TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መግለጫ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ዛሬ " ለዜጎች መብት መከበር የሚሟገተው ጋዜጠኛ መብት ይከበር " በሚል መግለጫ አውጥቷል።

ማህበሩት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት መሻሻል እያሳየ እንደነበርና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ሲመሰክሩ እንደነበር አስታውሷል።

ይሁንና ይህ መሻሻል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሸረሸረ መሄዱን በብዙ ማሳያዎች መግለጽ እንደሚቻል እና ይህንንም የተለያዩ ማሳያዎች በመጥቀስ አብራርቷል።

(ከማህበሩ የተላከውን ሙሉ መግለጫ በዝርዝር ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተፈርዶበታል

በጣልያን ሀገር ገጠራማ ስፍራ በሆነችው ፍራሲሎንጎ ከተማ ፍየሎችን እያረባች በአይብና በፍየል ምርቶቿና በጠንካራ ሰራተኝነቷ የታወቀችውን ኢትጵያዊቷን አጊቱ ጉደታን ቤቷ ውስጥ እያለች በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው የ33 ዓመቱ ጋናዊ ስደተኛ ሱሌይማን አዳምስ 20 ዓመት እስር ተፈርዶበታል።

የትሬንቶ ፍርድ ቤት ሰኞ ዕለት በዋለው ችሎት ጋናዊው ሱሌይማንን በነፍስ ማጥፋት ወንጀል 15 ዓመት ከስምንት ወር እንዲሁም አራት ዓመት ከአራት ወር ወሲባዊ ጥቃት በመፈጸም ፍርድ አስተላልፎበታል።

በተወሰነው ቅጣት ቤተሰቧ ደስተኛ አይደለም።

ኢትዮጵያ ውስጥ የምትገኘው የአጊቱ እህት ሀወኒ ኤዳዎ ጉደታ ለቢቢሲ በሰጠችው ቃል ቤተሰቧ ፍርድ ቤቱ በገዳዩ ላይ ያሳለፈው የእስር ቅጣት በቂ ነው ብሎ እያምንም ብላለች።

ሀወኒ ኤዴዎ " ምንም እንኳን ቅጣቱ እሷን የሚመልሳት ባይሆንም፣ ከተፈጸመው ወንጀል አኳያ ውሳኔው በቂ አይደለም። እኛ የእድሜ ልክ አስራት ይፈረዳል ብለን ጠብቀን ነበር" ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።

@tikvahethiopia
ሸይኽ ቃሲም ሀጂ አልአሩሲ አርፈዋል።

ታላቁ አሊም ሸይኽ ቃሲም ሀጂ አልአሩሲ በህክምና እርዳታ ላይ እያሉ ማረፋቸው ተሰምቷል።

ሸይኽ ቃሲም ሀጂ አልአሩሲ በሀገራችን ኢትዮጵያ ለሱናው መስፋፋት የአንበሳውን ድርሻ ከሚወስዱት ግንባር ቀደም አሊሞች መካከል እንደነበሩ ተነግሯል።

በተጨማሪ በርካታ ለዲኑ የሚለፉ ወጣቶችን እና አሊሞችን ማፍራት የቻሉ እውቅ አሊም እንደነበሩ ተገልጿል።

በዳዕዋ ጉዟቸውም ብዙ ፈተናዎችን ያስተናገዱ አሊም ነበሩ።

መረጃውን ከኢትዮጵያ እስልምና እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንዲሁም ከኡስታዝ አቡበከር አህመድ ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

3 ጉዳዮች ከዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ፦

1ኛ. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከዛሬ የካቲት 8/2014 ጀምሮ ቀሪ የሚሆንበት የውሳኔ ሃሳብ በ63 ተቃውሞ፣ በ21 ድምፀ ታአቅቦ፣ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።

2ኛ. የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ በሁለት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ እና የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ ለማደንገግ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በአንድ ተቃውሞ፣ በሶስት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል፡፡

3ኛ. የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ለዝርዝር እይታ ለከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA 3 ጉዳዮች ከዛሬው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ፦ 1ኛ. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከዛሬ የካቲት 8/2014 ጀምሮ ቀሪ የሚሆንበት የውሳኔ ሃሳብ በ63 ተቃውሞ፣ በ21 ድምፀ ታአቅቦ፣ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል። 2ኛ. የመንግስት ሰራተኞች ጡረታ ለመደንገግ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ በሁለት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ እና የግል ድርጅቶች ሰራተኞች ጡረታ ለማደንገግ የቀረበውን ረቂቅ…
#መንግሥት እና የ #ግል ሠራተኞች ጡረታን ለመደንገግ የቀረበው አዋጅ ምን ይዟል ?

ለመንግሥት ሠራተኞች ፦

• የተሻሻለው የጡረታ ዐዋጅ የጡረታ ዕድሜን ጣራ ' 60 ዓመት ' እንዲሆን እና ጡረተኛው በሕይወት ሳለ የሚያገኘው የጡረታ መጠን ሲያልፍ ለትዳር አጋር 50 በመቶ የጡረታው ተጠቃሚ እንዲሆን ይፈቅዳል።

• የፖሊስና መከላከያ መዋጮ ከግለሰቡ የሚደረገው ሌሎች የግልና የመንግሥት ሠራተኞች እንደሚያዋጡት 7 በመቶ ሆኖ ከመንግሥት አካል የሚደረግለት መዋጮ ግን ወደ 33 በመቶ ከፍ እንዲል ተደርጓል።

ለግል ድርጅቶች ሠራተኞች ፦

• በድርጅቶች ምክንያት ሳይዋጣ የቀረን ገንዘብ በሦስት ወር ውስጥ ገቢ ካልተደረገ በቀጥታ ድርጅቱ ካለው ማንኛውም የባንክ አካውንት ገቢ እንዲደረግበት ያስገድዳል።

• የግል ድርጅት ባለቤቶች በድርጅቱ ሠራተኛ ሆነው በጡረታ ማዕቀፉ ውስጥ እንዳይገቡ አዋጁ አግዷል።

• ከ10 ዓመት በላይ ያገለገለ ሠራተኛ ዕድሜው ለጡረታ በሚደርስበት ጊዜ የዕድሜ ልክ ጡረታ ተከፋይ እንዲሆን አዋጁ ይፈቅዳል።

• የሚሰበሰበው የጡረታ መዋጮም ወደ ኢንቨስትመንት በማስገባት ገቢን ማሳደግ ለጡረተኞች የክፍያ ማሻሻያ የሚያደርግበትን እድል ይፈጥራል።

• አንድ አሰሪ የ ግል ድርጅት ፍቃዱን በሚያድስበት ወቅት የሠራተኞቹን መዋጮ ካላስገባ ፍቃዱ የማይታደስበት አስገዳጅ አንቀጽም ተካቷል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነሳ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሃገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቷል። ምክር ቤቱ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የወሰነው። ይህን ውሳኔ ተከትሎ÷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ስራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት…
" አሁንም ከእስር ያልተለቀቁ ሰዎች በአፋጣኝ ከእስር ይለቀቁ " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየካቲት 8 ቀን 2014 ዓ/ም ከጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተለይ በሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ እንዲነሳ መወሰኑን ኮሚሽኑ በበጎ መመልከቱን ገልጿል።

ኮሚሽኑ በአስቸኳይ ሁኔታ ወቅት ከአዋጁ አተገባበር ጋር ተያይዞ በቁጥጥር የዋሉ እና አሁንም ያልተለቀቁ ሰዎች በአፋጣኝ እንዲለቀቁ በድጋሚ አሳስቧል።

በተጨማሪ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቁጥጥር ስር ውለው የተለቀቁ ሰዎችም በእስር ስለመቆየታቸው ማረጋገጫ ባለማግኘታቸው ወደ ስራ መመለስ አለመቻልን ጨምሮ ለተለያዩ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውን ባደረገው ክትትል መገንዘቡን ኮሚሽኑ ገልጿል።

ስለሆነም ሰዎች በእስር የቆዩበትን ጊዜ ማስረጃ እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች የመስጠቱን ሂደት እንዲፋጠንና ሰዎች ወደ መደበኛ ሕይወታቸው መመለስ እንዲችሉ እንዲደረግ ኢሰመኮ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ምንድነው የሆነው ?

• " በፋብሪካው ላይ የተፈጸመ ጥቃት የለም " - የስኳር ኮርፖሬሽን ቃል አቀባይ አቶ ረታ ደመቀ

• " ነዳጅ አጥቶ ቆሞ ነበር። ዛሬ ደግሞ ሥራ ጀምሯል " - የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኛ

የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ በአካባቢው ካለ የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የስኳር ምርት ሥራውን አቋርጦ እንደነበር የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ገለፀ።

ኮርፖሬሽኑ ይህን የገለፀው ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ነው።

የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ረታ ደመቀ በአካባቢው ባለው የደኅንነት ችግር ምክንያት ወደ ፋብሪካው ነዳጅ ማቅረብ ባለመቻሉ ከየካቲት 02/2014 ዓ.ም ወዲህ አቁሞ እንደነበር ተናግረዋል።

" ብሉምበርግ " የዜና ምንጭ ፤ " ፋብሪካው ሥራውን ለማቆም የተገደደው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር እያለ የሚጠረው እና መንግሥት ሸኔ የሚለው ታጣቂ ቡድን በፋብሪካው ላይ ባደረሰው ጥቃት ነው " ሲል ዘግቦ ነበር።

የስኳር ኮርፖሬሽን ቃል አቀባይ በፋብሪካው ላይ ጥቃት ተፈጽሞበታል ምባሉን ትክክል እንዳልሆነ ገልጸዋል።

አቶ ረታ ፥ " በአከባቢው የደኅንነት ችግር ስላለ እንጂ በፋብሪካው ላይ የተፈጸመ ጥቃት የለም ፤ ምክንያቱ የነዳጅ አቅርቦት ችግር ነው " ብለዋል።

አሁን ላይ ነዳጅ ፋብሪካው ጋር በመድረሱም ፋብሪካው ወደ ሥራ እንደሚመለስ ገልጸዋል።

አንድ ስሙን መናገር ያልፈለገ የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኛ በተመሳሳይ ፋብሪካው ሥራውን አቋርጦ የነበረው በነዳጅ እጥረት እንጂ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት እንዳልሆነ ተናግሯል።

ሰራተኛው " ፋብሪካው ነዳጅ አጥቶ ቆሞ ነበር። ዛሬ ደግሞ ሥራ ጀምሯል " ሲል መናገሩን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
'ኸልት ፕራይዝ'

' ዓለም አቀፍ አሸናፊዎች 1 ሚሊዮን ዶላር 💵 ሽልማት ይበረከትላቸዋል '

የዓለም አቀፍ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ውድድር " ኸልት ፕራይዝ " በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከየካቲት 5 ጀምሮ መካሄድ ጀምሯል።

"ኸልት ፕራይዝ" ተማሪዎችን ማዕከል ያደረገው እና በዓለም ላይ ላሉ የተለያዩ ማህበራዊ ተግዳሮቶች መፍትሄ ይሰጣሉ ተብለው የሚታሰቡ የቢዝነስ ሃሳቦች ላይ የሚያተኩር ዓለም አቀፍ ፕሮግራም ነው።

ይህ ፕሮግራም በተለይ የተለያዩ የቢዝነስ ሃሳብ እና የስራ ፈጠራ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች ዓላማቸውን ማሳካት እንዲችሉ ይረዳል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተሳታፊነት ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ የተዘጋከው ውድድር ከካዛና ግሩፕ ጋር በመተባበር ሲሆን እስከ መጋቢት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ይካሄዳል።

ከ100 በላይ ቡድኖች ተመዝግበው 35 ቡድኖች ተመርጠዋል።

በቀጣይ ስልጠና መርሀግብር ያለ ሲሆን ከስልጠናው በኃላ ለዳኞች ቀርበው የተመረጡ በአፍሪካ ደረጃ ኢትዮጵያንና አ/አ ዩኒቨርሲቲን ወክለው ይወዳደራሉ።

ቲክቫህ "ኸልት ፕራይዝ" አስተባባሪዎች እንደሰማው ለውድድር ለሚሳተፉ የምዝገባ ጊዜ ቢጠናቀቅም የተደራጀ ሀሳብ በቡድን ይዘው ለሚመጡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተማሪዎች ብቻ ቀሪ ጥቂት ቦታዎች አሉ።

በተጨማሪ የቢዝነስ ሃሳብና የስራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ስልጠና በቅርቡ የሚጀምር ሲሆን መሳተፍ የሚፈልጉ የማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

ስልጠናው በአካል በአ/አ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች ነው የሚሰጠው።

የተደራጀ ሀሳብ ያላቸው የAAUና AASTU ተማሪዎች ለመመዝገብ👇
forms.gle/vtUQb5meNevymea87

ስልጠናውን መሳተፍ የሚፈልጉ👇
forms.gle/7sXqfktgrVzU1SpDA

@tikvahethiopia
#የካቲት2010

የ2010 ዓ/ም በተለይም የካቲት ወር በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በርካታ ክስተቶች የተስተናገዱበት ፤የካቲት 8 ደግሞ ታሪካዊ ቀን ተብሎ ሊመዘገብ የሚችል ነው።

ለረጅም ዓመታት በእስር ቤት እንዲማቅቁ የተፈረደባቸው ፖለቲከኞች ፣ የሃይማኖት አስተማሪዎች፣ በርካታ ወጣቶች ከእስር እንዲፈቱ የተደረገበት ፤ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ ያስገቡበት ወር ነው።

ከብዙ ትውስታዎች በጥቂቱ ፦

- መላው ሀገሪቱ ከፍተኛ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ የነበረችበት ወቅት ነበር።

- በበርካታ ከተሞች በተለይ በኦሮሚያ ክልል እና አማራ ክልል እንዲሁም በደቡብ ክልል የወጣቶች የ #ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ላይ ተቃውሞ እጅግ የበረታበት ነበር። ተቃውሞው እስረኞች እንዲለቀቁ፣ ፍትህ እንዲሰፍን፣ መንግስት ዜጎችን መግደል እንዲያቆም ሲጠየቅበት የነበረ ነው።

- በተለይ በኦሮሚያ ክልል እጅግ በርካታ ከተሞች ፣ በአማራ ፣ በደቡብ ክልሎች በሚገኙም ከተሞች መንግስትን በመቃወም የስራ ማቆም እና ቤት የመቀመጥ አድማ የተደረገበት ወር ነበር።

- መንግስት እስረኞችን ለመፍትታ የወሰነበት በዚህም ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ (በወቅቱ) ጉዳያቸው በህግ ተይዞ የነበሩ 329 ተጠርጣሪዎች ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንዲለቀቁ የወሰነበት በአጠቃላ 746 እንዲፈቱ የተባለበት ወር ነበር።

- እነ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ፣ አቶ አንዱአለም አራጌ፣ አቶ አበበ ቀስቶ እና አቶ እስክንድር ነጋ የይቅርታ መጠየቂያ ደብዳቤ አንፈርምም ያሉበት ወር ነው።

- ከሰባት እስከ ሃያ ሁለት አመታት እስር የተበየነባቸው የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት አንዳችም ያጠፋነው ጥፋት የለም በሚል "የምንጠይቀውም ይቅርታ የለም " የይቅርታ ፎርም አንፈርምም ያሉበትም ወር ነው።

- የ2010 የካቲት ወር የኦፌኮው ከፍተኛ አመራር አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ጉርሜሳ አያና፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ጌቱ ጋሩማ፣ አቶ ተስፋዬ ሊበን እና አቶ በየነ ሩዳ ከእስር የተለቀቁበት ነው።

- የዞን ዘጠኞቹ (የቀድሞ) እነ አቶ በፍቃዱ ኃይሉ ፣ አቶ አጥናፍ ብርሃኔ እና አቶ ናትናኤል ፈለቀ ክስ የተቋረጠበት ወር ነበር የካቲት 2010 ዓ/ም።

- እነ አቶ አዱአለም አራጌ ፣ አቶ እስክንድር ነጋ ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ፣ አቶ ኦልባና ለሌሳ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታየ ፣ አርቲስት ሴና ሰለሞን ፣ አርቲስት ኤልያስ ክፍሉ ፣ ወ/ሮ ጫልቱ ታከለ ፣ ወ/ሮ እማዋይሽ ፣ አቶ ማሙሸት አማረ፣ ኦኬሎ አኳይ (የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዘዳንት)፣ አቶ አንዱአለም አያሌው ፣ እነ አቶ ብርሀኑ ተክለያሬድ ከእስር የተለቀቁበት ወር ነበር።

* የካቲት 8 / 2010 (በዛሬዋ ቀን) የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከኢህአዴግ ሊቀመንበርነት እና ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡበትና ይህንኑም በመግለጫ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያሳወቁበት ቀን ነበር።

- በ2010 የካቲት ወር የሚንስትሮች ምክር ቤት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በሁሉም ሀገሪቱ ክፍል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ የወሰነበት እና ወደ ምክር ቤት የመራበት ነበር።

- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአስቸኳይ ስብሰባ የካቲት 23/2010 ዓ/ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በ395 ድጋፍ፣ በ88 ተቃውሞ እና በ7 ድምጸ ታእቅቦ ያፀደቀበት። በኃላም የተፈጠረው የቁጥር ስህተት መነጋገሪያ ነበረበት በወቅቱ አፈጉባኤ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ ህዝብን " ይቅርታ " የጠየቁበት ወር ነበር።

- የአዋጁ መታወጅ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲከሰት ያደረገም ነበር። በነበሩ ግጭቶች ቀደም ብሎ በወሩ ውስጥ በነበሩ ተቃውሞዎች በርካታ ወጣቶች የተገደሉበት ነበር።

- የአማራ ክልል በጎንደርና ጭልጋ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ የ224 ተጠርጣሪዎች ክስ ያቋረጠበት።

- የጎንደሯ ወጣት ንግስት ይርጋ ከእስር የተፈታችበት ወር ነው (የካቲት 13 ቀን 2010) ።

- የኢትዮጵያ መንግስት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌን (አሁን በህይወት የሉም) ጨምሮ 18 ሰዎች በይቅርታ እንዲፈቱ የወስነበት ወር ነው።

- የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አደርገዋል ተብለው የተከሰሱት ኮሎኔል አንተነህ ደምስ፣ ኮሎኔል አለሙ ጌትነት፣ ብ/ጀነራል አሳምነው ፅጌ (አሁን በህይወት የሉም)፣ ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ከእስር የተፈቱት በዚሁ የካቲት ወር ነው።

- የኦህዴድ (የቀድሞ የኢህአዴግ አባል ድርጅት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ዶ/ር ዐቢይ አህመድን ሊቀመንበር አድርጎ የመረጠበት ወር ነው። (ዶክተር ዐቢይ የአሁን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር /የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዜዳንት ናቸው)

- ሱማሌ ክልል 1500 እስረኞችን ከእስር የፈታበት ነው።

- የቀድሞው ሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበሩት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከእስር የተፈቱበት ወር ነው። እሳቸው ሁለት ጊዜ "ፈርመው እንዲወጡ" ተብሎ ሲጠየቁ ወንጀል እንዳልፈፀሙ በመግለፅ የይቅርታ ፎርም ላይ አልፈርምም ብለው ነበር። (አሁን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ናቸው)

(ከላይ የዘረዘርናቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ ገፃችን በየካቲት ወር 2010 ላይ ከተለዋወጥናቸው በርካታ መረጃዎች / በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሂደት በወሩ ውስጥ ከታዩ ክስተቶች ጥቂቶቹን ያስታወስንበት ነው)

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
1.4 MB
#ሪፖርት

የህወሓት /TPLF/ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል ገብተው በቆዩባቸው ጊዜያት ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ በሲቪሎች ላይ ግድያ እና የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ከሐምሌ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተቆጣጥረዋቸው በነበሩ አካባቢዎች፤ ከጦር እና በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸም ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ ወንጀሎችን ስለመፈጸማቸው የሚያመለክቱ ማስረጃዎች መኖራቸውን አምነስቲ ገልጿል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል " የትግራይ ኃይሎች በአማራ ክልል ከተሞች የሚገኙ በርካታ ንጹሃን ሰዎችን ሆነ ብለው ገድለዋል ፣ ሴቶች እና ታዳጊዎችን አስገድደው በቡድን ደፍረዋል፤ እንዲሁም የግል እና የሕዝብ ንብረት አውድመዋል " ብሏል።

የህወሓት ታጣቂዎች በጭና እና ቆቦ ከተሞች እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙ ስፍራዎች ላይ ጥቃት ያደረሱት ከነሐሴ 2013 ዓ.ም. አጋማሽ እስከ መስከረም 2014 ዓ.ም. መጀመሪያ ባሉት ጊዜያት ነው።

ታጣቂዎቹ በአካል ላይ ከሚደርሱት ጥቃቶች በተጨማሪ የግድያ ማስፈራሪያዎች፣ ብሔር ተኮር ስድቦች እና ማንቋሸሾች በተጠቂዎች ላይ ሲደርሱ ነበር።

ቆቦ ላይ ከታጣቂ ነዋሪዎች እና ከሚሊሻዎች የገጠማቸውን መገዳደር ለመበቀለ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የበቀል እርምጃ ሲወስዱ እንደነበር አምነስቲ ሪፖርት አድርጓል።

የህወሓት/TPLF/ታጣቂዎች ተቆጣጥረዋቸው በነበሩ በእንዚህ የአማራ ክልል አካባቢዎች ዓለም አቀፍ መሠረታዊ የሆኑ የሰብዓዊ ሕጎችን አለማክበራቸውን ገልጿል።

(ሙሉ ሪፖርት በPDF ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት.pdf
#ሪፖርት

ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል (የፆታዊ ጥቃት) ፦

(ቢቢሲ)

ከሐምሌ ወር 2013 ዓ/ም ጀምሮ በጭና እና በዙሪያዋ እድሜያቸው 14 የሚሆኑ ሴት ታዳጊዎችን ጨምሮ የህወሓት ታጣቂዎች በርካታ ሴቶችን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ መድፈራቸውንና አስገድደው ምግብ እንዲያበስሉላቸው አድርገዋል።

ቃላቸውን የሰጡት 14 የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎች በቡድን፤ አንዳንዶቹ ልጆቻቸው ፊት መደፈራቸውን ተናግረዋል።

አንዲት የ7ኛ ክፍል ተማሪ እና 14 ዓመት ታዳጊ ከእናቷ ጋር በመኖሪያቸው ድር-ባሕር በህወሓት ታጣቂዎች መደፈሯን ተናግራለች።

ይህች ታዳጊ ፥ "ረፋድ 5 ሰዓት አካባቢ መሳሪያ የያዙ ሁለት ወጣቶች ወደ ቤታችን ሲመጡ ከእናቴ እና ከአያቴ ጋር ነበርኩ። አንደኛው የወታደር ልብስ ነው የለበሰው ሌላኛው ደግሞ የሲቪል ልብስ። ትግርኛ እና አማርኛ እየቀላቀሉ ነው የሚያወሩት። 'ቤተሰቦቻችን ተደፍረዋል አሁን እናንተን የምንደፍርበት ተራ ነው' አሉን። አንደኛው ከቤት ውጪ እኔን ደፈረኝ። ሌላኛው ደግሞ ቤት ውስጥ እናቴን ደፈረ። እናቴ አሁን ታማለች። . . . ምን እንደተፈጠረ አናወራም" ስትል ተናግራለች።

የ29 ዓመቷ ሰላም ለ15 ሰዓታት በዘለቀ ቆይታ እንዴት 4 የህወሓት ታጣቂዎች እየተፈራረቁ አስገድደው እንደደፈሯት ተናግራለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተነሳ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሃገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስቷል። ምክር ቤቱ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የወሰነው። ይህን ውሳኔ ተከትሎ÷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ስራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት…
#USA

አሜሪካ በኢትዮጵያ ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዙ አዋጅ እንዲነሳ መወሰኑን በመልካም ጎኑ እንደምትቀበል ገልፃለች።

ውሳኔው እየቀጠለ ያለውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ለሚደረገው ጥረት በኢትዮጵያ መንግሥት የተወሰደ አንድ አዎንታዊ እና በጎ እርምጃ ነው ብላዋለች።

አሜሪካ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቷ ባወጣችው መግለጫ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደመነሳቱ አዋጁን ተከትሎ በቁጥጥር ሥር የዋሉ እና ክስ ያልተመሰረተባቸው ሰዎች በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቃለች።

የእስረኞች መፈታት ሁሉን አካታችና ውጤታማ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ ያስችላልም ብላለች።

አሜሪካ ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ፣ ያልተቋረጠ የሰብአዊ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን ፣ በሁሉም የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ጥቃቶች ላይ ግልፅ ምርመራዎች እንዲደረጉ እና ግጭቱን በድርድር እንዲፈታ ከሁሉም አካላት ጋር መነጋገሯንና መጣሯን እንደምትቀጥል ገልፃለች።

@tikvahethiopia