TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Russia #Poland #Germany አዲስ አበባ ያለው የሩስያ ኤምባሲ ያሰራጨው መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል፤ በኤምባሲዎች መካከልም ውዝግብ ፈጥሯል። የሩስያ ኤምባሲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ለሩስያ ድጋፋቸውን የሚገልፁ በየዕለቱ ብዙ ደብዳቤዎች ፣ በመቶዎች የሚቆጠር አስተያየት እንደሚደርሰው ገልጿል። ይህ መልዕክት እየደረሰው ያለው ከገፁ ተከታዮች መሆኑን አመልክቷል። ኤምባሲው " ሀገሮቻችን…
#Ukraine

በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩክሬን ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ፥ ሩስያ በዩክሬን ላይ በፈፀመችው ወረራ ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍን እና አብሮነት የገለፁትን ተከታዮቹን አንደሚያደንቅ ገልጿል።

" ወዳጆቻችን እናመሰግናለን " ያለው የዩክሬን ኤምባሲ ወረራውን የፈፀመችው ሩስያ በሁሉም ዩክሬናውያን ከተሸነፈች በኃላ ኤምባሲው ቁርጠኛ ለሆኑ የፌስቡክ ወዳጆቹ በሎተሪ ወደ ዩክሬን ከክፍያ ነፃ የመግቢያ ቪዛ ሊሰጥ እያሰበ መሆኑን አሳውቋል።

ኤምባሲው እስከዛሬ ንቁ የሆኑ የፌስቡክ አክቲቪስቶች ብሎ የ38 ሰዎችን (ኢትዮጵያውያን) ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩስያ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ለሩስያ ድጋፋቸውን የሚገልፁ በየዕለቱ ብዙ ደብዳቤዎች ፣ በመቶዎች የሚቆጠር አስተያየት እንደሚደርሰው ገልጾ ፤ " ሀገሮቻችን በችግር ጊዜ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት እንደዚህ አይነት ጠንካራ ፣ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ፣ ወዳጃዊ ግንኙነት ስላላቸው ኩራት ይሰማናል " ማለቱ አይዘነጋም።

ኢትዮጵያውያን ተከታዮቹ እያሳዩት ላለው ድጋፍና ከሩስያ ጎን እንደሚቆሙ መምረጣቸውን በእጅጉ እንደሚያደንቅ መግለፁ ይታወሳል።

ይህን የሩስያ ኤምባሲ መልዕክት ተከትሎ በአዲስ አበባ የፖላንድ እና የጀርመን ኤምባሲዎች የሩስያን ኤምባሲ የሚቃወም ጠንካራ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
" ዩክሬን በቅርቡ NATOን የምትቀላቀልበት ምንም መንገድ የለም " - ቦሪስ ጆንሰን

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ሀገራቸው ዩክሬን የNATO ወታደራዊ ጥምረትን ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት ልታቋርጥ እንደምትችል ሀሳብ ማቅረባቸው ተሰምቷል።

ይህንን ሃሳባቸውን ተከትሎም የብሪታንያው ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን ለሚዲያዎች እንደተናገሩት ዩክሬን በቅርቡ NATOን የምትቀላቀልበት ምንም መንገድ እንደሌለ እና ይህም ለሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ግልፅ እንደተደረገ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " ወደፊት ግን ውሳኔው ለዩክሬን ዜጎች እና ለተመረጠው መሪዋ (ቮድሚር ዜሌኒስኪ) የተተወ ነው ፤ እኛ ግኝ እንደግፋቸዋለን " ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ዜሌኒስኪ ከሩስያ ጋር የተኩስ አቁም እና ሩስያ ጦሯን ከዩክሬን እንድታስወጣ ለማድረግ ድርድር እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም ሩስያ በዩክሬን ላይ ምታካሂደው ወታደራዊ እርምጃ እንዲቆም ከተፈለገ በዋነኝነት ካስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ ዩክሬን NATOን እቀላቀላለሁ የምትለውን ሀሳቧን እርግፍ አድርጋ እንድትተው እና ገለልተኝነቷን እድታረጋግጥ የሚል ነው።

