TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
PHOTO : የ2022 የቤል ግሬድ የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል።

ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።

ትላንት ለሊት ላይ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊያን🇪🇹 አትሌቶቻችን ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።

በ1500 ሜትር ሴቶች ውድድር ፦

1ኛ. አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ ለሀገራችን ስታስገኝ ፤
2ኛ. አክሱማዊት እምባዬ ለሀገራችን የብር ሜዳሊያ አገኝታለች፡
3ኛ. ሂሩት መሸሻ ሶየነሐስ ሜዳሊያ ለሀገራችን አስገኝተያለች።

ለሀገሯ ወርቅ ያስገኘችው ጉዳፍ 3:57.19 የገባችበት ደቂቃ አዲስ የሻምፒዮናው ሪከርድ ማስመዝገብ ችላለች።

ኢትዮጵያ ቀደም ብሎ በ3,000 ሜትር ሴቶች ውድድር በለምለም ኃይሉ ባገኘችው ወርቅ እና እጅጋየሁ ታዬ ባገኘችው የነሐስ ሜዳሊያ የሻምፒዮናውን የሜዳሊያ ሰንጠረዥ በሁለት ወርቅ፣ አንድ ብር እና ሁለት ነሐስ በድምሩ 5 ሜዳሊያዎች በአንደኝነት እየመራች ትገኛለች።

More : @tikvahethsport
#zTruck

በኢትዮጵያ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ 3 መተግበሪያዎች በዚህ ሳምንት ይፋ ሆነዋል።

መተግበሪያዎቹ ይፋ የሆኑት በ " ዚ ትራክ የትራንስፖርት አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር " ነው።

ዚ ትራክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት ፤ በሞባይል ስልክና በኮምፒውተር ላይ ተጭነው የሚሰሩ ሶስት መተግበሪያዎችን ሰርቶ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

መተግበሪያው በሀገራችን ውስጥ ያለውን የሎጀስቲክ አሰራር የሚያሻሽሉና የሚያቀሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጅን በመጠቀም ምርታማነትን የሚጨምሩ፣ የሃገርን እድገት የሚያፋጥኑ ናቸው ብሏል።

በኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት አስተዳደር እና ኢንኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እውቅና እንዳለውም ተገልጾልናል።

መተግበሪያዎቹ በጭነት ትራንስፖርት ሥራ ለተሰማሩ አስተላላፊዎች አሽከርካሪዎች ደንበኞች አስጫኞች በቀላሉ እና በግልጽ የሚግባቡበት ሲሆን በቅንጅት እየተናበቡ የጭነት አገልግሎት ሰጪውንና ፈላጊውን አገናኝተው የተጫነው እቃ፦
👉 የት እንደደረሰ፣
👉 መቼ በአስጫኙ እጅ እንደሚገባ፣
👉 በግልፅ ለከፋዩም ሆነ ለአገልግሎት ሰጪው ተመኑ ስንት እንደሆነ ታውቆ ጭነቱ በአስተማማኝ ይዞታና በቅልጥፍና ወደፈለጉበት ቦታ የሚደርስበት ዘመናዊ አሰራር የሚከተል መሆኑ ድርጅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

@tikvahethiopia
" ሥራ ፈጣሪ አልቃሻ አይደለም " - አቶ ክብረት አበበ

ጠብታ አንቡላንስ ትላንትና በአዲስ አበባ ጥይት ቤት በሚባለው አከባቢ 700 ካሬ ሜትር በሚሆን መሬት ላይ ሁለገብ አገልግሎት መስጫ ዋና መስሪያ ቤቱን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥና የቁፋሮ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት አካሂዷል።

የጠብታ አንቡላንስ መስራች አቶ ክብረት አበበ ከ13 ዓመት በፊት መኖሪያ ቤታቸውን ሸጠው የመሰረቱት ተቋም አሁን ላይ 15 አምቡላንሶችና ከ65 በላይ ቋሚ እና ከ27 በላይ ጊዜያዊ ሰራተኞች አሉት።

በሀገር ውስጥ እንዲሁም እስከ ኤርትራ ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ አልፎም እስከ ባንኮክና ህንድ ድረስ አገልግሎት እየሰጠም ይገኛል።

ይህንን ሁሉ አልፈው የመሰረተ ድንጋይ በማስቀመጥ እንዲሁም ቁፋሮውን ያስጀመሩት የህንጻ ግንባታ ምሥራቅ አፍሪካ ሀገራትን የሚያገለግል ኮሌጅ፣ የዲያግኖስቲክ ማዕከል፣ የድንገተኛ አደጋ መከላከያ ቁሳቁሶች ማምረቻ፣ የአንቡላንስ ዲስፓች ሴንተር እንዲሁም የሄሊኮፕተር አንቡላንስ ማረፊያ ይኖረዋል ብለዋል።

በአደጋ ወቅት አንገት ቀና ማድረግና አለማድረግ የሰውን ህይወት ይወስናል የሚሉት አቶ ክብረት የመጀመሪያ ደረጃ ድንገተኛ ህክምናን ሀብታም ደሃ ሳንለይ መስጠታችን NGO ሳይሆኑ ማኅበረሰብን እያገለገሉ መለወጥ እንደሚቻል ለብዙዎች ትምህርት መሆን ችለናል ብለዋል።

እንደ አገልግሎታቸወ ከመንግሥት መሬት ለማግኘት ብዙ ቢጥሩም አለመሳካቱን የሚናገሩት መስራቹ ''ሥራ ፈጣሪ አልቃሻ አይደለም ቢከለክሉኝም ከእናት ባንክ ተበድሬ መሬቱን ገዝቻለው ይህንን ህንጻም ለመጨረስ 150 ሚሊዮን ብር ያስፈልገናል፥ ለጊዜው ባይኖረንም እንደምንጨርሰው ግን አንጠራጠርም'' ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (UAE) ወደ ትግራይ ክልል የምግብ እርዳታ ላከች። ሀገሪቱ 35 ቶን ምግብ የጫነ አውሮፕላን ወደ የትግራይ ክልል መዲና መቐለ በዛሬው እለት መላኳን ገልጻለች፡፡ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አምባሳደር ሞሀመድ ሳሊም አልረሽድ ፥ " የተደረገው የምግብ እርዳታ በትግራይ ክልል ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ ለመርዳት ነው " ብለዋል፡፡ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ…
#Tigray , #Mekelle📍

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ወደ ትግራይ ክልል 30 ቶን የምግብ ድጋፍ ላከች።

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ለትግራይ ህዝብ አስፈላጊ እርዳታ በአየር ለማጓጓዝ በሚደረገው የሰብአዊ ድጋፍ ጥረት 30 ቶን የምግብ ድጋፍ የጫነ አውሮፕላን ወደ ትግራይ ክልል መዲና መቐለ መለኳ ተሰምቷል።

ድጋፉ 5,600 ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ከ7,000 በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

አሁን ባለው ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የቤተሰቦችን በተለይ የሴቶችን እና የህጻናትን ፍላጎት ይደግፋል ተብሏል።

ባለፈው ወር የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ወደ ትግራይ ክልል 35 ቶን የምግብ እርዳታ መላኳ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

መንግሥት ትግራይን ጨምሮ በጦርነት እና ግጭቶች የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እና ነዋሪዎችን ለማቋቋም ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ፕሮጀክቱን ይፋ ያደረገው የገንዘብ ሚኒስቴር ሲሆን ከውጭ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው።

አሁን ይፋ የሆነው ለመፈፀም አምስት ዓመታት ይፈጃል የተባለው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን ትግራይ፣ አማራ ፣ አፋር ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል፤ እንዲሁም በምዕራብ ኢትዮጵያ በኩል ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ቅድሚያ አግኝተዋል።

ይፈጃል ከተባለው ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ከዓለም ባንክ የሚገኝ ሲሆን ቀሪውን የኢትዮጵያ መንግስት ይሸፍነዋል።

በፕሮጀክቶቹ ከታቀዱት ተግባራት መካከል ፦

👉 በግጭት የተጎዱ ወገኖችን አፋጣኝ ፍላጎት ማሟላት፤
👉 ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ተጎጂዎች እንዲያገግሙ፤ አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላት ማቋቋም፤
👉 መሰረተ ልማቶችን መልሶ ማቋቋም፤
👉 ለመልሶ ሟቋቋም የሚደረገውን ጥረት በዘላቂነት መደገፍ የሚችሉ ተቋማትን ማጠናከር ይገኙበታል።

ፕሮጀክቱን ለማስፈፀምና ለመከታተል የተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶችን ያካተተ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ፕሮጀክቱን ለማስፈፀም ዋና ኃላፊነት የተሰጠው ለገንዘብ ሚኒስቴር ነው።

ፕሮጀክቱ ግጭት እና ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ላይ ከመንግስት ድጋፍ ውጭ መግባት እና መስራት ከሚችሉ የ3ኛ ወገን አካላት ጋር በመዋዋል ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ውል የሚገቡት የ3ኛ ወገን አካላት ፕሮጀክቶቹን ግልፅ እና ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ተፈፃሚ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው ፤ የአካባቢው አስተዳደር ሚናን በመተካትም የፕሮጀክት ሂደቱን የማመቻቸት እና ውጤታማ የማድረግ ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳሉ መባሉን ሪፖርተር አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA መንግሥት ትግራይን ጨምሮ በጦርነት እና ግጭቶች የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት እና ነዋሪዎችን ለማቋቋም ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል። ፕሮጀክቱን ይፋ ያደረገው የገንዘብ ሚኒስቴር ሲሆን ከውጭ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው። አሁን ይፋ የሆነው ለመፈፀም አምስት ዓመታት ይፈጃል የተባለው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን ትግራይ፣ አማራ ፣…
#ETHIOPIA

IOM (ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት) በመስከረም 2014 ዓ/ም ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ እና በጦርነትና በግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም ይፋ በተደረገው ፕሮጀክት ላይ በቀረበው ሰነድ መሰረት ፦

👉 በኢትዮጵያ ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች አሉ፤ ይህ ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለቱይ ተፈናቃዮች መካከል ትልቁ ነው።

👉 ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች መካከል ከ50 % በላይ ሴቶች ሲሆኑ ቢያንስ 720 ,000 ህፃናትም ተፈናቅለዋል።

👉 ከ4.2 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች 80 % በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ናቸው ፤ 50 በመቶዎቹ (2.08 ሚሊዮን ገደማ) ባለፉት 6 እና 7 ወር የተፈናቀሉ ናቸው።

👉 ከአጠቃላይ ተፈናቃዮች ወደ 90 % (1.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች) በትግራይ ክልል ናቸው።

NB : በሰነዱ ያልተካተቱ ተፈናቃዮች በአፋር እና አማራ ክልሎች የሚገኙ ሲሆን አጠቃላይ የተጎጂዎች ልየታ እና ምዘና በአሁን ወቅት እየተካሄ እንደሚገኝ ሪፖርተር አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዶ/ር በለጠ ሞላን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ።

አቶ መልካሙ ሹምዬ ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ ፤ ፓርቲው ለ3 ቀናት የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ሲያካሂድ እንደቆየና የሥራ አስፈፃሚ አባላቱን በአዲስ በማደራጀት ማጠናቀቁን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት፦

👉 ዶ/ር በለጠ ሞላ - ሊቀመንበር
👉 አቶ መልካሙ ሹምዬ - ምክትል ሊቀመንበር
👉 ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ - የውጭ ግንኙነት ኃላፊ
👉 አቶ ዩሱፍ ኢብራሒም - የሕግ ጉዳዮች ኃላፊ
👉 አቶ ክርስቲያን ታደለ - የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ክፍል ኃላፊ
👉 አቶ ጋሻው መርሻ - የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ
👉 አቶ ጣሂር መሐመድ - የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ
👉 ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃ/ማርያም - የአብን ጽ/ቤት ኃላፊ
👉 አቶ ሐሳቡ ተስፋየ - አደረጃጀት ጉዳዮች ኃላፊ አድርጎ የሥራ አስፈፃሚውን በአዲስ አደራጅቷል።

ከተመረጡት የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚዎች መካከል ሦስቱ አዲስ መሆናቸው ተገልጿል።

ፓርቲው ዛሬ 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ማካሄድ መጀመሩን #ኢብኮ / #አሚኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ አሽቆለቆለ። በዩክሬንና ሩስያ ጦርነት ምክንያት ባለፉት ሳምንታት የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ ማሻቀቡ ፤ በበርሜልም እስከ 140 ዶላር ድረስ ደርሶ ነበር። በዚህ ሳምንት ግን የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ መቀነሱ ተነግሯል። አሁን ላይ ፤ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል 98.50 ዶላር ሲሆን በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት 1 በርሜል ነዳጅ 96.14 ዶላር በሆነ…
#Update

የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 💵

🛢️ እ.ኤ.አ. ህዳር አንድ 👉 68 ዶላር
🛢️ እ.ኤ.አ. ታህሳስ አንድ 👉 77 ዶላር
🛢️ እ.ኤ.አ. ጥር አንድ 👉 89 ዶላር
🛢️ እ.ኤ.አ. የካቲት አንድ 👉 97 ዶላር
🛢️ ዛሬ ላይ የአንድ በርሜል የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 👉 108 ዶላር ደርሷል።

የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከቀናት በፊት ባለፉት ሳምንታት ከታየው ከፍተኛ ጭማሪ (እስከ 140 ዶላር ድረስ ደርሶ ነበር) ወርዶ ከአንድ መቶ ዶላር በታች የነበር ሲሆን አሁን ወደ ላይ እያሻቀበ ይገኛል።

መረጃው ከቢዝነስ ኢንሳይደር የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
PHOTO : የ2022 የቤል ግሬድ የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል። ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል። ትላንት ለሊት ላይ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊያን🇪🇹 አትሌቶቻችን ከአንድ እስከ ሶስት ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል። በ1500 ሜትር ሴቶች ውድድር ፦ 1ኛ. አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ ለሀገራችን ስታስገኝ ፤ 2ኛ. አክሱማዊት እምባዬ ለሀገራችን የብር ሜዳሊያ አገኝታለች፡ 3ኛ. ሂሩት…
ፎቶ ፦ ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 የደመቀችበት የቤልግሬድ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ዛሬ ቀጥሎ የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች።

ዛሬ በተካሄደ የ3000 ሜትር ውድድር ሰለሞን ባረጋ እና ለሜቻ ግርማ ተከታትለው በመግባት የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል።

የቤልግሬድ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል።

ሁሉንም የስፖርታዊ ጉዳዮችን በ @tikvahethsport ይከታተሉ።