TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

በዚህ ትውልድ ያለነው ወጣቶች ፣ ጎልማሶች ፣ በእድሜም የገፋን ሰዎች ጭምር በሰው ልጆች ሊደረጉ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ እጅግ በርካታ አስደንጋጭ አሰቃቂ ግፎችን በቪድዮ፣ በፎቶ ተመልክተናል።

ይህ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ መሰባሰቢያ ከተፈተ ጀምሮ (ያለፉትን 3ና 4 ዓመታት) እጅግ በርካታ አሰቃቂ ክስተቶችን፣ የሰው ልጅ አንገት የሚያስደፉ ድርጊቶችን ታዝበናል፤ በይፋም እርስ በእርስ መረጃ ተለዋውጥናል።

በየጊዜው የነበሩ እጅግ ዘግናኝ ከህግ ሆነ ከሞራልም ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን ወደ ኃላ ተመልሰን ለመዘርዘር ጊዜውም አይበቃን ፤ በተለይም ከቲክቫህ ጋር ዓመታትን ያሳለፋችሁ የምታውቁት ነው።

ሌላው ይቅር በቅርብ ጊዜ እንኳን ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተነሳ በኃላ እጅግ አሰቃቂ የሆኑ ቪድዮዎች ተሰራጭተው ስለጉዳዩ መረጃ መለዋወጣችን የቅርቡ ትውስታችን ነው።

ዛሬ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የተሰራጨው አሰቃቂ ቪድዮ በርካቶችን ያስደነገጠ ያሳዘነ ሆኗል። ቪድዮውን እዚህ አምጥቶ ማጋራት ትክክል እንዳልሆነ ታውቁታለቹ ፤ በጥቅሉ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ የሰው ልጅ #በህይወት_እያለ በእሳት እንዲቃጠል ሲደረግ የሚያሳይ ነው።

ከቪድዮው ጋር በተያያዘ እነማን ? መቼ ? የት ? እና እንዴት ? ስለሚለው ጉዳዩ ይመለከተኛል የሚል አካል በአስቸኳይ ወጥቶ ማብራሪያ መስጠት ይጠበቅበታል።

በተለይም ደግሞ በቪድዮው ላይ የፀጥታ ኃይሎችን የደንብ ልብስ ያደረጉ ሰዎች በግልፅ ስለሚታዩ ተቋማቱ ማብራሪያ መስጠት አለባቸው።

የሰብዓዊ መብት ተቋማትም ጉዳዩን ሊከታተሉትና ለህዝብ ሊያሳውቁ ይገባል።

እንዲህ ያለው ነገር በቪድዮ አደባባይ ላይ ሲወጣ መነጋገሪያ ይሆናል እንጂ ያልተቀረፀው ፣ ህዝብ ያላወቀው ስንት ጉድ ይኖር ይሆን ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሚዘጉ መንገዶች ! ነገ በመስቀል አደባባይ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስከሬን ሽኝት ይካሄዳል ፤ የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም ደግሞ መጋቢት 4 /2014 ዓ/ም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚፈፀም ይሆናል። ነገ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፦ 👉 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ 👉
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሐግብር በአሁን ሰዓት መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የሃይማኖት አባቶች ፣ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የውጪ አገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ፎቶ ፦ ENA / የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በዚህ ትውልድ ያለነው ወጣቶች ፣ ጎልማሶች ፣ በእድሜም የገፋን ሰዎች ጭምር በሰው ልጆች ሊደረጉ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ እጅግ በርካታ አስደንጋጭ አሰቃቂ ግፎችን በቪድዮ፣ በፎቶ ተመልክተናል። ይህ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ መሰባሰቢያ ከተፈተ ጀምሮ (ያለፉትን 3ና 4 ዓመታት) እጅግ በርካታ አሰቃቂ ክስተቶችን፣ የሰው ልጅ አንገት የሚያስደፉ ድርጊቶችን ታዝበናል፤ በይፋም እርስ በእርስ…
#Update

በትላንቱ እጅግ አሰቃቂ እና አሳዛኝ እንደ ሰው ልጅም አንገት አስደፊ ቪድዮ ላይ የተከሰተው ክስተት በተመለከተ የተገኘው መረጃ ፦

👉 ቀኑ ፦ በግልፅ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም።

👉 ክልል ፦ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል

👉 ዞን ፦ መተከል ዞን

👉 ወረዳ ፦ ጉባ ወረዳ

👉 ቀበሌ ፦ አይሲድ ቀበሌ

👉 በእንደዛ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ፦ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም

👉 የድርጊቱ ተሳታፊዎች በቁጥጥር ስር ስለመዋላቸው ፦ አይታወቅም

👉 የተወሰደ እርምጃ በተመለከተ ፦ መንግስት አጣርቼ እርምጃ ወስዳለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በትላንቱ እጅግ አሰቃቂ እና አሳዛኝ እንደ ሰው ልጅም አንገት አስደፊ ቪድዮ ላይ የተከሰተው ክስተት በተመለከተ የተገኘው መረጃ ፦ 👉 ቀኑ ፦ በግልፅ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም። 👉 ክልል ፦ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 👉 ዞን ፦ መተከል ዞን 👉 ወረዳ ፦ ጉባ ወረዳ 👉 ቀበሌ ፦ አይሲድ ቀበሌ 👉 በእንደዛ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ፦ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም…
" አጣርቼ እምርጃ ወስዳለሁ " - መንግስት

ትላንትና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨውን አሰቃቂ ቪድዮ (የሰው ልጅ በህይወት እያለ ሲቃጠል የሚያሳይ) በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ አውጥቷል።

መንግስት ድርጊቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ ሰሞኑን መፈፀሙን ገልጿል።

ድርጊቱ እጅግ አሰቃቂ ፣ ጭካኔ የተሞላበት እና ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ድርጊት ነው ያለው መንግስት መነሻቸውም ሆነ ማንነታቸው ምንም ይሁን ምን ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን አጣርቼ ህጋዊ እርምጃ ወስዳለሁ ብሏል።
 
" ድርጊቱ ከኢትዮጵያዊነት ባህል ፣ እሴት እና ከማንኛውም የሰብዓዊነት እሳቤ ያፈነገጠና እጅግ አሰቃቂ ወንጀል ነው " ያለው መንግስት " ይህ እኩይ ድርጊት መጠፋፋትን ያፈጥን ካልሆነ በቀር ሰላምንም ሆነ ፍትህን እውን ሊያደርግ አይችልም " ብሏል።

መንግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ህገወጥነት ለመቆጣጠር እና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ከክልሉ እና ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር እየተሰራ ይገኛል ብሏል።
 
" የንፁሃን ዜጎችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላትን ከዚህ በኋላ አልታገስም " ያለው መንግስት " በወንጀል ስራ ላይ የተሰማሩና የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላት ከወዲሁ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስባለሁኝ " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Russia የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ እና ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ። ፑቲን ፤ " ገንዘብ ሳይከፈላቸው ለሩሲያ መዋጋት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ " ካሉ በኋላ፤ " እነዚህን ሰዎች ወደ ጦር ግንባር በመላክ ማድረግ የሚፈልጉትን መተባበር አለብን " ብለዋል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተነስተው በዶንባስ ግዛት ከሩሲያ…
#Update

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሩሲያ ለመዝመት ጥያቄ ላቀረቡ የሌላ ሀገር ዜጎች " ተመዝግባችሁ ፍላጎታችሁን ፈፅሙ " አሉ።

በሩሲያ የደህንነት ጉባኤ ስብሰባ ላይ ፑቲን እንዳሉት ምንም እንኳ የውጭ ዜጎች ቢሆኑም በሩሲያ ከሚደገፉ ኃይሎች ጎን ለመሰለፍ የፈቀዱ ሁሉ ፍላጎታቸው እንዲሟላ ያሻል ብለዋል።

የሩሲያው የመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ በተለይ ከመካለኛው ምሥራቅ አካባቢ ብቻ 16 ሺ የሚሆኑ ሰዎች በፍቃደኝነት ለመዋጋት ፍላጎት አሳይተዋል ብለዋል።