ሩስያ፤ ዩክሬን ለሀገሯና ለህዝቧ በምንም መልኩ ስጋት እንደማትሆን እስካላረጋገጠች ጊዜ ድረስ እርምጃዋን እንደምትቀጥል ነው እየገለፀች የምትገኘው።

ዩክሬን የNATO ጥምረትን ለመቀላቀል ለዓመታት ስትታገል ቆይታለች፤ ነገር ግን ይህ እርምጃዋ ሩሲያን በእጅጉ አስቆጥቷታል፤ ሩስያ በአጠገቧ ሌላ የNATO አባል ሀገር ፈፅሞ ማየት አትፈልግም።

[ በሌላ መረጃ ፦ የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ነዳጅ ፍለጋ የገልፍ ሃገራትን ጎብኝተዋል። እንደ ስካይ ኒውስ መረጃ ዛሬ በዩኤኡ እና ሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት አድርገዋል። ]

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE ትላንትና ህ/ተ/ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ 13 ሀገራዊ እና 13 ክልላዊ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አሳስቧል። ማሳሰቢያው ከተሰጣቸው ፓርቲዎች መካከል ፦ ብልፅግና፣ ኦፌኮ፣ አብን ፣ ኦነግ ፣ ነእፓ፣ ኦብነግ፣ መኢአድ ይገኙበታል።…
#NEBE

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 26 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርጉ ማሳሰቡ ይታወሳል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በዚህም እስካሁን ጠቅላላ ጉባኤ ያካሄዱ ፓርቲዎች ብልጽግና ፣ ህዳሴ ፣ ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ ፣ ጋህነን መሆናቸውን አመልክቷል።

እንደ ምርጫ ቦርድ ማብራሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ በጊዜ ገደቡ መሰረት ቀን ያሳወቁ 3 ፓርቲዎች አሉ።

ቦርድ 12 ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ ተጨማሪ ጊዜ ጠይቀው ምላሽ የሰጣቸው መሆኑንም አሳውቋል።

ከእነዚህ መካከል ፦ ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ አንዱ ሲሆን ለጉባኤው አስፈላጊ የሆኑ የፋይናንስና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች አስቻይ ባለመሆናቸው ገልጾ መጋቢት 18 ቀን 2014 እንዲያካሂድ ጠይቆ ተፈቅዶለታል።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፓርቲው አባላቶች በእስር ላይ ስለሚገኙ፣ የፓርቲው የክልል ጽህፈት ቤቶች ተዘግተው ስለሚገኙ፣ በግጭቶች ምክንያት በበርካታ የኦሮምያ ዞኖች እና ሌሎ ች ክልሎች ውስጥ ያለው ሁኔታ ያልተረጋጋ ስለሆነ በሚል አቤቱታ አቅርቦ መጋቢት 17 እና 18/2014 ዓ/ም እንዲያካሂድ ቦርዱ ፈቅዶለታል።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ/ም እንዲያካሂድ ጠይቆ ቦርዱ ፈቅዶለታል።

4 ፓርቲዎች ደግሞ በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ባለው ከፍተኛ የጸጥታ ችግር የተነሳ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ እንደማይችሉ ጠቅሰው ቦርዱ ፈቅዶላቸዋል ከእነዚህም መካከል ዓረና ፓርቲ ይገኝበታል።

3 ፓርቲዎች ደግሞ ለቦርዱ የማራዘም ጥያቄ አቅርበው ውሳኔ ያልተሰጠባቸው እና ምክንያታቸው እየታየ ያለ ሲሆን ፓርቲዎቹ ፤ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ናቸው።

ሙሉውን ያንብቡ telegra.ph/NEBE-03-16

@tikvahethiopia
#MoE

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱና ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላቸው ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች የሚከተሉትን ማስተካከያዎች እንዲያደርጉ ጠይቋል ፦

