TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ? ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ "የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት ጀመረ" የሚሉ በርካታ መልዕክቶች እየተዘዋወሩ ይገኛሉ። መንግስት በዚህ ጉዳይ በይፋ ያሳወቀው ነገር ባይኖርም ከዚህ ቀደም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ኃይል ለማመንጨት መቃረቡ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲሰራጩ ለነበሩት የግድቡ መረጃዎች ምንጫቸውን ለማወቅ ብናስስም ልንደርስበት…
#GERD

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ነገ እሁድ የካቲት 13 ቀን 2014 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር አጀንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ሁለት ስማቸው ያልተገለፀ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ በዛሬው ዕለት ዘግቧል።

ዛሬ አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣን [ስማቸው ያልተገለፀ] " ነገ የግድቡ የመጀመሪያው የሃይል ማመንጫ ይሆናል" ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ሌላ ሁለተኛ ከፍተኛ ባለስልጣን መረጃውን ማረጋገጣቸውን ገልጿል።

ሁለቱም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት ጉዳዩ በይፋ ስላልተገለፀ ነው ተብሏል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቅርቡ ኃይል ማመንጨት እንደሚጀምር የገለፀ ሲሆን መቼ ? ለሚለው ግን መረጃ አልሰጠም ነበር።

ይኸው ጉዳይ ባለፉት ቀናት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር ነበር፤ ነገር ግን በመንግስት በኩል ይፋዊ መረጃ አልተሰጠም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አንደኛው ሁኒት [ ዩኒት 10 ] ኃይል ማመንጨት መጀመሩን የግድቡ ሰራተኞች ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል። @tikvahethiopia
#GERD

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሆሮ ፦

"... ማመንጨት ተጀመረ እንጂ ፕሮጀክቱ ተጠናቀቀ ማለት አይደለም።

ፕሮጀክቱን ለመጠናቀቅ አሁን ብለው ሁኔታ ከሁለት ዓመት ተኩል እስከ ሶስት ዓመት ሊፈጅብን ይችላል።

ስለዚህ ህዝቡ ከመጀመሪያውም ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያውያን ፕሮጀክት ነው። ፋይናንስ ሚደረገው በመንግስትና በኢትዮጵያ ነው ስለዚህ ይሄን ተገንዝበን ፕሮጀክቱን እስከመጨረሻው ፋይናንስ ማድረግ አለብን።

የኢትዮጵያን እውነታ አሁን ተርባይኑን መቶ ነው ውሃ እየፈሰሰ ያለው ስለዚህ ኢትዮጵያ ከዚህ ውሃ ምንም የምትቀንሰው ነገር ስለሌለ ዓለምም ይህን እንዲረዳ እያንዳንዳችን ተረባርበን ለፕሮጀክቱ ዲፕሎማት ሆነን መንቀሳቀስ አለብን። "

@tikvahethiopia
#ITena

• በስትሮክ፣ በአደጋ፣ እና በሌሎች በሽታዎች ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለተፈጠረ አለመንቀሳቀስ (Paralysis)
• እድሜ በመግፋት ለሚፈጠሩ ጉድለቶች እንደ አልዛይመርስ፤ ዲሜንሻ
• ከተለያዩ ቀዶ ጥገናዎች ለማገገም
• በሙሉ (Coma) ወይም በከፊል የንቃተ ህሊና መቀነስ ላላቸው ታካሚዎች እንክብካቤ
• ለካንሰር እና ተከታታይ የህክምና ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች

👉በ 0901222233 ይደውሉልን

Telegram FB IG LinkedIn Twitter 🌍

🏥 አድራሻችን ጀሞ ከ ጀሞ ሞል 200m ገባ ብሎ፡፡
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሆሮ ፦ "... ማመንጨት ተጀመረ እንጂ ፕሮጀክቱ ተጠናቀቀ ማለት አይደለም። ፕሮጀክቱን ለመጠናቀቅ አሁን ብለው ሁኔታ ከሁለት ዓመት ተኩል እስከ ሶስት ዓመት ሊፈጅብን ይችላል። ስለዚህ ህዝቡ ከመጀመሪያውም ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያውያን ፕሮጀክት ነው። ፋይናንስ ሚደረገው በመንግስትና በኢትዮጵያ ነው ስለዚህ ይሄን ተገንዝበን ፕሮጀክቱን…
#የምስራች🎉

አባይ ኃይል መስጠት ጀመረ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዛሬ ኃይል መስጠት ጀምሯል።

ግድቡ ዛሬ ኃይል ማመንጨት የጀመረው ካሉት 13 ተርባይኖች ውስጥ በአንዱ ተርባይን አማካኝነት ነው።

አንዱን ተርንባይን በመጠቀም ወደ ስራ የገባው ግድቡ 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሙከራ ሂደት ሲያደርግ የነበረ ሲሆን የሙከራ ሂደቱ ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ኃይል መስጠት ጀምሯል።

ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ የግድቡን የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ሂደቱን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ፎቶ ፦ አሚኮ & TK.SS

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች ጋር በመሆን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ተርባይን ኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ስነ ስርዓት ላይ።

ፎቶ ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

@tikvahethiopia