TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Instagram ሩስያ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ኢንስታግራም እንደሚታገድ አስታወቀች። በሜታ ኩባንያ ስር የሚተዳደረው ኢንስታግራም ከሰኞ ጀምሮ እንደሚታገድ ሩስያ ገልፃለች። ይህ ውሳኔ የተላለፈው ሜታ ከዩክሬን ጦርነት ጋር ተያያዞ በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች ‘ለተወሰነ ጊዜ’ እንደሚፈቀድ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው። ሜታ በፌስቡክ እና ኢስታግራም ላይ " ሞት ለወራሪው…
ሩስያ ኢንስታግራምን ዘጋች።

ሜታ ኩባንያ በኢንስታግራም ላይ በሩስያውያን ላይ የጥቃት ፣ የግጭት ቀስቃሽ ፣ እና የጥላቻ ጥሪዎች እንዲተላለፉ መፍቀዱን ተከትሎ ሀገሪቱ ከዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርጋዋለች።

ኢስታግራም ከመዘጋቱ 48 ሰዓት በፊት ተጠቃሚዎች የፎቶ እና ቪድዮ ፋይሎቻቸውን ወደሌላ የማህበራዊ ሚዲያ እንዲያዞሩ ጊዜ ተሰጥቷቸው ነበር።

2021 ላይ ኢንስታግራም ባካሄደው ቆጠራ በሩስያ ወደ 60 ሚሊዮን ገደማ ተጠቃሚዎች እንዳሉት ሪፖርት አድርጎ ነበር።

ሩስያ ከዚህ ቀደም ፌስቡክን መዝጋቷ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ኢንስታግራምን ዘጋች። ሜታ ኩባንያ በኢንስታግራም ላይ በሩስያውያን ላይ የጥቃት ፣ የግጭት ቀስቃሽ ፣ እና የጥላቻ ጥሪዎች እንዲተላለፉ መፍቀዱን ተከትሎ ሀገሪቱ ከዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርጋዋለች። ኢስታግራም ከመዘጋቱ 48 ሰዓት በፊት ተጠቃሚዎች የፎቶ እና ቪድዮ ፋይሎቻቸውን ወደሌላ የማህበራዊ ሚዲያ እንዲያዞሩ ጊዜ ተሰጥቷቸው ነበር። 2021 ላይ ኢንስታግራም…
#Telegram

በአሁን ሰዓት ቴሌግራም በሩስያ ቀዳሚው እና ተመራጩ የመልዕክት መለዋወጫ ሆኗል።

በተለይ ሩስያ ኢንስታግራም እና ፌስቡክን ማገዷን ታከትሎ ቴሌግራም በቀዳሚነት ተመራጩ የመልዕክት መለዋወጫ ሊሆን ችሏል።

የዩክሬን ፕሬዜዳንት ዜሌስንኪን ጨምሮ በርካታ የዩክሬን እና የሩስያ ባለስልጣናት ፣ ሚዲያዎች ፣ ፖለቲከኞች ፣ ተቋማት መልዕክት ለመለዋወጥ ቴሌግራምን የሚጠቀሙ ሲሆን በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት በመረጃ ልውውጥ ትልቁን ስፍራ የያዘ የማህበራዊ ሚዲያ ሆኗል።

ቴሌግራም ከዚህ በፊት ማለትም በ2018 ላይ በሩስያ ባለስልጣናት ለሁለት ዓመታት ታግዶ እንደነበር እና እገዳው 2020 ላይ መነሳቱ ይታወሳል። በወቅቱ እገዳው የተጣለበት የተጠቃሚዎችን መረጃ እንዲሰጥ ተጠይቆ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነበር።

በአሁን ሰዓት እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ቴሌግራም የዩክሬን ተጠቃሚዎቹን መረጃ ለሩስያ ያቀብላል ተብሎ ስሙ ቢነሳም የኩባንያው መስራች በትውልድ ሩስያዊው እና በኡሁን ሰዓት በዩኤኢ #ዱባይ ነዋሪነቱን ያደረገው ፓቨል ዱሮቭ ኩባንያው የዩክሬን ተጠቃሚዎችን መረጃ አሳልፎ እንዳልሰጠ ፥ ይህንንም እንደማያደርግ በምንም ሁኔታ ለተጠቃሚዎቹ መብት እንደሚቆም ገልጿል።