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ የተባለ ሲሆን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 11/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩ ማሳሰቢያ የተላለፈ ሲሆን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ ሚኒስቴሩ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ለተለያዩ ግለሰቦች የሙሉ አምባሳደርነት እና የአምባሳደርነት ሹመት ሰጡ። በዚህም መሠረትም፡- 1/ አቶ ተፈራ ደርበው 2/ አቶ ደሴ ዳልኬ 3/ ዶክተር ስለሺ በቀለ 4/ ጄኔራል ባጫ ደበሌ 5/ ጄኔራል ሀሰን ኢበራሂም 6/ ወ/ሮ ሽትዬ ምናለ 7/ ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ 8/ አቶ ረሻድ መሀመድ 9/ አምባሳደር ጀማል በከር 10/ አቶ ፈይሰል ኦሊይ…
#Update

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ የተሾሙ አምባሳደሮች የተመደቡባቸው ሀገራት ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

አምባሳደሮቹ የተመደቡባቸውን ሀገራት ፦

1. አምባሳደር ተፈራ ደርበው —ጃፓን
2. አምባሳደር ደሴ ዳልኬ—ደቡብ ኮሪያ
3. አምባሳደር ዶ/ር ስለሺ በቀለ—አሜሪካ
4. አምባሳደር ባጫ ደበሌ — ኬንያ
5. አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም–ግብፅ
6. አምባሳደር ዳባ ደበሌ –ሩዋንዳ
7. አምባሳደር ጀማል በከር–ፖኪሲታን
8. አምባሳደር ፈይሰል አሊይ__ኳታር
9. አምባሳደር ኢሳያስ ጎታ—ሞሮኮ
10. አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው–አውስትራሊያ
11. አምባሳደር ምህረተአብ ሙሉጌታ—ስዊዲን
12. አምባሳደር ፍቃዱ በየነ–ኤርትራ

ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ ሆኖ በተለያዩ ሀገሮች የተሾሙ አምባሳደሮች ፦

13. አምባሳደር ጣፋ ቱሉ–ብራዚል
14. አምባሳደር ዶ/ር ገነት ተሾመ–ኩባ
15. አምባሳደር ሽታዬ ምናለ– ኮትዲቯር
16. እምባሳደር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ-ኢንዶኔዥያ
17. አምባሳደር ረሻድ መሀመድ– ዝምባብዌ

በቆንስል ጅነራልነት የተመደቡ ፦

18. አምባሳደር አንተነህ ታሪኩን -ገዳሪፍ
19. አምባሳደርአክሊሉ ከበደ–ዱባይ
20. አምባሳደር ሰይድ መሐመድ-ሀርጌሳ
21. አምባሳደር አወል ወግሪስ–ባህሬን

በምክትል የሚሲዮን መሪነት፦

22. አምባሳደር አሳየ አለማየሁ–ጋና
23. አምባሳደር ኃይላይ ብርሃነ–ጀርመን
24. አምባሳደር ብዙነሽ መሠረት–ህንድ
25. አምባሳደር ዮሴፍ ካሳዬ–ኒው ዮርክ
26. አምባሳደር ዘላለም ብርሃን–ዋሽንግተን
27. አምባሳደር ፍርቱና ዲባኮ– ቤልጅየም
28. አምባሳደር ወርቃለማሁ ደሰታ –ኬንያ
29. አምባሳደር ውብሸት ደምሴ–እንግሊዝ
30. አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል–ፓኪስታን

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

የባንካችንን የቴሌግራም ቦት በመጠቀም በአቅራቢያዎ የሚገኙትን የአቢሲንያ ባንክ ኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች እና የቨርቹዋል ባንኪንግ ማዕከሎች ያለምንም መጉላላት በቀላሉ ያግኙ!

የቴሌግራም ቦት ሊንክ : https://t.iss.one/BOA_ATM_bot
#WHO

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል በላይ የሰዎች ጤና አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘው በትግራይ ክልል ውስጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ያሉት ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ " "በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል በላይ በትግራይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጤና በአደጋ ላይ ይገኛል" ብለዋል።

"አዎ እኔ ከትግራይ ነኝ። ይህ ቀውስ እኔን፣ ቤተሰቤን እና ጓደኞቼን በግል ይጎዳል። ግን እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር፤ በስጋት ውስጥ ያለን ጤና የመጠበቅ እና የመንከባከብ ኃላፊነት አለብኝ። በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም የዓለማችን ክፍል በላይ በትግራይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ጤና አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል" ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ፤ በክልሉ ላለው ሰብዓዊ ቀውስ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት ይፋዊ ያልሆነ እቀባን ተጠያቂ አድርገዋል።

