TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ukraine

በዩክሬን ያሉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሀት ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጎ እንደ ፖላንድ ወዳሉ ጎረቤት ሀገራት እንዲሄዱ እንዲያመቻችላቸው ተማፅነዋል።

ሌሎች ሀገራት ከዩክሬን ዜጎቻቸውን በማስውጣት ላይ ይገኛሉ።

ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ዩክሬን ሀገር የሄዱ 49 የሀገራችን ዜጎች የሆኑ ተማሪዎች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ግን ከ400 እስከ 500 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ እንደሚገኙ ይገመታል።

ኬንያ ከ270 በላይ የሆኑ ዜጎቿን ከዩክሬን ለማስውጣት እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑ ታውቋል።

#EliasMesert

@tikvahethiopia
#Ukraine

በዩክሬን ዩኒቨርሲቲዎች ከሚማሩ የውጭ ሀገር ተማሪዎች በግምት 20% የሚሆኑት ከአፍሪካ የሄዱ ናቸው። ከእነዚህ መከከል በግምት 4000 የናይጄሪያ ተማሪዎች ይገኙበታል።

አሁን ላይ ዩክሬን ውስጥ ባለው ጦርነት የንግድ በረራዎች በመቋረጣቸው ምክንያት በዩክሬን ያሉ ተማሪዎች እጣፋንታ በእጅጉ እያሳሰባቸው መሆኑን የናይጄሪያ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እየገለፁ ይገኛሉ።

የሀገሪቱ መንግስትም ለተማሪዎቹ አንዳች መፍትሄ ይፈልግ ዘንድ ተማፅኖ እየቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ukraine በዩክሬን ዩኒቨርሲቲዎች ከሚማሩ የውጭ ሀገር ተማሪዎች በግምት 20% የሚሆኑት ከአፍሪካ የሄዱ ናቸው። ከእነዚህ መከከል በግምት 4000 የናይጄሪያ ተማሪዎች ይገኙበታል። አሁን ላይ ዩክሬን ውስጥ ባለው ጦርነት የንግድ በረራዎች በመቋረጣቸው ምክንያት በዩክሬን ያሉ ተማሪዎች እጣፋንታ በእጅጉ እያሳሰባቸው መሆኑን የናይጄሪያ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እየገለፁ ይገኛሉ። የሀገሪቱ መንግስትም…
" የተማሪዎቹ እንዲሁም የሌሎችም ዜጎቼ ደህንነት በእጅጉ ያሳስበኛል " - የጋና መንግስት

የጋና መንግስት በዩክሬን ውስጥ የሚገኙ ከ1 ሺ በላይ የጋና ዜግነት ያላቸው ተማሪዎች እና ሌሎችም ጋናውያን የፀጥታና ደህንነት ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስበው አሳውቋል።

የጋና መንግስት ይህን ያለው ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ ነው።

ዜጎቹ በቤታቸው ወይም በመንግስት የመጠለያ ቦታዎች እንዲጠለሉ ጠይቋል። ከባለሥልጣኖቹ ፣ ከሚመለከታቸው የዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖች እና ቆንስላው ጋር በመሆን ተጨማሪ እርምጃዎች ለመውሰድ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የስንዴ ዋጋ📈 የአውሮፓ የስንዴ ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ አሳየ። ሩስያ #በዩክሬን ከወሰደችው ወታደራዊ ዘመቻ በኃላ የስንዴ ዋጋ ከፍተኛ /ሪከርድ በሆነ ሁኔታ ጭምሪ ማሳየቱ ተነግሯል። @tikvahethiopia
የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ📈

የሩስያ የመንግስት የዜና ወኪል በአውሮፓ #የተፈጥሮ_ጋዝ ዋጋ በአንድ ሺህ ኪዩቢክ ሜትር 52 በመቶ ወደ 1,560 ዶላር በላይ መጨመሩን ገልጿል።

ጭማሪው የመጣው #ከዩክሬን_ቀውስ ጋር በተያያዘ ጀርመን አወዛጋቢውን የሩሲያ ጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ካገደች በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ📈 የሩስያ የመንግስት የዜና ወኪል በአውሮፓ #የተፈጥሮ_ጋዝ ዋጋ በአንድ ሺህ ኪዩቢክ ሜትር 52 በመቶ ወደ 1,560 ዶላር በላይ መጨመሩን ገልጿል። ጭማሪው የመጣው #ከዩክሬን_ቀውስ ጋር በተያያዘ ጀርመን አወዛጋቢውን የሩሲያ ጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ካገደች በኋላ መሆኑ ተገልጿል። @tikvahethiopia
የሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት መዘዝ ፦

📉 የሩሲያ ሩብል ወርዶ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ሆኗል።

📈 ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በ7% ወደ 105 ዶላር ጨምሯል።

📈 የስንዴ ዋጋ በዘጠኝ ዓመት ውስጥ ሪከርድ በሆነ ሁኔታ ንሯል።

📈 ወርቅ በከፍተኛ ሁኔታ ዋጋው ጨምሯል።

📈 የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ በ1 ሺ ኪዩቢክ ሜትር 52 በመቶ ወደ 1,560 ዶላር በላይ ንሯል።

📉 ቢትኮይን ወደ 35,000 ዶላር ወርዷል።

በሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት እንደ ቅጥል ከሚረግፈው የሰው ልጆች ህይወት ባለፈ ጦርነቱ እዛው ተወስኖ የሚቀር ሳይሆን መላው ዓለምን በኢኮኖሚ ቀውስ ሊያናውጠው እንደሚችል ይሰጋል። ሀገራት በስደተኞች ይጨነቃሉ ፣ የሸቀጥ ዋጋ ከፍ ይላል፣ የምግብ ዋጋ ይንራል ..ወዘተ ተብሎ ተፈርቷል።

ሀገራት እና ተቋማት ጦርነት ቆሞ ሰላማዊ መፍትሄ ይፈለግ ዘንድ እየተማፀኑነው። ምዕራባውያኑ ሩሲያን አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት በማዕቀብ እናሽመደምዳታለን እያሉ እየዛቱ ነው።

ከየሀገራቱ ሩስያ ላይ ማዕቀብ እንደጉድ መዝነብ ጀምሯል።

ቀጣዮቹ ቀናቶች ምን ይዘው እንደሚመጡ ለመገመትም አደጋች ሆኗል። የጦርነት ተፅእኖው በአንድ ቦታ ላይ ተወስኖ የሚቀር አይደለምና ሀገራት ለሚመጣው ሁሉ እየተዘጋጁ፣ ጎራቸውንም እየለዩ ይመስላል።

@tikvahethiopia
" ከሩስያ ጋር በዩክሬን አንዋጋም " - አሜሪካ

የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በሰጡት መግለጫ #ዩክሬን ውስጥ ከሩስያ ጋር ወደ ውጊያ እንደማይገቡ ተናግረዋል።

ባይደን " ፑቲን ጠብ አጫሪ አጥቂ ናቸው ፤ ይህንን ጦርነት መርጠዋል። እሳቸው እና አገራቸው ውጤቱን ይሸከማሉ " ብለዋል።

በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሉን ባይደን አሳውቀዋል።

ጆ ባይደን ፥ " የእኛ ሃይሎች በዩክሬን ውስጥ ከሩሲያ ጋር ግጭት ውስጥ አይደሉም እንዲሁም አይገቡም " ያሉ ሲሆን " ሃይሎቻችን በዩክሬን አይዋጉም የኔቶ አጋሮቻችንን እና የኔቶ ግዛትን እያንዳንዱን ኢንች ግን እንከላከላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ 7ሺ የአሜሪካ ወታደሮች ወደጀርመን እንደሚያመሩ አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደን " ሩሲያ በኩባንያዎቻችን ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሳይበር ጥቃቶችን የምትቀጥል ከሆነ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነን " ሲሉ ዝተዋል።

@tikvahethiopia
የኪዬቭ እጣፋንታ ምን ይሆን ?

" ኪዬቭ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በሩሲያ ኃይሎች እጅ ልትወድቅ ትችላለች " - የደህንነት ባለስልጣን

አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የምዕራቡ ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣን የዩክሬን አየር መከላከያ ስለተወገደ ኪየቭ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በሩሲያ ኃይሎች ልትወድቅ እንደምትችል መናገራቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል።

ባለስልጣኑ የሩሲያ ወታደሮች በዲኒፐር ወንዝ በሁለቱም በኩል ወደ ዩክሬን እየገሰገሱ ሲሆን ዋና ከተማይቱን ለመያዝ የተቃረቡ ይመስላሉ ብለዋል።

የሩስያ ጦር ኃይሎቹን ወደ አገሪቱ ውስጥ ለማስገባት የሚጠቀምባቸው በርካታ የአየር ማረፊያዎችን መቆጣጠሩ ተነግሯል።

እኚሁ የደህንነት ባለስልጣን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወታደራዊ እርምጃዎች በምስራቅ፣ ደቡብ እና በመሃል ሀገሪቱ ላይ ያተኮሩ ቢሆንም፣ መላው ዩክሬን የመቆጣጠር አላማ እንዳላቸው ይታመናል ብለዋል።

አክለው የፑቲን የመጨረሻ ጨዋታ በኪዬቭ የሚገኘውን መንግስት አስወግደው የሚታዘዝላቸውን የአሻንጉሊት አገዛዝን ማስቀመጥ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ አገራቸውን ለመከላከል ቃል የገቡ ሲሆን " እሳቸው እና መንግስታቸው በዋና ከተማው እንደሚቆዩ አረጋግጠዋል።

የደህንነት ባለሥልጣኑ ሩሲያውያን ኪዬቭን ሲቆጣጠሩ 3 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ከተማ ከፍተኛ የሆነ ጥቃት ሊደርስባት ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን ከሰዓታት በፊት እያካሄዱ ስላሉት ወታደራዊ ዘመቻ በሰጡት መግለጫ " ሊስቆመን የሚሞክር፣ በሀገራችን እና በህዝባችን ላይ ተጨማሪ አደጋ የሚጥል ማንኛውም አካል በታሪኩ አይቶት የማያውቀው እጣፋንታ ይገጥመዋል " ሲሉ ዝተው ነበር።

@tikvahethiopia
#እንኳን_ለዐቢይ_ጾም_አደረሳችሁ !

ቅዱስ ፓትርያርኩ ዐቢይ ጾምን በማስመልከት ለመላው ኦርቶዶክሳዊያን አባታዊ መልዕክት አስተላለፉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሀይማኖት የዐቢይ ጾም መግባትን አስመልክተው ዛሬ የካቲት 18/2014 ዓ.ም ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ በመልዕክታቸው ፥ " በመዋዕለ ጾሙ ስለ ሀገርና ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ፣ ስለ ሕዝባችን ዘላቂ ፍቅርና ስምምነት አጥብቀን እንድንጸልይ ፣ እንደዚሁም በግጭቱና በድርቁ ለተጎዱ ወገኖቻችን ካለን በማካፈል የችግሮቻቸው ተካፋይ እንድንሆን ከዚህም ጋር ለሀገራዊ ሰላም እና ፍቅር መሳካት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ መዋዕለ ጾሙን እንድናሳልፍ በእግዚአብሔር ስም መልእክታችንን እናስተላልፋለን " ብለዋል።

* የመልዕክቱ ሙሉ ቃል ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ukraine በዩክሬን ያሉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሀት ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጎ እንደ ፖላንድ ወዳሉ ጎረቤት ሀገራት እንዲሄዱ እንዲያመቻችላቸው ተማፅነዋል። ሌሎች ሀገራት ከዩክሬን ዜጎቻቸውን በማስውጣት ላይ ይገኛሉ። ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ዩክሬን ሀገር የሄዱ 49 የሀገራችን ዜጎች የሆኑ ተማሪዎች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ግን ከ400…
#Update

" ከመንቀሳቀሳችሁ በፊት ከኤምባሲያችን ጋር ተመካከሩ " - በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ

በዩክሬይን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በርሊን፣ ጀርመን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲያሳውቁ መልዕክት ተላልፏል።

በርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት " ዩክሬይን ውስጥ በትምህርት ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ ዜጎች በአሁኑ ወቅት በገጠማችሁ ችግር ምክንያት ከመንቀሣቀሣችሁ በፊት ለዜጎቻችንን ደህንነት በማንኛውም ጊዜ በሞባይል ስልክ ቁጥር +491767269094 እና በemail [email protected] ከኢምባሲያችን ጋር እንድትመካከሩ በአደራ ጭምር እናሣስባለን " ብሏል።

ትላንት በዩክሬን ያሉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሀት ውስጥ እንደሚገኙ መግለፃቸውና የኢትዮጵያ መንግስት የቻለውን ሁሉ ጥረት አድርጎ እንደ ፖላንድ ወዳሉ ጎረቤት ሀገራት እንዲሄዱ እንዲያመቻችላቸው መማፀናቸው አይዘነጋም።

ለከፍተኛ ትምህርት ዩክሬን የሚገኙ በርካታ የሀገራችን ዜጎች የሆኑ ተማሪዎች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ከ400 እስከ 500 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ እንደሚገኙ ይገመታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኪዬቭ እጣፋንታ ምን ይሆን ? " ኪዬቭ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በሩሲያ ኃይሎች እጅ ልትወድቅ ትችላለች " - የደህንነት ባለስልጣን አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የምዕራቡ ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣን የዩክሬን አየር መከላከያ ስለተወገደ ኪየቭ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በሩሲያ ኃይሎች ልትወድቅ እንደምትችል መናገራቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል። ባለስልጣኑ የሩሲያ ወታደሮች በዲኒፐር ወንዝ በሁለቱም በኩል ወደ ዩክሬን…
" ሩስያ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል አቅዳለች " - የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ ሚካሂሎ ፖዶሊያክ ሩስያ ኬያቭን ለመያዝ እና ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን ለመግደል አቅዳለች ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን አሁንም ድረስ በኪዬቭ እንደሚገኙ የገለፁት አማካሪው በዩክሬን ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን በሰጡት መግለጫ " ባለን መረጃ ጠላት እኔን ቁጥር አንድ ኢላማ አድርጎኛል፤ ቤተሰቦቼን ደግሞ ቁጥር ሁለት ኢላማ አድርጓል። የሀገሪቱን መሪ በማጥፋት ዩክሬንን በፖለቲካ ማጥፋት ነው የሚፈልጉት ። የጠላት አጥፊ ቡድኖች ወደ ኪዬቭ መግባታቸውንም መረጃ አለን ነዋሪዎች ተጠንቀቁ የታወጀውንም ሰዓት እላፊ አክብሩ " ብለዋል።

ፕሬዜዳንቱ " እኔ በዋና ከተማዋ ነው የምቆየው፣ ቤተሰቦቼም ዩክሬን ናቸው። ልጆቼም ዩክሬን ናቸው። ቤተሰቦቼ ከዳተኞች አይደሉም የዩክሬን ዜጋ ናቸው " ሲሉም ተደምጠዋል።

ዩክሬን NATO እንዲደርስላትም እየተማፀነች ነው።

እስካሁን ድረስ ምዕራባውያኑ ኃያላን ሀገራት ማዕቀብ ከመጣል ባለፈ ወደ ዩክሬን ገብተው ከሩሲያ ጋር ውጊያ የመግጠም ሀሳብ ያላቸው አይመስልም፤ አሜሪካም ትላንት በፕሬዜዳንቷ ጆ ባይደን አማካኝነት ወታደሮቿን ከሩሲያ ጋር ለማዋጋት ወደ ዩክሬን እንደማታስገባ ማሳወቋ ይታወሳል።

አሁንም ጦርነት ቆሞ ለሰላም እድል እንዲሰጥ ጥሪዎች የቀጠሉ ሲሆን ሩስያ ውስጥም ጦርነቱን በመቃወም ሰልፎች እየተደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል ከዚህ ጋር በተያያዘም የታሰሩ ሰዎች በርካታ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ከመንቀሳቀሳችሁ በፊት ከኤምባሲያችን ጋር ተመካከሩ " - በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዩክሬይን በትምህርት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት በርሊን፣ ጀርመን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንዲያሳውቁ መልዕክት ተላልፏል። በርሊን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት " ዩክሬይን ውስጥ በትምህርት ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ…
#update

" በተቻለ ፍጥነት ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጣችሁ ግቡ " - በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ

በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት የኢትዮጵያ ዜጎች ችግር እንዳይገጥማቸው በጀርመን በርሊን የሚገኘው ኤምባሲ ክትትል እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

ዜጎቻችን ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው መግባት እንዲችሉም ከፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር መነጋገር እና መፃፃፍ መቻሉን የገለፀው ኤምባሲው ኢትዮጵያውያን ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው እንዲገቡ ተፈቅዷል ብሏል።

በዩክሬን የሚኖሩ እና ወደ ድንበር ጉዞ በማድረግ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በተቻለ ፍጥነት ወደ ፖላንድ ግዛት በመግባት ወደ ኢትዮጵያ በተቻለ ፍጥነት እንዲጓዙ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሩስያ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል አቅዳለች " - የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ የዩክሬን ፕሬዝዳንት አማካሪ ሚካሂሎ ፖዶሊያክ ሩስያ ኬያቭን ለመያዝ እና ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን ለመግደል አቅዳለች ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን አሁንም ድረስ በኪዬቭ እንደሚገኙ የገለፁት አማካሪው በዩክሬን ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ገልፀዋል። በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪን በሰጡት መግለጫ " ባለን መረጃ…
" ሁሉም ፈርቷል "

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ፦

" ዛሬ 27 የአውሮፓ መሪዎችን ዩክሬን በNATO ውስጥ እንድትሆን ጠየኳቸው ፤ በቀጥታ ነው የጠየኳቸው፤ ሁሉም ሰው ፈርቷል ፤ መልስ አይሰጥም። እኛ ግን አንፈራም ፤ እኛ ምንም ነገር አንፈራም።

ሀገራችንን ለመከላከል አንፈራም ፤ ሩሲያን አንፈራም ፤ ከሩሲያ ጋር ለመነጋገር አንፈራም፤ ስለአገራችን የደህንነት ዋስትናዎች ለመናገር ፤ ስለማንኛውም ነገር ለመናገር አንፈራም ፤ ስለ ገለልተኝነት ለመናገር አንፈራም።

በአሁኑ ጊዜ የNATO አባል አይደለንም ግን ምን ዋስትና እናገኛለን ? ከሁሉም በላይ ደግሞ የትኞቹ አገሮች ዋስትና ይሰጡናል ? "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሁሉም ፈርቷል " የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ፦ " ዛሬ 27 የአውሮፓ መሪዎችን ዩክሬን በNATO ውስጥ እንድትሆን ጠየኳቸው ፤ በቀጥታ ነው የጠየኳቸው፤ ሁሉም ሰው ፈርቷል ፤ መልስ አይሰጥም። እኛ ግን አንፈራም ፤ እኛ ምንም ነገር አንፈራም። ሀገራችንን ለመከላከል አንፈራም ፤ ሩሲያን አንፈራም ፤ ከሩሲያ ጋር ለመነጋገር አንፈራም፤ ስለአገራችን የደህንነት ዋስትናዎች ለመናገር ፤ ስለማንኛውም…
#Update

" ብቻችንን አጋፍጠውናል " - ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ " ብቻችንን አጋፍጠውናል " ሲሉ ምዕራባውያንን ወቅሰዋል።

ዜሌኒስኪ " ሃገራችንን ለመጠበቅ በብቸኝነት እየተዋጋን ያለነው እኛው ነን " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

" ማን አግዞን ከጎናችን ሆኖ ተዋጋ? " ሲሉ የሚጠይቁት ፕሬዝዳንቱ " ማንም "ሲሉ መልሰዋል።

" ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደተወን ነው የተሰማኝ፤ እንደሚደግፉን ነበር ቃል ሲገቡልን የነበሩት፤ ሆኖም ሞትን እንድንጋፈጥ ብቻችንን ትተውናል " ሲሉም ነው ፕሬዝዳንቱ የተናገሩት፡፡

ዜሌንስኪ ሃገራቸው ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን የተናገሩ ሲሆን ይህን ማለቷ ግን ከፍራቻ እንዳልሆነ መጠቆማቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

@tikvahethiopia