TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ ምርቶችን የሚያመጡ ነጋዴዎችን የሚቆጣጠር አዲስ መመርያ ማዘጋጀቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ እየታየ ባለው ከፍተኛ የዋጋ ንረት ሳቢያ እንደ ስኳር፣ የምግብ ዘይት፣ስንዴ፣ፓስታና ማካሮኒ የመሳሰሉ መሠረታዊ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ባለፈው ዓመት መፈቀዱ ይታወሳል።

ነገር ግን ነጋዴዎች የተሰጠውን ዕድል በሕገወጥ መንገድ እየተጠቀሙበት በመሆኑ አዲስ መመርያ ማዘጋጀት ማስፈለጉን ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚስቴሩ ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የተፈቀዱ የፍጆታ ምርቶች ታሪፍ የማይከፈልባቸው በመሆናቸው ኅብረተሰቡ በቅናሽ ዋጋ እንዲገዛ ለማድረግና የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለመቀነስ ቢሆንም አስመጪዎች ግን በከፍተኛ ዋጋ እየሸጡ መሆናቸውን ማወቅ ተችሏል ብሏል።

ከቀረጥ ነፃ ዕድልን የሚጠቀሙ አስመጪዎች በተጠበቀው መሠረት እየሠሩ እንዳልሆነ የገለፀው ሚኒስቴሩ ምርቶቹን ያለ ደረሰኝና በከፍተኛ ዋጋ እየሸጡ እንደሆነ ገልጿል።

ይህን መሠረት በማድረግ አስመጪዎችን የሚቆጣጠር መመርያ ተዘጋጅቷል።

አዲሱ መመርያ አስመጪዎች ያስመጡትን የምርት መጠን፣ ዓይነትና ያስመጡበትን ጊዜ ጉምሩክ ኮሚሽን መዝግቦ ለንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ለክልል ንግድ ቢሮዎች የሚያስተላልፍበትን አሠራር ይዟል።

ጉምሩክ ኮሚሽን በሚሰጠው መረጃ መሠረት የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ንግድ ቢሮዎች ምርቱ ለማን እንደተከፋፈለ፣ በምን ያህል ዋጋ እንደተሸጠና በሕጋዊ መንገድ መሸጡን ያረጋግጣሉ።

ይህ አዲስ መመሪያ ከ2 ሳምንት በኋላ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይጠበቃል። አስመጪዎቹ ከቀረጥ ነፃ የገቡ ምርቶችን ለኅብረት ሥራ ማኅበራትና ለሸማቾች ማኅበራት ቅድሚያ ሰጥተው እንዲያቀርቡ ያዛል።

ምንጭ፦ሪፖርተር (telegra.ph/RE-03-06-2)

@tikvahethiopia
" የምግብ ዘይት የለም ይሉናል፤ አለ የሚባልባት ደግሞ በከፍተኛ ዋጋ ነው የሚሸጠው "

በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የምግብ ዘይት አለመኖር ቢኖርም ደግሞ ዋጋው የሚቀመስ እንዳልሆነ ገልፀዋል።

ለአብነት ከአዲስ አበባ ቲክቫህ አባላት በመጣው መልዕክት በተለያዩ አካባቢዎች ባለ5 ሊትር የምግብ ዘይት ካለ እንኳን ከ850-950 ብር ድረስ እንደሚሸጥ ጠቁመዋል። ባለ አንድ ሊትር ከ165-180 ብር ድረስ እንደሚሸጥ ገልፀዋል።

በተለያዩ ክልል ከተሞች ያሉ የቲክቫህ አባላት የምግብ ዘይት የዋጋ ጭማሪ እንደተደረገበት ጠቁመው 5 ሊትሩ የለም እንደሚባሉ ካለም ከ750-900 ብር ድረስ እንደሚሸጥ ገልፀዋል።

በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ ዘይት ተወደደ የሚለውን ሲሰሙ ያላቸውን ዘይት የመደበቅ ድርጊት የሚፈፅሙም አካላት ሊኖሩ ስለሚችሉና ክትትል እንደሚያስፈልገው ጠቁመዋል።

መልዕክታቸውን የላኩ ነዋሪዎች መንግስት ችግሩን መርምሮ እጅግ በጣም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥና ገበያውን እንዲያረጋጋ ጠይቀዋል።

በሌላ ተያያዥ ጉዳይ፦

የባህር ዳር ከተማ በበላየነህ ክንዴ ለከተማው የሚቀርበው የፊቤላ ዘይት በወቅቱና በበቂ መጠን እየቀረበ ባለመሆኑ ከክልሉ ንግድ ቢሮ ጋር በመነጋገር 883,000 ሊትር ፓልም ዘይት ከውጭ ተገዝቶ በ " አለ በጅምላ " በኩል መቅረቡን አሳውቋል።

በነገው ዕለት በሁሉም ክፍለ ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት ያካሄዳል ብሏል።

በአ/አ ከተማ ደግሞ የምግብ ዘይት በድብቅ ይዘው ለማሸሽ የሞከሩ ህገወጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከተማው አሳውቋል።

መንግስትንና ህብረተሰቡን ለማጋጨትና አርቴፊሻል የዋጋ ንረትን በመፍጠር ህዝቡን ለማስጨነቅ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ሃይሎች በመኖራቸው ህብረተሰቡ ጥቆማ ይስጠኝ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የምግብ ዘይት የለም ይሉናል፤ አለ የሚባልባት ደግሞ በከፍተኛ ዋጋ ነው የሚሸጠው " በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የምግብ ዘይት አለመኖር ቢኖርም ደግሞ ዋጋው የሚቀመስ እንዳልሆነ ገልፀዋል። ለአብነት ከአዲስ አበባ ቲክቫህ አባላት በመጣው መልዕክት በተለያዩ አካባቢዎች ባለ5 ሊትር የምግብ ዘይት ካለ እንኳን ከ850-950 ብር ድረስ እንደሚሸጥ ጠቁመዋል። ባለ አንድ ሊትር…
#BahirDar📍

በባህር ዳር የምግብ ዘይት መሸጫ ዋጋ ይፋ ሆነ።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ንግድ መምሪያ የምግብ ዘይት መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።

ከነገ ከ28/06/2014 ዓ.ም ጀምሮ መሰራጨት የሚጀምረው ፓልም ዘይት መግዣና መሸጫ ዋጋ መረጃ ይህንን ይመስላል ፦

ቸርቻሪዎች / ሸማቾች ህ/ስ/ማ ከአለ በጅምላ የሚገዙበት የጅምላ ዋጋ ፦

1. ባለ 20 ሊትር 👉 1575.6 ብር ፣
2. ባለ 5 ሊትር 👉 408.6 ብር፣
3. ባለ 3 ሊትር 👉 251.10 ብር ሲሆን፣

ቸርቻሪዎች / ሸማቾች ህ/ስ/ማ #ለተጠቃሚው_ማህበረሰብ የሚያሰራጩበት ዋጋ ደግሞ ፦

1. ባለ 20 ሊትር 👉 1641.80 ብር ፣
2. ባለ 5 ሊትር 👉 425.80 ብር፣
3. ባለ 3 ሊትር 👉 261.70 ብር መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia
ሳፋየር አዲስ ሆቴል ተከፍቷል።

"በወቅታዊ ጉዳዮች" ምክንያት በሚል ለ3 ወር ተዘግቶ የነበረው በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ከቦሌ መድሃኒዓለም ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው ባለ አራት ኮከቡ " ሳፋየር አዲስ ሆቴል " ተከፈተ።

ሆቴሉ ባለፈው ማክሰኞ መከፈቱን ሪፖርተር ያስነበበ ሲሆን ሶስት ወር ተዘግቶ ከቆየ በኃላ “ምንም ችግር የለበትም” በመባሉ መከፈቱ ነው የተነገረው።

ሳፋየር አዲስ ህዳር 24 ቀን 2014 ዓ/ም ከመታሸጉ በፊት ከ3 ጊዜ በላይ በፀጥታ ኃይሎች ተፈትሾ የነበረ ሲሆን ህዳር 21 ላይ የመጨረሻ ፍተሻ ተደርጎበት በሁለተኛው ቀን ታሽጓል።

የሆቴሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ወርቁ፣ ሆቴሉ ሲዘጋም ሆነ ሲከፈት ምንም ዓይነት ገለጻ ለሆቴሉ አስተዳደር እንዳልተደረገ እና ሆቴሉ በተዘጋባቸው ያለፉት ሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ክስ እንዳልተመሠረተ አስታውቀዋል፡፡

በሆቴሉ ውስጥ በተደረጉት ሁሉም ፍተሻዎች ምንም ነገር አለመገኘቱንና ይኼንን የሚገልጽ ፊርማ ፍተሻውን ያካሄዱ አካላትና የሆቴሉ አስተደዳር መፈራረማቸውን ያስታውሰዋል። በዚህም ምክንያት " በቶሎ ይከፈታል " በሚል ጉዳዩን ሲከታተሉ መቆየታቸውን አስረድተዋል፡፡

ነገር ግን ሆቴሉ ታሽጎ ከቆየ 3 ወር በኃላ ሊከፈት ችሏል።

የወረዳው ንግድና ኢንደስትሪ ልማት ጽሕፈት ቤት ሆቴሉን የከፈተው የከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ በክፍለ ከተማው በኩል በደብዳቤ ስለደረሰው መሆኑን ለሪፖርተር ገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ከወራት በፊት በተለያዩ ምክንያቶች እንዲዘጉ መደረጋቸው ይታወሳል።

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ከተዘጉት ሆቴሎች መካከል ካሌብና ሀርመኒ ሆቴሎች ይገኙበታል፡፡

ተጨማሪ : telegra.ph/Reporter-03-06

@tikvahethiopia
#Dessise #Kombolcha

በዛሬው ዕለት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የ #ደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሆነው ሲሾሙ አቶ መሀመድ አሚን ደግሞ የ #ኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።

የደሴ ከተማ አሰተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 9ኛ ዓመት 31ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝን የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

በሌላ በኩል የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ መሀመድ አሚን ኮምቦልቻ ከተማን በከንቲባነት እንዲመሩ ሾሟቸዋል።

@tikvahethiopia
#Kombolcha📍

የኮምቦልቻ ከተማ ከሶስት ቀን ቡኃላ የምግብ ዘይት ስርጭት ይከናወናል ብሏል።

የከተማው ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት ከ3 ቀን በኃላ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ቀበሌዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ፅ/ቤቱ ከሚያደርገው የቁጥጥር ሥራ በተጨማሪ አቅርቦቱ ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ስለሆነ ነዋሪዎች በተፈጠረው ያልተገባ የዋጋ ንረት አላስፈላጊ ወጪ እንዳያወጡ አሳስቧል፡፡

የዋጋ ንረትን ለማባባስ ከሚሰሩ ህገወጦች ጋርም ተባባሪ እንዳይሆኑም ጠይቋል።

ከነገ ሰኞ ጀምሮ በሚያደርግ ቁጥጥር ነጋዴዎች የገዙበትን ደረሰኝ እንዲያቀርቡ ካልሆነ ደግሞ አሁን የተጨመረ የዋጋ ጭማሪን ያለምንም ምክንያት ባስቸኳይ ወደ ነበረበት ዋጋ ሽያጭ እንዲመልሱ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ማህበረሰቡ ለሚደረገው ሕግ ማስከበር ሥራ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ጥሪ መቅረቡን ከኮምቦልቻ ከተማ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Ukraine

ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጋር ወዳጅ የሆኑ ሀገራት (አሜሪካ እና አጋሮቿ) ፕሬዜዳንቱ በሩሲያ ሃይሎች ቢያዙ ወይም ቢገደሉ በእሳቸው ቦታ ላይ ስለሚኖረው ‘የመተካካት ሂደት' እየተወያዩ መሆናቸውን ኒውዮርክ ታይምስ ዛሬ አስነብቧል።

አሜሪካ እና አጋሮቿ ሩስያ የሚታዘዝላትን መንግስት በኬዬቭ እንዳታስቀምጥ ስጋት አላቸው ተብሏል። ለሚቀመጠው መንግስትም እውቅና እንደማይሰጡ እና ይህም እንዳይሆን እንደሚከላከሉ ነው አቋማቸው።

ከዚህ ቀደም የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፕሬዜዳንት ቮልድሚር ዜሌስንኪ የምትመራውን ዩክሬን " የምዕራቡ ዓለም አሻንጉሊት " ሲሉ የጠሯት ሲሆን የዩክሬን ጦር ከአስተዳደራቸው ስልጣን እንዲነጥቅና እንዲቆጣጠር ጥሪ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል።

አሁንም በዩክሬን እና በሩስያ መካከል ጦርነቱ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን የዩክሬኑ ፕሬዜዳንት ህዝባቸው እንዲፋለም ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

በተጨማሪ " ዓለም ለሩስያ ሮኬቶች እና አውሮፕላኖች የአየር ቀጠናችንን የመዝጋት ኃይል አለውና ይዝጋልን ፤ የዩክሬንን ሰማይ አስተማማኝ ለማድረግም የጦር አውሮፕላኖች ያስፈልጉናል " የሚል ጥሪ እያቀረቡ ነው።

ትላንት ቭላድሚር ፒቲን በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ ክልከላ ለማድረግ የሚሞክር የትኛውም ኃይል በጦርነቱ ውስጥ ተሳትፎ እንዳደረገ እንደሚታይ እና እንዲህ ያለው እርምጃ ለአውሮፓ እና ለዓለም አስከፊ መዘዝ የሚያስከትል እንደሆነ ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም አረፉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቀድሞ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቶ ዛሬ እሁድ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን የኢኦተቤ መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" ፈርስት ሂጅራ ልዩ ፌስቲቫል "

የመጀመሪያው ስደት (first hijra) (እናንተ በሃገሬ ላይ ሹሞች (ባለመብቶች) ናችሁ!) በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የዓለማችን ዜጎች የሚያሳትፍ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል በኢትዮጵያ ለማዘጋጀት ዝግጅቶች እየተደረጉ ይገኛል።

ይህ ዓለም አቀፍ የሆነ ፌስቲቫል ሚዘጋጀው በዳራ ሚዲያና ኤቨንትስ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት እና ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጾልናል።

የመጀመሪያው ስደት የተሰኘው ይኸው ዝግጅት ዓላማ አድርጎ የተነሳው የሃገራችን ውለታ፣ የመጀመሪያው ስደት፣ ነጃሺን፣ ኢ/ያውያን ሱሐቦችና ታቢዖች ሚና በሚገባ በመዘከር ለሀገራችን ጠንካራ ሀገረ-መንግስት ግንባታ እና በዓለማቀፍ ደረጃ የሚገባን ጥቅም በክብር፣ በሃላል ቱሪዝም ፣ኢንቨስትመንትና ቢዝነስ እንዲያስገኘልን ማስቻል መሆኑ ተፈልጾልናል።

የመጀመሪያው ስደት ፌስቲቫል የወቅቱ ሁኔታ ያገናዘቡ በይዘትና በአቀራረባቸው ልዩ የሆኑ ኢንተርናሺናል ፈርስት ሂጅራ ሃላል ቱሪዝም፣ ኢንቨስትመንት እና ቢዝነስ ኤክስፖና ከሚያዚያ 19 እስከ ሚያዚያ 23 ይዘጋጃል ተብሏል።

ግንቦት 6 እና 7 ዝክረ ነጃሺ ሽልማት ፣ ዝክረ ነጃሺ ትያትር እና ፈርስት ሂጅራ የሩጫና የእርምጃ ፌስቲቫል እንደሚዘጋጅ በተጨማሪ ዲያስፖራዎችን የሚያሳትፍ ማዕድ ማጋራት ፣የደም ልገሳ እና መፅሓፍት አሰባስበን ለማረሚያ ቤቶች የመለገስ ዝግጅት እንደሚኖር ተገልጾልናል።

በፈርስት ሂጅራ የሩጫና የእርምጃ ፌስቲቫል በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶችና የወንዶች አቅጣጫ በተለያየ መስመር በማድረግ የእስልምና እምነት እሴት ባከበረ መልኩ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

(የአዘጋጆቹ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Update

ሩሲያ በዩክሬን ጊዜያዊ የተኩስ አቁም አድርጋለች።

ያወጀችው ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ለዜጎች ሰብዓዊ መተላለፊያ ለማመቻቸት ያለመ ነው ተብሏል።

በኬቭ ፣ ማሪፖል ፣ ካርኪቭ እና ሱሚ ከተሞች #ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም ተገልጿል።

@tikvahethiopia
" እኛ የእናተ ባርያ ነን ? " - ጠ/ሚ ኢምራን ካሃን

ምዕራባውያን የአፍሪካ ሀገራትንና ሌሎችንም የዓለም ሀገራት ሩስያን እንዲያወግዙ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው።

ከእነዚህ ሀገራት መካከል አንዷ ፓኪስታን ናት። በምዕራባውያኑ ፓኪስታን ሩስያን አውግዢ የሚል ጥያቄ ከቀናት በፊት ቀርቦላታል።

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራትን ጨምሮ የ22 ዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች መሪዎች እኤአ መጋቢት 1 ፓኪስታን በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን " ወረራ " የሚያወግዝ ውሳኔ ሀሳብ እንድትደግፍ በጋራ ድብዳቤ ፅፈው ነበር።

ፓኪስታን ግን በጉባኤው ገለልተኛ አቋም ይዛ ነበር የወጣችው።

ይህን ተከትሎ የፓኪስታን ጠ/ሚ ኢምራን ካን ሀገራቸው የሩስያን ድርጊት እንድታወግዝ ግፊት ለማድረግ የሞከሩትን የምዕራባውያን ልዑካንን አጥብቀው ተችተዋል።

ኢምራን ካሃን ፥ " ስለኛ ምንድነው የምታስቡት ? እኛ የእናተ ባርያ ነን ... አድርጉ ሁሉ የምትሉንን የምናደርግ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

አክለው " የአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮችን መጠየቅ እፈልጋለሁ፤ ለህንድ እንዲህ አይነት ደብዳቤ ፅፋችኃል ? " ሲሉ ሌላ ጥያቄ አቅርበዋል።

ካሃን ህንድና ፓኪስታን ለሁለት ጊዜ ጦርነት በገቡበት በካሽሚር ጉዳይ የአውሮፓ ሀገራት ህንድ ያደረገችውን ድርጊት አልገሰፁም ሲሉም ኮንነዋል።

ጠቅለይ ሚኒስትሩ ፥ ፓኪስታን በአፍጋኒስታን የነበረውን የምእራቡ ህብረትን ኔቶ ስለደገፈች ተጎድታለች ፥ ከምስጋና ይልቅ ትችት ነው የገጠማት ብለዋል።

" ከሩሲያ ጋር ወዳጆች ነን፣ ከአሜሪካም ጋር ወዳጆች ነን፤ ከቻይና እና ከአውሮፓ ጋርም ወዳጆች ነን፤ በየትኛውም ካምፕ ውስጥ አይደለንም " ያሉት ኢምራን ካሃን ፓኪስታን ገለልተኛነቷን ይዛ ትቀጥላለች የዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ከሚሞክሩት ጋር ትሰራለች ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kombolcha📍 የኮምቦልቻ ከተማ ከሶስት ቀን ቡኃላ የምግብ ዘይት ስርጭት ይከናወናል ብሏል። የከተማው ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት ከ3 ቀን በኃላ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ቀበሌዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የዘይት ስርጭት እንደሚያደርግ አስታውቋል። ፅ/ቤቱ ከሚያደርገው የቁጥጥር ሥራ በተጨማሪ አቅርቦቱ ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ስለሆነ ነዋሪዎች በተፈጠረው ያልተገባ የዋጋ ንረት አላስፈላጊ…
#Dessie📍

ደሴ ከተማን ሙሉ በሙሉ ማዳረስ የሚያስችል ከ605 ሺህ ሊትር በላይ ዘይት ከፌቤላ የዘይት ማምረቻ ኢንዱስትሪ ጋር በመተባበር በተያዘው ሳምንት ለነዋሪዎች እንደሚከፋፍል የከተማዋ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የዘይት አቅርቦቱ በ 'ሸማች ማህበር' በኩል ይቀርባል የተባለ ሲሆን በገበያው ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመከላከል የቁጥጥር ስራም እየተሰራ ነው ተብሏል። 

በከተማዋ በሸማች ማህበራት በኩል የሚቀርበው የዘይት ዋጋ ፡-

1. ባለ 3 ሊትር 👉 290 ብር ከ06 ሳንቲም

2. ባለ 5 ሊትር 👉 474 ብር ከ40 ሳንቲም

3. ባለ10 ሊትር 👉 936 ብር ከ69 ሳንቲም

4. ባለ 20 ሊትር 👉 1 ሺህ 834 ብር ከ66 ሳንቲም

5. ባለ 25 ሊትር 👉 2 ሺህ 277 ብር ከ90 ሳንቲም መሆኑ ተገልጿል፡፡

 @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ችሎት

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የታሰሩበት 33 አባላቱ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን አስታወቀ።

ከ33ቱ መካከል ሁለቱ ለለ14 ቀን ሲቀጠሩ ቀሪዎቹ 31 አባላቱ ለሀሙስ መጋቢት 1 ተቀጥረዋል ብሏል።

ተከሳሾቹ ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡት ለሁለት ቡድን ተከፍለው ሲሆን 31ዱ እስረኞች ከልደታ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው የቀረቡት።

ሁለቱ ደግሞ ጊዮርጊስ የሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው የቀረቡት።

ፖሊስ ለፍርድ ቤት ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በአድዋ እና ካራማራ ክብረ በዓላት ብጥብጥ እና ሁከት ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው ነው ብሏል።

ያንብቡ ፦ telegra.ph/Balderas-03-07

@tikvahethiopia