በተጨማሪ በዚሁ መግለጫቸው ላይ ድርጅታቸው 95 ሺ ሜትሪ ቶን መድኃኒት ወደ ትግራይ ለማድረስ ፍቃድ አለማግኘቱን ተናግረዋል። ላለፉት 500 ቀናት የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሥታት በትግራይ ያሉ 6 ሚሊዮን ሰዎችን ይፋዊ ባልሆነ እቀባ ሥር አድርገዋል ብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ላቀረቡት ክስ የኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ የሰጠ ሲሆን ክስ መሰረተ ቢስ ነው ብሎታል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም "መድኃኒቶችን ወደትግራይ ክልል እንዳናስገባ የኢትዮጵያ መንግሥት ፈቃድ አልሰጠንም" በሚል ያቀረበው ክስ መሰረተ ቢስ ነው ሲል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ፤ ማንም የከለከላቸው የለም ፤ ቀድሞ ፈቃድ እንደተሰጣቸው እየታወቀ መዋሸቱ አግባብ አይደለም ብሏል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-03-17

@tikvahethiopia
#Worebabo📍

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 609 የብሬን ጥይትና ሌሎችን ህገ ወጥ ቁሳቁሶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረባቦ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

ፖሊስ ፤ በወረባቦ ወረዳ በቀን 05/7/2014 ህገ ወጥ መሳሪያዎችና እቃዎች ጭኖ ከጭፉራ አቅጣጫ ወደ ሃይቅ ዋናውን መንገድ ይዞ ሲመጣ የነበረ " ኮድ 3 B38052 AA " የሆነ የጭነት አይሱዙ ቢሲቲማ ከተማ ኬላን በመጣስ ለማምለጥ የሞከረ ቢሆንም የጸጥታ ሃይሎች ባደረጉት ክትትል በ02 ቀበሌ ሃራ መገጠያ አካባቢ ከሌቱ 10:00 አካቢቢ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድቷል።

መኪናው በቁጥጥር ውስጥ ሲውል ፦
👉 39 ካርቶን ጎልዴን ሲጋራ፥
👉 33 ካርቶን የሺሻ አፕል፥
👉 305 የክላሽ ጥይት፥
👉 609 የብሬን ጥይት ፥
👉 10 የቱርክ ጥይት፥
👉 22 የUNHCR የእርዳታ ኬንዳ እና 11 ብርድልሶች በጸጥታ አካሉ ተይዟል ተብሏል።

የመኪና አሽከርካሪ የተሰወረ ሲሆን 3 ተጠርጣሪዎችና መኪናው በቁጥጥር ስር መዋሉም የወረባቦ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይፈለጋል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከላይ በምስሉ ላይ ያለውን ግለሰብ በወንጀል እንደሚፈልገው አሳውቋል። ግለሰቡ የተለያዩ ሀሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣትና በመጠቀም ከተለያዩ ባንኮች ብር አጭበርብሮ በማውጣት ወንጀል እንደሚፈለግ ነው ፖሊስ የገለፀው። ፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪውን የሚመለከት ማንኛውም መረጃ ካልዎት እንዲያሳውቁ ጥሪ ያቀረበ ሰሆን ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቋል። ስልክ…
#ተይዟል

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከጥቂት ቀናት በፊት በጥብቅ ሲፈልገው የነበረ ግለሰብ መያዙን አሳውቋል።

ፖሊስ የካቲት 29 ቀን 2014 ዓ/ም ባወጣው ማስታወቂያ ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየውን ግለሰብ በወንጀል እንደሚፈልገው ገልጾ ነበር።

ግለሰቡ የተለያዩ ሀሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣትና በመጠቀም ከተለያዩ ባንኮች ብር አጭበርብሮ በማውጣት ወንጀል እንደሚፈለግ ነበር ፖሊስ ገልጾ የነበረው።

ዛሬ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ እንዳሳወቀው ግለሰቡ በተለያዩ ስሞች በመጠቀም ለመሰወር ቢሞክርም በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

@tikvahethiopia
#Tigray

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ከትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ ጋር በተያያዘ መግለጫ አውጥቷል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት የትግራይ ክልልን ሰብአዊ ችግር ለመፍታት በአፋር መስመር የሰብአዊ ድጋፍ የሚያደርሱ ተሽከርካሪዎች በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲንቀሳቀሱ በማመቻቸት ገንቢ የሆነ ሚና ሲጫወት መቆየቱን እና አሁንም ሚናውን መቀጠሉን ገልጿል።

በዚህም መሰረት ዛሬ መጋቢት 17 (እኤአ) 20 የጭነት ተሽከርካሪዎች ምግብ እና 3 ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ወደ መቐለ መንቀሳቀስ ጀምረዋል ሲል አሳውቋል።

የሰብዓዊ ዕርዳታውን ከፍ ለማድረግ እና የክልሉን መሰረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት በየቀኑ ወደ ትግራይ የሚያቀኑት የጭነት ተሽከርካሪዎች ቁጥር 40 ለማድረስ እንደሚሰራ አመልክቷል።

በተጨማሪም 17 አጋሮች መድሃኒትን (ክትባትን ጨምሮ) የህክምና ቁሳቁሶችን እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ወደ ትግራይ ክልል እንዲያስገቡ ፍቃድ አግኝተዋል ብሏል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው 11 አጋሮች 275 ሺ 192 ኪ.ግ የሚመዝኑ የህክምና ግብአቶችን በአየር በረራ ማድረሳቸውን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በአፋር ክልል በድጋሚ በተፈፀመው ጥቃት ከ700,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው እና በአባአላ በኩል ወደ ትግራይ የሚወስደው የሰብአዊ እርዳታ መስመር እንዲዘጋ ማድረጉን አመልክቷል። ጥቃቱ በአፋር ክልል ቂሊቤቲ ረሱ ዞን ወደ 5 ወረዳዎች ከፍ ብሎ ከ300,000 በላይ ሰዎችን እንዲፈናቀሉ ማደረጉን ገልጿል።

ከሰመራ 38 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሰርዶ 43 ምግብ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ቆመው እንደሚገኙም ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

ሆኖም ግን ዛሬ ከተደረጉት ጥብቅ ጥረቶችና ውሳኔዎች በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ያለውን የሰብአዊ ችግር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Update

አሜሪካ የሶማሊያን 'የዲሞክራሲ ሂደት አደናቀፉ' ባለቻቸው ተጨማሪ ሶማሊያውያን ላይ የቪዛ ዕገዳ ጥላለች።

ሀገሪቱ ይህን ያሳወቀችው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቷ አማከኝነት ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንክን ትላንት ባወጡት መግለጫ የሶማሊያ መንግሥት የምክር ቤታዊ ምርጫ ሂደቱን ማክሰኞ እአአ መጋቢት 15 /2022 ሊያጠናቅቅ ራሱ ያወጣውን ቀነ ገደብ ተግባራዊ ሳያደርግ መቅረቱን ተከትሎ የዲሞክራሲ ሂደቱን በማደናቀፍ ተጠያቂ ወይም ተመሳጣሪ ናቸው በተባሉ ተጨማሪ ሰዎች ላይ አሜሪካ የቪዛ ማዕቀብ እርምጃ መውሰዷን አሳውቀዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ምንም እንኳን ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አበረታች እርምጃ የታየ ቢሆንም አሁንም ያልተያዙ ከሠላሳ ስድስት በላይ ክፍት የምክር ቤት መቀመጫዎች እንዳሉ አመልክተዋል።

የምርጫው ሂደት መዛባት ላይ እንዲሁም ዲሞክራሲያዊ ተቋማትን የሚደግፉ እና ሂደቱ ግልጽ እንዲሆን የሚጥሩ ጋዜጠኞች እና ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የወከባ የእስር እና የጥቃት ዒላማ እየተደረጉ መሆኑን የሚያመለክቱ ተዓማኒ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ቀጥለዋል ሲሉም አንቶኒ ብሊንከን መግለፃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia