TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
😢

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ መሪዎች ተጎድተውም ቢሆን ኢትዮጵያን አንድ እንዲያደርጉ በእንባ ተማፀነች።

ኮማንደር ደራርቱ ተማፅኖዋን ያሰማችው በቤልግሬድ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ላይ ከዓለም አንደኛ ሆኖ ላጠናቀቀው የአትሌቶች እና አሰልጣኞች ቡድን በተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ላይ ነው።

" የሀገራችን ጉዳይ ሁላችንንም ያመናል " ያለችው ደራርቱ " የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን አባቶቻችን ናቸው በእርግጠኝነት ደግሞ ነገ ሌላ ቀን ነው ኢትዮጵያ ታርቃ አንድ ሆና ትቆማለች " ስትል ተናግራለች።

ኮማንደር ደራርቱ ፤ ከትግራይ ክልል የተገኙ ድንቅ አትሌቶችን ክብር ይገባችኃል ያለች ሲሆን " በብዙ ፈተናዎች አልፈው በብዙ ተፅእኖ አልፈው የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ስላደረጉ ምስጋና አቅርባለች።

" በእርግጠኝነት ቤተሰቦቻችሁ የት እንዳሉ ታውቃላችሁ " ያለችው ደራርቱ " ግድ የላችሁም እንወዳችኃለን እናከብራችኃለን ፤ እንደልጆቻችን ነው አሁንም የምናያችሁ ስለሆነም ትግራይ ዛሬ ብቻዋን አይደለችም ከኢትዮጵያ ጋር ነች፤ ነገም ከኢትዮጵያ ጋር ትሆናለች " ስትል ተናግራለች።

ኮማንደር ደራርቱ፤ የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት መሪዎች ተጎድታችሁም ቢሆን ለኢትዮጵያ ህዝብ ብላችሁ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓት ስትል በእንባ የተማፀነች ሲሆን " ከእግዚአብሔር ጋር ትችላላችሁ። እናተ አንድ ካደረጋችሁ ኢትዮጵያ አንድ ትሆናለች። " ብላለች።

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ አሜሪካ ፤ በ " H.R. 6600 " ኢትዮጵያንም ሆነ ትግራይን ለመጥቀም ሳይሆን ለመበተን እንደሆነ ተናግራ መሪዎች ከተስማሙ የሚፀድቅበት ምክንያት ስለሌለ ለወደፊት ኢትዮጵያ ሲሉ እዲስማሙ ተማፅናለች።

ህዝቡም በመተባበር #ኢትዮጵያን አንድ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርባለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
😢 ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ መሪዎች ተጎድተውም ቢሆን ኢትዮጵያን አንድ እንዲያደርጉ በእንባ ተማፀነች። ኮማንደር ደራርቱ ተማፅኖዋን ያሰማችው በቤልግሬድ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ላይ ከዓለም አንደኛ ሆኖ ላጠናቀቀው የአትሌቶች እና አሰልጣኞች ቡድን በተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ላይ ነው። " የሀገራችን ጉዳይ ሁላችንንም ያመናል " ያለችው ደራርቱ " የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን…
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በእንባ ተሞልታ ያቀረበችው ተማፅኖ ፦

" ... የሀገራችን ጉዳይ ያመናል ሁላችንንም። ... ሁላችንንም የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን አባቶቻችን ናቸው ። በእርግጠኝነት ደግሞ ነገ ሌላ ቀን ነው ኢትዮጵያ ታርቃ አንድ ሆና ትቆምና የኢትዮጵያን ባንዲራ ታውለበልባለች።

ስለዚህ አይክፋችሁ ክብር ይገባችኃል። በብዙ ፈተናዎች አልፋችሁ በብዙ ተፅእኖ አልፋችሁ የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ስላደረጋችሁ በጣም እናመሰግናለን።

ትግራይ ትላንትም ብትሆን ኢትዮጵያ ናት ፤ ዛሬም ኢትዮጵያ ናት ፤ ነገም ኢትዮጵያ ነች ስለዚህ እባካችሁ መሪዎቻችን እባካችሁ...እባካችሁ ... እባካችሁ ተጠቅማችሁ አይደለም ፤ ተጎድታችሁ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓት እባካችሁ !!! ከእግዚአብሔር ጋር ትችላላችሁ። ስለዚህ መሪዎቻችን ተጎድታችሁ ለኢትዮጵያ ብላችሁ ፣ ለህዝብ ብላችሁ እናተ አንድ ካደረጋችሁ ኢትዮጵያ አንድ ትሆናለች።

