TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Waghimra

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ያሉ ተፈናቃዮች የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።

አስተዳደሩ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት " ዋግ ከችግር ቆፈን ላይ ወድቃለች፤ የመከራ ቃፊር እየናጣት ነው የሚደርስላት ትሻለች " ብሏል።

አሁን ላይ ከአበርገሌ፣ ከጻግብጂ፣ ከዝቋላ፣ ከሰቆጣ ዙሪያ፣ ዛታ፣ ወፍላና ኮረም በጦርነት ምክንያት በየቀኑ ከ2000 ሰው በላይ የተፈናቀለ ወለህ ሜዳ ላይ ሰፍሯል እንዲሁም በሰቆጣ ከተማ ከተለያዩ ቦታዎች የሰፈረው ከ52,000 (ከሀምሳ ሁለት ሺህ ) በላይ ህዝብ መሆኑ ተገልጿል

ቤት ንብረቱን ጥሎ በመጠለያ የሚኖረው ማህበረሰብ የማይቻል ችግር ተሸክሟል ተብሏል።

አዛውንቶች፣ እናቶች፣ ህጻናት በአስቸጋሪ ሆኔታ ላይ የሚገኙ ሰሆን ከእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸው እርሀባቸውን እንዳይችሉ በበሽታ ተቆራምደዋል ተብሏል።

አዛውንቶች፣ ጧሪ የሌላቸው ሽማግሌዎች በሽታው፣ እርጅናው እና ረሀቡ እየተፈራረቀባቸው ሞታቸውን እየናፈቁ ነው።

" ዋግ ላይ መቋጫ የሌለው ችግር ፣ እፎይታ የሌለው መከራ፣ እየተፈራረቀ ነው " ያለው አስተዳደሩ " የሰው ልጅ እንደዘበት ሜዳ ላይ ወድቋል ፤ በዋግ ህዝብ ላይ የመከራ ጅራፍ አልለይ ብሏል፤ የችግር ድምጽ በህጻናት አእምሮ ሰፍሮ የሳቅ አንደበታቸው ተዘግቷል " ሲል አስተድቷል።

በዋግ ያሉ ተፈናቃዮች በየጊዜው የሚመጣው የነፍስ ማቆያ እርዳታ ለጥቂት ጊዜ እንቆይ ይሆናል እንጂ ችግራችን በመሰረታዊነት ሊቀርፍልን አይችልም ያሉ ሲሆን ፤ በዋናነት ችግሩ የሚቀረፈው አከባቢያቸው ነጻ ሆኖ ወደቀያችን ሲመለሱ መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስት ለአከባቢው #ትኩረት ሰጥቶ ማህበረሰቡን ሊታደግ ይገባል ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከዋግኽምራ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል። ከተሰጠው ቀነ ገደብ በኋላ መረጃዎችን ያልሰጡ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ አይችሉም። ባንኮች ባለፉት 6 ወራት መመርያው በሚጠይቀው መሥፈርት መሠረት የደንበኞቻቸውን መረጃ እየሰበሰቡ ነው፡፡  ይህንኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ ተከትለው…
#NBE

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት ባንኮች የደንበኞቻቸውን የተሟለ መረጃ እንዲያጠናክሩ የተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ባለፈው የካቲት 20 ቀን 2014 ተጠናቋል።

መረጃዎችን ያልሰጡ የባንክ ደንበኞች አካውንታቸውን #ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ ሆነዋል (በሚሊዮን ሊቆጠሩ ናቸው ተብሎ ይታመናል) ፤ አካውንታቸውን ማንቀሳቀስ የሚችሉትም በመመሪያው መሰረት መረጃ ሲሰጡ ብቻ ነው።

የ " መታወቂያ እድሳት " ግን እንቅፋት የሆነባቸው ብዙ ናቸው ለእነሱ የታሰበ ነገር ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።

ባንኮች ደንበኞቻቸው መረጃ እንዲሞሉ ላለፉት 6 ወራት ያህል በዋና ዋና ሚዲያዎች፣ በማህበራዊ ሚዲያ ፣ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ፣ በባንኮች የማስታወቂያ ቦርድ ላይ ጥሪ ሲያቀርቡ የነበረ ሲሆን አንዳንድ ባንኮች በመጨረሻው ሳምንት በስልክ እየደወሉ ለመቀበል ጥረት አድርገዋል።

ከቀነገደቡ መጨረሻ በፊት የባንክ ኃላፊዎች በመመርያ የተደነገገውን ማስፈጸም ከባድ ሥራ በመሆኑ መረጃ የማሰባሰቡ ሥራ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገዋል የሚል አስተያየት ቢሰጡም ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምላሽ ሳይሰጥ ጊዜው አልቋል።

በዚሁ አጋጣሚ በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ የግጭት ፣ የጥላቻ መልዕክቶች፣ ፌዝ ፣ ስድብ እና አሉታዊ ነገሮች ለብዙሃን በፍጥነት እና በብዛት ሼር ከማድረግ ይልቅ ወሳኝ ጠቃሚ መልዕክቶች የማጋራት ልምድና ኃላፊነት ሊጨምር ይገባል።

ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጠቃሚ መልዕክቶችን በአግባቡ ብናጋራ መረጃ ላልሰማው ወገናች እንዲሰማ እንዲሁም ደግሞ በመጨረሻ ቀናት ከሚፈጠር ወከባ ብዙ ሰዎችን መካከል ይቻላል።

@tikvahethiopia
#USAID

የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ወደ ትግራይ የሚደረጉት የእርዳታ በረራዎች መጨመራቸውን አሳውቀዋል።

ከታህሳስ ወር ጀምሮ 210 ሜትሪክ ቶን የህክምና እንዲሁም ስነምግብ አቅርቦቶች ትግራይ ክልል መድረሳቸውን ፓወር አመልክተዋል።

ነገር ግን ብቸኛው የተቸገሩትን ሁሉ ለመድረስ የሚያስችለው ፤ የጭነት ተሽከርካሪዎች የሚሄዱበት መንገድ እንደተዘጋ ነው ብለዋል።

700 ሺህ ሰዎች የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ያሉት ሳማንታ ፓወር " የኢትዮጵያ መንግስት ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦትን ማመቻቸት አለበት " ብለዋል።

@tikvahethiopia
የየካቲት ወር የዋጋ ግሽበት 📈

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ የየካቲት ወር 2014 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ33.6 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት የየካቲት ወር 2014 ዓ/ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ41.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በያዝነው ወር በአብዛኛው በእህሎች ዋጋ ጭማሪ የታየ ሲሆን በአንፃሩ የአትክልት ዋጋ ላይ ቅናሽ ታይቷል፡፡

ምንጭ፦ ካፒታል ጋዜጣ

@tikvahethiopia
#ይፈለጋል

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከላይ በምስሉ ላይ ያለውን ግለሰብ በወንጀል እንደሚፈልገው አሳውቋል።

ግለሰቡ የተለያዩ ሀሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣትና በመጠቀም ከተለያዩ ባንኮች ብር አጭበርብሮ በማውጣት ወንጀል እንደሚፈለግ ነው ፖሊስ የገለፀው።

ፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪውን የሚመለከት ማንኛውም መረጃ ካልዎት እንዲያሳውቁ ጥሪ ያቀረበ ሰሆን ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቋል።

ስልክ ፡ 0115309139 (ዘውትር በስራ ሰዓት ከ2:30-11:30)
ስልክ : 0111119475 / 0111711012 (በማንኛውም ሰዓት)
ነፃ የስልክ መስመር 861

@tikvahethiopia
#Ukraine

የዩክሬን መንግሥት ስንዴ፣ አጃ እና መሰል የእህል ምርቶች ከሀገር ውጭ ለገበያ እንዳይቀርቡ ማገዱ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

የግብር እና ምርቶችን የሚመለከተው አዲሱ ሕግ ዩክሬን ውስጥ የተደነገገው በዚህ ሳምንት መሆኑን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

በአሁን ሰዓት ከሩስያ ጋር በጦርነት ላይ የምትገኘው ዩክሬን የምድራችን ከፍተኛ የስንዴ አምራች ሀገር ናት።

በተጨማሪ ዓለማችን ግማሹን የሱፍ አበባ እና ከዚህ ሰብል የሚገኙት ዘይትና ሌሎች ምርቶችን የምታገኘው በአሁን ሰዓት ጦርነት ላይ ካሉት 2ቱ ሀገራት ነው።

ዩክሬን በበቆሎ ምርቷም በዓለማችን የምትታወቅ ሀገር ናት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ወጣት ናዝራዊት...🔝 የናዝራዊት አበራ ታላቅ ወንድም #ያይራድ_አበራ እናታቸው በፍፁም ሰላም እና ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጿል። ናዝራዊት ቻይና #ጉዋንዡ ከተማ እንደምትገኝ፣ የኢትዮጲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠበቃ ቀጥሮ እየተከራከራከሩ እንደሆነ ገልጾ ጉዳዩም መልካም ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል። የፍርድቤት ውጤት ክትትል ላይ ነን #በፀሎት እርዱን ሲልም ጠይቋል። በፌስቡክ ላይ የሚሰራጨው ወሬ ከእውነት…
#ተፈርዶባታል

ናዝራዊት አበራ በቻይና ሀገር ያለአግባብ ከዕፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ እንድትከሰስ እና እንድትታሰር ያደረገቻት ጓደኛዋ ስምረት ካህሳይ አንተሀቡ ላይ የቅጣት ዉሳኔ ተላልፎባታል።

ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የካቲት 25/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው።

ስምረት በ15 ዓመት እስራትና በ1 መቶ ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት እንድትቀጣ ነው የተወሰነው።

ስምረት ካህሳይ በአሁን ሰዓት #ተሰውራ እንደምትገኝ የተገለፀ ሲሆን ፍ/ቤት የኢሚግሬሽን ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጄንሲ ወደ ውጭ ሀገር ስትወጣ ወይም ሀገር ውስጥ ስትገባ ተከታትሎ በመድረስ ለፌደራል ፖሊስ አሳልፎ እንዲሰጥና የፌደራል ፖሊስ ተከሳሿን አፈላልጎ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የፍትህ ሚኒስቴር ተከሳሽ ስምረት ያለችበትን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ከፍትህ ጎን በመቆም ለፌዴራል ፖሊስ ጥቆማ እንዲያደርግ አሳስቧል።

ናዝናዊት ላይ የሆነው ምንድነው ?

ጓደኛዋ ስምረት ህዳር 2011 ወደ ሀገር ያስገባችውን 5 በሻምፖ እቃ የታሸገ ኮኬን ዕፅ ለናዝራዊት ወደ ቻይና አብረን እንሂድ ብላ በማግባባት ቪዛ እና የአየር ትኬት ካስጨረሰች በኋላ ታህሳስ 11/2011ዓ.ም ለናዝራዊት አበራ የሂውማን ሄር ማጠቢያ ነው ቻይና ውሰጅልኝ ብላ ከላከቻት በኋላ እሷ የአባቷን ሞት ምክንያት በማድረግ ትቀራለች፡፡

ናዝራዊት ቻይና ደርሳ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገባት ፍተሻ የያዘችው 5 ሻምፖ መሰል 5 ኪ.ግ የሚመዝን የኮኬን ዕፅ መሆኑ ተደርሶበት ለእስር ተዳርጋለች።

በዚህም ነው ስምረት ክስ ተመስርቶባት ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ በ15 ዓመት እስራትና በ1 መቶ ሺ ብር ገንዘብ ቅጣት እንድትቀጣ የተወሰነው።

ያንብቡ፦ telegra.ph/JM-03-09

ፎቶው ፦ የናዝራዊት

@tikvahethiopia
NATO ሩስያ ላይ ዛተ።

የNATO ዋና ፀሀፊው ጄንስ ስቶልተንበርግ ፤ የጥምረቱ ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ በሚያቀርቡበት መስመር ላይ ሩስያ ጥቃት እንዳትፈፅም አጥብቀው አስጠንቅቀዋል።

ሩስያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎች ድጋፍ በሚቀርብበት መስመር ላይ ጥቃት ከሰነዘረች ጦርነቱ በአደገኛ ሁኔታ እንደሚባባስ አስገንዝበዋል።

ስቶልተንበርግ ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጡት እሳቸው ፣ የካንዳ ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ ፣ የስፔን እና የላትቪያ መሪዎች ከላትቪያ ዋና ከተማ ሪጋ ወጣ ብሎ በሚገኘው " አዳዚ " የNATO የጦር ሰፈር ጉብኝት ካደረጉ በኃላ ለCBC በሰጡት ቃለምልልስ ነው።

ጄንስ ስቶልተንበርግ የጥምረቱ ሀገራት ዩክሬን እራሷን እንድትከላከል እየረዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

"ሩሲያ ወራሪ ነች፤ ዩክሬን ደግሞ እራሷን እየተከላከለች ነው " ያሉት ዋና ፀሀፊው " በየትኛውም የNATO ሀገር ፣ የNATO ግዛት ላይ ምንም ዓይነት ጥቃት ቢፈፀም አንቀጽ 5 ወደ ተግባር ይገባል " ብለዋል።

ይህ " አንቀጽ 5 " በNATO የመመሰረቻ ውል ውስጥ ራስን የመከላከል አንቀጽ ሲሆን በአንድ አባል ሀገር ላይ የሚፈጸም ጥቃት በ30ውም አባል ሀገራት ላይ የተፈፀመ ጥቃት ተደርጎ ነው የሚወሰደው።

ሩሲያ ከቀናት በፊት ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ ሚያደርጉ የምዕራባውያን ሀገራት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቃ ይህን ማድረግ ካልቻሉ ግን ዓለም አቀፋዊ ውድመት ይከሰታል ስትል ዝታ ነበር።

@tikvahethiopia
#EahiExpress

ፈጣን ፣ ከሁሉም አይነት የንግድ እንቅስቃሴ ጋር የሚሄድ እና ተአማኒነት ያለው መልዕክት የማድረስ አገልግሎት እንሰጣለን።

ለበለጠ መረጃ፦ በ670 ወይም 0945080808 ይደውሉ ወይም www.eshiexpress.com ይጎብኙ

ሶሻል ሚዲያ፦ Telegram: https://t.iss.one/EshiExpress Facebook: https://www.facebook.com/eshiexpress LinkedIn: https://www.linkedin.com/eshi-express
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምግብ ዘይት ጉዳይ አስተያየት ሰጥተው ነበር ?

በኢትዮጵያ ባለው የዘይት እጥረትና የዋጋ ውድነት ምክንያት ነዋሪዎች ክፉኛ ተማረዋል። በዚህም አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እንዲፈለግና ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ከምግብ ዘይት ውድነትና መጥፋት ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለጉዳዩ ዜጎች ብዙ እያሉ ነው። የዘይት መጥፋቱን፣ ህዝቡን እያማረረ ያለውን የኑሮ ውድነት መቀለጃ ያደረጉ አንዳንድ ሰዎችም አልጠፉም።

ከምግብ ዘይት ጋር ተያይዞ ግን የሀገሪቱ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል የተባለው ንግግር በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በብዛት ተሰራጭቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ የእርሻ ቦታ ላይ ሆነው ለምግብነት የሚውል ቦለቄ እያሳዩ "...እኛ በምግብ ራሳችንን አልቻልንም እንላለን ግን ደግሞ #ዘይቱን፣ በርካታ ሽንኩርት፣ ቅቤ ጨማምረን የመመገብ ስርዓታችን በጤናችን ብቻ ሳይሆን ዋጋን ከፍ አድርጎታል።...1 ኪሎ ይሄን ገዝቶ ሶስት አራት ሰው እራት ሊያበላ ይችላል ፤ ለጤናውም ጥሩ ነው ውሃ ብቻ ይበቃዋል" እያሉ ሲናገሩ ይደመጣል።

ይኸው ንግግር ነው ለሰሞኑ የዘይት ዋጋ ውድነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝቡ ተናግሩ እየተባለ እየተሰራጨ የሚገኘው።

ነገር ግን ይህ ንግግርና ቪድዮ ከዛሬ 4 ወር በፊት የተሰራጨ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ሆነ #በአርሲ_ዞን የመስክ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የተናገሩት ነው።

በዚህ ጉብኝታቸው ወቅት በአርሶ አደሮች የለማውን የ #ቦለቄ ምርት ከጎበኙ በኃላ ለሚዲያዎች የሰጡት አስተያየት አሁን ላይ ከምግብ ዘይት ጋር ተያይዞ ጠቅለይ ሚኒስትሩ ለህዝቡ የተናገሩት መልዕክት ተብሎ እየተሰራጨ ነው።

