TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ችሎት

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የታሰሩበት 33 አባላቱ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን አስታወቀ።

ከ33ቱ መካከል ሁለቱ ለለ14 ቀን ሲቀጠሩ ቀሪዎቹ 31 አባላቱ ለሀሙስ መጋቢት 1 ተቀጥረዋል ብሏል።

ተከሳሾቹ ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡት ለሁለት ቡድን ተከፍለው ሲሆን 31ዱ እስረኞች ከልደታ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው የቀረቡት።

ሁለቱ ደግሞ ጊዮርጊስ የሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው የቀረቡት።

ፖሊስ ለፍርድ ቤት ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በአድዋ እና ካራማራ ክብረ በዓላት ብጥብጥ እና ሁከት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው ነው ብሏል።

ያንብቡ ፦ telegra.ph/Balderas-03-07

@tikvahethiopia
#AddisAbaba📍

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሶስት መጋዘን አለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀ።

አስተዳዳደሩ በዛሬው እለት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ " ሙሉጌታ መናፈሻ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በህብረተሰቡ ጥቆማ በሶስት መጋዘን በርካታ መጠን ያለው የምግብ ዘይት ክምችት በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል

በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት በፎቶ አስደግፎ ለህዝብ አሰራጭቷል።

የተያዘው የምግብ ዘይት በመጠን ምን ያህል እንደሆነ ባይገለፅም በርካታ መጠን ነው ያለው ተብሏል። ነገር ግን የምግብ ዘይቱን ማን እንዳከማቸው ፤ ድርጅት ከሆነም የትኛው ድርጅት ይህን ድርጊት እንደፈፀመ ፤ በሶስቱም መጋዘን የተገኘው ክምችት የአንድ ድርጅት ወይ ግለሰብ ነው አይደለም ስለሚለው የተብራራ ነገር የለም።

የምግብ ዘይቱ በቁጥጥር ስር የዋለው አጠቃላይ የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ሰው ሰራሽ የዋጋ ውድነት በመፍጠርና ምርቶችን በመደበቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ህገወጥ ደላሎችንና ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር በተቋቋመ ግብረ ሃይል ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሆኑ ተገልጿል።

አሁንም የአ/አ ነዋሪዎች ጥቆማ በመስጠት ርብርብ እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሩ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#Russia

ሩስያ በሀገሯ ፣ በኩባንያዎችና በህዝቧ ላይ " ወዳጃዊ ያልሆኑ " ድርጊቶችን የፈፀሙና እርምጃ የወሰዱ / ወዳጅ ያልሆኑ ሀገራትን እና ግዛቶችን ዝርዝር በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጋለች።

እነዚህም ፦

🇺🇦 ዩክሬን
🇺🇸 አሜሪካ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇪🇺 የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት
🇦🇺 አውስትራሊያ
🇨🇦 ካናዳ
🇮🇸 አይስላንድ
🇯🇵 ጃፓን
🇲🇨 ሞናኮ
🇲🇪 ሞንቴኔግሮ
🇳🇿 ኒውዚላንድ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇹🇼 ታይዋን (ቻይና እንደ ተገንጣይ ግዛቷ የምትቆጥራት ሲሆን እሷ ግን ነፃ እና ሉዓላዊ ሀገር ነኝ በሚል እራሷን ችላ ነው የምትተዳደረው)
🇸🇲 ሳን ማሪኖ
🇸🇬 ሲንጋፖር
🇰🇷 ደቡብ ኮሪያ
🇨🇭 ስዊዘርላንድ
🇦🇱 አልባንያ
🇦🇩 አንዶራ
🇱🇮 ሌይቼንስቴይን
🇫🇲 ማክሮኔዢያ
🇲🇰 ሰሜን ሜቄዶንያ ናቸው።

ከላይ የተጠቀሱት ሀገራት እንዲሁም ግዛቶች በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ጥለዋል ወይም በሚጣለው ማዕቀብ ላይ ተቀላቅለዋል የተባሉ ናቸው።

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

ድማሚት ፈንድቶ የ7 ህፃናት ህይወት ጠፋ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ግራር ውኃ በተባለ ቀበሌ ለመንገድ አገልግሎት የተቀመጠ ድማሚት ፈንድቶ የ7 ህጻናት ህይወት ማለፉን አሚኮ የወረዳውን ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

አደጋው የተከሰተው በቀን 27/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 11:30 ገደማ ነው።

አደጋው የተከሰተው በሱር ኮንስትራክሽን አማካኝነት ሲሰራ በነበር የመንገድ ፕሮጀክት የቁሳቁስ ካምፕ ላይ ሲሆን በዚህ ውስጥ የአካባቢው ህጻናት ለጭዋታ ሲገቡና ሲወጡ እንደነበር ፓሊስ ገልጿል።

ፖሊስ ኅብረተሰቡ ህጻናት ወደ ካምፑ እንዳይገቡና ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#Update

መንግስት 40 ሚሊየን ሊትር ዘይት በአጭር ጊዜ ወደ ሀገር ቤት አስገባለሁ አለ።

በዛሬው ዕለት የንግድ እና ቃጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ 40 ሚሊየን ሊትር ዘይት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር ቤት ይገባል ብሏል።

ሚኒስቴሩ ከሰሞኑን በዘይት ምርቶች ላይ የተስተዋለው የዋጋ ጭማሪ የአለም አቀፍ ገበያው ላይ በመጣው ለውጥ ምክንያት ነው ብሏል።

በዚህም ለውጥ ምክንያት የተፈጠረውን የምርት እጥረት መነሻ በማድረግ በንግድ ማህበረሰብ ዘንድ የተፈጠረው ውዥንብር የዋጋ ጭማሪውን አባብሶታል ሲልም ገልጿል።

የአቅርቦት እጥረቱን ለማቃለል በአጭር ጊዜ መፍትሄ 40 ሚሊየን ሊትር ዘይት አስገባለሁኝ ብሏል።

በረዥም ጊዜ መፍትሄነት የምርት አቅርቦቱንና ፍላጎቱን ማጣጣም እንዲቻል የገበያ ሁኔታውን የሚያጠና ቡድን መዋቀሩን ሚኒስቴሩ መግለፁን ኤፍ .ቢ .ሲ . ዘግቧል

@tikvahethiopia
#Update

ሩስያ ያስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች ከተሟሉ በዩክሬን የምታካሂደውን ወታደራዊ ኦፕሬሽን #ወዲያው እንደምታቆም አስታወቀች።

ሩስያ ያስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች ፦

1ኛ. ወታደራዊ እርምጃ እንድታቆም።

2ኛ. ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ ህገመንግስቷን እንድትቀይር (እንደ #NATO አይነት ጥምረት ውስጥ እንዳትገባ እንድታረጋግጥ)

3ኛ. ክሬሚያን እንደ ሩሲያ ግዛት እንድትቀበል።

4ኛ. የዶንቴስክ ​​እና የሉሀንስክ ተገንጣይ ሪፐብሊኮችን እንደ ነፃ ሀገር እንድትቀበል የሚሉት ናቸው።

እነዚህ ከተሟሉ ሩስያ ዩክሬን ውስጥ ምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ ወዲያውኑ እንደምታቆም ገልፃለች።

የክሬምሊን ቃልአቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በስልክ ለሮይተርስ በሰጡት ቃል ፤ ዩክሬን ቅድመ ሁኔታዎቹን እንደምታውቅ እና ተፈፃሚ የሚሆኑ ከሆነ የወታደራዊ ዘመቻው ወዲያውኑ እንደሚቆም እንደተነገራት ገልፀዋል።

ከዩክሬን ወገን በኩል ወዲያው የተሰጠ ምላሽ የለም።

በሌላ በኩል ፥ የሩስያ እና ዩክሬን ሶስተኛው ዙር ድርድር ዛሬ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba📍

በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረውን የምግብ ዘይት እጥረት ለመፍታት 6.6 ሚሊዮን ሊትር ዘይት እየተሰራጨ መሆኑን እና ህብረተሰቡ ከነገ ጀምሮ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ማግኘት እንደሚችል ተገልጿል።

ይህንን የገለፀው የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ነው።

ለከተማው የተሰራጨው ምግብ ዘይት ከፊቤላ 3.1 ሚሊዮን ሊትር የሚጠጋ ፤ ከሸሙ ፋብሪካ 1.5 ሚሊዮን ሊትር የሚሆን ፤ ከንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን 2.4 ሚሊዮን ሊትር እንደሆነ ቢሮው ጠቁሟል።

በሌላ በኩል ቢሮው የዳቦ ጭማሪ ችግር ለመፍታት የሸገር ዳቦ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ እንዲያመርት እየተደረገ ነው ያለ ሲሆን በእያንዳንዱ ዳቦ ላይ 1 ብር ከ15 ሳንቲም ድጎማ በማድረግ በ2 ብር ከ10 ሳንቲ ለተጠቃሚ እየቀረበ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba📍

የምግብ ዘይት በ #መፀዳጃ_ቤት ውስጥ ተከማችቶ ተገኘ።

በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 03 ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ክ/ከተማው በ11 ሱቆች ላይ ተደረገ ባለው ፍተሻ 442 ሊትር ዘይት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን አሳውቋል።

ፍተሻ የተደረገው በወቅታዊ የዋጋ ንረት ምክንያት ካሉ 6 ቀጠናዎች በ3ቱ ቀጠናዎች ላይ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል።

ክ/ከተማው በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት ባልተገባ ቦታ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ተደብቆ መገኘቱን የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ድርጊት የሚፈፅሙትን "ሌባን ሌባ " ሲል እንዲያጋልጥ ጥሪ አቀርቧል።

በአግባቡ በስራቸው ላይ የሚገኙ ነጋዴዎች አሁን በያዙት ልክ ዘይትን ወደ ፊት በማምጣት መሸጥ ይኖረባቸዋል የተባለ ሲሆን ህገወጥ ስራዎችን በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፍቃድ መሰረዝን ጨምሮ ጠበቅ ያሉ እርምጃዎች ይወሰዳል ሲል ክፍለ ከተማው አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #USA

አሜሪካ በአጠቃላይ 250 ሜትሪክ ቶን (MT) የሚሆን ሰብአዊ አቅርቦት ለዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የኢትዮጵያ ጽ/ቤት እና ለኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን ልትለግስ መሆኑ ተገለፀ።

ይህን የገለፀው በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ነው።

የእርዳታ አቅርቦቱ አሜሪካ በአማራ እና አፋር ክልሎች በቀጠለው ግጭት ለተጎዱ በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ ድጋፍ የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑን ተነግሯል።

አምባሳደር ትሬሲ ኤ ጃኮብሰን የአደጋ ጊዜ አቅርቦቱን ለIOM የኢትዮጵያ ቢሮ ተጠባባቂ ኃላፊ ጂያን ዣኦ እና ለኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን የምክትል ኮሚሽነር ነሲቡ ሁሴን ነገ በሚከናወን የርክክብ ሥነ ስርዓት እንደሚያስረክቡ ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
የዳቦ ጭማሪ ግብፃውያንን አስቆጥቷል።

ዩክሬን እና ሩስያ የገቡበት ጦርነት ጦስ ለዓለም እየተረፈ ነው። የነዳጅ ፣ የስንዴ ዋጋ በዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ይገኛል።

የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ከፍተኛ ስጋት ከደቀነባቸው የአፍሪካ ሀገራት አንዷ ደግሞ ግብፅ ናት።

በግብፅ የዳቦ ዋጋ በ50% ጨምሯል። የግብፅ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት የዱቄት ዋጋ በቶን 7,000 የግብፅ ፓውንድ (445 ዶላር) ከነበረበት ወደ 11,000 የግብፅ ፓውንድ (700 ዶላር) ከፍ ብሏል።

ይህ ጭማሪ ዜጎችን አስቆጥቷል።

የዱቄት አቅራቢዎችን እና የዳቦ መጋገሪያ ባለቤቶች የዱቄት ጭማሪው በዳቦ እንዲሁም በሌሎች ውጤቶች ላይ ከ25-50% ጭማሪ እንዲኖር ማድረጉን ተናግረዋል።

አንዳንድ ነዋሪዎች ደግሞ በግብፅ እጅግ የተለመዱ ባህላዊ ሳንድዊችዎች 25% የዋጋ ጭማሪ እንደታየባቸው ገልፀዋል።

70% የሚሆነው የግብፅ የስንዴ አቅርቦት የሚገባው ከሩሲያ እና ከዩክሬን ሲሆን ተባብሶ የቀጠለው ጦርነት በሀገሪቱ ላይ ሌላ መዘዝ ይዞ እንዳይመጣ ክፉኛ ስጋትን ደቅኗል።

@tikvahethiopia