... ስፖርት ወንድማማችነት ፣ ፍቅር ፣ ሰላም ነው!! ለሰላም ፣ ለፍቅር ቆመው እነዚህ ልጆች ምንም ሳይበግራቸው ለዚህ ውጤት በቅተዋልና አሁንም ቢሆን ክብር ይገባቸዋል። እናከብራችኃለን። በእርግጠኝነት ቤተሰቦቻችሁ የት እንዳሉ ታውቃላችሁ ግድ የላችሁም እንወዳችኃለን እናከብራችኃለን ፤ እንደልጆቻችን ነው አሁንም የምናያችሁ ስለሆነም ትግራይ ዛሬ ብቻዋን አይደለችም ከኢትዮጵያ ጋር ነች፤ ነገም ከኢትዮጵያ ጋር ትሆናለች።

አሜሪካ ትግራይን ለመጥቀም አይደለም፤ ኢትዮጵያንም ለመጥቀም አይደለም ለመበተን ነውና H.R. 6600 የሚባልው አሁን ሊፀድቅ በመንገድ ላይ ያለው መሪዎቻችን ስለህዝባችን አይተው ፤ ስለወደፊት ኢትዮጵያ አይተው ከተስማሙ H.R. 6600 የሚፀድቅበት ምክንያት የለውም።

ህዝባችን ከመንግስቶቻችን ጎን ቆሞ ሁላችንም የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ ህዝብ እኔ የትግራይ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ ስል ምቾት አይሰማኝም እንደኢትዮጵያ ነው ሁላችንም የምናየው ፤ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦቻችን ኢትዮጵያ ናቸው ፤ ትላንትናም ተባብረውና ኢትዮጵያውያን እዚህ ያበቁትና ነገም ዛሬም እንተባበር ኢትዮጵያን አንድ እናድርጋት።

እኛ ልጆቻችሁ ከኦሮሞ የመጣ፣ ከአማራ የመጣ፣ ከትግሬ የመጣ፣ ከጉራጌ ከየትም የመጣው ለዚህ ነው አንዷን ባንዲራ ከፍ ያደረግነው ስለሆነም ብሄር ሳንለን፣ ሃይማኖት ሳንለይ፣ ፆታ ሳንለን፤ ባንዲራችንን ያነሳነው ስለተባበርን ነው፤ በፅናት ስለቆምን ነው። ለእናተም አያቅትም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም የኢትዮጵያ መንግስትም እባካችሁ ...ስለስለነገዋ ኢትዮጵያ አንድነት፣ ስለብልፅግናዋ ፣ ስለእድገቷ፣ ስለሰላሟ፣ እባካችሁ አያቅታችሁም እኛም ከጎናችሁ አለን ስፖርት ሰላም ነው ፤ ስፖርት ፍቅር ነው ብለናል ተያይዘን ኢትዮጵያን አንድ እናድርጋት። እግዚአብሔር ደግሞ አንድ ያድርግልን። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ከጤናቸው ጋር በተያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውን አረጋግጧል። በሌላ በኩል ፤ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በቅርቡ መሾማቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል። አቶ ግርማ ፤ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የካበተ ልምድ ያላቸው ሲሆኑ አየር…
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለ38 ዓመታት ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገናና ኢንጂነሪንግ፣ እንዲሁም ኦፕሬሽን ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉት አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሹመዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ትላንት አዲሱን የአቶ ተወልደ ገ/ማርያም ተተኪ እንደሚያሳውቅ መግለፁ እይታወሴ።

አዲስ እንደተቋቋመ የተነገረለት የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ አቶ ተወልደ ገ/ማርያምን ተክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን አሳውቀዋል።

አቶ መስፍን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ፣ የጥገናና ኢንጂነሪንግ፣ እንዲሁም ኦፕሬሽን ዳይሬክተር በመሆን ያገለገሉ ሲሆን እኤአ ከ2019 ጀምሮም የአየር መንገዱ ስራ አመራር ቦርድ ውስጥ ሲያገለግሉ ነበር።

ከዚያ ቀጥለውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ 40 በመቶ ድርሻ ያለበትን አስኪ አየር መንገድን ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን በመምራት ላይ ነበሩ።

በሌላ በኩል አዲስ የተዋቀረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ፦
👉አቶ ግርማ ዋቄ የቦርድ - ሰብሳቢ፣
👉 አቶ ተክለወልድ አጥናፉ - አባል
👉 አቶ ተመስገን ጥሩነህ - አባል
👉 ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ - አባል
👉 አቶ ታደሰ ጥላሁን - አባል
👉 አቶ ረታ መላኩ - አባል
👉 አቶ አለማየሁ አሰፋ - አባል ሆነዋል።

@tikvahethiopia
4ኛው ዙር ስልጠና ተጀመረ!

ስቴም ፓወር (STEM POWER) ከቪዛ (VISA) እና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ባለፉት ዙሮች ከ450 በላይ ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ስልጠናውን ከተከታተሉ መካከል ንግድ ፍቃድ በማውጣት ሥራቸውን የጀመሩ ይገኙበታል። ሌሎቹም የቴክኒካል እና ማማከር ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።

አሁን ላይ 4ተኛ ዙር ሥልጠና ለመስጠት በምዝገባ ላይ እንገኛለን።

የሥልጠናው ፕሮግራም የሚያካትተው ፦

• የተከታታይ 9 ቀን የሥራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የገንዘብ አያያዝ ሥልጠና

• 3 ወር የንግድ ማበልጸግ እና ማማከር አገልግሎት (Business Development and Consultation, including coaching and pitching)

• 8 ወር የተለያየ የማማከር ድጋፍ, ክትትል እና ሜንቶርሺፕ

• ፕሮቶታይፕ መስሪያ ጥሬ ዕቃዎችን ጨምሮ ነጻ የማምረቻ ላብራቶሪ አገልግሎት

በስልጠናው የሚሳተፉ፦

👉 የሥራ ፈጠራ ክህሎቱን ማዳበር እና ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች መጠቀም የሚፈልግ፤

👉 የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ላላቸው ቅድሚያ እንሰጣለን፤

👉 ሴት የሥራ ፈጣሪዎች እንዲመዘገቡ እናበረታታለን፤

በሥልጠናው መሳተፍ የምትፈልጉ በተለይ የፈጠራ ሀሳብ ያላችሁ እስከ መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓም ተመዝግባችሁ ስልጠናውን እና ሌሎች አገልግሎቶቹን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ 👇
https://forms.office.com/r/TtnFJdedji

#StemPower #VISA #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Kereyu Incident Investigation Report.pdf
" የእርቅ ሂደቱ የወንጀል ተጠያቂነትን መተካት ወይም ማስተጓጎል የለበትም " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ ለተፈጸመው ግድያ የወንጀል ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ስራ በተመለከተ መግለጫ ልኮልናል።

ኢሰመኮ በመግለጫው ላይ ፤ በጅላ አባላቱ ላይ ግድያ የፈጸሙና ያስፈጸሙ አባላት ላይ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች ያሉበትን ደረጃ መገምገሙን ገልጿል።

ኮሚሽኑ ፤ የተፈጸመውን ግድያ ለመመርመር ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የተውጣጣ መርማሪ ቡድን ተቋቁሞ ሥራ የጀመረ መሆኑና እስከ መጋቢት 4/2014 ዓ.ም ድረስም 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው የሚገኝ መሆኑን አሳውቋል።

ኢሰመኮ የክልሉ መንግስት ተጠያቂነት ለማረጋገጥ እየሰራ ያለው ስራ አበረታች ቢሆንም በሂደቱ ላይ ክፍተቶች የታዩ መሆኑን አመልክቷል።

ከተያዩት ክፍተቶች መካከል ፤ በአካባቢው ማህበረሰብ በግድያው ተሳፍቶ ያላቸው መሆኑ የተጠቆሙ / በድርጊቱ ዋነኛ ፈፃሚ ናቸው የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር አልዋሉም / ምርመራም እየተደረገባቸው አይደለም።

ከዚህ ባለፈ ተጠርጣሪዎቹ በመንግስት ስራ ኃላፊነት ቦታዎች የሚገኙ ጭምር ስለሆነ በምርመራ ሂደቱ ጫና እያደረሱ ፤ ለሂደቱ አስፈላጊ ድጋፍ ማድረግ የሚገባቸው የፀጥታ እና የአስተዳዳር አካላትም ሥራው በሚፈለገው ፍጥነት እንዲጠናቀቅ በቂ ትብብር እያደረጉ እንዳልሆነ ተገልጿል።

በተጨማሪም ፤ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎችም በህግ በተቀመጠው ጊዜ ወደ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።

ያንብቡ : https://telegra.ph/EHRC-03-24

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Waghimra በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ያሉ ተፈናቃዮች የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸው ተገልጿል። አስተዳደሩ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት " ዋግ ከችግር ቆፈን ላይ ወድቃለች፤ የመከራ ቃፊር እየናጣት ነው የሚደርስላት ትሻለች " ብሏል። አሁን ላይ ከአበርገሌ፣ ከጻግብጂ፣ ከዝቋላ፣ ከሰቆጣ ዙሪያ፣ ዛታ፣ ወፍላና ኮረም በጦርነት ምክንያት በየቀኑ ከ2000 ሰው በላይ የተፈናቀለ ወለህ ሜዳ ላይ ሰፍሯል…
#Waghimra📍

የሰሜን ጦርነት ክፉኛ ከጎዳቸው አካባቢዎች መካከል የአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋነኛው ነው፤ በዛ ስላለው አስከፊ ሁኔታ ከዚህ ቀደም መገለፁ የሚታወስ ነው።

አሁንም ግን ችግሩ መፍትሄ ሳይገኝለት የቀጠለ ሲሆን በተላይ ደግሞ ህፃናት አልሚ ምግብ ባለመኖሩ የተነሳ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።

ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፤ በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕጻናትን ጤናና ህይወት ለመታደግ የሚያስችል ድጋፍ በአስቸኳይ ማግኘት ካልተቻለ አስከፊ ነገር ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ከፍያለው ደባሽ ፦ " አሁን ሕፃናት አፋቸውና አፍነጫቸው ቆስሏል። እንደተላላፊ በሽታ ይህ እያደገ ይሄድና ከ77ቱም የበለጠ እልቂት ሊኖር ይቸላል። ምግብ የሌላቸው ሕፃናት በሽታ ሲጨመርባቸው የሚከሰተው ችግር ቁልጭ ብሎ የሚታይ ነው " ብለዋል።

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አብዘኛው ቆላማ ወረዳዎች በድርቅ በመጎዳታቸው፣ በቂ የሰብል ምርት ባለመኖሩ እንዲሁም በርካታ አካባቢዎች በህወሓት ቁጥጥር ሥር ስለነበሩ ከ61 ሺ 600 በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ።

ከተፈናቃዮቹ መደበኛ እና መደበኛ ባልሆነ መጠለያ ውስጥ የሚገኙት 18 ሺህ 700ዎቹ ሲሆኑ በመደበኛ መጠለያ የሚገኙት ከ2 ሺህ አይበልጡም ፤ የተቀሩት ተፈናቃዮች ግን ከመጠለያ ውጪ ነው የሚገኙት።

ለተፈናቃዮች አስፈላጊውን ማኅበራዊ አገልገሎት በበቂ ሁኔታ ማቅረብ አለመቻሉንም የብሄረሰብ አስተዳደሩ አመልክቷል።

ነዋሪዎችና ተፈናቃዮችም ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ችግሩ እየባሰ መሆኑን ጠቅሰው፣ መንግሥትና የእርዳታ ድርጅቶች ለሕጻናት ልጆች እና ለእነሱም ህይወት መቆየት የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ተማፅነዋል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ውሳኔ አሳለፈ።

መንግስት ባወጣው መግለጫ ፤ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑን አመልክቷል።

እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንደሚቀንስ በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል።

በመሆኑም በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ችግር በአፋጣኝ የመፍታት ኃላፊነቱ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን በመረዳት የአስቸኳይ የሰብዓዊ አቅርቦቶች ወደ ትግራይ ክልል በበቂ ሁኔታ መድረስ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማሳካት የተቻለውን ሁሉ ጥረት ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ እና የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ ከተለመደው የተለዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ ውሳኔ ከወጣበት ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ መተላለፉን አብስሯል።

መንግስት ዓለም ዓቀፉ የለጋሾች ማህበረሰብ እያቀረበ ያለውን ድጋፍ እና እርዳታ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ጥሪ አቅርቧል።

የሰብዓዊ እርዳታ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን የገለፀው መንግስት ጥረቱ እና ቁርጠኝነቱ የሰብዓዊ ሁኔታውን በማሻሻል ረገድ የሚኖረው ስኬት የሚረጋገጠው በሌላኛው ወገን የሚገኘው አካል በተመሳሳይ ለዚህ አላማ በሚኖረው ቁርጠኝነት ልክ ነው ብሏል።

ውሳኔው ውጤት ማምጣት እንዲችል በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም የጥቃት እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ እና በጉልበት ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎች እንዲወጡ መንግስት ጠይቋል።

(ሙሉውን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahetiopia
የቴ/ሙ/ስ/ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ በ2014 ዓ.ም የሰልጣኞች ቅበላ መቁረጫ ነጥብን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት በመጀመሪያ ዙርና 2ኛ ዙር የ2013 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ከላይ በምስሉ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት የቴ/ሙ/ስ/ ተቋማት ተቀብለው እንደሚያሰለጥኑ ተገልጿል።

በትምህርት ሚኒስቴር የመቁረጫ ነጥብ መሠረት ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ አምጥተው ነገር ግን በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ገብተው ለመሰልጠን ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች በደረጃ 5 ወይም 4 መሰልጠን እንደሚችሉ ተገልጿል።

አካል ጉዳተኞች በሚያመቻቸው እና በመረጡት ሙያና የስልጠና ደረጃ ገብተው እንዲሰለጥኑ ተፈቅዷል።

የመቁረጫ ነጥቡ ለ2014 ዓ.ም የስልጠና ቅበላ ብቻ የሚያገለግል ነው ተብሏል።

Note: የቴ/ሙ/ስ/ ተቋማት ተጠሪነታቸው ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተዛውሯል።

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ውሳኔ አሳለፈ። መንግስት ባወጣው መግለጫ ፤ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑን አመልክቷል። እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንደሚቀንስ በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል። በመሆኑም በከፍተኛ…
#UK

ዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ መንግሥት ያሳለፈውን ውሳኔ በደስታ እንደምትቀበል እና መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ምላሹን ለማሳደግ የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።

ዩናይትድ ኪንግደም ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን እና ያልተገደበ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲደርስ ያሳለፈውን ውሳኔ በደስታ እንደምትቀበል ገልፃለች።

የትግራይ ባለሥልጣናትም ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቃለች።

ዩናይትድ ኪንግደም ፤ መንግስት የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ምላሹን ለማሳደግ የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን አስታውቃለች።

የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ከሰዓት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ማቆሙን ማብሰሩ እና ዓለም አቀፍ ለጋሾች እያቀረቡ ያለውን ድጋፍ እና እርዳታ #በከፍተኛ_መጠን_እንዲጨምሩ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።

እስካሁን በትግራይ ክልል በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ የተሾሙ አምባሳደሮች የተመደቡባቸው ሀገራት ዝርዝር ይፋ አድርጓል። አምባሳደሮቹ የተመደቡባቸውን ሀገራት ፦ 1. አምባሳደር ተፈራ ደርበው —ጃፓን 2. አምባሳደር ደሴ ዳልኬ—ደቡብ ኮሪያ 3. አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ—አሜሪካ 4. አምባሳደር ባጫ ደበሌ — ኬንያ 5. አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም–ግብፅ 6. አምባሳደር ዳባ ደበሌ –ሩዋንዳ 7. አምባሳደር ጀማል…
#DrEngSeleshiBekele

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ቃለመሃላ ፈፀሙ።

በቅርቡ በአሜሪካ ሀገር የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ዛሬ ከፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በመቀበል ቃለመሃላ መፈፀማቸውን ገልፀዋል።

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በተረጋገጠ የትዊተር ገፃቸው ላይ ፥ " ዛሬ በአሜሪካን አገር የኢትዮጵያ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ለመሆን ከክ/ት ፕ/ት ሣሕለወርቅ ዘውዴ በመቀበል ቃለመሐላ ፈፅሜያለሁ " ብለዋል።

አክለው ፥ " ለመልካም ግኑኝነት፣ የአገሬን ፍላጎት፣ ክብር እና ጥቅም ለማስጠበቅ እተጋለሁ " ሲሉ ገልፀዋል።

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር (በቀድሞ) በነበሩ ሰዓት በተለይም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በዓለም መድረክ የኢትዮጵያን እውነት ይዘው በመሟገት እና ጥቅሟ እንዳይነካ በመታገል እንዲሁም በተመደቡበት ቦታ ሀገራቸውን በትጋት በማገልገል ይታወቃሉ።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Sudan

በኢትዮጵያ እና በሱዳን ድንበር ላይ በምትገኘው በረከት ከተማ እና አካባቢዋ በኢትዮጵያ መንግስት ጦር እና በህወሓት ኃይሎች መካከል ጦርነት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለፁለት አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ነዋሪዎቹ ለበከፍተኛ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት መከፈቱንና ተኩስ መስማታቸውን ተናግረዋል ፤ ከሁመራ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በረከት ተኩስ መሰማት ከጀመረ አራት ቀናት መቆጠሩን ነው ያመለከቱት።

ጦርነቱን የተቀሰቀሰው በሱዳን ግዛት ውስጥ በሚገኙት የሃምዳይት እና የሉግዲ አካባቢዎች እንደሆነ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ፤ " ጦርነቱ የተጀመረው ሱዳን በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ነው " ያሉ ሲሆን ከዚህ በፊት ከሁመራ ወደ ሱዳን ተሰደው የነበሩ ዜጎች አሁን ላይ በሱዳን ግዛት ሆነው ጦርነት መክፈታቸውን አስረድተዋል።

ከበረከት በተጨማሪም በሁመራ ከተማ በሚገኘው ዲማ የፍተሻ ጣቢያ አካባቢ ጦርነት እንዳለ ገልፀዋል።

ጦርነት እንደተቀሰቀሰበት የተገለጸው ዲማ የሚባለው የፍተሻ ጣቢያ በሁመራ በኩል ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሚዋሰኑበት ድንበር ነው፡፡

ጦርነቱ በሱዳን ግዛት በኩል በመቅሰቀሱ ጉዳዩ የኢትዮጵያ እና ሱዳን እንደሆነ የሚገልጹ አካላት ያሉ ቢሆንም ይህ ግን ትክክል እንዳልሆነ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

አሁን ያለው ጦርነት በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ሳይሆን በኢትዮጵያ መንግስት ጥምር ጦር እና ሱዳን በሚገኙ የህወሃት ታጣቂዎች መካከል መሆኑን ነዋሪዎች ማስረዳታቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ያለው ነገርም ሆነ ያወጣው መግለጫ የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ ይገኛሉ። ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ የሚገኙት ከመጋቢት 12- መጋቢት 13 በሚቆይ የስራ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከአፍሪካ ህብረት (AU) እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ባለስልጣናት እንዲሁም ከሰብአዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ለመነጋገር ነው። ልዩ መልዕክተኛው ትላንትና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ…
#USA #ETHIOPIA

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ በኢትዮጵያ ካደረጉት የስራ ጉብኝት በኃላ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ፤ በአሁኑ ወቅት በቀጠናው የጆ ባይደን አስተዳደር ዋነኛ ትኩረት በጦርነት ብዙ መስቅልቅል ላጋጠመው ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ ነው ብለዋል።

ልዩ መልዕክተኛው የአሜሪካ መንግሥት ትኩረቱን በትግራይ አድርጎ ለሌሎች አካባቢዎችም የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ ላይ ትኩረት አድርጓል ሲሉ አሳውቀዋል።

" ... ከዚህ በላይ ትልቅ ትኩረት ሊያገኝ የሚችል ጉዳይ የለም " ያሉት አምባሳደር ሳተርፊልድ " የምናደርገውና እያልነው ያለው ይህን ዓላማ [የሰብዓዊ እርዳታ ማቅረብ] ማሳካት እና ማስቀጠል ማስቻል ነው " ብለዋል።

አምባሳደር ሳተርፊልድ ከመጋቢት 12- መጋቢት 13 /2014 ዓ/ም በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት እንዲሁም ከረድዔት ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ተነጋግረዋል።

ምንጭ፦ ሮይተርስ

@tikvahethiopia