የዘይት ጉዳይ ግን ህዝብን ማማረሩን የቀጠለ ሲሆን መፍትሄ ይፈለግ ዘንድ ጥሪ እየቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
" ለተጎጂዎች የሚሆን ገንዘብ ማግኘት አልቻልኩም " - ተመድ

በአፍሪካ ቀንድ ለተከሰተው አስከፊው ድርቅ ለተጋለጡ ህዝቦች መርጃ የሚሆን ገንዘብ ማግኘት እንዳልቻለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) አስታውቋል።

ተመድ 🇺🇳 ከሳምንታት በፊት ፦

በኢትዮጵያ 🇪🇹
በሶማሊያ 🇸🇴
በኬንያ 🇰🇪 ለተከሰተው ድርቅ 13 ሚሊዮን ህዝብ ለከፋ ችግር መጋለጡን አስታውቆ ነበር ለዚህም መረጃ እንዲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የገንዘብ እርዳታ እንዲያደርግ ተማፅኖ ነበር።

ነገር ግን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዩክሬን ጦርነት ላይ ሙሉ ትኩረቱን ስላደረገ ላቀረበው ጥያቄ ተገቢ መልስ እንዳላገኘ ተመድ ትላንት አስታውቋል።

በተለይ በጎረቤታችን ሶማሊያ ለረሃብ ለተጋለጠው 4.5 ሚሊዮን ህዝብ መርጃ እንዲሆን ከተጠየቀው 1.46 ሚሊዮን ዶላር እስካሁን ማግኘት የቻለው 3 በመቶ ብቻ መሆኑን መግለፁን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ከዚህ ቀደም በዩክሬኑ ጦርነት ምክንያት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፊቱን ወደዩክሬን ስለሚያዞር በድርቅ ፣ በጦርነት ክፉኛ የተጎዱ እንደኢትዮጵያ ፣ ሶማሊያ ፣ ኬንያ ያሉ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ሊያሳድር እንደሚችል ሲነገር ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ #ሩሲያን በማውገዝ እና ወታደሮቿን ከዩክሬን እንድታስወጣ በቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ዛሬ ድምፅ ሠጠ። በዚህም ከ193 ሀገራት መካከል 141 ሀገራት ድጋፍ ሲሰጡ ፣ 5 ሀገራት ውሳኔ ሀሳቡን ተቃውመዋል፣ 35 ሀገራት ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል። #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ጨምሮ 13 ሀገራት በድምፅ አሰጣጡ ላይ ሙሉ በሙሉ አልተሳተፉም። የውሳኔ ሀሳቡን የተቃወሙ…
" ... ኢትዮጵያ ወንበሩን ባዶ በማድረግ ስብሰባውን ማለፏ በበሳል ዲፕሎማሲ የተደረገ ውሳኔ ነው " - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሩሲያ - ዩክሬን ቀውስ ላይ በመከረው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ወንበሯን ባዶ በማድረግ ስብሰባውን ማለፏ በበሳል የዲፕሎማሲ ውሳኔ የተደረገ ነው አለ።

ኢትዮጵያ በዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ዙሪያ በተመድ ጠቅላላይ ጉባኤ ላይ ሩስያን በማውገዝ ወታደሮቿንም እንድታስወጣ በሚል በቀረበው የውሣኔ ሃሳብ ላይ ሙሉ በሙሉ ድምፅ ሳትሰጥ መውጣቷ ይታወሳል።

በዚሁ ጉዳይ ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ዲና የሩሲያ – ዩክሬን ግጭት ከሌላው የሚለየው ከግጭቱ ጀርባ ያሉ ሃይሎች ማንነት ነው ያሉ ሲሆን በግጭት ውስጥ ያሉት አካላት #ኒውክሌር የታጠቁ ናቸው ብለዋል።

" በዚህ ጦርነት አሸናፊ የሚሆን የለም " ያሉት ቃል አቀባዩ ሁለቱም አካላት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ኢትዮጵያ መጠየቋን አስታውሰዋል።

አምባሳደር ዲና በሁለቱ ወገኖች ቀውስ ላይ በመከረው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ወንበሩን ባዶ በማድረግ ስብሰባውን ማለፏ በበሳል ዲፕሎማሲ የተደረገ ውሳኔ ነው ሲሉ መግለፃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia