TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፤ ኢትዮጵያን ከሌሎች አገራት ጋር የሚኖራትን የጸጥታ፣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ግንኙነት በሌሎች ኃይሎች በጎ ፈቃድ እንዲንጠለጠልና ራሷን የማትከላከል ሽባ አገር ያደርጋታል ያሉትን ረቂቅ ህጎች [ HR.6600 እና S.3199 ] እንዳይፀድቁ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ዘመቻ እንዲያደርጉ ይፋዊ ጥሪ አቀረቡ።…
#US #ETHIOPIA

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ፤ በ'US House of Rep.' እየታየ ካለው HR 6600 ረቂቅ ሕግ በተጨማሪ በ'US Senate S 3199' የተባለ ረቂቅ ሕግ ቀርቦ እ.ኤ.አ ማርች 23 በሴኔቱ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ለማየት ቀጠሮ መያዙን ገልፀዋል።

አምባሳደሩ ረቂቅ ሕጎቹ:-
- የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት የሚገፉ፣
- በኮቪድ እና በኑሮ ውድነት የተጎዳውን ኢኮኖሚ በውጭ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዳያገግም የሚያደርጉ፣
- በጦርነት ቤተሰቡን፣ ቤት ንብረቱን ያጣው ወገናችን ፈጥኖ እንዳይቋቋም የሚያደርጉ እና
- የወደሙ የትምህርት፣ የጤናና ሌሎች የመሰረተ-ልማቶች ፈጥነው እንዳይሰሩ የውጭ ብድርና እርዳታ የሚያስከለክሉ ናቸው ሲሉ አብራርተዋል።

በዚህም በአሜሪካ የሚገኙ ወገኖች ከየአካባቢያቸው ለተመረጡ ለሴኔት እና ለኮንግረስ አባላት ፦
👉ስልክ በመደወል፣
👉ደብዳቤ በመጻፍ፣
👉በኢሜል፣
👉በፒቲሽን በመፈረም፣
👉በአካልም እየተገኘ በማነጋገር እና በሌሎች አግባቦች እንዲቃወሙት በማድረግ ኢትዮጵያውያንን ታደጉ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#USA

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ የሚገኙት ከመጋቢት 12- መጋቢት 13 በሚቆይ የስራ ጉብኝት ከኢትዮጵያ መንግስት፣ ከአፍሪካ ህብረት (AU) እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ባለስልጣናት እንዲሁም ከሰብአዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ለመነጋገር ነው።

ልዩ መልዕክተኛው ትላንትና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ከሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እና ከአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ፣ የሰላም እና ጸጥታ ኮሚሽነር ባንኮሌ አዴኦዬ ጋር መክረዋል።

ምክክራቸው ትኩረቱን ያደረገው በሱዳን እና ኢትዮጵያን ጨምሮ በቀጠናው ጉዳዮች ላይ እንደነበር ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት በሰላም እንዲፈታ ለማድረግ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ ላይ የሚታየውን አለመረጋጋት ለመፍታት የሾመቻቸው አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከዚህ ቀደምም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንደነበሩ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ቻይና ውስጥ 133 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737 አውሮፕላን መከስከሱን የቻይና መገናኛ ብዙኃንን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል። የቻይና ኢስተርን አየር መንገድ ንበረት የሆነው ይህ ቦይን 737 ወድቆ መከስከሱ የተነገረው ጓንግዡ ግዛት ውስጥ ነው። አስካሁን በአደጋው ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰዎች የታወቀ ነገር የለም። የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት አውሮፕላኑ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

ቻይና ከትላንናው የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ እስካሁን አንድም የተረፈ ሰው አልተገኘም ብላለች።

ትናንት 132 ሰዎች አስፍርኖ የነበረ " ቦይንግ 737-800 " አውሮፕላን በቻይና ምስራቃዊ ክፍል በደቡባዊ ጓንጊዢ ተራራማ ቦታ ላይ መከስከሱ ይታወሳል።

ምባልባት ከአደጋው የተረፈ ሰው ይኖር እንደሆነ በነፍስ አድን ሰራተኞች ፍለጋ ቢደረግም እስካሁን በህይወት የተረፈ ሰው ማግኘት አለመቻሉን የቻይና መንግስት አስታውቋል፡፡

የነፍስ አድን ሰራተኞች ከአውሮፕላን መከስከስ አደጋው በህይወት ያለ ሰው የማግኘት ተስፋቸው መደብዘዙን ማሳወቃቸውን TRT ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ማግኘት የነበረብንን የደረጃ ዕድገት አላገኘንም " - በካፋ ዞን የሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር መምህራን

ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ ማግኘት የነበረባቸውን የደረጃ ዕድገት ባለማግኘታቸው ለችግር መጋለጣቸውን በካፋ ዞን የሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር መምህራን ገለፁ።

መምህራኑ ያላቸውን ጥያቄ በየደረጃው ላሉ የመንግስት አካላት ቢያቀርቡም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡

መምህራኖቹ ፥ “... ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ ማግኘት የነበረብንን የደረጃ ዕድገት ባለማግኘታችን / ማግኘት የነበረብንን ክፍያ ባለማግኘታችን ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጫና ከመጋለጣችን በላይ የስነልቦና ተፅዕኖ ደርሶብናል ” ሲሉ ነው ቅሬታቸውን ያቀረቡት።

ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ምላሽ የሰጡት የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ሃላፊ አቶ ጥበቡ ገዛኸኝ እንዳሉት ዞኑ ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ ለሰራተኞች ደመወዝ ብቻ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ጉድለት ያሳያል ብለዋል፡፡

ጉድለቱን ለማካካስ እንዲቻል ከክልልና በየደረጃው ከሚገኙ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፤ የመምህራን ደረጃ ዕድገትም ከችግሮቹ መካከል አንዱ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በበኩላቸው ፤ ለጉዳዩ ትኩረት ያለመነፈጉን ገልፀው ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ዞኑ የበጀት ውስንነት ቢኖረውም ለመምህራን ደረጃ ዕድገት ቅድሚያ በመሰጠት ኮሚቴ ተዋቅሮ ምላሽ እንዲሰጥ ይሰራል ብለዋል።

መምህራኑም ችግሩን ከግንዛቤ በማስገባት የዜግነት ሃላፊነታቸውን እየተወጡ ምላሹን በትዕግስት እንዲጠባበቁ መጠየቃቸውን የደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ሐጂ ሀሰን ገመዳ አረፉ።

ታላቁ ዓሊም ሐጂ ሀሰን ገመዳ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ታላቁ ዓሊም ሐጂ ሀሰን ገመዳ እድሜያቸውን በዳዕዋ እና ኢልም በማስቀራት ያሳለፉ ሲሆን ለየትኛውም የሀገራችን መንግስት ሳይንበረከኩ በፅናት የዳዕዋ አገልግሎታቸውን ያስቀጠሉና ፍሬ ማፍራት የቻሉ ነበሩ።

ከአፄ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት እስከ ኢህአዴግ ድረስ ለአምስት ያህል ጊዜ ታስረዋል።

ታለቁ ዓሊም ሐጂ ሀሰን ገመዳ ባደረባቸው ህመም የህክምና ክትትል ሲያደረጉ ቆይተው ትላንት ለሊት አርፈዋል። የሐጂ ሀሰን እድሜ ከ120 - 130 ባለው መከከል እንደሆነ ይነገራል።

በቅርቡ " ሂጅራ ባንክ " በሻሸመኔ ከተማ የከፈተውን ቅርጫፍ በስማቸው እንዲሆን አድርጎ ነበር።

ትላንት ለሊት ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት ሐጂ ሀሰን ገመዳ የቀብር ስነስርዓታቸው ዛሬ በሻሸመኔ ከተማ ተፈፅሟል።

በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ አቶ ጀዋር መሐመድ እና ዶ/ር ጄይላን ከድር ጨምሮ እጅግ በርካታ ሰው ተገኝቶ ነበር።

መረጃው ከሂጅራ ባንክ ፣ ከኡስታዝ አህመዲን ጀበል ፣ ከምእራብ አርሲ ኮሚኒኬሽን ያሰባሰብነው ነው።

https://t.iss.one/tikvahethAFAANOROMOO

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል። ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንዲያደርጉ ጠይቋል ፦ 1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣…
#MoE

የማመልከቻ ቀኑ ተራዘመ።

የትምህርት ሚኒስቴር ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እንዲያስተካክሉ የሰጠው ጊዜ ትላንት መጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ ይፋ ባደረገው ማስታወቂያ ለተጨማሪ ቀናት አራዝሟል።

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾ የሚከተሉትን መረጃዎች እንዲመለከቱ ጠይቋል ፦

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቻውን እስከ መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በ https://Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ ጠይቋል፤ ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ ሚኒስቴሩ የማናስተናግድ መሆኑን አሳውቋል።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ ሚኒስቴሩ ያሳሰበ ሲሆን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
" No to War ! No to NATO ! "

የካናዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜላኒ ጆሊ ንግግራቸው በተቃውሞ ተቋረጠ።

በሞንትሪያል የውጭ ግንኙነት ካውንስል ንግግር ሲያደርጉ የነበሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜላኒ ጆሊ ንግግራቸው የፖለቲካ እና የፀረ ጦርነት አክቲቪስት እንደሆነ በተነገረለት ካናዳዊው ኢቭ ኢንግለር አማካኝነት ተቋርጧል።

ኢንግለር ፥ ካናዳ ጦርነቱን ከማባባስ ትታቀብ ፤ ዩክሬንን በወታደራዊ ትጥቅ ከመደገፍ ታቀቡ ፤ ወታደሮችን ማሰልጠን አቁሙ ፤ ኬየቭን ለምን ወደ ሚኒስክ ስምምነት አልገፋችሁም ? ለምን ? ፣ ልታፍሩ ይገባል ፤ ' No to War , No to NATO ' ወደ ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ልትገፉን ነው ፤ ዩክሬንን በሩስያ ላይ ለእጅ አዙር ጦርነት መጠቀም አቁሙ " ሲል ተደምጧል።

ክስተቱን በእጅ ስልኩ እየቀረፀ ተቃውሞን ያሰማው ኢቭ ኢንግለር በደህንነት ሰዎች እየተገፋ ከአዳራሹ እንዲወጣ ተደርጓል።

ካናዳ ዩክሬንን እያስታጠቁ ካሉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በ 'ኦጋዴን' ተፋሰስ ያለውን የነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መጠን እና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነቱን ለማጥናት የሚያስችል ስምምነት በኢትዮጵያ መንግስትና በአሜሪካ ኔዘርላንድስ ስዌል እና አሶሼት ኢንክ በተባለ ኩባንያ መካከል ትላንት ተፈፅሟል።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን በተገኙበት የኢትዮጵያ ማዕድን ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ እና የኩባንያው ምክትል ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ዎልፍ ተፈራርመዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ዎልፍ ፦

" ... የኢትዮጵያ ህዝብ ከውጭ ከሚመጣ የነዳጅ ምርት አቅርቦት በመላቀቅ የሀገሩን ሀብት መጠቀም እንዲችል የተጀመረውን ጥረት እናደንቃለን።

ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር በኦጋዴን ተፋሰስ ያለውን ክምችት እና ሃብት ለማየት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመናል። ይህም ሚኒስቴሩ በሀገሪቱ ያለውን የነዳጅ ክምችት እና ሃብት መጠን በአግባቡ እንዲረዳና ቀጥሎም ኢኮኖሚያዊ አዋጭነት ባለው መንገድ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል እንዲያቅድ ይረዳዋል።

የጥናት ስራውን በሚቀጥለው ሰኞ / ሳምንት እንጀምራለን። ፕሮጀክቱ የ4 ወር ጊዜ ያለው ሲሆን በዚህ ጊዜ ለማጠናቀቅ ብቁ ሰዎችን እናመጣለን "

ኢ/ር ታከለ ኡማ (የማዕድን ሚኒስትር) ፦

" ... ይሄን የተፈጥሮ ጋዝን ለይቶ አውቆ ፣ ኢኮኖሚያዊ አዋጭነቱን እንዲሁም ለምን እንደምንጠቀም በአራት ወር ጊዜ ውስጥ ለመንግስት ካስረከበ በኃላ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት በከፊል ለመዳበሪያ ምርት በከፊል ለኢነርጂ የምንጠቀምበት ይሆናል "

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ፦

" ... ኢትዮጵያ በኦጋዴን ያለው እምቅ ሃብት ለመጠቀም በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ ከሆነው ኩባንያ ጋር በመስራቷ ደስተኛ ነኝ። ኩባንያው ጥልቅ እውቀት ባላቸው ባለሞያዎቹ ብቻ ሳይሆን ለደንበኞቹ ስኬት ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርግ ነው። "

ከዛሬ 4 ዓመት በፊት (ሰኔ 20/2010 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ በPOLY GCL የተሰኘው የቻይና ኩባንያ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ የድፍድፍ ነዳጅ የሙከራ ምርት እንደምትጀምር ገልፀው እንደነበር ይታወሳል።

ሰኔ 20 /2010 ዓ/ም ላይ ሚዲያዎች በነጋታው ማለትም በ (ሰኔ 21) የድፍድፍ ነዳጅ የሙከራ ምርት እንደሚጀመር ቦታውም በምስራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኦጋዴን ኤሊሊ አከባቢ መሆኑን መግለፃቸው የሚዘነጋ አይደለም።

በወቅቱ በሙከራ ደረጃ በቀን 450 በርሚል ድፍድፍ ነዳጅ የማውጣት ስራ ይጀመራል ፤ ወደ ጅቡቲም ከመስከረም 2011 ጀምሮ የፕይፕ ዝርጋት ስራ ይጀመራል ሲባል ነበር።

ያንብቡ : telegra.ph/SOMALI---OGADEN-03-23
#Oxfam

" ኦክስፋም " ከአፍሪካ ቀንድ አስከፊ ድርቅ ጋር በተያያዘ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

ኦክስፋም ፥ በአፍሪቃ ቀንድ በተከሰተው አስከፊ ድርቅ ለረሐብ ለተጋለጠው ሕዝብ መርጃ የሚዉል ገንዘብ ካልተገኘ ከፍተኛ ሰብአዊ ድቀት ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል።

👉ኢትዮጵያን፣
👉 ሶማሊያን
👉 ኬንያን በመታዉ ድርቅ 13 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሐብ መጋለጡን WFP ካስታወቀ 2 ወር ሊሞላ ነው።

ድርጅቱ እንዳስታወቀዉ ለረሐብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ መርጃ የሚዉል የምግብ እሕል መግዢያ 6 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገዋል።

የብሪታንያዉ ግብረ ሰናይ ድርጅት ኦክስፋም ትናንት እንዳስታወቀዉ ለርዳታ ከተጠየቀዉ ገንዘብ እስካሁን የተገኘዉ 3 ከመቶ ብቻ ነዉ።

የኦክስፋም የበላይ ኃላፊ ጋብርኤላ በቸር እንዳሉት ባሁኑ ወቅት ምስራቅ አፍሪቃ በዓለም አቀፉ መድረክ ርዕስ አለመሆኑ " ጨካኝ " ሐቅ ነዉ። ብለውታል።

" ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በተለይ ምዕራቡ ዓለም ሙሉ ትኩረቱን በዩክሬኑ ጦርነት ላይ በማድረጉ ሌሎች በርካታ ሰብአዊና ፖለቲካዊ ቀዉሶች እየተዘነጉ ነዉ " ያሉት ኃላፊው " ምሥራቅ አፍሪቃን የመታዉ ድርቅ በመዘንጋቱ በያዝነዉ 2022 በብዙ መቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች በረሐብ ሊሞቱ አይገባም። " ብለዋል።

ባሁኑ ወቅት ድፍን ዓለም " የተቃጠለች " ያክል ስሜት ቢኖርም ለጋሾች ሰብአዊ መብትንና ሰብአዊ ቀዉስን በመከላከሉ ረገድ አንዱን ከሌላዉ ሊመርጡ አይገባም ሲሉ በቸር ማስገንዘባቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ማጀስቲክ

ማጀስቲክ ኢንቴሪየር ዲዛይን እና የፊኒሺንግ ስራዎች ለቢሮዎች ፤ለሆቴልና ካፌዎች፤ ለተለያዩ የንግድ ሱቆች እና ለመኖሪያ ቤቶች የሚሆኑ ፡-
- Interior design & Architectural planning
- Finishing works
- Wood working & Furniture በማንኛውም ጊዜና ቦታ ካሉበት ሆነው ምን ማሰራት እንደሚፈልጉ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ባለሙያዎቻችንን ያማክሩ፡፡ አድራሻዎቻችን፡- 0901911111/0901919991/ 0911253679/89
Telegram:- @majestic_interior
Contact :- @majesticinteriors
📍 A.A,Getu commercial Center,Office 418 & 404