የቴሌግራም መስራቹ ፤ በእናቱ በኩል ቤተሰቦቹ ከኪየቭ እንደሆኑ ጠቁሞ እስከ አሁን ድረስም በዩክሬን የሚኖሩ ብዙ ዘመዶች እንዳሉት ገልጿል። አሁን ያለው አሳዛኝ ግጭትም " ለእኔም ሆነ ለቴሌግራም ግላዊ ነው " ሲል ነው ሁኔታውን የገለፀው።

የድምፅ እና ቪድዮ ጥሪዎችን፣ የምስጥራዊ የመልዕክት ልውውጦች (ቻት) እንደማያነብ የሚናገርለት ቴሌግራም በምንም ሁኔታ የተጠቃሚዎቹን መረጃ አሳልፎ እንደማይሰጥ የገለፀ ሲሆን ለተጠቃሚዎቹ መብት እንደሚቆም አረጋግጧል።

@tikvahethiopia
" ... በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ሰራተኛው በቃላት ከሚገለፀው በላይ በጣም እየተቸገረ ነው ፤ ... እየኖረ አይደለም ማለት ይቻላል " - አቶ ካሳሁን ፎሎ

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ኑሮ ውድነት በተለይ ደግሞ በዝቅተኛ ደሞዝ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ሊቋቋሙት እንዳልቻለ አስታውቋል።

ኑሮ ውድነቱ በተለይ የዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ሰራተኞች ላይ የበረታበት አንዱ ምክንያት ዝቅተኛ የደሞዝ እርከን በህግ የተወሰነ ባለመሆኑ ነው ብሏል።

የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዜዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 በሰጡት ቃል በኢትዮጵያ ያለውን የኑሮ ውድነት በዝቅተኛ ደሞዝ ተቀጥረው የሚሰሩ ዜጎች ሊቋቋሙት አልቻሉም ብለዋል።

አቶ ካሳሁን ፎሎ ፦

" ዓለም በኮሮና በመጠቃቱ የኮሮና ቀውስ ነው ያለው በእኛ ሀገር ግን ከዛ በተጨማሪ አሁን ባለው ሁኔታ ኢንፍሌሽን ከፍተኛ መሆኑ ኑሮ ውድነቱ ተባብሷል። በዚህ ምክንያት አይደለም ሁለት ጊዜ ሊበላ አንድ ጊዜ መብላት አልቻለም ሰራተኛው። እየኖረ አይደለም ማለት ይቻላል።

ይሄ የሆነበት ምክንያት ኢንፍሌሽኑ ከፍተኛ ነው የሰራተኛው ደሞዝ አነስተኛ ነው ። እንደሌላው ሀገር ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል የለንም በኛ ሀገር።

ሌሎች ሀገር ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል በየአመቱ እየተከለሰ ተግባራዊ የሚደረግ ነው ነገር ግን ይሄ እኛ ሀገር የለም/በሀገር አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል አለመኖሩ " አንዱ ምክንያት ነው ብለዋል።

ሌላኛው ፦

" አንድንድ ድርጅቶች የውጭ ምንዛሬ እጥረት ስላለባቸው ከውጭ ቀጥታ እቃ የሚያመጡ ድርጅቶች እሱም እየቀነሰ ስራም እየቀነሰ በመሆኑ እንዲሁም የገበያ ላይ ያለው የሸቀጥ ዋጋ ከፍተኛ በመሆኑ በዚህ ሳምንት እንደምናየው የዘይት እንኳን በገበያ ያላ ምን ያክል እንደሆነ ይታወቃል " ሲሉ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በተለይም በፋብሪካዎች ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች የህይወታቸው ሁኔታ እያሳሰበው መሆኑን ገልጿል።

