TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Russia

የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ እና ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ።

ፑቲን ፤ " ገንዘብ ሳይከፈላቸው ለሩሲያ መዋጋት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ " ካሉ በኋላ፤ " እነዚህን ሰዎች ወደ ጦር ግንባር በመላክ ማድረግ የሚፈልጉትን መተባበር አለብን " ብለዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተነስተው በዶንባስ ግዛት ከሩሲያ ጦር ጎን መሰለፍ የሚፈልጉ 16 ሺህ ሰዎች አሉ ሲሉ ለፑቲን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለፀጥታ ምክር ቤታቸው ምዕራባውያን " በግልጽ ዓለም አቀፍ ሕጎችን በመተላለፍ ተዋጊዎችን ለዩክሬን እየቀጠሩ ነው " ሲሉ መናገራቸውን ቢቢሲ ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም ዩክሬን በ "አፍሪካ" በተለያዩ ሀገራት በሚገኙት ኤምባሲዎቿ በኩል በ #ቅጥር ለዩክሬን የሚዋጉ ሰዎችን እንደምትፈልግ ማስታወቋ በኃላ ይህ ጥሪው ቁጣን ፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE ትላንትና ህ/ተ/ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ 13 ሀገራዊ እና 13 ክልላዊ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በማድረግ እንዲያስገቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ አሳስቧል። ማሳሰቢያው ከተሰጣቸው ፓርቲዎች መካከል ፦ ብልፅግና፣ ኦፌኮ፣ አብን ፣ ኦነግ ፣ ነእፓ፣ ኦብነግ፣ መኢአድ ይገኙበታል።…
ገዢው ብልፅግና ፓርቲ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።

ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ዛሬ 1ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

ፓርቲው ጉባኤውን በአዲስ አበባ ከተማ የሚያካሂድ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀናት ይቆያል።

በአሁኑ ሰዓት ላይ የጉባኤው የመክፈቻ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ሲሆን የፓርቲው ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የጉባኤው ተሳታፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ታድመዋል።

ዛሬ ጉባኤውን የጀመረው ብልፅግና ፓርቲ ፤ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያከናውኑ እና አስፈላጊ የሆኑ የሰነድ ማሻሻያዎችን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስገቡ ማሳሰቢያ ከሰጣቸው 13 ሀገራዊ እና 13 ክልላዊ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

" ነዳጅ እና ጋዝ አምራች ሀገራት አቅርቦታችሁን ጨምሩ " - G7

በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሀገራት ስብሰብ G7 ፤ ሩስያ በዩክሬን ላይ በፈፀመችው "ወረራ" በዋጋ ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ ለመቋቋም ትላልቅ የነዳጅ እና ጋዝ አምራች ሀገራት አቅርቦቶችን እንዲያሳድጉ አሳስቧል።

የG7 የኢነርጂ ሚኒስትሮች በጋራ ባወጡት መግለጫ ነዳጅ እና ጋዝ አምራች ሀገራት ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ እንዲሰሩ እና ወደ ዓለም አቀፍ ገበያዎች የሚደርሰውን ምርት የማሳደግ አቅማቸውን እንዲፈትሹ ጠይቀዋል።

በዚህ ላይ ኦፔክ (የነዳጅ አምራች አገራት ኅብረት) ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

በተጨማሪም ሚኒስትሮቹ በመግለጫቸው የጋዝ ዋጋ መጨመርን ለማስቆም ውጤታማ እርምጃዎችን ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የG7 የኢነርጂ ሚኒስትሮች የኃይል ምርቶች ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ጭማሪ በቤትውስጥ እና በንግድ ስራዎች “በተለይም በአውሮፓ ሀገራት” ላይ ያለው ጫና “አሳሳቢ” ነው ብለዋል።

ታዳጊ አገራት ውስጥ ያለውም ጫና እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል።

የሩስያና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ በዚህ ሳምንት የነዳጅ ዋጋ በ14 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በመታይወቅ መልኩ ጨምሮ 140 ዶላር ድረስ ደርሶ እንደነበር ይታወሳል።

ከዚህ ባለፈ የG7 አባል ሀገር አንዷ የሆነችው አሜሪካ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ከሩስያ የኃይል አቅርቦቶችን (ነዳጅ፣ ጋዝ) ገዝታ እንደማታስገባ እንዲሁም ሌላኛዋ የG7 አባል ብሪታኒያም ከአመቱ መጨረሻ በኃላ ተመሳሳይ እርምጃ እንደምትወስድ ማስታወቋ ሩስያም ለምዕራባውያኑ ድርጊት አፀፋ ለአውሮጳ የምታቀርበውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቷን እንደምታቋርጥ መግለጿ በነዳጅና ጋዝ ምርቶች ላይ አሁን እየጨመረ ካለውም በላይ ጭማሪ እንዳያሳይ ተሰግቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NBE በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ባለፈው የካቲት 20 ቀን 2014 ተጠናቋል። መረጃዎችን ያልሰጡ የባንክ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ ሆነዋል (በሚሊዮን ሊቆጠሩ ናቸው ተብሎ ይታመናል) ፤ አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉትም በመመሪያው መሰረት መረጃ ሲሰጡ ብቻ ነው። የ " መታወቂያ እድሳት…
በሁለት ወር ተራዝሟል !

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ላለፉት 6 ወራት ባንኮች የደንበኞቻቸውን መረጃ የማደራጀትና የማጥራት ስራ ሲሰሩ ነበር።

በተለያዩ ምክንያቶች መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ ላልቻሉ ደንበኞች ተጨማሪ የ2 ወር ጊዜ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

የባንክ ደንበኞች ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ከወዲሁ ወደ ባንክ በመሄድ መረጃቸውን ወቅታዊ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

#CBE

@tikvahethiopia
የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ በመስቀል አደባባይ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስከሬን ሽኝት ይካሄዳል ፤ የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም ደግሞ መጋቢት 4 /2014 ዓ/ም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚፈፀም ይሆናል።

ነገ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፦

👉 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ

👉 ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ

👉 ከአራት ኪሎ ፣ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት

👉 ከፒያሳ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሐራምቤ ሆቴል መብራት

👉 ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር

👉 ጦር ኃይሎች ፣ በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት

" #ይለፍ_ለሌላቸው_ተሽከርካሪዎች " ከጥዋቱ 12:30 ጀምሮ ዝግጅቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በእለቱ የብፁእነታቸው አስከሬን ከመስቀል አደባባይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ (ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን) በሚንቀሳቀስበት ወቅት ፦

👉 ከመስቀል አደባባይ ፣ በብሔራዊ ቤተ መንግስት፣ ውጭ ጉዳይ ፣ አራት ኪሎ ፣ ቅድስት ማርያም የሚወስደው መንገድ፣

#መጋቢት_4 የብፁዕነታቸው የቀብር ስነ-ስርዓት የሚፈፀም በመሆኑ የቀብር ስነ-ስርዓቱ እስከሚፈፀም ወደ ቅድስት ማርያም ፣ አራት ኪሎ እና ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆነ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አሳውቋል።

ለታዳሚዎች ፦ ለጋራ ደህንነት ፍተሻ መኖሩን እንዲገነዘቡም ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በዚህ ትውልድ ያለነው ወጣቶች ፣ ጎልማሶች ፣ በእድሜም የገፋን ሰዎች ጭምር በሰው ልጆች ሊደረጉ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ እጅግ በርካታ አስደንጋጭ አሰቃቂ ግፎችን በቪድዮ፣ በፎቶ ተመልክተናል።

ይህ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ መሰባሰቢያ ከተፈተ ጀምሮ (ያለፉትን 3ና 4 ዓመታት) እጅግ በርካታ አሰቃቂ ክስተቶችን፣ የሰው ልጅ አንገት የሚያስደፉ ድርጊቶችን ታዝበናል፤ በይፋም እርስ በእርስ መረጃ ተለዋውጥናል።

በየጊዜው የነበሩ እጅግ ዘግናኝ ከህግ ሆነ ከሞራልም ውጭ የሆኑ ድርጊቶችን ወደ ኃላ ተመልሰን ለመዘርዘር ጊዜውም አይበቃን ፤ በተለይም ከቲክቫህ ጋር ዓመታትን ያሳለፋችሁ የምታውቁት ነው።

ሌላው ይቅር በቅርብ ጊዜ እንኳን ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከተነሳ በኃላ እጅግ አሰቃቂ የሆኑ ቪድዮዎች ተሰራጭተው ስለጉዳዩ መረጃ መለዋወጣችን የቅርቡ ትውስታችን ነው።

ዛሬ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የተሰራጨው አሰቃቂ ቪድዮ በርካቶችን ያስደነገጠ ያሳዘነ ሆኗል። ቪድዮውን እዚህ አምጥቶ ማጋራት ትክክል እንዳልሆነ ታውቁታለቹ ፤ በጥቅሉ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ የሰው ልጅ #በህይወት_እያለ በእሳት እንዲቃጠል ሲደረግ የሚያሳይ ነው።

ከቪድዮው ጋር በተያያዘ እነማን ? መቼ ? የት ? እና እንዴት ? ስለሚለው ጉዳዩ ይመለከተኛል የሚል አካል በአስቸኳይ ወጥቶ ማብራሪያ መስጠት ይጠበቅበታል።

በተለይም ደግሞ በቪድዮው ላይ የፀጥታ ኃይሎችን የደንብ ልብስ ያደረጉ ሰዎች በግልፅ ስለሚታዩ ተቋማቱ ማብራሪያ መስጠት አለባቸው።

የሰብዓዊ መብት ተቋማትም ጉዳዩን ሊከታተሉትና ለህዝብ ሊያሳውቁ ይገባል።

እንዲህ ያለው ነገር በቪድዮ አደባባይ ላይ ሲወጣ መነጋገሪያ ይሆናል እንጂ ያልተቀረፀው ፣ ህዝብ ያላወቀው ስንት ጉድ ይኖር ይሆን ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሚዘጉ መንገዶች ! ነገ በመስቀል አደባባይ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አስከሬን ሽኝት ይካሄዳል ፤ የቀብር ስነ-ስርዓታቸውም ደግሞ መጋቢት 4 /2014 ዓ/ም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚፈፀም ይሆናል። ነገ መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ/ም የሚካሄደው የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፦ 👉 ከቦሌ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ 👉
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሐግብር በአሁን ሰዓት መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የሃይማኖት አባቶች ፣ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የውጪ አገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ፎቶ ፦ ENA / የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በዚህ ትውልድ ያለነው ወጣቶች ፣ ጎልማሶች ፣ በእድሜም የገፋን ሰዎች ጭምር በሰው ልጆች ሊደረጉ ይችላሉ ተብለው የማይገመቱ እጅግ በርካታ አስደንጋጭ አሰቃቂ ግፎችን በቪድዮ፣ በፎቶ ተመልክተናል። ይህ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ መሰባሰቢያ ከተፈተ ጀምሮ (ያለፉትን 3ና 4 ዓመታት) እጅግ በርካታ አሰቃቂ ክስተቶችን፣ የሰው ልጅ አንገት የሚያስደፉ ድርጊቶችን ታዝበናል፤ በይፋም እርስ በእርስ…
#Update

በትላንቱ እጅግ አሰቃቂ እና አሳዛኝ እንደ ሰው ልጅም አንገት አስደፊ ቪድዮ ላይ የተከሰተው ክስተት በተመለከተ የተገኘው መረጃ ፦

👉 ቀኑ ፦ በግልፅ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም።

👉 ክልል ፦ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል

👉 ዞን ፦ መተከል ዞን

👉 ወረዳ ፦ ጉባ ወረዳ

👉 ቀበሌ ፦ አይሲድ ቀበሌ

👉 በእንደዛ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ፦ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም

👉 የድርጊቱ ተሳታፊዎች በቁጥጥር ስር ስለመዋላቸው ፦ አይታወቅም

👉 የተወሰደ እርምጃ በተመለከተ ፦ መንግስት አጣርቼ እርምጃ ወስዳለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በትላንቱ እጅግ አሰቃቂ እና አሳዛኝ እንደ ሰው ልጅም አንገት አስደፊ ቪድዮ ላይ የተከሰተው ክስተት በተመለከተ የተገኘው መረጃ ፦ 👉 ቀኑ ፦ በግልፅ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም። 👉 ክልል ፦ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 👉 ዞን ፦ መተከል ዞን 👉 ወረዳ ፦ ጉባ ወረዳ 👉 ቀበሌ ፦ አይሲድ ቀበሌ 👉 በእንደዛ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ፦ አይታወቀም / ይፋ አልሆነም…
" አጣርቼ እምርጃ ወስዳለሁ " - መንግስት

ትላንትና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የተሰራጨውን አሰቃቂ ቪድዮ (የሰው ልጅ በህይወት እያለ ሲቃጠል የሚያሳይ) በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ አውጥቷል።

መንግስት ድርጊቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ አይሲድ ቀበሌ ሰሞኑን መፈፀሙን ገልጿል።

ድርጊቱ እጅግ አሰቃቂ ፣ ጭካኔ የተሞላበት እና ከሰብአዊነት ያፈነገጠ ድርጊት ነው ያለው መንግስት መነሻቸውም ሆነ ማንነታቸው ምንም ይሁን ምን ድርጊቱን የፈፀሙ አካላትን አጣርቼ ህጋዊ እርምጃ ወስዳለሁ ብሏል።
 
" ድርጊቱ ከኢትዮጵያዊነት ባህል ፣ እሴት እና ከማንኛውም የሰብዓዊነት እሳቤ ያፈነገጠና እጅግ አሰቃቂ ወንጀል ነው " ያለው መንግስት " ይህ እኩይ ድርጊት መጠፋፋትን ያፈጥን ካልሆነ በቀር ሰላምንም ሆነ ፍትህን እውን ሊያደርግ አይችልም " ብሏል።

መንግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ህገወጥነት ለመቆጣጠር እና በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ከክልሉ እና ከመላው የጸጥታ አካላት ጋር እየተሰራ ይገኛል ብሏል።
 
" የንፁሃን ዜጎችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላትን ከዚህ በኋላ አልታገስም " ያለው መንግስት " በወንጀል ስራ ላይ የተሰማሩና የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላት ከወዲሁ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስባለሁኝ " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Russia የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚመጡ እና ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች ለሩሲያ መዋጋት ይችላሉ አሉ። ፑቲን ፤ " ገንዘብ ሳይከፈላቸው ለሩሲያ መዋጋት የሚፈልጉ ሰዎች አሉ " ካሉ በኋላ፤ " እነዚህን ሰዎች ወደ ጦር ግንባር በመላክ ማድረግ የሚፈልጉትን መተባበር አለብን " ብለዋል። የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተነስተው በዶንባስ ግዛት ከሩሲያ…
#Update

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለሩሲያ ለመዝመት ጥያቄ ላቀረቡ የሌላ ሀገር ዜጎች " ተመዝግባችሁ ፍላጎታችሁን ፈፅሙ " አሉ።

በሩሲያ የደህንነት ጉባኤ ስብሰባ ላይ ፑቲን እንዳሉት ምንም እንኳ የውጭ ዜጎች ቢሆኑም በሩሲያ ከሚደገፉ ኃይሎች ጎን ለመሰለፍ የፈቀዱ ሁሉ ፍላጎታቸው እንዲሟላ ያሻል ብለዋል።

የሩሲያው የመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ በተለይ ከመካለኛው ምሥራቅ አካባቢ ብቻ 16 ሺ የሚሆኑ ሰዎች በፍቃደኝነት ለመዋጋት ፍላጎት አሳይተዋል ብለዋል።

መዋጋት የሚፈልጉት ሩሲያ ለምትደግፋቸው የዩክሬን ተገንጣይ ኃይሎች እንደሆነ ተመላክቷል።

አሜሪካ እንደምትለው ከእነዚህ ሰዎች መካከል ብዙዎቹ የከተማ ሽምቅ ውጊያ የካበተ ልምድ ያላቸው ሶሪያዊያን ይገኙበታል።

ሞስኮ የባሻር አል አሳድ ቀኝ እጅና ደጋፊ ስትሆን በሶሪያው የእርስ በእርስ ጦርነት ጊዜ አሳድን ከሥልጣን ከመወገድና ከሞት የታደገች አገር ናት።

ፑቲን ለሩሲያ ወደው ለመዝመት ጥያቄ ያቀረቡ በሙሉ በዶንባስ ከሩሲያ አጋሮች ጋር ተሰልፈው መዋጋት እንዲችሉ ሁኔታዎች በፍጥነት እንዲመቻቹ አዘዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሾይጉ ከዩክሬን የተማረኩ የሚሳኤል መቃወሚያዎች ሉሃንስና ዶኔትስክ ተዋጊዎች እንዲሰጡ ሐሳብ ያቀረቡ ሲሆን፣ ፑቲን "እንዳልከው አድርግ" የሚል ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

ይህን ተከትሎ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ "ከሶሪያ የሚነሱ ወንበዴዎች ሕዝባችንን ሊጨርሱ እየመጡ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የውጭ ዜጎች ወዶ ዘማቾች ወደሩሲያ ብቻ ሳይሆን ወደ ዩክሬንም እያመሩ እንደሆነ መረጃዎች የወጡ ሲሆን ዜሌንስኪም ቢሆኑ ይህን አምነዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ 16 ሺ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኛ የሆኑ የሌላ አገር ዜጎችን ጨምሮ ለዩክሬን ለመዝመት ፍላጎት ማሳየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ከ70 በላይ #ኢትዮጵያውያን 🇪🇹 ፖላንድ ገብተዋል " - በኢትዮጵያ የፖላንድ ኤምባሲ

በአዲስ አበባ የሚገኘው የፖላንድ ኤምባሲ ሩስያ ዩክሬን ላይ ወረራ ከፈፀመች በኃላ በፖላንድ ስላለው ሁኔታ ከተማሪዎች እና ከቤተሰቦች በርካታ ጥያቄዎች እየደረሰው መሆኑን ገልጿል።

በፖላንድ ግዛት ምንም አይነት የፀጥታ ችግር የለም ያለው ኤምባሲው እንደሁል ጊዜው ዩኒቨርሲቲዎች ክፍት ናቸው ፣ ትምህርትም ቀጥሏል ፤ እንዲሁም ሆስፒታሎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት (ባቡር፣ ባስ) ፣ ሬስቶራንቶች፣ ቢሮዎች ሁሉ እንደሁልጊዜ ስራ ላይ ናቸው ብሏል።

በአሁን ሰዓት ከ1,500 በላይ ተማሪዎች በፖላንድ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተጠቁሟል።

ኤምባሲው ሩስያ በዩክሬን ላይ ህገወጥ ወረራ ከፈፀመች አንስቶ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ጦርነት ሽሽት ወደ ፖላንድ መግባታቸውን አመልክቶ ከእነዚህም መካከል በርካታ አፍሪካውያን እንደሚገኙበት እና ከ70 በላይ የሚሆኑትም #ኢትዮጵያውያን 🇪🇹 መሆናቸውን ገልጿል።

ፖላንድ ጦርነት ሸሽተው ወደ ሀገሯ የሚመጡ ሰዎች ደንበር ላይ የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙና ፤ የምግብና መጠለያ ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን እያደረገች እንደሆነው በአዲስ አበባ የፖላንድ ኤምባሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የሽኝት መርሐግብር በአሁን ሰዓት መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው። በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የሃይማኖት አባቶች ፣ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የውጪ አገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል። በተጨማሪም ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።…
#Update

የአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሽኝት በመስቀል አደባባይ ተካሂዳል።

በአሁን ሰዓት ላይ የቅዱስነታቸው የክብር አስከሬን ከመስቀል አደባባይ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት ያደረገውን ጉዞ አጠናቆ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ደርሷል።

በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ልዩ ለዩ መንፈሳዊ ሥርዓቶች ከተከናወኑ በኋላም ጉዞ ወደ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሚደረግ ሲሆን በካቴድራሉ ሥርዓተ ጸሎት እና ፍትሀት ሲደረግ አድሮ እሁድ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ ሥርዓተ ቀብሩ የሚፈጸም ይሆናል።

ምንጭ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ፌስቡክን አገደች። ሩስያ በሀገሯ ውስጥ ፌስቡክ የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት እንዳይሰጥ ሙሉ በሙሉ ዘግታዋለች። ሩስያ ከጥቅምት 2020 ጀምሮ ቢያንስ 26 በሚሆኑ የሩሲያ ሚዲያዎች እና የመረጃ ምንጮ ላይ መድልዎ መፈፀሙን ገልፃለች። በተጨማሪም በቅርብ ጊዜ ከክሬምሊን ጋር የተቆራኙ የሚዲያ ምንጮች RT Newsና Sputnik News በመላው አውሮፓ እንዲገደቡ መደረጉን አመልክታለች። ይህንንም…
#Instagram

ሩስያ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ኢንስታግራም እንደሚታገድ አስታወቀች።

በሜታ ኩባንያ ስር የሚተዳደረው ኢንስታግራም ከሰኞ ጀምሮ እንደሚታገድ ሩስያ ገልፃለች።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ሜታ ከዩክሬን ጦርነት ጋር ተያያዞ በፌስቡክ እና ኢንስታግራም ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች ‘ለተወሰነ ጊዜ’ እንደሚፈቀድ ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ ነው።

ሜታ በፌስቡክ እና ኢስታግራም ላይ " ሞት ለወራሪው ሩስያ፣ ሞት ለሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና ሞት ለቤላሩሱ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ " የሚሉ ልጥፎች በበርካታ አገራት ፈቅዷል እነዚህም አርሜኒያ ፣ አዘርባጃን ፣ ኢስቶኒያ ፣ ጆርጂያ ፣ ሃንጋሪ ፣ ላቲቪያ ፣ ሊቱዌኒያ ፣ ፖላንድ ፣ ሮማኒያ፣ ሩሲያ፣ ስሎቫኪያ እና ዩክሬን ናቸው።

ነገር ግን ድርጅቱ ንፁሃንን ኢላማ የሚያደርጉ ግጭትን ቀስቃሽ ንግግሮች እንደማይፈቅድ ገልጿል።

ሩስያ ፤ " ሜታ በፌስቡክ እና ኢስታግራም በዜጎቼ ላይ የጥቃት ጥሪዎች እንዲለጠፉ መፍቀዱ ከዚህ በፊት ተደርጎ የማይታወቅ ነው " ያለች ሲሆን በኢስታግራም በሩስያውያን ላይ የኃይል ጥቃት እንዲፈፀሙ ጥሪዎች እየተዘዋወሩ ነው ብላለች።

ይህን ተከትሎ ከሰኞ ጀምሮ ኢስታግራም በምድሪቱ ላይ እንደሚታገድ አሳውቃለች።

በሀገሪቱ ያሉ የኢንስታግራም ተጠቃሚዎች ባላቸው 48 ሰዓታት ውስጥ ፎቶ እና ቪድዮዎቻቸውን ወደ ሌላ ማህበራዊ ሚዲያ እንዲያዘዋውሩ እንዲሁም ለጓደኞቻቸው፣ ለተከታዮቻቸው እንዲያሳውቁ መልዕክት ተላልፏል።

ሩስያ ከዚህ በፊት #ፌስቡክ የተሰኘውን የሜታ ኩባንያ አካል የሆነውን የማህበራዊ ሚዲያ ማገዷ ይታወሳል።

@tikvahethiopia