TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NCDO

በወሎ እና በአፋር በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ።

#ነሲሓ_የበጎ_አድራጎትና_የልማት_ድርጅት (NCDO) በወሎ እና በአፋር በጦርነቱ ምክንያት ይበልጥ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።

ድርጅቱ ከሳምንት በፊት በአፋር ክልል ከሰመራ ከተማ በ270 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው ኢሪብቲ ከተማና በጭፍራ ከተማ በመገኘት በጀርመን ኮሎን ኤን አር ቬ የባርባሮሳ ፕላትስ ጓደኛማማቾች ጋር በመተባበር በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ እና ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።

ወሎ ውስጥ ከዓለም አቀፍ የሐረሪ ተወላጆችና ሐረሪ ደርሲ ጋር በመተባበር በኩታበር ወረዳ፣ በቦሩ ሜዳ፣ በሐይቅ ከተማ፣ በወረባቦና ቢስቲማ ከተማ በመገኘት ላለፉት ተከታታይ 3 ቀናት ከበጎ አድራጊ ግለሰቦች ያሰባሰበውን ድጋፍ ለተጎጂዎች አከፋፍለዋል። በወሎ ውስጥ ብቻ በጠቅላላ ለ1 ሺህ አባወራዎች የአንድ ወር አስቤዛ የተሰጠ ሲሆን፤

ለአንድ አባወራ፦
1) ዘይት: 1 ሊትር
2) ዱቄት: 10 ኪሎ
3) ሩዝ: 4 ኪሎ
4) ፓስታ: 4 እሽግ
5) መኮረኒ: 4 ኪሎ
6) የህፃናት አልሚ ምግብ እና ብስኩት
7) የተለያዩ ያገለገሉ አልባሳት ተበርክተዋል።

ጉዳቱ እጅግ የከፋ በመሆኑ የተነሳ ሌሎችም አካላት ርብርብ ያደርጉ ዘንድ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
#Belgium, #Brussels📍

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ቤልጂየም ብራሰልስ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከተነሳ ወዲህ ወደ ምዕራብ አውሮፓ ያደረጉት የመጀመሪያ ጉዟቸው ነው።

ወደ ብራሰልስ ያቀኑት በአፍሪካ ህብረት እና በአውሮፓ ህብረት የጋራ ጉባዔ ላይ ለመገኘት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጉባኤው ቀደም ብሎ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርልስ ሚቸል ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን ገልፀዋል።

የአውሮፓ ህብረት እና የኢትዮጵያን ግንኙነት፣ ቀጣናዊ እንዲሁም አህጉራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አሳውቀዋል።

በተጨማሪም በአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኧርፒላይነን ጋር ተገናኝተው ኢትዮጵያ ለዕድገቷ የምታደርጋቸውን ጥረቶች በተመለከተ መወያየታቸውንና አጋርነትን ለማጠናከር በሚያስችሉን አካሄዶች ላይ መምከራቸውን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#Afar

ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በህወሓት ጥቃት ምክንያት አፋር ውስጥ የደረሰውን የሰብዓዊ ቀውስ በሚዛናዊነት እንዳላየው የአፋር ክልል መንግስት ገልጿል።

አሁንም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እየደረሰ ያለውን ጉዳት እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርቧል።

የአፋር ክልል ፤ ህወሓት አፋርን ከትግራይ ክልል ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ላይ በፈፀመው ወረራ መጋሌ፣ በራህሌ፣ ኤረብቲ፣ እንዲሁም አብአላ ከተማን በመያዝ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች እንዲሰደዱ ፤ በሚወረውረው ከባድ መሳሪያም አቅመ ደካማ ወገኖች ለአካል ጉዳትና ለሞት መዳረጋቸውን ፣ ከዚህ ባለፈ ሆን ተብሎ ዝርፊያ እየተፈፀመ መሆኑን አስረድቷል።

የተፈናቀሉ ሰዎች በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን በተለያዩ ቦታዎች ተበትነው መጠለያ ጣቢያ ሊመጡ ያልቻሉ ወገኖች መኖራቸው ተገልጿል።

የአፋር ክልል ህዝብ ተገቢውን ትኩረት ያላገኘ ሲሆን ክልሉ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለአርብቶ አደሩ ፣ እየሞተ ላለው ማህበረሰብ ተገቢውን ትኩረት እንዳልሰጠ በመግለፅ ወቅሷል።

ማህበረሰቡ ከየትኛውም ጊዜ በላይ አሁን ላይ ድጋፍ የሚሻ መሆኑን አመልክቷል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰብዓዊነትን በእኩልነት እንዲያስተናግድ ፣ የደረሰውን ጉዳት በአካል ተገኝቶ ከመመልከት ጀምሮ ከህዝቡ ጎን እንዲቆም የአፋር ክልል ጥሪ አቅርቧል።

ክልሉ የጦርነቱ ሰለባዎችን ለመርዳት ጥረት እያደረገ ቢሆንም ከደረሰው ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት አንፃር በውስን አካላት ጥረት ችግሩን መቅረፍ እንደማይቻል አስገንዝቧል። መንግስት እና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ፣ የተራድኦ ድርጅቶች እጃቸውን እንዲዘረጉ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
" ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሆነ በመገናኛ ብዙሃን ትኩረት አልተሰጠውም " - የአፋር የአርብቶ አደር ማህበር

የአፋር የአርብቶ አደር ማህበር የአፋር ክልል ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሆነ በመገናኛ ብዙሃን ትኩረት አልተሰጠውም ሲል ወቅሷል።

ተፈናቃዮቹ ባሉበት አስከፊ ሁኔታ የሞት አደጋ ውስጥ መውደቃቸውን ገልጿል።

የማህበሩ አስተባባሪ የሆኑት ቫለሪን ብራውኒንግ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ የሰብዓዊ ድጋፍ ያንን ያህል ሰፊ ነው። በዚያ ላይ በተበታተነ ሁኔታ ላይ ነው የሚገኙት ይህም ሌላ ፈተና ነው። ምግብ የለም ፣ ውሀ የለም ፣ አስፈላጊ ነገሮች ሁሉ የሉም። የተፈናቀሉት ሰዎች በረሃብ በጥማት እና በበሽታ ምክንያት የሞት አሰጋ አንዣቦባቸዋል። " ብለዋል።

ማህበሩ በግመል እና በሌላም አማራጭ ተንቀሳቃሽ የጤና ባለሞያዎች ቡድን አሰማርቶ ተፈናቃዮችን ለመድረስ ጥረት አድርጎ የነበር ሲሆን መድረስ የቻለው ግን ጥቂቶችን ብቻ ነው። በርካቶች ወደ መጠለያ ጣቢያ ለመምጣት ስጋት አለባቸው።

ብራውኒንግ ፥ " ረጅም ርቀት የሚወነጨፉ ታንኮች እና ከባድ መሳሪያዎች ባስከተሉት ጉዳትና ይሄን ተከትሎ በፈጠረባቸው ጭንቀት ወደ መጠለያ ጣቢያዎች ለመምጣት ይፈራሉ ቤተሰቦቻቸውን ጭምር በጦርነቱ አጥተዋል። በዚህም በጣም ጭንቀት ውስጥ በመሆናቸው ወደ አስፓልት መንገዶች አይወጡም፤ አንድ ላይ መሆን አይፈልጉም፤ በሚችሉት ሁሉ ቤተሰቦቻቸው ለአደጋ ሳይጋለጡ የሚቆዩባቸውን ተግባር ነው የሚሰሩት " ብለዋል።

የአፋር የአርብቶ አደር ማህበር ተፈናቃዮች ያሉበት ሁኔታ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሆነ በመገናኛ ብዙሃን ተገቢው ትኩረት እንዳልተሰጠው ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።

@tikvahethiopia
የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማትና_እውቅና_ፈቃድ_የተሰጣቸው_የትምህርት_መስኮች.pdf
6 MB
#ETA

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀራቸውን አጠቃላይ የ350 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት መስኮቻቸውን የእውቅና ፈቃድ የሚገልጽ የተሟላ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

ከ350ው 330ዎቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ 20 ተቋማት በርቀት ትምህርት እውቅና የተሰጣቸው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በክልል መንግስታት የሚተዳደሩ ተቋማት ይገኙበታል።

የእውቅና ፈቃድ ባልታደሰባቸው የትምህርት መስኮች #አዲስ_ተማሪ_መቀበል_እንዳይችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ይፋ የተደረገው መረጃ እስከ የካቲት ወር ድረስ ያለውን የእውቅና ፈቃድ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል።

በሂደት ላይ ያሉ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ውሳኔ ሲያገኙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የእውቅና ፈቃድ ሲሰረዝና በሌሎች ምክንያቶች የውሳኔ ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት የመረጃ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል አሳውቋል።

በመሆኑም ፦
- ተማሪዎች፣
- ወላጆች፣
- ቀጣሪና የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች ፣
- የሚዲያና ማስታወቂያ ተቋማት ፣ እንዲሁም መላው ህብረተሰብ የተቋማቱን ወቅታዊ መረጃ በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል።

ተቋማት ይፋ ከተደረገው የእውቅና ፈቃድ መረጃ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ቢያስተምሩ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ባለስልጣኑ አሳውቋል፡፡

ይፋ በተደረገው መረጃ የማስተካከያ ጥቆማ የሚኖራቸው ተቋማት በህጋዊ ተወካዮቻቸው በኩል ለባለስልጣኑ ማሳወቅ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

[ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እውቅና ፈቃድ የተሰጣቸው የትምህርት መስኮች ከላይ በ #PDF ተያይዟል ]

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

ድርቅ ወገኖቻችን ክፉኛ እየጎዳበት ካለው የሀገራችን ክፍል አንዱ የሶማሌ ክልል ነው።

የክልሉ ካቢኔ የድርቁን አደጋ ምላሽ ለመስጠት 500 ሚልየን ብር ተጨማሪ በጀት እንዲፀደቅ ውሳኔ አሳልፏል።

ተጨማሪ በጀቱ በተለይም ለተለያዩ ምግቦች መግዣ ፣ ለውሃ ፣ ለጤናና ለእንሰሳት መኖ አቅርቦት የሚመደብ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም ካቢኔው በተለያዩ ደንቦችና ረቂቅ አዋጆች ላይ ውሳኔ በማሳለፍ ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል።

ካቢኔው ያፀደቀው ተጨማሪ በጀት፣ ደንቦችና አዋጆች ቅዳሜ የክልሉ ምክር ቤት በሚያደርገው ጉባኤ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

እንደ አዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መረጃ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ' 74 መኪናዎች ' ተሰርቀዋል።

ቁጥሩ ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ2 ጭማሪ አሳይቷል።

በከተማዋ የመኪና ስርቆት ጉዳይ አሁንም ድረስ መፍትሄ አልተገኘለትም ተብሏል።

Credit : Ethio FM

@tikvahethiopia
#MFAEthiopia

ሶስት ጉዳዮች ከዛሬው ሳምንታዊ የአምባሳደር ዲና ሙፍቲ [የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ] መግለጫ !

1ኛ. ህወሓትን ከአሸባሪነት የመሰረዝ ጉዳይ

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ " ህወሓትን ከአሸባሪነት የመሰረዝ ጉዳይን የኢትዮጵያ ደህንነት ይመለከተናል የሚሉ ሃይሎች እያነሱት ነው ፤ እስካሁን ግን የተወሰነ ነገር የለም " ብለዋል።

" እነዚህ ሀይሎች ከህወሓት ጋር ተደራደሩ እያሉን ነው " ያሉት አምባሳደር ዲና ፤ " እኛ ለምን እንደዚህ አላችሁ አንልም፣ የራሳችንን ሃሳብ ነው የምንሰጠው ፣ በዚህ ላይ መንግስት የወሰደው አቋም አለ "ሲሉ ተናግረዋል።

2ኛ. የ " ኤች አር 6600 " ጉዳይ

የአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በቅርቡ ያሳለፈው " ኤች አር 6600 " የተሰኘው የውሳኔ ኃሳብን በተመለከተ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ " የውሳኔ ሀሳቡ ቀረበው በኮንግረስ ነው፣ እኛ ግን ስለመቀራረብ እያወራን ያለነው ከአስተዳደሩ ጋር ነው " ብለዋል።

3ኛ. በሳዑዲ አረቢያ በስቃይ ላይ ስላሉ ወገኖች

በሳዑዲ እስር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ ሳዑዲ አረቢያ ሄዶ የነበረው ልዑክ የዜጎች ስቃይን አስመልክቶ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርጎ መመለሱን አምባሳደር ዲና አስታውቀዋል።

መንግስት ዜጎችን የመመለስ ግደታ አለበት ያሉት አምባሳደሩ ፤ መንግስት ለዚህ ልምድ እንዳለውና በእስር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ብሔራዊ ኮሚቴ በማቋቋም እዲመጡ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

በሳዑዲ አረቢያ እና በኢትዮጵያ መካካል የሚኖረው ግንኙት ዙሪያም “በእሰር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ካስወጣን በኋላ እናወራለን” ሲሉ ገልጸዋል።

#ከአልዓይ_ኒውስ

@tikvahethiopia
#GedeoZone , #Yirgachefe 📍

ከያቤሎ ወደ አዲስ አበባ 65 ሰዉ ጭኖ ስጓዝ የነበረ የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ 34983 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተገልብጦ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

አደጋው የደረሰው በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ " ቆንጋ ቀበሌ " ነው።

በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የ #ስድስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ አደጋ ደርሷል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በይርጋጨፌና ዲላ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሚገኝ የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Bank_of_Abyssinia

ጠንካራ ሴት ለመሆን የሚከፈለውን ዋጋ በደንብ እንረዳለን፣ ህልምዎና ፍላጎትዎ እንዲሳካ የአደይ ቁጠባችን ያግዝዎታል ! ባንካችን ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ያዘጋጀውን ። አደይ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ በመክፈት የልዩ አገልግሎቶቹና ጥቅሞቹ ተጋሪ ይሁኑ።

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://t.iss.one/BoAEth
TIKVAH-ETHIOPIA
#WaraJarso የወረ ጃርሶ ወረዳ ነዋሪዎች በታጣቂዎች እንቅስቃሴ ሰላማቸውን እንዳጡ መግለፅ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። በአካባቢው እንደሚንቀሳቀሱ የተነገረላቸው በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የሸኔ ታጣቂዎች እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ይገልፃሉ። ከወረዳ እስከ ዞን ከፍ ሲል እስከ ክልሉ መንግስት ድረስ ለአካባቢው መፍትሄ ይፈለግ ዘንድ አቤቱታ ቢቀርብም ተጨባጭ ለውጥ ሊመጣ አልቻለም። ከሳምንታት…
#ወረጃርሶ_ወረዳ

" መፍትሄ ያላገኘው የወረጃርሶ ወረዳ ጉዳይ "

ከጥቂት ቀናት በፊት በ " ወረጃርሶ ወረዳ " ስላለው ስጋት ፣ የፀጥታ ችግር፣ የዜጎች ታፍኖ መወሰድ፣ ግድያ፣ የንብረት ውድመት፣ የእህል ቃጠሎ ጉዳይ መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም። [ https://t.iss.one/tikvahethiopia/67499?single ]

ነዋሪዎች በፀጥታ ችግር መሰቃየት ከጀመሩ ረጅም ጊዜ ቢቆዩም መፍትሄ ግን እንዳላገኙ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ነበር።

በዞን ፣ በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ኤቤቱታ ቢያቀርቡም ምላሽ ስላላገኙ ከሳምንታት በፊት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የፌዴራል መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ነዋሪዎች ጥቃት እየደረሰባቸው ያለው በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪነት በተፈረጀው የሸኔ ታጣቂ ኃይል መሆኑን ይገልፃሉ።

ከሳምንታት በፊት በዚሁ አካባቢ ጉዳይ አንድ የኦሮሚያ ክልል መንግስት የፀጥታ ኃላፊ የሸኔ እንቅስቃሴ ከክልሉ በላይ እንዳልሆነ በቡድኑ ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የቀሩ ካሉ አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣ ተናግረው ነበር።

ከሰሞኑን በወረዳው በርካታ ንፁሃን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ግድያ መፈፀሙ ተሰምቷል። እስካሁን በርካታ ሰዎች መገደላቸው የተነገረ ሲሆን ቤተሰቦች መርዶ እየተነገራቸው ነው።

በዚህ ጥቃት ምክንያት ትላንት ጎሃፅዮን ላይ ህዝባዊ ሰልፍ ተደረጎ መከላከያ ወደ አካባቢው እንዲገባ ጥሪ ቀርቧል።

የወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ ለአሚኮ በሰጠው ቃል በወረዳው የሸኔ ታጣቂዎች እንቅስቃሴ እየሰፋ በመምጣቱ ተጨማሪ የፀጥታ ኃይል እንዲላክ ክልሉን መጠየቁን ገልጿል። ስለሰሞኑን ግድያ መረጃ አለኝ የሚለው ፖሊስ ገዳዮቹን እያሰስኩ ነው ብሏል።

@tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ውጤት መቼ ይገለፃል ?

በርካታ የ ' ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ' ተማሪዎች ፣ ወላጆች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መቼ እንደሚገለፅ መረጃ እንድናጋራቸው ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ባገኘው መረጃ መሰረት የ12ኛ ክፍል የሁለተኛ ዙር ፈተና እርማት እየተጠናቀቀ ይገኛል።

እስከ የካቲት 15 ድረስ ዘገየ ቢባል እስከ የካቲት 20 ድረስ የውጤት ስራው ተጠናቆ ሊገለፅ እንደሚችል ሰምተናል።

ውጤት ከተገለፀ በኃላ በፍጥነት ወደ ምደባው እንደሚገባ የተገለፀልን ሲሆን በጣም ዘገየ ቢባል እስከ የካቲት 30 ድረስ ተማሪዎች ምደባቸውን እንዲያውቁ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ተብለናል።

ከምደባው በፊት ግን ቅሬታዎችን ቀድሞ ለመፍታት ይረዳ ዘንድ አዎንታዊ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ማመልከቻቸውን በፍጥነት እንዲያስገቡ ተጠይቋል።

ማመልከት የሚችሉት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ፣ መስማት የተሳናቸው እና የማየት ችግር ያለባቸው ተማሪዎች፣ ልዩ ልዩ የጤና ችግር ያለባቸው ተማሪዎች፣ የሚያጠቡ እናት ተማሪዎች ፣ የተመሳሳይ ጾታ መንትዮች ሲሆኑ ዝርዝር መረጃ በዚህ ይገኛል [ https://t.iss.one/TikvahUniversity/2623 ]

በሌላ በኩል ፤ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ስለ ፈተና እርማት ጠይቀናቸው እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልፀውልናል።

በሁለተኛ ዙር ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ጋር አብሮ እንደሚገለጽ ነግረውናል።

ተማሪዎች እና ወላጆች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ መልዕክት እናስተላልፋለን።

@tikvahethiopia
#Update

የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ከዚህ ቀደም በሃገር አቀፍ ደረጃ በታወጀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታግደው የነበሩ አገልግሎቶች ከሰኞ የካቲት 14 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚጀምሩ አሳውቋል።

ኤጀንሲው ፥ ከ #አዲስ_የነዋሪነት_መታወቂያ_አገልግሎት ውጭ ከሰኞ የካቲት 14/2014 ጀምሮ የታገዱ አገልግሎቶች እንደሚጀምሩ እና በሁሉም ክ/ከተማ በየወረዳው በተዘጋጀ መርሃ ግብር ነዋሪው እንዲስተናገድ መልዕክት አስተላልፏል ።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

ሜጀር ጀነራል መሠለ በለጠ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ሁነው ተሾሙ።

የአማራ ክልል መንግስት ክልሉ የገጠመውን የህልውና አደጋ በአግባቡ በመመከት የህዝቡን የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ ማድረጉን ዛሬ የካቲት 10 አሳውቋል።

በዚህም፦

1. የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር የፀጥታ አማካሪ ፤

2. የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጀነራል መሠለ በለጠ የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ዋና አዛዥ ሁነው ተሹመዋል ።

@tikvahethiopia