#ማጀስቲክ
ማጀስቲክ ኢንቴሪየር ዲዛይን እና የፊኒሺንግ ስራዎች ለቢሮዎች ፤ለሆቴልና ካፌዎች፤ ለተለያዩ የንግድ ሱቆች እና ለመኖሪያ ቤቶች የሚሆኑ ፡-
- Interior design & Architectural planning
- Finishing works
- Wood working & Furniture በማንኛውም ጊዜና ቦታ ካሉበት ሆነው ምን ማሰራት እንደሚፈልጉ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ባለሙያዎቻችንን ያማክሩ፡፡ አድራሻዎቻችን፡- 0901911111/0901919991/ 0911253679/89
Telegram:- @majestic_interior
Contact :- @majesticinteriors
📍 A.A,Getu commercial Center,Office 418 & 404

TIKVAH-ETHIOPIA
" ከ20 ሺህ በላይ የተማሪዎች ቅሬታዎች ላይ ምላሽ ተሰጥቷል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ከፈተና እርማት እና ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው የፈተናው እርማት ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በጥንቃቄ የተከናወነ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ፈተና እርማት ላይ የቴክኒክ ችግር ማጋጠሙን…
#Update
ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጠ።
የትምህርት ሚኒስቴር ከ " 12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ውጤት እና ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ " ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍል ከ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ጋር ተያይዞ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው የ12ኛ ክፍል ፈተና በ2 ዙር እንዲሰጥ መደረጉንና በመጀመሪያው ዙር የስነ-ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ከፈተናው ቀን ቀድሞ በመውጣቱና የውጤት ግሽበት በመምጣቱ እንዲሰረዝ መደረጉን ተናግረዋል።
በመጀመሪያ ዙር ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው በመጀመሪያው ዙር ፈተና ከወሠዱት 544ሺ 682 ተማሪዎች ውስጥ 44 ከመቶዎቹ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል።
በሁለተኛው ዙር ከተፈተኑት 53ሺ 997 ተማሪዎች ውስጥ 28 ከመቶዎቹ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ሲሆን ከመጀመሪያው ዙር 554 ሺ 682 ተፈታኞች ውስጥ ደግሞ 25 ከመቶዎቹ ይመደባሉ ብለዋል።
የ10 ክፍል የማትሪክ ፈተና በመቅረቱ ምክንያት በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች በዘንድሮው አመት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ወስደዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው አራት ዩኒቨርሲቲዎቻችን መቀበል በማይችሉበት ሁኔታ ከአምናው የተሻለ ቁጥር ያለው ተማሪ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉን አብራርተዋል።
በትግራይ ያሉ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውና ዘንድሮም ይመደቡ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉ 48ሺ ተማሪ የቅበላ አቅም አጥተናል ብለዋል።
ነገር ግን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር በ43 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 152 ሺ 14 ተማሪዎች እንዲመደቡ መደረጉና ይህም ከአምናው የቅበላ አቅም ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል።
ፀጥታ ችግር ያጋጠማቸው አከባቢዎች በተመለከተ የተለየ መቁረጫ ነጥብ ለመወሰን የሚያስገድድ የውጤት ትንተና ስላልተገኘ በበመደበኛው የመቁረጫ ነጥብ ተስተናግደዋል ብለዋል።
በባለፈው አመት በ47 ዩኒቨርሲቲዎች 147 ሺህ ተማሪዎች ምደባ የተደረገ ሲሆን ዘንድሮ በ43 ዩኒቨርሲቲዎች 152ሺ 014 ተማሪዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።
ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር
@tikvahethiopia

#ETHIOPIA 🛫 #SAUDI_ARABIA
ለበርካታ ወራት የተቋረጠው ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ አረቢያ (ጄዳ እና ሪያድ) በረራ መጀመሩ ተገልጿል።
ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተቋርጦ የነበረው በረራ ከመጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደቀጠለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
ለበርካታ ወራት የተቋረጠው ከኢትዮጵያ ወደ ሳዑዲ አረቢያ (ጄዳ እና ሪያድ) በረራ መጀመሩ ተገልጿል።
ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተቋርጦ የነበረው በረራ ከመጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደቀጠለ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
MSF በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች እንቅስቃሴ አቆመ። ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (MSF) በአቢይ አዲ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት (በማዕከላዊ እና ምስራቃዊ ትግራይ) እንቅስቃሴ ማድረግ አቋረጠ። MSF እአአ ጁን 24 በትግራይ ክልል በ3 ባልደረቦቹ ላይ በተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ምክንያት ነው ከላይ በተገለፁት ቦታዎች የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴውን ያቆመው። MSF በሌሎች የትግራይ ክልል አባቢዎች አቸኳይ…
" የኢፌዴሪ መንግስት ምላሽ እና ማብራሪያ ይስጠን " - MSF
ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (MSF) ባለፈው ዓመት ትግራይ ክልል ውስጥ ስለተገደሉት ሠራተኞቹን በተመለከተ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቧል።
MSF ይህን ጥያቄ ያቀረበው የ " ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ " ከግድያው ጋር በተያያዘ አንድ የምርመራ ዘገባ ይፋ ካደረገ በኃላ ነው።
MSF ጋዜጣው ላይ የቀረበው ዘገባ ለሠራተኞቼ ግድያ የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እና አዛዡን ተጠያቂ ያደርጋል ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ለዚህ ሪፖርት ምላሽ ይስጠኝ ሲል ጠይቋል።
ጋዜጣው https://www.nytimes.com/2022/03/17/world/africa/ethiopia-tigray-aid-workers-killed.html የመከላከያ አባላት፤ የእርዳታ ሠራተኞች እና ግድያውን የሚመረምሩ ሰዎችን ዋቢ አድርጎ በሰራው ዝርዝር ዘገባ፤ 3ቱ ሠራተኞች እያፈገፈጉ በነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት መገደላቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።
የMSF ስፔን ፕሬዝደንት ፖውላ ጊል ባወጡት መግለጫ የሠራተኞቹን ግድያ በተመለከተ ድርጅቱ በራሱ ያካሄደው ምርመራ በቀጥታ ገዳዮቹ እነማን እንደሆኑ እና ምክንያታቸው ምን እንደሆነ ማወቅ አልቻለም ብለዋል።
ምንም እንኳን ጋዜጣው በእርዳታ ሠራተኞች ላይ ግድያ የተፈፀመው በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች እንደሆነ ቢያመለክትም በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል አስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

" ትምህርት ሚኒስቴር የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጥልን " - ተማሪዎች በትግራይ ክልል ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች (መቐለ፣ ኣክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ) በርካታ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ትምህርታቸው እንዲያጠናቅቁ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል። ከነዚህ ተማሪዎች መካከል የ2013 ተመራቂ ተማሪዎች ይገኙበታል። እንዚህ ተማሪዎች ላለፉት ወራት ትምህርታቸውን ተከታትለው…
#Update
በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተመራቂ ተማሪዎች ቴምፖራሪ ዲግሪ እንዲሰጣቸው ተወስኖላቸዋል።
ይህ ውሳኔ መወሰኑ የተሰማው በ23 ዩኒቨርሲቲዎች በጊዚያዊነት የተመደቡ የተመራቂ ተማሪዎች ተወካዮች ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ዛሬ ተገናኝተው ከመከሩ በኃላ ነው።
የተማሪዎች ተወካዮቹ የተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ቴምፖራሪ ዲግሪ እንዲሰጧቸው ከትምህርት ሚኒስቴር ለተቋማቱ ተሻሽሎ የተጻፈ ደብዳቤ መመልከታቸውን ለ @tikvahuniversity ተናግረዋል።
የተሸሻለው ደብዳቤ ለተቋማቱ እንደተላከም ቲክቫህ ከአንድ ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊ ማረጋገጥ ችሏል።

" አጣርቼ እምርጃ ወስዳለሁ " - መንግስት ትላንትና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨውን አሰቃቂ ቪድዮ (የሰው ልጅ በህይወት እያለ ሲቃጠል የሚያሳይ) በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ አውጥቷል። መንግስት ድርጊቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ ሰሞኑን መፈፀሙን ገልጿል። ድርጊቱ እጅግ አሰቃቂ ፣ ጭካኔ የተሞላበት እና ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ድርጊት ነው ያለው…
#Update
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን የተፈጸመውን ሰውን አቃጥሎ የመግደል ድርጊት የሚመረምር የወንጀል ምርመራ ቡድን ወደ አካባቢው (መተከል ዞን) ረቡዕ መሰማራቱን ተሰምቷል።
ይህ ቡድን 5 አባላት ያሉት ሲሆን ከፍትህ ሚኒስቴር እና ፌደራል ፖሊስ በተውጣጡ መርማሪዎች የተዋቀረው ነው።
በዚህ የምርመራ ቡድን ውስጥ ከፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ሶስት ባለሙያዎች መካተታቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
ቀሪ ሁለቱ አባላት ከፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የተወከሉ ናቸው።
የወንጀል ምርመራው በሁለቱ የፌደራል ተቋማት የሚከናወን መሆኑን እና የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት የአጋዥነት ሚና እንደሚኖረው " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " የየፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
በመተከል ዞን፣ ጉባ ወረዳ፣ አይሲድ ቀበሌ ከሁለት ሳምንት በፊት የተፈጸመው በህይወት ያለን ሰው አቃጥሎ የመግደል ድርጊት በመንግስት የጸጥታ አባላት ተሳትፎ ጭምር መከናወኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ባለፈው እሁድ አስታውቆ እንደነበር አይዘነጋም።
መንግስትም ማንነታቸው ምንም ይሁን ምን ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ቃል ቀብቶ እንደነበር ይታወሳል።

#Update የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ #ሩሲያን በማውገዝ እና ወታደሮቿን ከዩክሬን እንድታስወጣ በቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ዛሬ ድምፅ ሠጠ። በዚህም ከ193 ሀገራት መካከል 141 ሀገራት ድጋፍ ሲሰጡ ፣ 5 ሀገራት ውሳኔ ሀሳቡን ተቃውመዋል፣ 35 ሀገራት ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ጨምሮ 13 ሀገራት በድምፅ አሰጣጡ ላይ ሙሉ በሙሉ አልተሳተፉም። የውሳኔ ሀሳቡን የተቃወሙ…
" በዩክሬን ጉዳይ ገለልተኛ መሆን አይቻልም " - አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ
በቅርቡ ተጠርቶ በነበረው የተመድ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ብዙ የአፍሪካ ሃገሮች በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ላይ ተአቅቦ ማስመዝገባቸው “ሃገሮቹ ከማንም ጋር አለመወገናቸውን የሚያሳይ ቢሆንም በዚህ ጉዳይ ገለልተኛ መሆን እንደማይቻል” በድርጅቱ የአሜሪ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ አስታወቁ።
ዛሬ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ የሩሲያን ወረራ መዘዝ አፍሪካዊያኑ ሃገሮች እንዲገነዘቡት ለማድረግ ተጨማሪ ጥረቶች እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
“[ሃገሮቹ] ያንን አቋም መያዛቸው መብታቸው ቢሆንም ሁኔታውን ከዓለምአቀፍ ሥርዓት አኳያ መመልከትም ትክክለኛው አካሄድ ነው” ብለዋል።
“ይህ ቀዝቃዛ ጦርነት አይደለም " ያሉት አምባሳደሯ " በአሜሪካና በሩሲያ ወይም በምዕራቡና በሩሲያ መካከል ያለ ፉክክርም አይደለም።” ሲሉ ተደምጠዋል።
በመቀጠልም ፤ “ ይህ ሩሲያ በጎረቤቷ ላይ የከፈተችው ጥቃት ነው፤ ሩሲያ በመንግሥታቱ ድርጅት አስኳል እሴቶች ላይ የፈፀመችው ጥቃት ነው፤ እየተጋፈጥን ያለነው ዩክሬን ላይ ከፈፀመችው ጥቃት ጋር ነው ” ብለዋል።
“በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል ያለ ወረራ ጦርነት አይደለም” ሲሉ አምባሳደሯ ማሰስባቸውን ቪኦኤ ቢቢሲን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።
በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ከተመዘገበው የተአቅቦ ድምፅ ግማሽ ያህሉ የአፍሪካ ሃገሮች ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በድምፅ አሰጣጡ ላይ አልተሳተፈችም። በወቅቱ በነበረው ድምፅ አሰጣጥ ኢትዮጵያ ወንበሩን ባዶ በማድረግ ስብሰባውን ማለፏ በበሳል ዲፕሎማሲ የተደረገ ውሳኔ መሆኑ ከቀናት በፊት መግለፁ ይታወሳል።

#አዲስ_የልብ_ህክምና
የልብዎ ጤንነት ያለበት ሁኔታ ያውቃሉ?
ሙሉ የልብ ምርመራ በማድረግ የልብዎ ጤንነት ያለበትን ደረጃ ይወቁ። ይሄን ጥቅል በመግዛት ለወዳጅ ዘመዶ ያበርክቱ
ዛሬዉኑ ደዉለዉ ቀጠሮ ያስይዙ
0952343434
Telegram 👉:https://t.iss.one/addiscardiachospitalplc
ለልብዎ ከልብ እንሰራለን

''...በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ምላሽ እየጠበኩ ነው'' የአበክመ ት/ቢሮ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የፈተና በውጤት እና መቁረጫ ነጥቡ ዙሪያ አስፈላጊው ማብራሪያ እንዲሰጥ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ጥያቄ አቅርቤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ዛሬ ተገቢው ማብራሪያ እንደሚሰጥ ገልጾልኛል ሲል…
የቀጠለው ቅሬታ ...
የምስረቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ከ12ኛ ክፍል ፈተና ጋር በተያያዘ የተነሳው ቅሬታ ነፃ እና ገለልተኛ በሆኑ አካላት ተጣርቶ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጠው ጠየቀ።
መምሪያው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ዉጤት በማስመልከት ለትምህርት ሚኒስቴር ቅሬታ ማቅረቡን እና ተገቢ ምላሽ ሊሰጠዉ እንደሚገባም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።
በዞኑ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በ40 ት/ቤቶች በሶሻል ሳይንስ 15,222 ተማሪዎች ተፈትነው 1765 ተማሪዎች 11.6% ማለፋቸው በናቹራል/ተፈጥሮ/ሳይንስ ደግሞ 7,075 ተፈትነው 1,619 (22.8%) ተማሪዎች ብቻ ማለፋቸውን ተመላክቷል።
የዞኑ ትምህርት መምሪያ ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና አስተራረም እና የውጤት አሞላል ችግር ያለበት መሆኑን በተደጋጋሚ ብንገልጽም የተሰጠው ምላሽ አጥጋቢ እንዳልሆነ ገልጿል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ባወጣው መግለጫ ፥ ለቀረበው ቅሬታ ምክንያት ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል አንደኛው የአብርሃ አፅብሃ 2ኛ ድረጃ ት/ቤት አንድ ተማሪ (አማኑኤል ፀሐይ) በመጀመሪያ የተለቀቀው ውጤት 162 ሆኖ በኦንላይ ቅሬታ ቢያቀብርም ሳይፈታለት ቀርቶ በአካል በሀገር አቀፍ ፈተና አገልግሎት ቀርቦ ሲያስፈትሽ 647 ሆኖ ተገኝቷል ብሏል።
ሌላው ተማሪዎች ፈተና ሲወስዱ በክልሉ ጦርነት የነበረበት ወቅት በመሆኑና ወላጆችም ግንባር የዘመቱ በመሆናቸው ተማሪዎች በስነልቦና ጫና ውስጥ ሆነው ፣ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እየሰሙ መፈተናቸውን ይህ እየታወቀ እንደ ሰላማዊ ጊዜ ከሌሎች ክልሎች እኩል የመግቢያ ውጤት መወሰኑ ችግር ያለበት እና ኢፍትሃዊ እንደሆነ ገልጿል።
ያንብቡ : telegra.ph/East-Gojjam-03-19

#Ukraine #Russia
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሩሲያ ጋር ውጤት የሚያስገኝ የሰላም ንግግር በአስቸኳይ ማድረግ እንደሚፈልጉ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ለሕዝባቸው ባስተላለፉት የቪድዮ መልዕክት በግዛታቸው ውስጥ ግዙፍ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ካለችው ሩሲያ ጋር " ካለምንም መዘግየት ትርጉም ያለው " የሰላምና የደኅንት ንግግር እንዲጀመር ጠይቀዋል።
ይህ ሩሲያ በአገራቸው ላይ በከፈተችው ወረራ በፈጸመችው "ስህተት" የሚደርስባትን ጉዳት ለመቀነስ ያላት ብቸኛው እድል ነው ሲሉ ዜሌንስኪ ተናግረዋል።
" ለመገናኘት፣ ለመነጋገርና የዩክሬንን የግዛት አንድነት እንዲሁም ፍትህን ወደነበረበት ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው " ሲሉ ዜሌነስኪ ለሩሲያ ጥሪ አቅርበዋል።
" ይህ ካልሆነ ግን ሩሲያ ከሚገጥማት ውድቀት ለመውጣት በርካታ ትውልዶችን መጠበቅ ሊያስፈልጋት ይችላል " ማለታቸውን #ቢቢሲ ዘግቧል።
በሌላ በኩል ፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ሀሙስ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት አገራቸው ጦርነቱን ለማቆም ከዚህ በፊት ይፋ አድርጋው የነበረውን ቅድመ ሁኔታዎች በድጋሚ ገልፀዋል።
ዋነኞቹ ቅድመ ሁኔታዎች ፦
- ዩክሬን NATOን እንደማትቀላቀል ማረጋገጥ።
- ዩክሬን ትጥቅ እንድትፈታ፣
- በዩክሬን የሩሲያ ቋንቋ እንዲከበር እና የናዚ አመለካከት አራማጅ ናቸው የተባሉ ኃይሎችን ዩክሬን እንድትቆጣጠር፣
- ክራይሚያ የሩሲያ ግዛት መሆኗን፣ በቅርቡ ነጻነታቸውን ላወጁት ምሥራቃዊ የዩክሬን ግዛቶች ደግሞ እውቅና እንድትሰጥ ዋነኞቹ የሩሲያ ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው።

#PMOEthiopia
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)
@tikvahethiopia
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
(ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ)
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PMOEthiopia የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ (ዝርዝሩን ከላይ ያንብቡ) @tikvahethiopia
#Turkey #Ethiopia
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ አካሂዶት በነበረው 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ከቱርክ ሪፐብሊክ ጋር የተደረጉ ወታደራዊ የትብብር ስምምነቶችን ላይ ውይይት አድርጓል።
ምክር ቤቱ ፤ ቱርክና ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ ጥብቅ ወዳጅነት ያላቸው መሆኑን በማስታወስ ቱርክ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን አጋር መሆኗን በተደጋጋሚ ያረጋገጠች አገር ናት ብሏል።
በዚህ መነሻነት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቱርክ አንካራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቀት ነሃሴ 12 ቀን 2013 ዓ/ም የተፈረሙ ሶስት ስምምነቶች ለምክር ቤቱ ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ገልጿል።
ከስምምነቶቹ አላማ ፦
👉 በትምህርትና ስለጠና፣
👉 የጋራ ወታደራዊ ልምምዶች፣
👉 በመከላከያ ኢንዱስትሪ ግንባታ፣
👉 የሳይበር ጥቃት መከላከል፣
👉 በሰላም ማስከበር፣
👉 የወታደራዊ ፋይናንስ ትብበብር፣
👉 በባህር ላይ ዉንብድና መከላከል ላይ በሚደረጉ ዘመቻዎች ለመተባበር የሚያስችል ማዕቀፍ መፍጠር ነው ብሏል።
ምክር ቤቱ በቀረቡት ሶስት የሁለትዮሽ ስምምምነቶች ላይ በመወያየት ይጸድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ መወሰኑ ተገልጿል።