TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን አሁን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የመጀመሪውን ዳታ ሴንተሩን አስመልክቶ ለሚዲያዎች ገለፃ ያደርጋል። በስፍራው የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ገለፃውን ተከታትለው ዝርዝር መረጃው ይልኩላችኃል። @tikvahethiopia
#Update

ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መግለጫ ፦

• ከፊታችን ሚያዝያ 1ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የተመረጡ የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት ይጀምራል። ከሚጀመሩ አገልግሎቶች መካከል ፦
- የጽሁፍ አገልግሎት፣
- የዳታ፣
- የድምጽ በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ የቴሎኮም አገልግሎቶች ናቸው።

• ከሰኔ በኋላ ሁሉንም የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት ይጀመራል።

• አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር ፣ ጎንደር ፣ ደሴ ኮምቦልቻ ፣ ሀረር ፣ ድሬዳዋና ጅግጅጋ አገልግሎቶቹ ከሚጀመርባቸው አካባቢዎች ዋነኞቹ ናቸው።

• በ07 መነሻ ኮድ አገልግሎት ይሰጣል።

• የኢትዮ ቴሌኮምን የቴሌኮሙንኬሽን መሰረተ ልማቶች ለመጠቀም ድርድሮች እየተደረጉ ነው።

• በያዝነው የፈረንጆቹ 2022 ዓመት ውስጥ 2 ተጨማሪ የመረጃ ማዕከላት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች ይገነባል።

• በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ውስጥ ለግማሹ ህዝብ የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት እቅድ አለው። በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ 98% ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን አገልግሎት የመስጠት እቅድ ተይዟል።

#አልዓይን

ፎቶ ፦ ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? ኡስታዝ ከሚል ሸምሱ ፦ " እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ሀገራችን ከሌሎች ሀገራት ያላትን ዲፕሎማሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለማሻሻል እና ዲፕሎማሲውም የሀገራትን የጋራ ጥቅም ያስጠበቀ እንዲሁም የሀገሩን ክብር እና ሉዓላዊነት በጠበቀ መልኩ እንዲጎለበት ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ። ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሀገራትን የፖለቲካ አስተላለፍ በመከተል ወዳጅ የነበሩ ሀገራት ጎራቸውን…
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሳዑዲ ስላሉ ዜጎች ጉዳይ የተናገሩት ፦

" ... ባለፉት ወራት ችግር ውስጥ እያለንም ቢሆን በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር መልሰናል ከሳዑዲ።

አሁን ችግሩ ምንድነው ሳዑዲ አረቢያ እንደመንግስት ሪፎርም እየሰሩ ነው። የሀገሬው ዜጋ ስራ እንዲሰራ ፣ እና ኢኮኖሚያቸውን ለማሻሻል ከውጭ የመጡ ሰዎች ከዚህ ቀደም የሚሰሯቸውን ስራዎች በራሳቸው ለመስራት እና ለመቀነስ ፍላጎት አላቸው። መብታቸውም ነው ትክክልም ናቸው፤ ተገቢ ነው ከእነሱ አንፃር።

ከእኛ አንፃር ፈተና አለብን። ፈተናው ምንድነው ሰዎቹ illegal /በህገወጥ/ የሄዱ ናቸው። ሁሉም ፓስፖርት ያለው አይደለም፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም፤ ሁሉም ከዚህ ሳዑዲ የሄደ መሆኑን ማወቅ ያስቸግራል፤ የሰለጠኑ ገዳዮች አሉበት ይባላል ብዙ ጉዳይ ነው የሚወራው ቁጥሩ ግን ከፍተኛ ነው መቶ ሺዎች ነው።

ዝም ብለም ብናመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደተለመደው የራሱን ዜጎች ተቸግሮም ቢሆን ቂጣም ጎመኑንም ተካፍሎ ይኖራል የሚለው ጠፍቶን ሳይሆን መከራ አብሮ እንዳይነጣ ቆም ብሎ ማጥናት ማስላት ስለሚፈልግ ነው።

ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር በቅርበት እየሰራን ነው። Delegation ሄዷል በቅርቡ ሚኒስትሪያል ኮሚቴ በክቡር ምክትል ጠ/ሚ ሚመራ ተቋቁሟል በደንብ አጥንተን ዜጎቻንን እንመልሳለን።

ስንመልስ ጥፋት የሚያስከትሉ ሰዎች ካሉ ጥንቃቄ እናደርጋለን ፣ እንደዛ አይነት ምልክቶች ስላሉ ስጋት ስላለብን ነው ነገሩን ያዝ አድርገን ቆም አድርገን እየሰራን ያልነው። ንፁሃን አሉ የሚጎዱ ለምሳሌ መቶ ሰዎች አብሯቸው አስር ሰዎች ካሉ አብረው ከመጡ በኃላ የሚደርሰው ጥፋት እና አደጋ በተለይ በነበርንበት ሁኔታ አደገኛ ነበር ለዛ ነው ትንሽ የተቸገርነው። እያየን መስመር የሚይዝ ይሆናል። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ ድርድር የተናገሩት ፦ " ... አንድ የእስራኤል ፕሬዜዳንት በአንድ ወቅት ያሉትን ማስታወስ ፈልጋለሁ፤ እኚህ ፕሬዜዳንይ እስራኤል እየተዋጉ ከሀማሶች ጋር ከሂዝቦላህ ጋር ይደራደራሉ። በነገራችን ላይ TPLF ከኦነግ ጋር ይደራደር ነበር፣ ደርግ ከሻዕቢያ እና TPLF ጋር ይደራደር ነበር ድርድር ማለት እርቅ ማለት አይደለም። ድርድር ውስጥ ብዙ የሚገኙ ነገሮች አሉ።…
#የተጠቃለለ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የሰጧቸው ምላሾች [ የተጠቃለለ ] በአጭሩ ቀርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለም/ቤት አባላቱ ምላሽ ከሰጡባቸው ጉዳዮች መካከል የኢኮኖሚ ሁኔታ ፣ የዋጋ ግሽበት / የኑሮ ውድነት፣ ሙስና ፣ የተፈቱ እስረኞችን በተመለከተ ፣ አፋርን በተመለከተ፣ ኦነግ ሸኔን በተመለከተ ፣ የልዩ ሀይሎች ጉዳይ ፣ ድርቅን በተመለከተ ፣ የዲፕሎማሲ ምደባ ይገኙበታል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Dr-Abiy-Ahmed-02-22
#ታላቁ_የኢድ_ስግደት !

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ የተናገሩት ፦

" ... ከፊታችን ረመዳን እየመጣ ነው። ያው እንደምታውቁት የመጀመሪያው ሂጅራ የሚባለው ፣ የመጀመሪያው የእስልምና እንቅስቃሴ የተጀመረው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው / የነበረው እንቅስቃሴ የመጣው ወደ ኢትዮጵያ ነው።

የሚቀጥለው ረመዳን ኢድ ታላቁ የኢድ ስግደት በኢትዮጵያ ይደረጋል። ይሄንን ታላቁን የኢድ ስግደት ከሁሉም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መጥተው ድምቀት እንዲሰጡት ይጠበቃል።

ብዙ የአረብ ሀገራት በቂ ሙስሊም ያለን አይመስላቸውም። ግማሽ የሚያህለው ሙስሊም ያለበት ሀገር እናም በእምነቱ ጠንካራ Values ያለው ህዝብ መሆኑን ለዓለም ለማሳየት እስካሁን የነበረው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ አሁን ሰፋ ባለ ደረጃ የሚታሰብ ነገር አለ።

ዳያስፖራ መጥቶ ኢድን ከእኛ ጋር እንዲያከብር ሀገር ውስጥ ያላችሁ ሙስሊም ወንድሞቻችን በየሀገሩ ያሉ ኢትዮጵያውያን መጥተው ከእኛ ጋር በጋራ ኢድን እንዲያከብሩ ብታደርጉ በጣም ጠቃሚ ይሆናል "

@tikvahethiopia
#CHINA

ሹዌ ቢንግ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ተሾሙ።

#ቻይና በአሁኑ ወቅት በግጭት እየታመሰ ላለው የአፍሪካ ቀንድ ሹዌ ቢንግን ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ መሾሟ ታውቋል።

ሹዌ ቢንግ ቀደም ሲል በፓፑዋ ኒው ጊኒ የቻይና አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። በአፍሪካ፣ በአሜሪካ እና በኦሺንያ የመሥራት ልምድ እንዳላቸው የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ዛሬ ማክሰኞ አስታውቋል።

@tikvahethiopia
ፕ/ር ካሣሁን ብርሀኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት (PSIR) ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ የነበሩት ፕ/ር ካሣሁን ብርሀኑ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ፕ/ር ካሣሁን በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 15/2014 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት አሳውቋል።

ፕ/ር ካሣሁን ላለፉት 36 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትና ተመራማሪነት እንዲሁም በልዩ ልዩ ከፍተኛ የኃላፊነት ዕርከኖች አገልግለዋል።

በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የተለያዩ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በማበርከትም ይታወቁ ነበር፡፡

የቀብር ስነ ስርዓታቸው ነገ የካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 በየካ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ይፈፀማል፡፡

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የሚመሩ 11 ኮሚሽነሮችን ሹመት በ5 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል። በዚህ መሰረት ፦ 1ኛ. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ (ሰብሳቢ) 2ኛ. ወ/ሮ ሂሩት ገብረስላሴ (ምክትል ሰብሳቢ) 3ኛ. ዶ/ር አይሮሪት መሐመድ 4ኛ. ዶ/ር ተገኝወርቅ ጌቱ 5ኛ. ዶ/ር ዮናስ አዳዬ 6ኛ. ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ 7ኛ. አምባሳደር…
የኮሚሽነሮቹ ጉዳይ ?

የኢፌዴሪ የህ/ተ/ም/ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽንን 11 ኮሚሽነሮችን ትላንት ማስፅደቁ ይታወሳል።

ም/ቤቱ ዛሬ ባወጣው ዝርዝር ማብራሪያ ከመጨረሻዎቹ 42 እጩ ኮሚሽነሮች ዝርዝር ውስጥ ያልተካተቱ እጩዎች ኮሚሽነር ሆነው ተሰይመዋል ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክል አይደለም ብሏል።

ም/ቤቱ 632 ጥቆማዎች መቀበሉ የገለፀ ሲሆን ከነዚህ መካከል 42 በአንደኛ ደረጃ እና 75 በሁለተኛ ደረጃ ምድብ ለማደራጀት መቻሉን አስረድቷል።

42 እጩዎች ከተለዩ በኋላ ከሲቪክ ማህበራት ፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ ከሀይማኖት ተቋማት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች የተውጣጡ ተወካዮች በእጩዎቹ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እንዲሰጡ መደረጉን ገልጿል።

በም/ቤቱ ድረ ገጽ እና የፌስ ቡክ ገፁ የተደራጀ የእጩዎች ፕሮፋይል በማስቀመጥ ለሁለት ሳምንታት የህዝብ አስተያየቶች መሰባሰቡን አስታውሷል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሰቢና ም/ ሰብሳቢን የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ ቢሯ ቸው በመጥራት በ42ቱ እጩዎች ላይ ያላቸውን ሀሳብና አስተያየት እንዲቀርቡ ተደርጓል ብሏል።

በተለያ መንገድ የተሰበሰቡ 2,890 አስተያየቶች በማደራጀት የእጮዎችን ሁኔታ እንደገና ለማየት እንደ ግብአት ተጠቅመና ያለው ም/ቤቱ በዚሁ መሰረት ብዝሃነትን ፤ጾታን እና አድሜን መሰረት ያደረገ ማስተካከያ ተደርጓል ብሏል።

አንዳንዶቹ በዜግነት ኢትዮጵያ ያለመሆናቸው በመረጋገጡ እና አንዳንድ እጩዎች ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጻቸው ከ42ቱ የእጩዎች ዝርዝር እንዲሰረዙና በምትካቸው በ2ኛ ደረጃ ከተለዩት መካከል ወደ 42ቱ ተካተው በድጋሜ ለህዝብ አስተያየት በድረ ገፁ ላይ ለህዝብ አስተያየት ይፋ መደረጉን ገልጿል።

ከአስተያየቶቹ በኋላ አስራ አንዱ ኮሚሽነሮች ተለይተው በህ/ተ/ምክር ቤት ተሰይመዋል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መግለጫ ፦ • ከፊታችን ሚያዝያ 1ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ የተመረጡ የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት ይጀምራል። ከሚጀመሩ አገልግሎቶች መካከል ፦ - የጽሁፍ አገልግሎት፣ - የዳታ፣ - የድምጽ በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ የቴሎኮም አገልግሎቶች ናቸው። • ከሰኔ በኋላ ሁሉንም የቴሌኮም አገልግሎቶችን መስጠት ይጀመራል። • አዲስ አበባ ፣ ባህርዳር ፣ ጎንደር ፣…
#SafaricomEthiopia

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ቃሊቲ አካባቢ በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የገነባውን የዳታ ማዕከል አስጎብኝቷል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላትም በስፍራ ተገኝተው ማዕከሉን ተመልክተዋል።

የዳታ ማዕከሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹን መረጃዎች የሚይዝበት ሲሆን የኢትዮጵያ ደንበኞቹ መረጃቸው በዚሁ በኢትዮጵያ ውስጥ ይቀመጣል።

ሳፋሪኮም ፤ የሙከራ የድምጽ ፣ የአጭር ጹሑፍ (SMS) እንዲሁም የዳታ ሙከራዎች አሁን ላይ በገነባቸው መሰረተ ልማቶች መሳካታቸውን ማረጋገጡን አሳይቷል።

ድርጅቱ አገልግሎቱን ሲጀምር የዳታ አገልግሎቱን በ #4G የሚያስጀምር ሲሆን #3G እንዲሁም #2G መጠቀምም ያስችላል።

#5G የኢንተርኔት አገልግሎትም ለመስጠት ከወዲሁ እየሰራ ነው።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዛሬ ያስጎበኘውን የዳታ ማዕከል በፎቶ ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር በዚህ ያንብቡ : telegra.ph/SafaricomEthiopia-02-22

@tikvahethiopia
#PP

የገዢው ብልፅግና ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአሁን ሰዓት ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

ስብሰባው በዐበይት ሀገራዊ ጉዳዮችና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
#US

አሜሪካ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ተዋጊዎች በአማራ ክልል በነሀሴ ወር መጨረሻ እና በመስከረም መጀመሪያ 2021 የጾታዊ ጥቃትን ጨምሮ አሰቃቂ ድርጊቶች መፈፀማቸውን የሚገልፁ ሪፖርቶች በጣም እንዳሳሰባት ገልጻለች።

ሀገሪቱ ይህን ያለችው በቅርቡ የወጣውን የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርትን ተከትሎት ትላንት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትቴር መስሪያ ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ነው።

ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱትን የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ጥቃት እንዲያቆሙ አሜሪካ ጥሪ አቅርባለች።

ለችግሩ ዘላቂ እልባት መስጠት እንዲቻል ለተፈጸመው ግፍ ተዓማኒነት ያለው ምርመራ ተደርጎ ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል የሚለው ጽኑ አቋሟ መሆኑንም ሀገሪቱ ገልፃለች።

አሜሪካ የጭካኔ ድርጊቶችን የሚገልጹት ሪፖርቶች ቀጣይነት ያለውን ወታደራዊ ግጭት በእስቸኳይ ማስቆም አስፈላጊ መሆኑን አጉልቶ ያሳያል ብላለች።

ግጭቶች እና የጭካኔ ድርጊቶች እንዲቆሙ፣ ሰብዓዊ እርዳታዎች በተሟላ ሁኔታ እንዲዳረስ እና ሰላማዊ የመፍትሔ መንግዶችን ለማፈላለግ ከግጭቱ ተዋናዮች ጋር ተቀራርባ መስራቷን እንደምትቀጥል አሳውቃለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት በቀድሞ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ዋና ዳሬክተር በነ አቶ ጌታቸው አሰፋ መዝገብ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከሰው የነበሩ 22 ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ30 ሺ ብር ዋስ አሲዘው ከእስር ተፈተው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጠ። ብይኑን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። ዋስትና ከተፈቀደላቸው መካከል የብሔራዊ መረጃ…
#Update

የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ 22 ሰራተኞች የስር ፍርድ ቤት የፈቀደውን የዋስትና መብታቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሻረ።

ውሳኔውን የሻረው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 1ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ነው።

የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንንነት ቢሮ ምክትልዳሬክተር አቶ ያሬድ ዘሪሁን እና የተቋሙ የፀረሽብር ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ኡርጌን ጨምሮ 22 ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ፍርድ ቤቱን ጠይቀው የነበረ ሲሆን ከሳሽ ዓቃቤ ህግም ዋስትናው ሊፈቀድ እንደማይገባ እና ተደራራቢ ክስ እንዳለባቸው በማመላከት ተከሳሾቹ ቢወጡ ላይመለሱ እንደሚችሉ እና ከህወሓት የሽብር ቡድን ጋር ሊቀላቀሉ ይችላሉ ሲል በመቃወም ዘጠኝ ነጥቦችን ጠቅሶ መቃወሚያ አስገብቶ ነበር።

መዝገቡን የመረመረው ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ በዛሬው ቀጠሮ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር በሁለት አብላጫ ድምጽ በአንድ ዳኛ ልዪነት ተከሳሾቹ ከነበራቸው ስልጣን አንጻር በወንጀለኛ መቅጭያ ስነስርአት ህግ አንቀጽ 67/ሀ መሰረት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታን ፣ በዋስ ቢወጡ ግዴታቸውን አክብረው ላይቀርቡ ይችላሉ የሚለውን ግምት በመያዝ እና ተደራራቢ ክስ የቀረበባቸው እና ቅጣቱን በመስጋት ቢወጡ ተመልሰው ላይመጡ ይችላሉ የሚል ግምት በመያዝ ጭምር ዋስትናውን መሻሩን ችሎቱ በጽ/ቤት አብራርቷል።

ባሉበት ማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ውሳኔ ተሰጥቷል።

More : https://telegra.ph/Update-02-23

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
#ሰዎች_ለሰዎች

ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት 15 ሚሊዮን ዩሮ መድቧል።

በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም እ.ኤ.አ 1981 ዓ.ም የተመሰረተው ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት በአርባ ዓመት ታሪኩ ከፍተኛውን በጀት መመደቡን አስታውቋል።

በዚህም 15 ሚሊዮን ዩሮ ማለትም 900 ሚሊዮን ብር በጀት ጸድቋል። ድርጅቱ ዘንድሮ የተቋቋመበትን 40ኛ ዓመት ያከብራል።

ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት እነ አቶ አብዲ ኢሌ ተቃውሞ አሰሙ። ዛሬ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረ-ሽብር እና የህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀረቡት የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ጨምሮ 17 ተከሳሾች ተቃውሞ አሰምተዋል። እነ አቶ አብዲ ኢሌ ከኛ ጋር ታስረው የነበሩት እስረኞች ተፈተው እኛ የምንታሰርበት ምክንያት የለም ሲሉ ነው ተቃውሞ ያሰሙት። …
#ችሎት

" የስነልቦና ጉዳት ስለደረሰብን ምስክር የመስማት ፍላጎት የለንም ስለዚህ ረጅም ቀጠሮ ይሰጠን " ሲሉ እነ አብዲ መሀመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ፍርድ ቤቱን ጠየቁ።

" ከሌሎች የተለየ ወንጀልሳንሰራ ሌሎች ዕስረኞች ተፈተው እኛ ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም " በማለት 2 ቀጠሮ የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ መሀመድ ኡመርን ጨምሮ 11 ተከሳሾች ችሎት ሳይቀርቡ ቀርተው ነበር።

ዓቃቤ ህግም ተገደው እንዲቀርቡ አልያም በሌሉበት ጉዳያቸው እንዲታይ ችሎቱን ጠይቆ ነበር።

ፍርድ ቤቱ መርምሮ በጉዳዩ ላይ ትዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጥሮ የነበረ ሲሆን፤ ነገር ግን በዛሬው ቀጠሮ ሁሉም ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ተከሳሾቹም የስነ ልቦና ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ባሉበት ሁኔታ ምስክር የመስማት ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለጽ እረጅም ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ከሳሽ ዓቃቤ ህግ በበኩሉ ጥያቄያቸው ከህግ አንጻር አሳማኝ አደለም ሆኖም እረጅም ቀጠሮ ቢሰጣቸው እንደማይቃወም አብራርቷል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ ቀሪ የአቃቢህግ ምስክሮችን ለመስማት ለመጋቢት 19 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የማህበር ቤት ምዝገባ ተጠናቀቀ። ባለፉት 25 ቀናት ሲካሄድ በቆየው የማህበር ቤት ምዝገባ 12 ሺህ 609 ቤት ፈላጊዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው ከመጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየውን የማህበር ቤት ምዝገባ መጠናቀቁን ገልጿል፡፡ ቢሮው በ2005 ዓ.ም በ20/80 እና በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ከተመዘገቡት ቤት ፈላጊዎች…
#AddisAbaba

የማህበር ቤት ፈላጊዎች ምዝገባቸውን ዳግም በአካል እንዲያረጋግጡ ተጠየቀ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ካሉት የቤት አቅርቦት አማራጮች አንዱ የሆነውን የማህበር ቤት ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ሁኔታዎች በማጠናቀቅ ማህበራቱ ወደ ተግባር የሚገቡበትን ሁኔታ ማመቻቸቱን ገልጿል።

ቢሮው ከአሁን በፊት ፍላጎት ያላቸውን ነባር የ20/80 እና 40/60 የማህበር ቤት ፈላጊዎች ተደራጅተው እንዲሰሩ በኦላይን ምዝገባ ማካሄዱን ነው ያስታወሰው።

ዛሬ ሩቡዕ ባወጣው ማስታወቂያ ደግሞ ከዚህ በፊት በኦላይን የተመዘገቡ የማህበር ቤቱ ፈላጊዎችን ከየካቲት 16 እስከ መጋቢት 16/2014 ዓ.ም ድረስ በኦላይን ያከናወኑትን ምዝገባ በአካል እንዲያረጋግጡ አሳውቋል።

ለዚህም በአዲስ አበባ በራሳችሁ / በትዳር አጋራችሁ ስም ቤት ወይም መስሪያ ቦታ የሌላችሁ ወይም በሽያጭ አለማስተላለፋቸውን የሚገልጽ ቅፅ ከሚኖሩበት ወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በመውሰድ በተጠቀሰው ጊዜ ብቻ ምዝገባውን እንዲፈጽሙ ጠይቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በማስታወቂያው ተመዝጋቢዎች ተጨማሪ መረጃ ከሚኖሩበት ክፍለ ከተማ የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ማግኘት እንደሚችሉ አሳውቋል።

@tikvahethiopia