አቶ ካሳሁን ፎሎ ፦

" ሰራተኛው በተለይ ፋብሪካ ላይ ያለው አብዛኛው ደሞዙ 1000 ብር ነው። ለምሳሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ አካባቢ ያሉ ሰራተኞች 1000 ብር / 1250 ብር ነው ደሞዛቸው፤ የአበባ ሴክተርም አለ ሌሎች ሆቴሌም አለ... ሁሉም ሴክተር ላይ ትልቅ ችግር ነው ያለው።

ሰራተኛው ዘይት ገዝቶ መብላት አልቻለም፤ አይደለም ምግብ ቀርቶ ስለዚህ ሰራተኛው ከፍተኛ ችግር ላይ ነው ያለው።

አንዳንድ ድርጅቶች እያተረፉም ቢሆን ካለው ሁኔታ አንፃር የተወሰኑ ድርጅቶች ጭማሪ አድርገው ሊሆን ይችላል ከዛ ውጭ አብዛኛው ጋር ጭማሪ የለም አይደለም ጭማሪ የያዙትን ይዘው ለመቆየት በጣም ከፍተኛ ችግር ስለሆነ ሰራተኛ እየተበደለ ነው ያለው።

ነጋዴው ሰራተኛው ላይ ነው የሚጭነው።

ምግብም ከውጭ ገዝቶ የሚጠቀምም ሆነ በቤቱ አብስሎ የሚበላም ገዝቶ ስለሚበላ ሁሉም በሰራተኛው ላይ ነው የሚጭነውና ሰራተኛው በጣም እየተቸገረ ነው ያለው በቃላት ከሚገለፀው በላይ ነው ሰራተኛው እየተቸገር ያለው። በቃላት ለመግለፅ ያስቸግራል ። "

በሀገሪቱ ያለው የኑሮ ውድነቱ መፍትሄ ሊፈለግለት ይገባል የሚሉት አቶ ካሳሁን ኮንፌዴሬሽኑ የሰራተኞች ዝቅተኛ ደሞዝ በህግ እንዲወሰን ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል።

አቶ ካሳሁን ፎሎ ፦

" ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል የለም ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እንዲወጣ በ2011 ዓ/ም በወጣው አዲሱ የአሰሪና ሰራተኛ ህግ መሰረት የደመወዝ ቦርድ ተቋቁሞ ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ይወስናል የሚል እዛ አዋጅ ላይ ተቀምጧል።

ይሄ ዝቅተኛው የደሞዝ ወለል የሚያይ ቦርድ እንዲቋቋም በአሁኑ ስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በድሮ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ዓመት ረቂቅ ተዘጋጅቶ ውይይት አሰሪ ፣ ሰራተኛ፣ መንግስት በጋራ ከተወያየን በኃላ በጠ/ሚ ፅ/ቤት በኩል ሚስቴሮች ምክር ቤት ይቀርባል ተብሎ ነው ታስቦ የነበረው ፤ ቀርቧልም።

ነገር ግን ወደ መደበኛ ስራ ከምርጫ በኃላ ይታያል ተብሎ ነበር ከምርጫ በኃላ ያለው ሂደት በሀገራችን ላይ የሚታይ ስለሆነ መደበኛ ስራዎች እየሄዱ አይደለም አሁን ገና እየተጀመረ ነው፤ ይሄን ለማቅረብ እና ጥያቄውን ለማንሳት እኛም እየተዘጋጀን ነው" ሲሉ ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ፦

#ለመጀመሪያ_ዙር_ተፈታኞች !

👉 በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351

• በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ 300

• በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ 380

🔹በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300

• ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254

• በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250

• ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች 250

• በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ ነጥብ 280

🔹በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250

#ለሁለተኛ_ዙር_ተፈታኞች !

👉 በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር

• ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409

🔹 በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350

• ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች በመንግስት ዩኒቨርሲቲ ለመማር የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305

🔹 በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ300 በላይ

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል - ያንብቡ)

@tikvahethiopia
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆነ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ሳሙኤል (ዶ/ር) ለጋዜጠኞች የ12ኛ ክፍል መለቀቂያ ፈተና መቁረጫ ነጥብ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በሁለት ዙር ለተሰጠው የመልቀቂያ ፈተና የተሰጠው የማለፊያ ነጥብ የተለያየ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤት የሚከተለውን ይመስላል

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 363 ለሴት 351 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 351 ለሴት 339 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 300 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 380 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 300 ሆኗል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 264፣ ለሴት 254 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 254፣ ለሴት 250 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 250 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 280 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ 250 ሆኗል።

በሁለተኛ ዙር ፈተናቸውን የወሰዱ የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች ውጤትም ይፋ የሆነ ሲሆን በዚህም መሰረት

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር ለተፈጥሮ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞት ማለፊያ ነጥብ ለወንድ 423 ለሴት 409 ሲሆን በተፈጥሮ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 410 ለሴት 396 ማለፊያ ነጥብ መሆኑ ተገልጿል።ለተፈጥሮ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 350 ሆኗል።በተፈጥሮ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ማለፊያ ነጥብም 443 ሆኖ መቆረጡ ተገልጿል።

በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ እና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ350 በላይ መሆኑ ተነግሯል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መደበኛ ተፈታኞች የማለፊያ ነጥብ ለወንድ 317 ፣ ለሴት 305 ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስ በታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ላሉ መደበኛ ተፈታኞች ለወንድ 305፣ ለሴት 300 ማለፊያ ነጥብ ሆኖ ተቆርጧል።

ለማህበራዊ ሳይንስ መስማት ለተሳናቸው ሁለቱም ፆታዎች ማለፊያ ነጥብ 300 መሆኑን እና በማህበራዊ ሳይንስ ድጋሜ ተፈታኞች ለሁለቱም ፆታ የማለፊያ ነጥብ 335 እንደሆነ ተገልጿል።

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ ከ 300 በላይ መሆኑም ተገለጿል።

ውጤቱ ለመጀመርያ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ500 የተያዘ መሆኑን እና በሁለተኛ ዙር ተፈታኞች ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700 እዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 የተያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#AAU

" ... የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልሆኑ ግለሰቦች በግቢው ረብሻ ለመቀስቀስ ሞክረዋል። በአሁኑ ሰዓት አንድም የታሰረ ተማሪ የለም " - የአ.አ.ዩ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አማካሪ

@tikvahuniversity በአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትላንትና እሁድ ስለተከሰተው ነገር የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የኮሚዩኒኬሽን አማካሪ ኢንጂነር ውባየሁ ማሞን ጠይቋል።

ኢጂነር ውባየሁ ማሞ ፦ " ላለፉት ስድስት ቀናት የተለያዩ ነገሮች በግቢው አስተውለናል። ከተማሪዎቻችን ጋር ስንወያይ ቆይተናል። በመጨረሻ ከተማሪዎች አጀንዳ ውጪ የሆነ ነገር እንዳለ ስናውቅ እርምጃ ወስደናል " ብለዋል።

አማካሪው ፤ " ትላንት የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ያልሆኑ አልፈው ገብተው ረብሻ ለመቀስቀስ የሞከሩ ስምንት ግለሰቦች ተይዘው በሕግ ክትትል ስር ይገኛሉ " ሲሉም ገልፀዋል።

" ግለሰቦቹ የፖለቲካ አጀንዳ ይኖራቸዋል። " ያሉት ኢ/ር ውባየሁ " ንጹሀን ተማሪዎች ላይ ያልተገባ ነገር ለመፈጸም እንደገቡ ስላወቅን ግለሰቦቹን ለይተን ይዘናል " ሲሉ አስረድተውናል።

" በአሁኑ ሰዓት አንድም የታሰረ ተማሪ የለም። አንድም ከትምህርት ገበታው ያቋረጠ ተማሪ የለም። የመማር ማስተማር ሂደቱ ሙሉ በሙሉ እየሄደ ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

ኢ/ር ውባየሁ ፥ " በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን እየተወራ ያለው ሀሰት ነው። ትክክለኛ መረጃ እየወጣ አይደለም። ተማሪዎችንና ቤተሰብን የሚረብሽ ነገር ነው እየወጣ ያለው። " ብለዋል።

አማካሪው ፤ ትላንትና ግለሰቦቹ ለማምለጥ ሲሞክሩ ለመያዝ የተሰራ ነገር ነበር ያሉ ሲሆን በዚህም ምክንያት የተፈጠረው ችግር ወዲያው ከመንግስት አካላት ጋር በመሆን ተፈቷል ሲሉ ገልፀዋል።
 
@tikvahethiopia
#ነእፓ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን መጋቢት 18 እንደሚያካሂድ አሳውቋል።

የጉባኤው ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑንም ገልጿል።

1ኛ መደበኛ ጉባኤ ፓርቲውን ወደአዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነእፓ አሳውቋል።

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እና አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስገቡ ማሳሰቢያ ከሰጣቸው 13 ሀገራዊ እና 13 ክልላዊ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አንዱ ነው።

@tikvahethiopia
#Russia

ሩስያ ከዛሬ ማክሰኞ ጀምሮ ስንዴ፣ በቆሎ፣ አጃ፣ እና ስኳር ወደ ውጭ እንዳይላክ አገደች።

ሩስያ እህል ለቀድሞ የሶቪየት ሀገራት እንዳይላክ እና በአብዛኛው የስኳር ምርት ወደሌሎች ሀገራት እንዳይላክ ለጊዜው ማገዷ ተሰምቷል።

እገዳው እኤአ እስከ ሰኔ 30 ይቆያል ተብሏል።

ነገር ግን በልዩ የኤክስፖርት ፈቃድ አሁን ባለው የኮታ ሥርዓት ለነጋዴዎች መከፋፈሉ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ሩስያ እህል እና ስኳር እንዳይላክ ለጊዜው ማገዷ መሰማቱን ተከትሎ ከወዲሁ የዋጋ ጭማሪ እየተስተዋለ መሆኑ ተነግሯል።

ሩስያ በዓለማች ላይ ከፍተኛ እህል ላኪ ሀገር ስትሆን ቱርክ እና ግብፅ ደግሞ ከሩስያ በመግዛት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።

@tikvahethiopia
" በዚህ አመት 152 ሺህ ተማሪዎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ይቀላቀላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 152 ሺህ 14 ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመደበኛው ፕሮግራም ምደባ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

ይህም በአማካይ በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ፈተናውን 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ካመጡት ውስጥ 53 ፐርሰንት ያህል መሆኑ ተነግሯል።

በመንግስት ተቋማት ምደባ ከሚያገኙት ተማሪዎች ውስጥ 63ሺ 833 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች መሆናቸውም ነው የተገለፀው።

የዩኒቨርስቲ መግቢያ አነስተኛ ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው ሌሎች 135ሺ209 ተማሪዎች በተለያዩ አማራጮች ከፍተኛ ትምህርት መማር እንደሚችሉም ተነግሯል።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያን ፈተናን በሁለቱም ዙር የወሰዱ 598ሺ 679 ተማሪዎች ሲሆኑ ከዚህም ውስጥ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 287 ሺ 223 ናቸው ።

የትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዙር የተሰጠውን የ2013 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ውጤትን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት 623 መሆኑን አስታወቀ።

በሁለት ዙር በተሰጠው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት 623 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር ፈተና የተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት 563 ሲሆን በሁለተኛው ዙር የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት ደግሞ 623 መሆኑ ነው የተነገረው።

ከፍተኛ ውጤቱ በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ የተመዘገበ መሆኑ ታውቋል።

ፈተናው በመጀመሪያው ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከ 500 የተያዘ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ከ700፣ ለማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ነው የተያዘው።

