TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አርፈዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። የቅዱስነታቸውን ሽኝት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ተሰብስቦ በሚያስተላልፈው ውሳኔና በሚያወጣው መርሐ ግብር መሰረት የሚፈጸም መሆኑን የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል። አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ…
#USA

አሜሪካ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማትን ሀዘን ገለፀች።

አሜሪካ 🇺🇸 በአዲስ አበባ ባለው ኤምባሲዋ አማካኝነት በ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማትን ሀዘን ገልፃለች።

ሀገሪቱ በሀዘን ላይ ላሉ ሁሉ መፅናናትን ተመኝታለች።

@tikvahethiopia
#Russia

የሩስያ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ተቆጣጣሪ ቡድን የዩክሬን ግጭትን አስመልክቶ ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጩ ነው ባላቸው የብሪቲሽ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (#ቢቢሲ) እና የራዲዮ ሊብሪቲ ድረ-ገጾች ላይ ገደብ ጥሏል።

ሩስያ የምዕራባውያን ሚዲያዎች ፤ በውጭ ሀገራት ጦርነት ለምሳሌ እንደ #ኢራቅ ባሉ እና በሙስና እጃቸው ያለባቸው የገዛ የራሳቸው ሀገራት መሪዎች ተጠያቂ ማድረግ ሳይችሉ በከፊል እና ብዙ ጊዜ ፀረ-ሩሲያ የሆነ አመለካከትን ለዓለም ያስተላልፋሉ ስትል በተደጋጋሚ ስትወቅስ ቆይታለች።

ከዩክሬን ጋር በተያያዘ የሩስያ ባለስልጣናት "ወረራ" ሚለውን ቃል የማይጠቀሙ ሲሆን የምዕራባውያን ሚዲያዎች ዩክሬን ውስጥ በሩሲያኛ ተናጋሪ ህዝቦች ላይ የሚፈፀመውን " የዘር ማጥፋት ወንጀል " ሪፖርት እንደማያደርጉ ይናገራሉ።

ሩስያ ምዕራባውያን ሚዲያዎች ላይ ገደብ ከመጣሏ በፊት ምዕራባውያኑም በሩስያ ሚዲያዎች ላይ የተለያዩ ገደቦችን ጥለዋል።

ለአብነት ዩናይትድ ኪንግደም በሩስያ የሚደገፈው " ራሺያ ቱዴይ " ቴሌቪዥን ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ እንዳይታይ አግዳዋለች።

@tikvahethiopia
" እንቅጠራችሁ እና ዩክሬን ሄዳችሁ ከሩስያ ጋር ተዋጉልን " - የዩክሬን ኤምባሲ

ሴኔጋል ዳካር ከተማ ሚገኘው የዩክሬን ኢምባሲ በጎ ፈቃደኛ ሴኔጋላዊያን እና ሌሎችም የውጭ ሀገራት ዜጎች ወደ ዩክሬን አምርተው ከሩሲያ ጋር እየተደረገ ባለው ጦርነት እንዲዋጉ የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል።

ይህ ማስታወቂያ ሴኔጋልን አበሳጭቷል።

የሴኔጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዳካር የዩክሬን አምባሳደር ዩሪ ፒቮቫሮቭ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠርቷል።

ሚኒስቴሩ የኢምባሲው ድርጊት የሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ዙሪያ የወጣው የቬና ድንጋጌዎችን የሚጥስ ነው ብሏል።

ኤምባሲው ወደ ዩክሬን ሄደው እንዲዋጉ ያወጣወን የቅጥር ማስታወቂያ ቆይቶ ያጠፋ ቢሆንም በቀጣይ ምን አይነት እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚችል ግልጽ አይደለም በሚል የሴኔጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለፁን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ሴኔጋል በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ (UNGA) ላይ የቀረበውን " ሩስያ ዩክሬንን ወራለች ፤ ወታደሮቿንም ከዩክሬን ታስወጣ " የሚለውን የውሳኔ ሃሳብ ላይ የድምጸ ተዓቅቦ ካደረጉ ሀገራት አንዷ ናት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አርፈዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። የቅዱስነታቸውን ሽኝት በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ተሰብስቦ በሚያስተላልፈው ውሳኔና በሚያወጣው መርሐ ግብር መሰረት የሚፈጸም መሆኑን የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል። አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ…
#Russia

ሩስያ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማትን ሀዘን ገለፀች።

ሩስያ በአዲስ አበባ ባለው ኤምባሲዋ አማካኝነት በ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት የተሰማትን ሀዘን ገልፃለች።

የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት በዓለም ለሚገኙ የኦርቶዶክስ አማኞች ከባድ ሐዘን ነው ብላለች።

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ታላቅነት ማስቀጠልና መጠበቅ ውስጥ የማይተካ ሚና መጫወታቸውንም ሩስያ ገልፃለች።

ሩስያ በብፁዕነታቸው እረፍት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሆነን እናዝናለን ብላለች።

@tikvahethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር የቤት ውስጥ የመታሰር ጉዳይን አስመልክቶ ለፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን እና ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤቶች ደብዳቤ ፅፏል።

የፖለቲካ ፓርቲዎችን አቤቱታ የሚያጣሩ ቡድኖች ወደ አቶ ዳውድ ኢብሳ ቤት የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ/ም በመሄድ አቶ ዳውድ ያሉበትን ሁኔታ አጣርተዋል።

አጣሪዎቹ በሪፖርታቸው እንዳቀረቡት የቡድኑ አባላት የሊቀመንበሩ መኖሪያ ቤት ሲደርሱ አንኳክተው የከፈቱላቸው ሲቪል የለበሱ የፀጥታ ሰራተኞች መሆናቸውን ማንም ሰው መግባት እንደማይፈቀድለት ገልፀው ገብተው ለማየት መጀመሪያ ፍቃድ መጠየቅ ያለበት መሆኑን ከየት እንደመጡና ለምን እንደመጡ መጠየቃቸውን፣ በመጨረሻ እንዲጎበኟቸው መፈቀዱን ገልፀዋል።

የቡድኑ አባላት ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት የያዙት ቦርሳ መፈተሹን እንዲሁም ስልካቸውን ይዘው መግባት እንደማይችሉ እንደተገለፀላቸው በመጨረሻም ይህን ፈፅመው ከአቶ ዳውድ ጋር እንደተገናኙ ለቦርዱ ሪፖርት አቅርበዋል።

የአጣሪ ቡድኑ አባላት ከአቶ ዳውድ ጋር ባደረጉት ውይይት የተረዱት ከመጋቢት 24 /2013 ዓ /ም ጀምሮ ከቤት እንዳይወጡ የታጠቁ ሰዎች ግቢያቸው ውስጥ ተመድበው የከለከሏቸው መሆኑን ነው።

ምርጫ ቦርድም አቶ ዳውድ ኢብሳ የቤት ውስጥ እስረኛ ሆነው የመንቀሳቀስ መብታቸው እንደተገደበ ተገንዝቧል።

በመሆኑም ቦርዱ እኚህ የፓርቲ አመራር በየትኛውም የህግ አግባብ ተቀባይነት በሌለው ሁኔታ የሚገኙበትን የቤት ውስጥ እስር በአፋጣኝ መቆም እንዳለበት አስገንዝቧል።

ተቋማቱ በአቶ ዳውድ ኢብሳ ግቢ የመደቡትን ጥበቃ እንዲያነሱና የሊቀመንበሩን የመንቀሳቀስ መብት አስከብረው በአስቸኳይ ለቦርዱ እንዲገለፁም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ፥ ስዊድንን እና ፊንላንድን አስጠነቀቀች። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስዊድን እና ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል ከሞከሩ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ] እንደሚኖሩ አስጠንቅቋል። አሁን በዩክሬን እና ሩስያ መካከል ያለው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ሩስያ ፊንላንድ እና ስዊድንን ማስፈራራቷ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ፈጥሯል። የኃያላን ሀገራቱ ግብግብ በተለይ…
#NATO

NATO በዩክሬን እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ሁሉንም መረጃዎች የቅርብ አጋሮቼ ናቸው ላላቸው ስዊድን እና ፊንላንድ እያካፈለ መሆኑን ዋና ጸሃፊው ጄንስ ስቶልተንበርግ ዛሬ አስታውቀዋል።

ስቶልተንበርግ ዛሬ በብራስልስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ “ለሩሲያ ወረራ ምላሽ ለመስጠት ከፊንላንድ እና ስዊድን ጋር ያለንን ትብብር እና የመረጃ ልውውጥ ለማጠናከር ወስነናል " ብለዋል።

አክለውም ፥ " ሁለቱም ሀገሮች አሁን ላይ ስለ ቀውሱ በሁሉም የNATO ምክክር እየተሳተፉ ነው። ” ሲሉ ተደምጠዋል።

ከቀናት በፊት ሩሲያ ፥ ስዊድን እና ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል #ከሞከሩ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ] እንደሚኖሩ አጥብቃ ማስጠንቀቋ የሚዝነጋ አይደለም።

ሩስያ ሁለቱን ሀገራት አርፋችሁ ቁጭ በሉ ስትል ማስጠንቀቋ በዩክሬን ተባብሶ የቀጠለው ጦርነት ላይ ሌላ ከፍተኛ ዓለም አቀፋዊ ስጋት እና አደጋ ሊፈጥር እንደሚችል ሲነገር እንደነበር ይታወሳል።

አሁን ላይ ምንም እንኳን ሁለቱ ሀገራት የNATO አባል ባይሆኑም NATO ከሁለቱም ሀገራት ጋር ያለውን ገኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ወስኗል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ መርሀ ግብር ለመማር የሚመዘገቡ ተማሪዎች የሚከተሉትን የቅበላ መስፈርቶችን ማሟላት እንደሚኖርባቸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለሥልጣን አስታውቋል።

እነዚህም፡-

1. የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎች ከሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያስቀመጠውን የመቁረጫ ነጥብ ሊያሟሉ ይገባል፡፡

2. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች ከሆኑ ከሠለጠኑበት የሙያ መስክ ጋር ተዛማጅነት ባለው የሥልጠና መስክ በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በደረጃ 4 (ወይም በቀድሞ 10+3 ወይም 12+2) ያጠናቀቁ ሆነው በሙያው ደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC level 4) ተፈትነው ያለፉበትን፤ እንዲሁም በሙያው ቢያንስ የሁለት ዓመት ሥራ ልምድ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች በምዝገባው እለት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

3. ከውጭ ሀገር የተገኘ የትምህርት ማስረጃ ለዲግሪ መርሃ-ግብር መግቢያ የሚያገለግለው በባለስልጣኑ የአቻ ግምት ሲሰራለት ብቻ ይሆናል፡፡

4. በየተቋማቱ የሚዘጋጁትን የመግቢያ ፈተናዎች ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፤ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች በምዝገባው ዕለት ማቅረብ ያልቻለ ተመዝጋቢ ህጋዊ ተቀባይነት አይኖረውም።

ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ህጋዊ መመሪያዎችን ጥሶ የተገኘ ተቋም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የስነ ስርዓት መመሪያ መሠረት በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን ከህግ ውጪ ገብተው የሚማሩ ተማሪዎችም ሊደርስባቸው የሚችለውን የጊዜ፣ የገንዘብና የስነ-ልቦና ኪሳራ አውቀው አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለስልጣኑ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ASTU #AASTU ሁለቱ የኢትዮጵያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስገባ ነጥብ ያዝመዘገቡ ተማሪዎችን ለመቀበል በዛሬው ዕለት ጥሪ አቅርበዋል። ዩኒቨርሲቲዎቹ የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ አውጥተዋል። የመመዝገቢያ መስፈርቱ የሲቪክስ ትምህርትን ሳይጨምር የስድስት ትምህርት ድምር ውጤት ከዚህ በታች እንደተገለፀው…
#የተሻሻለ

የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ መስፈርቶች ላይ ማሻሻያ ተደርጎበታል።

የመመዝገቢያ መስፈት የሲቪክስ ትምህርትን ሳይጨምር የስድስት ትምህርት ድምር ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

• ለአዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ)

- ኢንጂነሪንግ ~ ለወንድ 375፣ ለሴት 370
- አፕላይድ ሳይንስ ~ ለወንድ 365፣ ለሴት 360

• ለሌሎች ክልሎች

- ኢንጂነሪንግ ~ ለወንድ 380 ፣ ለሴት 375
- አፕላይድ ሳይንስ ~ ለወንድ 370፣ ለሴት 365

የምዝገባ ጊዜው ከየካቲት 21 እስከ 30/2014 ዓ.ም ሲሆን ምዝገባው የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ይጠናቀቃል ተብሏል።

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ በኢንተርኔት www.aastu.edu.et እና www.astu.edu.et ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

የመግቢያ ፈተናው መጋቢት 07/2014 ዓ.ም ይሰጣል። (ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና አምባሳደር ድሪባ ኩማ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸው ፍርድ ቤቱ አዘዘ። የመጥሪያ ትዛዙን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። በነ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው የመርከብ ግዢ የሙስና ክስ ላይ በመከላከያ ምስክርነት ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲመሰክሩ ነው መጥሪያ እንዲደርሳቸው የታዘዘው።…
#ሀሰት_ነው !

የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከእስር ተፈቱ እየተባለ በማህበራዊ ድረ ገጽ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው።

ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከተከሰሱባቸው የሙስና ክሶች መካከል የመርከብ ግዢ እና የእርሻ መሳሪያ ግዥ ጋር ተያይዞ የቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶ/ ር ወርቅነህ ገበየሁን ጨምሮ ሌሎችም የመከላከያ ምስክሮች እንዲቀርቡ በታዘዘው ትዕዛዝ መሰረት የመከላከያ ማስረጃ ለመስማት ፍርድ ቤቱ በቀጠሮ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው ከህዳሴው ግድብ ምንጣሮ ጋር ተያይዞ በቀረበባቸው ሌላኛው የሙስና ክስ ነጻ የተባሉ ቢሆንም በቀሪ ክሶች ግን በቀጠሮ ላይ ይገኛሉ።

ከእስር ተፈተዋል እየተባለ የሚናፈሰው መረጃ ሀሰት ነው።

Credit : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
ሩስያ ፌስቡክን አገደች።

ሩስያ በሀገሯ ውስጥ ፌስቡክ የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት እንዳይሰጥ ሙሉ በሙሉ ዘግታዋለች።

ሩስያ ከጥቅምት 2020 ጀምሮ ቢያንስ 26 በሚሆኑ የሩሲያ ሚዲያዎች እና የመረጃ ምንጮ ላይ መድልዎ መፈፀሙን ገልፃለች።

በተጨማሪም በቅርብ ጊዜ ከክሬምሊን ጋር የተቆራኙ የሚዲያ ምንጮች RT Newsና Sputnik News በመላው አውሮፓ እንዲገደቡ መደረጉን አመልክታለች።

ይህንንም ተከትሎ ሩስያ ፌስቡክ ሙሉ በሙሉ በምድሯ ላይ አገልግሎት እንዳይሰጥ ዘግታዋለች።

@tikvahethiopia
የካራማራ ድል !

የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበትና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት ቀን ነው።

ዘንድሮ ይህ ድል 44ኛ አመት ሞልቶታል ቀኑም እየታሰበ ነው።

ከጦርነቱ በፊት ለረጅም ጊዜ የሶማሊያ ጦር በሶቪዬት ኅብረት ይደገፍ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ ከአሜሪካ ጋር ወዳጅነት ነበረው። በወቅቱ አሜሪካ እና የሶቪየት ህብረት በቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ ነበሩ።

በቅድሚያ በሶቪየት ህብረት ከፍተኛ ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ ካራማራ ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሶል፡፡

በጦርነቱ መጀመሪያ ሶማሊያን ስትደግፍ የነበረችው ሶቪየት ህብረት ወደ ኢትዮጵያ አዘንብላ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ አድርጋለች ፤ አሜሪካ ደግሞ ወደ ሶማሊያ ፊቷን አዙራለች።

በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመንና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል።

ከ16 ሺ በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። ደቡብ የመንም ጦሯን ለኢትዮጵያ አሰልፋ ነበር።

በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው የዚያድባሬን ጦር የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያ አንድነት ዳግም በጉልህ የታየበት ስለመሆኑ ይነገርለታል፡፡

በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የ " ካራማራ ድል " ዘንድሮም ለ44ኛ ጊዜ እየታሰበ ይገኛል፡፡

https://telegra.ph/Ethiopia-03-05

@tikvahethiopia