 ተሸከርካሪዎች በሰላም የትግራይ ክልል መዲና መቐለ መድረሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በፎቶ አስደግፎ አስታውቋል። ይህ ከታህሳስ 2014 ዓ.ም. አጋማሽ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በየብስ ትግራይ ክልል የደረሰ የሰብዓዊ ድጋፍ ነው። እንደ ዓለም ምግብ ፕሮግራም መረጃ ተጨማሪ ሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች እና ነዳጅ ዛሬ ይገባል። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ትላንትና…
#Tigray , #Mekelle 📍

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከ8 ወር በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ የነዳጅ ቦቴ ትግራይ መገባቱን አስታውቋል።

ዛሬ 47,000 ሊትር ነዳጅ መቐለ የደረሰ ሲሆን ፤ ድርጅቱ በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ ፍላጎት ለማሟላት በየሳምንቱ 200,000 ሊትር ነዳጅ ያስፈልጋል ብሏል።

ከትላንት አርብ ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ በየብስ እየገባ ይገኛል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከዚህ ቀደም በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ ፍላጎት ለማሟላት በየቀኑ 100 ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መግባት እንዳለባቸው መግለፁ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ለሰብዓዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ ማሳለፉ ፤ ከትግራይ ክልል በኩልም በጎ የሆነ ምላሽ መሰጠቱን ተከትሎ በችግር ላይ ለሚገኙ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ መግባት መጀመሩን የተለያዩ ሀገራት፣ የተለያዩ ረድኤት ድርጅቶች እያበረታቱ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#Tigray

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የህክምና፣ ምግብ እና የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችን ያካተተ ድጋፍ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ትግራይ ክልል ደርሷል፡፡

ይህም እ.ኤ.አ ከመስከረም 2021 በኋላ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ክልሉ የደረሰ የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ድጋፍ ነው፡፡

https://www.icrc.org/en/document/ethiopia-icrc-resumes-aid-convoys-tigray-after-six-months-0

@tikvahethiopia
#ZOnlineShopping

የጀርባና የወገብ ችግር አለቦት?
ሙሉ የጀርባ አና የወገብ ቀበቶ  950 ብር
የትከሻ ቀበቶ  650 ብር
የመቀመጫ  (Cushion)   850 ብር
የጀርባ መደገፊያ (Pillow)  750 ብር
የጀርባ መጉበጥ ችግርን ፣ የጀርባ ዲስክ መንሸራተት በእድሜ መግፋት የሚመጡ የጀርባ ችግሮች የሚከላከልና ቀጥያል እና ማራኪ ቁመና የሚያላብስ
ስልክ ፦ 0989055551 ፡ ያሉበት ቦታ በነፃ እናደርሳለን።
አድራሻ ፦ ቦሌ አቢሲንያ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ
#AutismDay

" ምሉዕ ፋውንዴሽን " የኦቲዝም ቀንን ትላንት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር አከበረ። የትላንቱ መርሐግብር '' ተለየው እንጂ አላነስኩም '' በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው።

በ2013 ዓ/ም የተመሰረተው የበጎ አድራጎት ማኅበሩ ፤ በኦቲዝምና ሌሎች ልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ልጆች፤ ታዳጊዎች እና ወላጆቻቸው ያማከለ የልህቀት ማዕከል ሲሆን በውስጡም ቤተመጻሕፍት ፣ የክህሎት ማስጨበጫ ፣ የልዩ ፍላጎት ልጆች ወላጆች ውይይት የሚያደርጉበትና ሌሎች ማኅበረሰብ ተኮር ስራዎችን የያዘ ነው።

በወ/ሮ ትዕግስት ኃይሉና አቶ ክንፈ ፅጌ የተመሰረተው ማኅበሩ የበኩር ልጃቸው በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖር ታዳጊ በመሆኑ በየትምህርት ቤቱ፣ በህጻናት መጫወቻ ስፍራዎች እንዲሁም በተለያዩ የህዝብ ተቋማት ላይ ያጋጠማቸውን ውጣ ውረዶች ሌሎች እንዳይጎዱበት ለማገዝ መቋቋሙን ሰምተናል።

በተጨማሪም በልጆቻቸው አካላዊ፣ አዕምሮአዊ እና ስነ-ልቦናዊ እድገት ላይ የነበረውን ውስንነት ለመቅረፍ የተጠቀሙባቸውን መንገዶች እና በዘርፉ ያካበቷቸውን ልምዶች ለሌሎች ለማጋራት በማሰብ የመኖሪያ ቤታቸውን ክፍት በማድረግ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲገለገሉበት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

ኦቲዝም የአዕምሮ ዕድገት መዛባት መንስዔ በውል ባይታወቅም የልጆቹን ዕምቅ አቅም በመፈለግና በማውጣት የተሻለ ዜጋ እንዲሆኑ ማስቻል ይቻላል።

በአፍሪካ የኦቲዝም የአዕምሮ መዛባት ችግር ስርጭት በስፋት ባይጠናም ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በዕድገት ችግር ውስጥ ካሉ ከመቶ ልጆች ውስጥ ከ 11 -33 የሚሆኑት በኦቲዝም የአዕምሮ ዕድገት መዛባት ውስጥ እንደሚኖሩ ግን አንዳንድ ጥናቶች ይጠቁማሉ።

@tikvahethiopia
A.F-1.pdf
229.5 KB
#MiT

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ሥራ ሃሳብ ውድድር ለማድረግ ተወዳዳሪዎች እየመዘገበ ነው።

የኅብረተሰብን ችግር ሊቀርፉ እና ህይወትን በማዘመን አስተዋጽዖ ሊያበረክቱ የሚችሉ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

ተማሪዎች፣ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ ተመራማሪዎች እና ተቋማት በውድድሩ እንዲሳተፉ ሚኒስቴሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ፦

https://mint.gov.et/wp-content/uploads/2022/03/A.F-1.pdf

@tikvahuniversity
" የነዳጅ ዋጋ ኢትዮጵያን በ1 ወር ውስጥ ብቻ 10 ቢሊዮን ብር አክስሯታል " - አቶ ታደሰ ኃለለማርያም

በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የጨመረው የነዳጅ ዋጋ በ1 ወር ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያን 10 ቢሊዮን ብር እንዳከሰራት ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ፤ የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ይሸጥበት ከነበረው 60 እና 70 ዶላር ወደ 140 ዶላር ማሻቀቡ፣ ኢትዮጵያ 10 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ እንዳስወጣት ወይም እንዳከሰራት አመልክቷል።

የድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለሪፖተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፤ እንደ ሌሎቹ አገሮች ሁሉ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ኢትዮጵያንም ዋጋ እያስከፈላት ነው ብለዋል።

በአንድ ወር ብቻ 10 ቢሊዮ ብር እንድታጣ ምክንያት መሆኑ እና ይህም ትልቅ ጉዳት መሆኑን ገልፀዋል።

" በወርኃዊ የነዳጅ ወጪዋም ወደ 250 ሚሊዮ ዶላር ከፍ እንዲል አስገድዷል " ያሉት አቶ ታደሰ ይህም መንግሥት ይህንን ልዩነት በመሸፈን በዓለም ዝቅተኛ በተባለ ዋጋ ነዳጅ እየተሸጠ የሚገኝ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል ብለዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመር የበለፀጉ አገሮችን ጭምር እየፈተነ የሚገኝ ሲሆን እንደ ፈረንሣይ ያሉ አገሮች በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ በማድረግ ህብረተሰቡ ነዳጅን ቆጥቦ እንዲጠቀም ሁሉ ማወጃቸውን አቶ ታደሰ አስታውሰው በኢትዮጵያ ነዳጅ ጭማሪ ባይደረግም ህብረተሰቡ በቁጠባ የመጠቀም ባህሉን ማዳበር አለበት ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ነዳጅ በምታስገባበት ዋጋ መሠረት ለገበያ ቢቀርብ የአንድ ሌትር የቤንዚን ዋጋ 76 ብር መሸጥ የነበረበት መሆኑንም የአቶ ታደሰ ገልፃ የሚያስረዳ ሲሆን አሁን ላይ ግን የአንድ ሌትር ቤንዚን ዋጋ 31 ብር ከ74 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
ድሬዳዋ ፤ አቶ እስቂያስ ታፈሰን ሸለመች።

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ15 አመት በላይ በተለያየ የአገልግሎት ስፍራ እና በአመራርነት ላገለገሉት አቶ እስቂያስ ታፈሰ የሽልማትና የእውቅና መርሀ-ግብር ትላንት ተካሂዷል።

ከተማ አስተዳደሩ ለአቶ እስቂያስ ዘመናዊ የቤት መኪና እንዲሁም የ100 ሺህ ብር ሽልማት ሸልሟል።

ይህ እውቅናና ሽልማት እንዲካሄድ ፤ የከተማው ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፣ የፕሮግራም አዘጋጅ ኮሚቴዎች፣ ወዳጆቹ፣ ጓደኞቹ፣ የከተማው ባለሃብቶች አስተዋፆ እንዳደረጉ ተነግሯል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ፤ አቶ እስቂያስ ታፈሰ ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ተከስቶ የነበረውን የፀጥታ ችግር ለማረጋጋት ከሌሎች አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ከፍተኛ አስተዋፆ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

በአመራርነት በቆየዩባቸው ጊዜያቶች ሁሉ ሰው አክባሪ ፣ ከሰው ጋር ዝቅ ብሎ ስራን መስራት የሚችሉ ፣ ከሰራተኞች ጋር እንደ አለቃ ሳይሆን እንደ ሰራተኛ መስራት የሚችሉ አመራር ነበሩ ብለዋል።

አቶ እስቂያስ ታፈሰ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከቀበሌ የህዝብ አደረጃጀት ኃላፊነት ቦታ አንስቶ በተለያዩ ቦታዎች ያገለገሉ ሲሆን እስከ ጥር 2014 የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሆነው መርተዋል።

አሁን በ " አማራ ባንክ " የቦርድ ሴክረቴሪ ጀነራል ሆነው ተመድበዋል።

ከዚህ ቀደም ድሬዳዋ በባለሃብቶች ተሳትፎ ለ3 ዓመታ በከተማው የነበረውን የፀጥታ ችግር እንዲፈታ እና አስተማማኝ ሰለም እንዲረጋገጥ ፤ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ አስተዋፆ ላደረጉ ለየቀድሞ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ 3.9 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የዘመነ መኪና ስጦታ መስጠቷ ፤ ለፀጥታ አካላትም የተለያየ መጠን ያለው ሽልማት ማበርከቷ ይታወሳል።

@tikvahethiopia