መዋጋት የሚፈልጉት ሩሲያ ለምትደግፋቸው የዩክሬን ተገንጣይ ኃይሎች እንደሆነ ተመላክቷል።

አሜሪካ እንደምትለው ከእነዚህ ሰዎች መካከል ብዙዎቹ የከተማ ሽምቅ ውጊያ የካበተ ልምድ ያላቸው ሶሪያዊያን ይገኙበታል።

ሞስኮ የባሻር አል አሳድ ቀኝ እጅና ደጋፊ ስትሆን በሶሪያው የእርስ በእርስ ጦርነት ጊዜ አሳድን ከሥልጣን ከመወገድና ከሞት የታደገች አገር ናት።

ፑቲን ለሩሲያ ወደው ለመዝመት ጥያቄ ያቀረቡ በሙሉ በዶንባስ ከሩሲያ አጋሮች ጋር ተሰልፈው መዋጋት እንዲችሉ ሁኔታዎች በፍጥነት እንዲመቻቹ አዘዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሾይጉ ከዩክሬን የተማረኩ የሚሳኤል መቃወሚያዎች ሉሃንስና ዶኔትስክ ተዋጊዎች እንዲሰጡ ሐሳብ ያቀረቡ ሲሆን፣ ፑቲን "እንዳልከው አድርግ" የሚል ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

ይህን ተከትሎ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ "ከሶሪያ የሚነሱ ወንበዴዎች ሕዝባችንን ሊጨርሱ እየመጡ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የውጭ ዜጎች ወዶ ዘማቾች ወደሩሲያ ብቻ ሳይሆን ወደ ዩክሬንም እያመሩ እንደሆነ መረጃዎች የወጡ ሲሆን ዜሌንስኪም ቢሆኑ ይህን አምነዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ 16 ሺ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ የሆኑ የሌላ አገር ዜጎችን ጨምሮ ለዩክሬን ለመዝመት ፍላጎት ማሳየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ከ70 በላይ #ኢትዮጵያውያን 🇪🇹 ፖላንድ ገብተዋል " - በኢትዮጵያ የፖላንድ ኤምባሲ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የፖላንድ ኤምባሲ ሩስያ ዩክሬን ላይ ወረራ ከፈፀመች በኃላ በፖላንድ ስላለው ሁኔታ ከተማሪዎች እና ከቤተሰቦች በርካታ ጥያቄዎች እየደረሰው መሆኑን ገልጿል።

በፖላንድ ግዛት ምንም አይነት የፀጥታ ችግር የለም ያለው ኤምባሲው እንደሁል ጊዜው ዩኒቨርሲቲዎች ክፍት ናቸው ፣ ትምህርትም ቀጥሏል ፤ እንዲሁም ሆስፒታሎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት (ባቡር፣ ባስ) ፣ ሬስቶራንቶች፣ ቢሮዎች ሁሉ እንደሁልጊዜ ስራ ላይ ናቸው ብሏል።

በአሁን ሰዓት ከ1,500 በላይ ተማሪዎች በፖላንድ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተጠቁሟል።

ኤምባሲው ሩስያ በዩክሬን ላይ ህገወጥ ወረራ ከፈፀመች አንስቶ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ጦርነት ሽሽት ወደ ፖላንድ መግባታቸውን አመልክቶ ከእነዚህም መካከል በርካታ አፍሪካውያን እንደሚገኙበት እና ከ70 በላይ የሚሆኑትም #ኢትዮጵያውያን 🇪🇹 መሆናቸውን ገልጿል።

ፖላንድ ጦርነት ሸሽተው ወደ ሀገሯ የሚመጡ ሰዎች ደንበር ላይ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙና ፤ የምግብና መጠለያ ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን እያደረገች እንደሆነው በአዲስ አበባ የፖላንድ ኤምባሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሐግብር በአሁን ሰዓት መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው። በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የሃይማኖት አባቶች ፣ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የውጪ አገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል። በተጨማሪም ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።…
#Update

የአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሽኝት በመስቀል አደባባይ ተካሂዳል።

በአሁን ሰዓት ላይ የቅዱስነታቸው የክብር አስከሬን ከመስቀል አደባባይ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት ያደረገውን ጉዞ አጠናቆ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ደርሷል።

በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ልዩ ለዩ መንፈሳዊ ሥርዓቶች ከተከናወኑ በኋላም ጉዞ ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚደረግ ሲሆን በካቴድራሉ ሥርዓተ ጸሎት እና ፍትሀት ሲደረግ አድሮ እሁድ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ ሥርዓተ ቀብሩ የሚፈጸም ይሆናል።

ምንጭ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ፌስቡክን አገደች። ሩስያ በሀገሯ ውስጥ ፌስቡክ የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት እንዳይሰጥ ሙሉ በሙሉ ዘግታዋለች። ሩስያ ከጥቅምት 2020 ጀምሮ ቢያንስ 26 በሚሆኑ የሩሲያ ሚዲያዎች እና የመረጃ ምንጮ ላይ መድልዎ መፈፀሙን ገልፃለች። በተጨማሪም በቅርብ ጊዜ ከክሬምሊን ጋር የተቆራኙ የሚዲያ ምንጮች RT Newsና Sputnik News በመላው አውሮፓ እንዲገደቡ መደረጉን አመልክታለች። ይህንንም…
#Instagram

ሩስያ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ኢንስታግራም እንደሚታገድ አስታወቀች።

በሜታ ኩባንያ ስር የሚተዳደረው ኢንስታግራም ከሰኞ ጀምሮ እንደሚታገድ ሩስያ ገልፃለች።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ሜታ ከዩክሬን ጦርነት ጋር ተያያዞ በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች ‘ለተወሰነ ጊዜ’ እንደሚፈቀድ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው።

ሜታ በፌስቡክ እና ኢስታግራም ላይ " ሞት ለወራሪው ሩስያ፣ ሞት ለሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሞት ለቤላሩሱ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ " የሚሉ ልጥፎች በበርካታ አገራት ፈቅዷል እነዚህም አርሜኒያ ፣ አዘርባጃን ፣ ኢስቶኒያ ፣ ጆርጂያ ፣ ሃንጋሪ ፣ ላቲቪያ ፣ ሊቱዌኒያ ፣ ፖላንድ ፣ ሮማኒያ፣ ሩሲያ፣ ስሎቫኪያ እና ዩክሬን ናቸው።

ነገር ግን ድርጅቱ ንፁሃንን ኢላማ የሚያደርጉ ግጭትን ቀስቃሽ ንግግሮች እንደማይፈቅድ ገልጿል።

ሩስያ ፤ " ሜታ በፌስቡክ እና ኢስታግራም በዜጎቼ ላይ የጥቃት ጥሪዎች እንዲለጠፉ መፍቀዱ ከዚህ በፊት ተደርጎ የማይታወቅ ነው " ያለች ሲሆን በኢስታግራም በሩስያውያን ላይ የኃይል ጥቃት እንዲፈፀሙ ጥሪዎች እየተዘዋወሩ ነው ብላለች።

ይህን ተከትሎ ከሰኞ ጀምሮ ኢስታግራም በምድሪቱ ላይ እንደሚታገድ አሳውቃለች።

በሀገሪቱ ያሉ የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ባላቸው 48 ሰዓታት ውስጥ ፎቶ እና ቪድዮዎቻቸውን ወደ ሌላ ማህበራዊ ሚዲያ እንዲያዘዋውሩ እንዲሁም ለጓደኞቻቸው፣ ለተከታዮቻቸው እንዲያሳውቁ መልዕክት ተላልፏል።

ሩስያ ከዚህ በፊት #ፌስቡክ የተሰኘውን የሜታ ኩባንያ አካል የሆነውን የማህበራዊ ሚዲያ ማገዷ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፅጌሬዳ_ግርማይ የአርባ ምርንጭ ዩኒቨርሲቲ እና የጋሞ ዞን ፖሊስ የተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ ህልፈትን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳሰቡ። የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር በድሩ ሂሪጎ " የአርባ ምንጭ አካባቢው በሰላም ግንባታ ለሀገራችን አርአያ፣ ምሳሌ የሚሆኑ አባቶች ያሉበት ከተማሪዎቻችን ጋርም በቅርበት የሚሰሩበት…
#Update

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ በወንጀለኛ ሕግ 539/1 ራሱን እንዲከላከል ብይን ተሰጦታል።

በሕግ ጥላ ስር የሚገኘው ተከሳሹ፤ በጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሚገኝ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር መርኪያ መንገሻ @tikvahuniversity ተናግረዋል።

" ከባድ ግድያ በመፈጸም የወንጀል ክስ ራሱን እንዲከላከል " የተነገረው ተከሳሹ ፤ " ወንጀሉ ከእድሜ ልክ እስራት እስከ ሞት የሚያስቀጣ " መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ በማቅረብ እንዲከላከል ለመጋቢት 20/2014 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጦታል።

ጥር 23 / 2014 ዓ.ም የተገደለችው የ20 ዓመቷ ተማሪ ፅጌሬዳ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ። ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ዛሬ 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል። ፓርቲው ጉባኤውን በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂድ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀናት ይቆያል። በአሁኑ ሰዓት ላይ የጉባኤው የመክፈቻ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ሲሆን የፓርቲው ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው አካላት…
#Update

ብልፅግና ፓርቲ እያካሄደ በሚገኘው 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው መርሃ ግብር የፓርቲውን ፕሬዜዳንት እና ምክትል ፕሬዜዳንቶች ምርጫ አካሂዷል።

በዚህም ጉባኤው ፦

👉 ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል። (ዶ/ር ዐቢይን የተጠቆሙት የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ነበሩ)

👉 አቶ አደም ፋራህ እንዲሁም አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ፕሬዚዳንቶች አድርጎ መርጧል። (አቶ አደም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሀሰን የተጠቆሙ ሲሆን አቶ ደመቀ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ነበር የተጠቆሙት)

በሌላ በኩል የም/ ፕሬዜዳንቶች ጥቆማ በተሰጠበት ወቅት አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ አደም ፋራህ ላይ እጩ ሆነው እንዳይቀርቡ ተቃውሞ አቅርበው ነበር።

ተቃውሞ ያቀረቡት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ፥ " አቶ አደም እጩ ሆነው መቅረብ የለበትም ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም አደም በአፋር እና ሶማሌ አካባቢ በተለይ በኢሳ እና አፋር ግጭት ላይ በቀጥታ እጅ ያለው ሰው በመሆኑ ይህን ግዙፍ ፓርቲ ምክትል ሆኖ መምራት ስለማይችል በእራሴ በኩል እቃወማለሁ " ብለዋል።

ምንም እንኳን አቶ አደም ፋራህ ላይ ተቃውሞ ቢቀርብም በአንድ ሶስተኛ ድምፅ አቶ አደም እጩ ሆነው ሊቀርቡ ችለዋል።

በዚህ ሂደት የጉባኤ ተሳታፊዎች ድጋፋቸውን ለመግለፅ ያልተቋረጠ ከፍተኛ ጭብጨባ ያሰሙ ሲሆን ዶ/ር ዐቢይ ፥ " ይሄ ትክክል አይደለም ...undemocratic አትሁኑ፤ የፈለገ ሰው ይመርጣል፤ የፈለገ ይቃወማል። በግርግር በወከባ፣ ምናምን የሚደረግ ነገር አይደለም። ጥሩ አይደለም እንደዚህ " ሲሉ ተደምጠዋል።

ከዚህም ለኃላ በተካሄደው ምርጫ አቶ አደም 1,330 ድምፅ አግኘተው ም/ፕሬዜዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

@tikvahethiopia
#EthioMartShopping

የጀርባና የወገብ ችግር አለቦት?
Call 0944039419
ያሉበት  ድረስ በነፃ እናደርሳለን
ሙሉ የወገብ  950 ብር;የጀርባ 650 ብር
የመቀመጫ Cushion  850 ብር
የጀርባ Pillow 750 ብር
የጀርባ መጉበጥ ችግርን ፣የጀርባ ዲስክ መንሸራተት በእድሜ መግፋት የሚመጡ የጀርባ ችግሮች የሚከላከልና ቀጥያል እና ማራኪ ቁመና የሚያላብስ።

ቦሌ መዳንያሃለም   2ኛ ፎቅ