TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia #Sudan

በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር ላይ በምትገኘው በረከት ከተማ እና አካባቢዋ በኢትዮጵያ መንግስት ጦር እና በህወሓት ኃይሎች መካከል ጦርነት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለፁለት አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ነዋሪዎቹ ለበከፍተኛ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት መከፈቱንና ተኩስ መስማታቸውን ተናግረዋል ፤ ከሁመራ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በረከት ተኩስ መሰማት ከጀመረ አራት ቀናት መቆጠሩን ነው ያመለከቱት።

ጦርነቱን የተቀሰቀሰው በሱዳን ግዛት ውስጥ በሚገኙት የሃምዳይት እና የሉግዲ አካባቢዎች እንደሆነ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ፤ " ጦርነቱ የተጀመረው ሱዳን በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ነው " ያሉ ሲሆን ከዚህ በፊት ከሁመራ ወደ ሱዳን ተሰደው የነበሩ ዜጎች አሁን ላይ በሱዳን ግዛት ሆነው ጦርነት መክፈታቸውን አስረድተዋል።

ከበረከት በተጨማሪም በሁመራ ከተማ በሚገኘው ዲማ የፍተሻ ጣቢያ አካባቢ ጦርነት እንዳለ ገልፀዋል።

ጦርነት እንደተቀሰቀሰበት የተገለጸው ዲማ የሚባለው የፍተሻ ጣቢያ በሁመራ በኩል ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሚዋሰኑበት ድንበር ነው፡፡

ጦርነቱ በሱዳን ግዛት በኩል በመቅሰቀሱ ጉዳዩ የኢትዮጵያ እና ሱዳን እንደሆነ የሚገልጹ አካላት ያሉ ቢሆንም ይህ ግን ትክክል እንዳልሆነ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

አሁን ያለው ጦርነት በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ሳይሆን በኢትዮጵያ መንግስት ጥምር ጦር እና ሱዳን በሚገኙ የህወሃት ታጣቂዎች መካከል መሆኑን ነዋሪዎች ማስረዳታቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ያለው ነገርም ሆነ ያወጣው መግለጫ የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ ይገኛሉ። ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ የሚገኙት ከመጋቢት 12- መጋቢት 13 በሚቆይ የስራ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከአፍሪካ ህብረት (AU) እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ባለስልጣናት እንዲሁም ከሰብአዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ለመነጋገር ነው። ልዩ መልዕክተኛው ትላንትና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ…
#USA #ETHIOPIA

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በኢትዮጵያ ካደረጉት የስራ ጉብኝት በኃላ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ፤ በአሁኑ ወቅት በቀጠናው የጆ ባይደን አስተዳደር ዋነኛ ትኩረት በጦርነት ብዙ መስቅልቅል ላጋጠመው ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ነው ብለዋል።

ልዩ መልዕክተኛው የአሜሪካ መንግሥት ትኩረቱን በትግራይ አድርጎ ለሌሎች አካባቢዎችም የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ ላይ ትኩረት አድርጓል ሲሉ አሳውቀዋል።

" ... ከዚህ በላይ ትልቅ ትኩረት ሊያገኝ የሚችል ጉዳይ የለም " ያሉት አምባሳደር ሳተርፊልድ " የምናደርገውና እያልነው ያለው ይህን ዓላማ [የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ] ማሳካት እና ማስቀጠል ማስቻል ነው " ብለዋል።

አምባሳደር ሳተርፊልድ ከመጋቢት 12- መጋቢት 13 /2014 ዓ/ም በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት እንዲሁም ከረድዔት ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ተነጋግረዋል።

ምንጭ፦ ሮይተርስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ውሳኔ አሳለፈ። መንግስት ባወጣው መግለጫ ፤ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑን አመልክቷል። እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንደሚቀንስ በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል። በመሆኑም በከፍተኛ…
#Update

ትግራይ ክልል እያስተዳደረ ከሚገኘው " ህወሓት " በኩል ምላሽ ተሰጠ።

ህወሓት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም እንደሚስማማ ገልጿል።

ህወሓት ይህን ያለው የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲደርስ ለማስቻል ግጭት ለማቆም መወሰኑን ካስታወቀ በኋላ ነው።

ህወሓት ባወጣው መግለጫ በበቂ መጠን እና ተቀባይነት ባለው ጊዜ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ጥሪውን እንደሚቀበል ገልጿል።

በትግራይ ካለው የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነና ተቀባይነት ባለው ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታው የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም ቁርጠኛ መሆኑን አብስሯል።

የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወደ ትግራይ ያልተገደበ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲደርስ ከባዶ ቃልኪዳን በመውጣት ተጨባጭ የሆኑ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጠይቋል።

" ፖለቲካዊ እና የሰብዓዊ ጉዳዮች ማገናኘትም ተቀባይነት አይኖራቸውም " ያለው ህወሓት ፤ የትግራይ መንግሥት እና ሕዝብ ለሰላም እድል ለመስጠት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ብሏል።

ትላንትና የፌዴራል መንግሥት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ያሳለፈው ውሳኔ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀቡ እና በኃይል ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ መጠየቁ ይታወቃል፤ ህወሓት በዚህ ላይ ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ውሳኔ አሳለፈ። መንግስት ባወጣው መግለጫ ፤ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑን አመልክቷል። እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንደሚቀንስ በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል። በመሆኑም በከፍተኛ…
#Update

አሜሪካ መንግስት ያሳለፈውን ውሳኔ አደነቀች።

አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ መንግሥት በአስቸኳይ ተግባራዊ የሚሆን ግጭት የማቆም እና ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ ትግራይ እንዲደርስ ለማድረግ ከሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች ጋር ለመሥራት ያሳለፈውን ውሳኔ አድንቃለች።

ውሳኔው ድጋፍ ለሚሹ ኢትዮጵያውያን በፍጥነት ለማቅረብ አስፈላጊ እርምጃ መሆኑን የጠቀሰችው አሜሪካ ፤ ለአገሪቱ ደኅንነትና ብልጽግና ሁሉን አካታች የሆነ ፖለቲካዊ ሂደት ለማስጀመር መሠረት እንደሚሆንም አሳውቃለች።

በሁሉም ወገኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እንዲቆሙና ከዚህ በፊት ለተፈጸሙ በደሎችና ጭፍጨፋዎች ተጠያቂነት እንዲኖርም አሜሪካ ጠይቃለች።

ይህንን ግጭት የማቆም ውሳኔን በመከተልም ተፋላሚ ወገኖቹ አስፈላጊ የደኅንነት ሁኔታዎችን ማመቻቸትን ጨምሮ በድርድር ላይ ወደተመሠረተ ዘላቂ ተኩስ አቁም እንዲደርሱ መምከሯን ቢቢሲ ዘግቧል።

አሜሪካ ፤ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሰላም እንዲፈታ እና ጦርነቱን ተከትሎ በችግር ላይ ለወደቁ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖች ሰብዓዊ እርዳታ ያለገደብ እንዲደርስ ጥረት ስታደርግ መቆየቷን በተደጋጋሚ የገለፀች ሲሆን ከቀናት በፊት ከመጋቢት 12- መጋቢት 13 /2014 ዓ/ም የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋን አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ከኢትዮጵያ ፣ ከAU፣ ከUN ባለስልጣናት እና ከረድኤት ድርጅት ተወካዮች ጋር እንዲነጋገሩ አድርጋለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለቀጣይ 3 ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ፈጽሞ የተከለከለ ነው " - የአ/አ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከተከራየበት ቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል ውሳኔ ማተላለፉ ይታወሳል፡፡ አስተዳደሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ " ይህ ያለንበት…
#ተራዝሟል

የመኖርያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪን እና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት መራዘሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዜጎችን ጥያቄና አገራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖርያ ቤት ተከራዮችን ለማስለቀቅና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ ለመገደብ ደንብ ማውጣቱን አስታውሷል።

ደንቡ ላለፉት ሶስት ወራት እንዲራዘምም ተደርጎ እንደነበር ገልጿል።

አሁንም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት እንዲራዘም የከተማው አስተዳደር መወሰኑን አሳውቋል።

ስለሆነም በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

" ኢትዮጵያዊ የመተሳሰብና የመተጋገዝ ባህላችንን በማሳደግ ፈታኝ ሁኔታዎች በጋራ ሆነን እንሻገር " ሲል የከተማ አስተዳደሩ ጥሪ አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray , #Mekelle📍 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ወደ ትግራይ ክልል 30 ቶን የምግብ ድጋፍ ላከች። የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ለትግራይ ህዝብ አስፈላጊ እርዳታ በአየር ለማጓጓዝ በሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ ጥረት 30 ቶን የምግብ ድጋፍ የጫነ አውሮፕላን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቐለ መለኳ ተሰምቷል። ድጋፉ 5,600 ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ከ7,000 በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል። አሁን…
#Tigray

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ተጨማሪ " 30.3 ሜትሪክ ቶን " የምግብ አቅርቦት ወደ ትግራይ ክልል ላከች።

የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ 5,700 ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ከ7,100 በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 30.3 ሜትሪክ ቶን የምግብ አቅርቦትን የጫነ አምስተኛ አይሮፕላን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቐለ ከተማ ልካለች።

ሀገሪቱ ድጋፉ እየጨመረ የመጣውን የአካባቢውን ነዋሪዎች ፍላጎት ለመማሟላት እና የኑሮ ሁኔታቸውን ለማሻሻል በአየር በረራ የሚደረገው ድጋፍ አካል ነው ስትል አስታውቃለች።

ሀገሪቱ ፤ እስካሁ ትግራይ ክልልን ጨምሮ አጠቃላይ ወደ ኢትዮጵያ በ9 አውሮፕላኖች 344.2 ሜትሪክ ቶን እርዳታን የላከች ሲሆን ፤ 65 ,000 ሴቶችን ጨምሮ ከ81,000 በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ አድርጓል።

ከዚህም ባለፈ በዚህ አመት በኢትዮጵያ ለሚደረጉ የእርዳታ ስራዎች እንዲውል ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር 85,000,000 ዶላር ለመለገስ ቃል ገብታለች።

መረጃው በዱባይ በእግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው Khaleej Times ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የማህበር ቤት ፈላጊዎች ምዝገባቸውን ዳግም በአካል እንዲያረጋግጡ ተጠየቀ። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ካሉት የቤት አቅርቦት አማራጮች አንዱ የሆነውን የማህበር ቤት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ሁኔታዎች በማጠናቀቅ ማህበራቱ ወደ ተግባር የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸቱን ገልጿል። ቢሮው ከአሁን በፊት ፍላጎት ያላቸውን ነባር የ20/80 እና 40/60 የማህበር ቤት ፈላጊዎች…
#ተራዝሟል

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የ2005 ዓ.ም የ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ተመዝጋቢ ሆነው በማኅበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት ቀደም ሲል በኦንላይን የተመዘገቡ አመልካቾች በየሚኖሩበት ወረዳ ቀርበው መረጃቸውን ከየካቲት 16 እስከ መጋቢት 16/2014 ዓ.ም ድረስ በአካል እንዲያረጋግጡ መገለጹ ይታወሳል።

ቢሮው በዛሬ ዕለት ባወጣው ማስታወቂያ አመልካቾች ምዝገባቸውን የሚያረጋግጡበትን ጊዜ እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም መራዘሙን አስታውቋል።

በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ ክልል በራሳችሁም ሆነ በትዳር አጋራችሁ ስም ቤት ወይም የቤት መስሪያ ቦታ የሌላችሁ ወይም ኖሯችሁ ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በስጦታ / በሽያጭ ያላስተላለፋችሁ መሆኑን እና ሌሎች መረጃዎችን በቅጽ 01 በማዘጋጀት ምዝገባችሁን እንድታሟሉ ጠይቋል።

ዲያስፖራ ሆነው በኦንላይን የተመዘገቡ የማኅበር ቤት ፈላጊዎች ደግሞ ከመጋቢት 19 ቀን 2014 እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ባምቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ 8ኛ ፎቅ ተመዝጋቢዎች ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በአካል ቀርባችሁ የተዘጋጀውን ቅፅ 001 እንዲሞሉ አስታውቋል።

ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ቀርባችሁ " ቅፅ -01 " እና " ቅፅ- 001 " ን ያልሞላችሁ ተመዝጋቢዎች በፈቃዳችሁ የተዋችሁት ተደርጎ እንደሚወሰድ የከተማው ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#UK

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ መጥተው ስለሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት እና ስለወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ከከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሰልጣናት ጋር ውይይት አድርገው የነበሩት የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ፤ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም እና ያልተገደበ የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ እንዲደርስ ለማድረግ ያሳየውን ቁርጠኝነት አጥብቀው እንደሚደግፉ አሳውቀዋል።

ቪኪ ፎርድ ፥ የትግራይ ባለስልጣናት ተኩስ በማቆም እና ከአፋር በመውጣት ምላሽ መስጠት አለባቸው ብለዋል።

የታየው ቁርጠኝነት በተግባር ሰብዓዊ እርዳታ ወደመላክ መተርጎም አለበት ያሉት ሚኒስትሯ ይህንንም የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለመደገፍ ዝግጁ ነው ሲሉ አብስረዋል።

ህወሓት ባወጣው መግለጫ የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ የሚደርስ ከሆነ ግጭት ለማቆም ዝግጁ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ከያዛቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች ለቆ ስለመውጣት ያለው ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopianAirlines የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለ38 ዓመታት ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዋል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገናና ኢንጂነሪንግ፣ እንዲሁም ኦፕሬሽን ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ትላንት አዲሱን…
#Update

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበር ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቅርቡ ከተሾሙት የአየር መንገዱ የቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ግርማ ዋቄ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ላይ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ተሊላ ዴሬሳ አዲስ ለተሾሙት የቦርድ ሰብሳቢ እንኳን ወደ ቤቶ በደህና ተመልሰው መጡ የሚል የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትን አስተላለፈው የሰራተኛ ማህበሩ እንደከዚህ ቀደሙ ሰራተኞችን አስተባብሮ ለድርጅቱና ለሰራተኛው ጥቅም በርትቶ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

የድርጅቱ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄም በአዲስ መንፈስ ለተሻለ ለውጥና ዕድገት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አስተባብረው ለመስራት ቁርጠኝነት እንዳላቸው አስታውቀው የሰራተኛ ማህበሩ ሚና ትልቅ በመሆኑ ለተሻለ ለውጥና እድገት በጋራ ለመስራት እንዲዘጋጁ ጥሪ አቅርበዋል።

Via Abdi Kuma

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ውሳኔ አሳለፈ። መንግስት ባወጣው መግለጫ ፤ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑን አመልክቷል። እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንደሚቀንስ በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል። በመሆኑም በከፍተኛ…
#AU #IGAD

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳፋቂ መሃመት የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን እንደሚያደንቁ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የበትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማድረስ የወሰነው ውሳኔ ይደነቃል ብለዋል።

በተጨማሪ ፤ የትግራይ ክልላዊ መንግስት ለሰብዓዊነት ተብሎ ግጭት ለማቆም የተላለፈውን ውሳኔ ለመመልከት እና በአስቸኳይ ግጭት ለማቆም ማወጁን እንደሚያደንቁ ገልፀዋል።

ለጋሾች እና የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በትግራይ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚያደርጉትን ድጋፍ በእጥፍ እንዲያሳድጉም ጥሪ አቅርበዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ ሁሉን አቀፍና በድርድር በሚመጣ የተኩስ አቁም ላይ ሁሉም ወገን እንዲደርስ ህብረቱ ጥረቱን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

በህብረቱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ከሁሉም ወገን እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ግጭቱን በፍጥነት ለመቋጨት የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሊቀመንበሩ አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ማቆሙን አድንቀዋል ፤ የትግራይ ክልል መንግስትም ውሳኔው ንለማክበር እና ግጭት ለማቆም በመወሰን ምላሽ በመስጠቱ አድንቀዋል።

ለትግራይ ክልል እና ሌሎች በድርቅና በምግብ እጦት ለተጎዱ ክልሎች ሰብዓዊ እርዳታ በተጠናከረ መልኩ እንዲደረግ ዓለም አቀፍ አጋሮች የቻሉትን ሁሉ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁሉም ወገኖች ብሄራዊ ውይይት ጨምሮ ለዘላቂ ሰላም መስፈን ሁሉንም የሰላም አማራጮችን እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
#ሹመት

አቶ ደሳለኝ ጣሰው የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ሆነው ተሾሙ።

አቶ ደሳለኝ ሹመቱ የተሰጣቸው የአማራ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ነው።

በተጨማሪም ዶ/ር አማረ ብርሃኑ የክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ሆነው በምክር ቤቱ ተሹመዋል።

መረጃው የአሚኮ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ukraine #Russia

ሩሲያ የዩክሬንን የአየር ክልል ለመዝጋት ከሚሞክር ኃይል ጋር ጦርነት እንደምትከፍት ገለፀች።

ሀገሪቱ ይህን የገለፀችው በዩክሬን እያካሄድኩ ነው ያለችውን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” የመጀመሪያውን ምዕራፍ ማጠናቀቋን ባሳወቀችበት ወቅት ነው።

ሀገሪቱ ተጠናቋል ባለችው የመጀመሪያ ምዕራፍ ያስቀመጠችው ግቦች እንደተሳኩ የገለጸች ሲሆን ብዙ የዩክሬን ግዛቶችን መቆጣጠሯን አሳውቃለች።

ሩስያ ጦሯ የዩክሬንን ዋና ከተማ ኪቭን ጨምሮ ካርኪቭ፣ ቼርኒሂቭመ ሱሚ እና ሚኮላይቭ የተባሉ አካባቢዎችን መክበቡን ገልፃለች። በተጨማሪ ኬርሶን እና ዛፖሮዚ የተባሉ የዩክሬን ግዛቶች አሁን ላይ በእጇ ላይ መውደቁን አሳውቃለች።

በዩክሬን የተገንጣዮች ግዛት የሆነችውን ሉሃንስክን ደግሞ 93 በመቶ መቆጣጠሯን አሳውቃለች።

የዩክሬንን የአየር ክልል ለመዝጋት ከሚሞክር ኃይል ጋር ጦርነት እንደምትከፍትም ዝታለች።

4 ሳምንታት ባስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰዎች ሲያልቁ ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ተሰደዋል።

መረጃው የአልዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia