TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ከዩክሬን ጋር ልትነጋገር ነው። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ከዩክሬን ልዑክ ጋር ለመነጋገር ከፍተኛ የልዑካን ቡድናቸውን ወደ ቤላሩስ ሚኒስክ ሊልኩ መሆኑ ተሰምቷል። ይህ የተሰማው የዩክሬን ፕሬዜዳንት ዜሌንስኪ ሃገራቸው ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን ከተናገሩ ከሰዓታት በኃላ ነው። ሞስኮ ዩክሬን የኔቶ አባል ለመሆን ያላትን ጥያቄ እንድታቆም እና ገለልተኛ አቋም እንድትይዝ ትፈልጋለች። ሚኒስክ…
" ቤላሩስ ውስጥ አንደራደርም " - የዩክሬን ፕሬዜዳንት
ሩስያ የልዑካን ቡድኗ ከዩክሬን አቻው ጋር ለመነጋገር ቤላሩስ መግባቱን አሳውቃለች።
የሩስያ ልዑካን ቡድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም ደግሞ የፕሬዚዳንት አስተዳደርን ያካተተ እንደሆነ ነው የተገለፀው።
ሀገሪቱ ንግግሮችን በጎሜል ለመጀመር ዝግጁ ነኝ ብላለች።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከሩስያ ጋር በቤላሩስ #እንደማይደራደሩ አሳውቀዋል። ምክንያቱ ደግሞ ቤላሩስ ፤ ሩስያ ሀገራቸውን ለማጥቃት እየተጠቀሙባት በመሆኑ ነው።
ሀገራቸው ለሰላም ንግግር ዝግጁ መሆኗን ግን ገልፀዋል።
ከቀናት በፊት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን ልዑክ ጋር ለመነጋገር ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ወደ ቤላሩስ ሊልኩ መሆኑ መነገሩ ይታወቃል።
በዚህም የልዑካን ቡድኑ ቤላሩስ ቢደርስም ዩክሬን በቤላሩስ እንደማትደራደር ገልፃለች።
@tikvahethiopia

#Somalia
አሜሪካ በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ እገዳ ጣለች።
አሜሪካ ፤ " የሶማሊያን የዲሞክራሲ ሂደት አደናቀፈዋል " ባለቻቸው በርካታ የሶማሊያ ባለስልጣናት ላይ የቪዛ እገዳ መጣሏን አስታውቃለች።
ሶማሊያ የሕግ አውጭ ም/ቤት አባላት ምርጫ ምታጠናቅቅበትን ቀነ ገደብ ተፈፃሚ ሳታደርግ ቀርታ በድጋሚ ወደ መጋቢት 6 አራዝማለች። የካቲት 25 መጠናቀቅ የነበረበት ምርጫ ነው ወደ መጋቢት 6 ያራዘመችው።
ሁኔታው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውም እንዲራዘም ሊያስገድድ ይችላል እየተባለ ነው።
በርካታ የፓርላማ መቀመጫዎች እስካሁን አልተሟሉም።
ከዚህ ጋር ተያይዞ አሜሪካ የሶማሊያን የዲሞክራሲ ሂደት አደናቅፈዋል ባለቻቸው በርካታ ባለስልጣናት ላይ የቪዝ እገዳ ጥላለች።
ሶማሊያ የህግ አውጪ እና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዋን "ግልጽና ተአማኒ በሆነ መንገድ እንድታጠናቅቅ " ስትል አሳስባለች።

#EOTC አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው ሆስፒታል ይገኛሉ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስም ሆስፒታል በመገኘት ጠይቀዋቸዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሕመም ምክንያት በሆስፒታል ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙትን 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ…
ፎቶ ፦ አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው ሆስፒታል እንደሚገኙ ይታወቃል።
ትላንት ቅዳሜ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሆስፒታል በመገኘት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን መጎብኘታቸው እና እግዚአብሔር ምሕረቱን እንዲልክላቸው ጸሎት በማድረስ መልካም ምኞታቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት ደግሞ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ሆስፒታል በመገኘት ጎብኝተዋቸዋል።
በተጨማሪ የኢፌዴሪ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም ቅዱስነታቸውን ጎብኝተዋቸዋል። ፕሬዜዳንቷ በቀደመው ጊዜ የቅዱስነታቸው የመንፈስ ቅዱስ ልጅ መሆናቸውን ገልፀው በቶሎ ድነው ከሆስፒታል እንዲወጡ ምኞታቸውን ገልፀዋል።
ቅዱስነታቸው በሀሌሉያ ሆስፒታል በመደበኛ ክል ህክምናቸውን እየተከታተሉ ሲሆን ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል አለመግባታቸው ተገልጿል።

አቶ ተስፋየ አባተ ተገደሉ።
የሀብሩ ወረዳ ኢንቨስትመንት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተስፋየ አባተ ያዘው መገደላቸው ተሰማ።
ኃላፊው ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ተመተው #ከትዳር_አጋራቸው ጋር ህይወታቸው ማለፉን የሀብሩ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት አስታውቋል።

" ቤላሩስ ውስጥ አንደራደርም " - የዩክሬን ፕሬዜዳንት ሩስያ የልዑካን ቡድኗ ከዩክሬን አቻው ጋር ለመነጋገር ቤላሩስ መግባቱን አሳውቃለች። የሩስያ ልዑካን ቡድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር እና ሌሎች ተቋማት እንዲሁም ደግሞ የፕሬዚዳንት አስተዳደርን ያካተተ እንደሆነ ነው የተገለፀው። ሀገሪቱ ንግግሮችን በጎሜል ለመጀመር ዝግጁ ነኝ ብላለች። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከሩስያ…
#Update
ዩክሬን ከሩስያ ጋር ለመነጋጋር ተስማምታለች።
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቢሮ ፤ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ለፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዘሌንስኪ ዛሬ ደውለውላቸው እንደተነጋገሩ ገልጿል።
የዩክሬን ልዑካን ከሩሲያ ልዑካን ጋር " ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ " በዩክሬን-ቤላሩስ ድንበር በፕሪፕያት ወንዝ አቅራቢያ ተገናኝተው ለመነጋገር መስማማታቸውን ቢሮው አሳውቋል።
አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በቤላሩስ ግዛት ያሉ አውሮፕላኖች፣ ሄሊኮፕተሮች እና ሚሳኤሎች የዩክሬን ልዑካን በሚጓዙበት፣ ተገናኝተው በሚነጋገሩበት እና በሚመለሱበት ጊዜ ያለንአንዳች እንቅስቃሴ እንደሚቆዩ ሃላፊነት መውሰዳቸው ተነግሯል።
የሩስያ መንግስት ዜና ተቋማት የዩክሬን ልዑክ ከሩስያ ልዑክ ጋር በቤላሩስ ፣ ጎሜል ክልል ለመነጋገር መስማማታቸውን ዘግበዋል፤ የዩክሬን ልዑክን ወክለው ስለሚገኙ ሰዎች ዝርዝር መረጃ አልሰጡም።
ይህ የስምምነት ከመሰማቱ ቀደም ብሎ ዩክሬን በቤላሩስ ከሩስያ ጋር እንደማትነጋገር ገልፃ ነበር፤ ምክንያቷ ሩስያ ሀገሪቱን እንድታጠቃ ቤላሩስን እየተጠቀመች በመሆኑ ነው።
በኃላም የሩስያው ልዑክ የውይይቱን ሃሳብ ያቀረበች እራሷ ዩክሬን ናት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ (በቤላሩስ ሰዓት አቆጣጠር) የዩክሬን ልዑካንን እንጠብቃለን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ነገር ኃላፊነቱን እራሷ ትውስዳለች ሲል አስፈራርቶ ነበር።

#Russia
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የጸረ ኑክሌር ኃይላቸው በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዙ፡፡
ፑቲን ከገቡበት የዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ከምዕራባውያን ሃገራት ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው ጦሩ በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ እንዲሆን ያዘዙት፡፡
ዛሬ ከከፍተኛ ባለስልጣናቶቻቸው ጋር በነበራቸው ውይይት የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) አባል የሆኑ ሃገራት ጠንከር ያለ መግለጫ እያወጡ መሆኑን እና ማዕቀቦችን እየጣሉ በመሆኑ ጸረ ኑክሌር ኃይሉ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆን አዘዋል፡፡
ትዕዛዙ ለሃገሪቱ ጦር አመራሮች የተሰጠ ነው፡፡
ይህ ሁኔታውን የበለጠ እንዳያባብሰውና ወዳልተፈለገ አስከፊ #የኑክሌር_ጦርነት እንዳያመራ ተሰግቷል፡፡
የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ማዕቀብን ጨምሮ ሌሎችንም እርምጃዎችን በሚወስዱ እና ጣልቃ በሚገቡ ሃገራት ላይ ጠንከር ያለ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ ሲያስጠነቅቁ ነበር።
#አልዓይን

ፎቶ ፦ አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው ሆስፒታል እንደሚገኙ ይታወቃል። ትላንት ቅዳሜ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሆስፒታል በመገኘት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን መጎብኘታቸው እና እግዚአብሔር ምሕረቱን እንዲልክላቸው ጸሎት በማድረስ መልካም ምኞታቸውን መግለፃቸው ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ደግሞ ጠ/ሚር…
#Update
ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዜዳንት ሙላቱ ተሾመ 4ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ህክምናቸውን እየተከታተሉ በሚገኝበት ሀሌሉያ ሆስፒታል ተገኝተው ጠይቀዋቸዋል።
ፎቶ ፦ Tikvah Family
@tikvahethiopia
ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እንዲሁም የቀድሞ ፕሬዜዳንት ሙላቱ ተሾመ 4ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ህክምናቸውን እየተከታተሉ በሚገኝበት ሀሌሉያ ሆስፒታል ተገኝተው ጠይቀዋቸዋል።
ፎቶ ፦ Tikvah Family
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዩክሬን ከሩስያ ጋር ለመነጋጋር ተስማምታለች። የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቢሮ ፤ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ለፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዘሌንስኪ ዛሬ ደውለውላቸው እንደተነጋገሩ ገልጿል። የዩክሬን ልዑካን ከሩሲያ ልዑካን ጋር " ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ " በዩክሬን-ቤላሩስ ድንበር በፕሪፕያት ወንዝ አቅራቢያ ተገናኝተው ለመነጋገር መስማማታቸውን ቢሮው አሳውቋል። አሌክሳንደር ሉካሼንኮ…
#Update
ሩስያ እና ዩክሬን ነገ ሰኞ መነጋገር ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት የሆኑት ዜለንስኪ የሰላም ድርድር በሚያደርገው ልዑክ ውስጥ እንደሌሉበት ተገልጿል።
በአሜሪካ የዩክሬን አምባሳደር ኦክሳና ማርካሮቫ ዛሬ እንደተናገሩት የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ነገ ሰኞ ከሩሲያ ጋር ሊደረግ በታቀደው የሰላም ድርድር ልዑክ ውስጥ በእርግጠኝነት የሉም።
ፕሬዚዳንቱ በአገራቸው እንደሚቆዩ እና እያደረጉ ያሉትን ውጊያ እንደሚቀጥሉ አምባሳደሯ ገልፀዋል።
አምባሳደር ኦክሳና ማርካሮቫ " ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ አገሪቷን ለመከላከል ውስነዋል። ስለዚህ እሱ ከታጠቁ ኃይሎች ጋር፣ ከዩክሬን ሕዝብ ጋር፣ አገሩን እየጠበቀ በኪየቭ ነው የሚገኘው " ብለዋል።
በሌላ በኩል የሰላም ንግግር ይጀመርባታል ከተባለችው ቤላሩስ አቅጣጫ ወደ ዩክሬን ሚሳኤል ተወንጭፎ ጉዳት ማድረሱን ከዩክሬን የሚወጡ ዘገባዎች እያሳዩ ይገኛሉ።
የቤላሩሱ ፕሬዜዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ከሰዓታት በፊት በቤላሩስ ግዛት ያሉ አውሮፕላኖች፣ ሄሊኮፕተሮች እና ሚሳኤሎች የዩክሬን ልዑካን ፦
- በሚጓዙበት ፣
- ተገናኝተው በሚነጋገሩበት እንዲሁም
- በሚመለሱበት ጊዜ ያለአንዳች እንቅስቃሴ እንደሚቆዩ ሃላፊነት እንደሚወስዱ የገቡትን ቃል አላከበሩም ፤ ዋሽተዋል በሚል ከዩክሬናውያን በኩል ብርቱ ትችት እየቀረበባቸው ነው።
የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ቀኑ በገፋ ቁጥር በመላው ዓለም የሚያሳድረው ሁሉን አቀፍ ተፅእኖ እያየለ እና እየጠነከረ ስለሚመጣ አቸኳይ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ከየአቅጣጫው ጥሪዎች እየቀረቡ ናቸው።

#BREAKING
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ስብሰባ ተቀምጦ ነበር። በዚህም ም/ቤቱ በዩክሬን ጉዳይ የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ [የ193 አባል ሀገራት] አስቸኳይ ልዩ ስብሰባ እንዲጠራ በድምፅ ወስኗል።
ስብሰባው ዛሬ ሰኞ ይካሄዳል።
ሩስያ ስትቃወም [ድምፅን በድምፅ የመሻር /veto power/ መብቷ እዚህ ላይ ተግባራዊ አይሆንም] ፤ ቻይና ፣ ህንድ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይህን አይነት ውሳኔ ሲወስን በ40 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በድርጅቱ ታሪክ ደግሞ 11ኛው መሆኑ ተነግሯል።
#የደገፉ_ሀገራት ፦
🇺🇸 አሜሪካ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇮🇪 አይርላድ
🇦🇱 አልባኒያ
🇬🇦 ጋቦን
🇲🇽 ሜክስኮ
🇧🇷 ብራዚል
🇬🇭 ጋና
🇰🇪 ኬንያ
#የተቃወሙ ፦
🇷🇺 ሩስያ
#ድምፀ_ተአቅቦ_ያደረጉ ፦
🇨🇳 ቻይና
🇮🇳 ሕንድ
🇦🇪 ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE)

#እንኳን_አደረሳችሁ !
ዐቢይ ፆም በዛሬው ዕለት ጀምሯል።
ፆሙን የጀመራችሁ ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ወርሃ ፆሙ በችግር ፣ በእጦት ፣ በአስከፊ ድርቅ ከምንም በላይ በሰላም እና ፀጥታ ችግር እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖችን የምናስብበት ፣ አቅም በፈቀደ ሁሉ ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ የምናደርግበት እንዲሆን እንማፀናለን።
በተጨማሪም ስለኢትዮጵያና ስለዓለም ደህንነት እና ሰላም ፈጣሪን አጥብቀን የምንማፅንበት ሊሆን ይገባል እንላለን።
መልካም የዐቢይ ፆም ይሁንላችሁ።
(Tikvah - Family)

#ዐቢይ_ፆም
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዐቢይ ፆምን በማስመልከት ፥ " መላው ኦርቶዶክሳዊያን ወርሃ ጾሙን ፈጣሬ ዓለማት መድሃኔዓለም ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ፍጹም ምህረቱን እንዲያወርድልን በመጸለይ ልናሳልፈው ይገባል " ስትል መንፈሳዊ መልዕክቷን አስተላልፋለች።
አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በሆስፒታል ህክምናቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ይታወቃል።