በአጠቃላይ ፈተናውን በሁለት ዙር 598 ሺህ 679 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 287 ሺ223 ተማሪዎች 50% እና ከዛ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
የነዳጅ ዋጋ አሽቆለቆለ።

በዩክሬንና ሩስያ ጦርነት ምክንያት ባለፉት ሳምንታት የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ ማሻቀቡ ፤ በበርሜልም እስከ 140 ዶላር ድረስ ደርሶ ነበር።

በዚህ ሳምንት ግን የነዳጅ ዋጋ በእጅጉ መቀነሱ ተነግሯል።

አሁን ላይ ፤ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል 98.50 ዶላር ሲሆን በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት 1 በርሜል ነዳጅ 96.14 ዶላር በሆነ ዋጋ እየተሸጠ ነው።

ይህም ባለፉት 2 ሳምንታት የታየ ከፍተኛ ቅናሽ ነው።

@tikvahethiopia
" በአፍሪካ የስንዴ እጥረት ሊከሰት ይችላል " - ተመድ

በሩሲያ እና በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በአፍሪካ የስንዴ እጥረት ሊከሰት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት አስጠነቀቀ።

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሩዝ በጦርነቱ ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ "የረሃብ ወጀብ" እና የምግብ ዋስትና እጦት ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በርካታ የአፍሪካ አገራት እና ድሃ አገራት በሩሲያ እና በዩክሬን የስንዴ ምርት ላይ ጥገኛ መሆናቸውን የገለፁት ዋና ፀሐፊው አሁን ግን በጦርነቱ ምክንያት ስጋት ውስጥ ወድቀዋል ብለዋል።

ከእነዚህ አገራት መካከል ቀድሞውኑም ሕዝባቸውን ለመመገብ የሚታገሉት ቡርኪና ፋሶ፣ ሶማሊያ እና የመን ይገኙበታል።

የተመድ ዋና ፀሀፊ ጉተሬዝ የዓለም የምግብ አቅርቦት ሥርዓትን ከመንኮታኮት ለመታደግ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ጉተሬዝ እየተካሄደ ባለድ ጦርነት ሳቢያ ረሃብ፣ የውሃና የመድኃኒት አቅርቦት ችግር እየገጠማቸው ላሉ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዩክሬናውያን ለመርዳት 40 ሚሊየን ዶላር እርዳታ እንደሚያስፈልግ ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#RUSSIA #USA

ሩስያ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት #ጆ_ባይደንን ጨምሮ ሌሎች የአሁን እና የቀድሞ ባለስልጣናት ወደ ሀገሬ ድርሽ እንዳትሉ ስትል ማዕቀብ ጣለች።

የሩሲያ መንግስት ወደ ሩስያ እንዳይገቡ እገዳ ከጣለባቸው መካከል ፦

👉 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

👉 የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን

👉 የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን

👉 የCIA ዳይሬክተር ዊሊያም በርንስ

👉 የኋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጀን ሳኪ፣

👉 የመከላከያ ሚኒስትር ሊዮይድ አውስቲን

👉 የቀድሞዋ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ይገኙበታል።

በተጨማሪ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ተሩዶ ወደ ሩሲያ እንዳይገቡ ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

ቀደም ሲል አሜሪካ በሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ላይ ማዕቀብ ጥላ ነበር።

መረጃው የአርቲ ኒውስ እና የአልዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ በቴ ኡርጌሳ ታሰሩ። የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ቡራዩ ከተማ መታሰራቸውን ከኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አቶ በቴ የታሰሩት ቡራዩ ፖሊስ ጣቢያ ነው። ወደቡራዩ የሄዱት የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞችን ለመጠየቅ ነበር ተብሏል። አብረዋቸው ወደ ቡራዩ የሄዱት ሹፌራቸውም ለእስር መዳረጋቸው ተገልጿል። @tikvahethiopia
#OLF

" ... በእጃችን ከሚሞት ብለው ነው የሰጡን " - ሚሎ ኡርጌሳ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ቃል አቀባይ የነበሩት አቶ በቴ ኡርጌሳ ከ1 ዓመት እስር በኋላ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር ተለቀዋል።

ምንም እንኳን አሁን አቶ በቴ ከእስር ቢለቀቁም በከፋ ህመም ላይ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

በቅርቡ እስር ላይ እያሉ ከሌሎች የታሰሩ ባልደረቦቻቸው ጋር የርሀብ አድማ አድርገው እንደነበር ተነግሯል፤ ከዚህ በኃላ ነው የጤናቸው ሁኔታ የከፋው።

የአቶ በቴ ወንድም ሚሎ ኡርጌሳ " በእስር ቤቱ ህመሙ ሲጠናበት ነው የቡራዩ ፖሊስ መምሪያ ቤተሰብ መጥተው እንዲወስዱ ያለው፡፡ " ያሉ ሲሆን አቶ ባቴ ካለፈው ቅዳሜ አንስቶ አዳራ በተባለ ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ በቴ ህመሙ የጠናባቸው አስቀድሞ ህክምና ባለማግኘታቸው እንደሆነ ወንድማቸው አስረድተዋል።

አቶ በቴ ከዚህ በፊት ታስረው ለፍርድ ቤት እንደቀረቡ በሁለተኛው ቀጠሮ የዋስትና መብት የተጠበቀላቸው ቢሆንም ፖሊስ ግን ከቤተሰብም ሰውሮ በተለያዩ እስር ቤትና ማዕከላት እንዳቆዩት ወንድማቸው ተናግረዋል።

ቡራዩ፣ አዋሽ እና ገላን የታሰሩባቸው ስፍራዎች ናቸው።

በዚህ ሁሉ ሂደት ላይ በመጨረሻ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር ሆነው የርሃብ አድማ በማድረጋቸው ለህመም መዳረጋቸውን የሚገልፁት ወንድማቸው ሚሎ የርሃብ አድማውን ተከትሎ ከገላን ወደ ቡራዩ ከተወሰዱ በኋላ ከቤተሰብ ጋር ተገናኝተው ምርመራ ሲያደርጉ ለከፋ ህመም የዳረጋቸው በሽታ እንደተገኘባቸው ገልፀዋል።

" ከዚህም በኋላም ቢሆን መልሰው አስረዋቸው ነበረ ቢሆንም በመጨረሻ በእጃችን ከሚሞት ብለው ነው የሰጡን " ሲሉ ወንድማቸው ሚሎ ኡርጌሳ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/DW-03-15

@tikvahethiopia
ሩስያ በይፋ ከአውሮፓ ምክር ቤት ጋር ተፋታች።

ሩስያ ከድርጅቱ መውጣቷን ለአውሮፓ ምክር ቤት በይፋ አሳውቃለች።

የሩስያ ዱማ ምክትል አፈጉባዔ ፒዮትር ቶልስቶይ ዛሬ ማክሰኞ እንዳስታወቁት ከሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ደብዳቤ ለድርጅቱ ዋና ፀሃፊ ተላልፏል።

" ከአውሮፓ ምክር ቤት ጋር የሚደረገውን ውይይት ለማቋረጡ ሁሉም ሃላፊነት በNATO አባል ሀገራት ላይ ነው " ያሉት ቶልስቶይ " ይህን ሁሉ ጊዜ በሰብአዊ መብቶች ርዕስ የራሳቸውን ጂኦፖለቲካዊ ፍላጎቶች ለማሟላት እና በሀገራችን ላይ ለሚሰነዘሩ ጥቃቶች ሲጠቀሙበት ቆይተዋል " ብለዋል።

አክለውም ፤ " ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በተጣለው ማዕቀብና በፖለቲካዊ ጫናዎች " ምክንያት ሩስያ ዓመታዊውን ክፍያ ለአውሮፓ ም/ቤት አትከፍልም ሲሉ አሳውቀዋል።

ቶልስቶይ ሩሲያ ድርጅቱን ለቃ የምትወጣው " በራሷ ፈቃድ " እንደሆነ ገልፀው ውሳኔው ሚዛናዊ እና የታሰበት ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia