TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቋሚ ሲኖዶስ ሰላማዊ እና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቤተክርስቲያንን መብት ለማስከበር እንደሚሰራ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የመስቀል አደባባይ፣ የጃንሜዳና ልሎች የቤተክርስቲያን ይዞታዎች ጉዳይ በተመለከተ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ይዞት በነበረው ቀጠሮ ዙሪያ ባካሔደው ስብሰባ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የሚደረገው ውይይት…
#update
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት በአሁን ሰዓት ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ስብሰባ ተቀምጠዋል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አልተገኙም።
በስብሰባው ያልተገኙት ቀድሞ በተያዘው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባ መሆኑ ተገልጿል።
ከተማ አስተዳደሩን በመወከል ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተገኝተዋል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ እና በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ለመነጋገር ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጥሪ አስተላልፎ ነበር።
ቅዱስ ሲኖዶስ ከመስቀል አደባባይና ሌሎች የኦርቶዶክሳውያን ላይ በተከሰቱ ችግሮች ዙርያ ዛሬ የካቲት 4 ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር በመወያየት ላይ ይገኛል።
በስብሰባው ላይ ከአቶ ዣንጥራር አባይ በተጨማሪ አቶ ጥራቱ በየነ የሥራ አስኪያጅ ፣ ዶ/ር ቀንአ ያደታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ፣ አቶ ተተካ በቀለ እና አቶ አለማየሁ እጅጉ ከአዲስ አበባ ብልጽግና ፖርቲ ተገኝተዋል።
ፎቶ፦ EOTCTV
@tikvahethiopia

#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት በአሁን ሰዓት ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ስብሰባ ተቀምጠዋል። የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አልተገኙም። በስብሰባው ያልተገኙት ቀድሞ በተያዘው የአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባ መሆኑ ተገልጿል። ከተማ አስተዳደሩን በመወከል ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ተገኝተዋል። ቅዱስ ሲኖዶስ…
#Update
የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የፊታችን ማክሰኞ በመንበረ ፓትርያርኩ የቋሚ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይገኛሉ።
ያሉትን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትም ቀጠሮ ተይዟል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በመስቀል አደባባይ ጉዳይ እና በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ለመነጋገር ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል።
በስብሰባው ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር አባይ ከሌሎይ ኃላፊዎች ጋር ከቋሚ ሲኖዶሱ ጋር ምክክር አድርገዋል።
በዚህም ስብሰባው ከንቲባዋ በተገኙበት የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 8 እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ቋሚ ሲኖዶስ በሌሎች አጀንዳዎች ውይይቱን መቀጠሉ ተገልጿል።

#Sumuni
ስራ ፈጣሪዎችን ከባለሀብቶች ጋር የሚያገናኝ መተግበሪያ " ስሙኒ " ምንድነው ? እንዴትስ ላግኘው ?
ትላንት " ስሙኒ " የተሰኘ ኩባንያ ከኮካ ኮላ ቢቭሬጅስ አፍሪካ-ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ስራ ፈጣሪዎችን ከባለሀብቶች ጋር የሚያገናኝ በመተግበሪያ እንዲሁም በድህረገጽ በይፋ አስጀምረዋል።
ስሙኒ የሥራ ፈጠራ ባለቤቶችንና ባለሃብቶች ማገናኛ በስራ ፈጠራ ስነምህዳር ውስጥ ያሉ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚገናኙበት እና የሚተሳሰሩበት የኦንላይን መድረክ ነው።
መድረኩ የውጭ ኢንቨስተሮች በሀገር ቤት ስታርታአፖች ላይ መዋለ ንዋይ እንዲያፈሱ በማስቻል ምንዛሪ በማስገኘት እንዲሁም የውጭ ኢንቨስትመንት በመሳብ ለኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት እድገት ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ታምኗል።
በተጨማሪም በባለድርሻ አካላት መካከል የኢኮኖሚ ትስስርና ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ለሀገሪቱ ዕድገት አስተዋፅዖ ያደርጋል።
ኮካ ኮላ ቤቭሬጅስ በስሙኒ መገናኛ መተግበሪያ በኩል በዚህ ዓመት ለ10 ስታርታፖች ለእያንዳንዳቸው 100,000 ብር ስራ ማስጀመሪያ ይሰጣል፡፡
በተጨማሪም 10,000 የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን፣ ወጣት ስራ ፈጣሪዎችን እና አነስተኛ የንግድ ባለቤቶችን አቅም ለመገንባት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የክህሎትና የዕውቀት ድጋፍ በማድረግ ከሌሎች ኢንቨስተሮችን የማገናኘት ስራ ይሰራል፡፡
መተግበሪያውን እና ድረገፁን እንዴት ላግኘው ?
ድረገፁ : https://139.59.95.164/sumuni.net/index.php
መተግበሪያው : https://play.google.com/store/apps/details?id=com.sumuni.sumuni_new

#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከመስቀል አደባባይ፤ ወይብላ ማርያም እና ባንዲራ ጋር ተያይዞ ማብራሪያ ሰጡ።
ከንቲባዋ ማብራሪያውን የሰጡት በከተማው ምክር ቤት ስበስባ ላይ ለተነሳ ጥያቄ ነው።
ወ/ሮ አዳነች በመስቀል አደባባይ የፕሮቴስታንት አማኞች የጠየቁት የገቢ አሰባሰብ ፕሮግራም ፍቃድ መሰጠቱትን ገልፀዋል።
ፕሮግራሙ ሊካሄድ አንድ ቀን ሲቀረው አንድ ከፕሮግራሙ ጋር ግንኙነት በሌለው ሰው እንወርሳለን የሚል ሃሳብ መንፀባረቁን ያስታወሱት ከንቲባዋ " ይህም በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቁጣ የፈጠረ " መሆኑን ገልፀዋል።
" በኃላም ግንኙነት ስናደርግ ይህን ያለው ከፕሮግራሙ ጋር ግንኙነት የሌለው ሰው መሆኑን ነግረናቸው ፤ ነገር ግን በዚህም ወገን ያለው አባባልና እሱን መሰረት አድርጎ የተፈጠረውን ስሜት ሁለቱም ሃይ ሊባሉ ይገባል አልናቸው " ሲሉ አስረድተዋል።
ወይዘሮ አዳነች ፥ " ጉዳዩ ጠንከር እያለ ሲሄድ በፕሮግራሙ እለት ተገኝተን ይሄ አደባባይ የሁላችንም ነው በማለት ማንም ወራሽ እና ተወራሽ እንደሌለ የሚጠቁም መልእክት አስተላልፈናል ይህ አባባል በዛ መድረክ ሲነገር የመጀመርያ አልነበረም፤ ሌሎችም ተናግረዋል፡፡ እኔ ራሴ ደጋግሜ በተለያዩ ፕሮግራሞች ተናግርያለሁ፡፡ " ብለዋል።
ጉዳዩን አሁን እንዲባባስ ያደረገው የተጫጫኑ ስሜቶች በመኖራቸው ምክንያት ነው ሲሉም ገልፀዋል።
አክለው ፥ " ጥያቄው ሲገፋ ያልነው በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንፍታ ነው ያልነው፡፡ በመረጃና በማስረጃ መፍታት የሚቻልባቸው ብዙ አማራጮች አሉ። " ብለዋል።
" ግንኙነት ለማድረግ ከመጀመርያው አንስቶ ብዙ ጥረት ተደርጓል " ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ " ከመጀመርያው የፓትርያርኩ መታመም አንስቶ በተለያዩ ምክንያቶች ተራዝሟል፡፡ " ብለዋል።
" እኔ በግሌ ፓትርያርኩ ጋር በመሄድም ጉዳየን በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ እንፍታ ብዬ አነጋግርያለሁ፡፡ ልዩነት አልነበራቸውም፡፡ ይህንን ሃሳባችሁን በደብዳቤ አስገቡልን አሉን ይህንንም አድርገናል " ሲሉ አስረድተዋል።
ከንቲባው ፥ " ከዚህ ቀደም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ እኛ ወደነሱ እሄዳለን፤ እነርሱም ወደእኛ እየመጡ በርካታ ጉዳዮችን ፈትተናል፡፡ ዛሬ እንኳን ግንኙነት ቀጠሮ አለ ስለተባለ የተወሰነው እዚህ ሆነን ጉባኤውን እናስኪድ ሌሎቻችን ደግሞ እዛ እንሂድ ብለን ተከፋፍለን ነው የሄዱት፡፡ እኛ ከሃይማኖት ጋር ፉክክር የምናደርግ መሪዎች አይደለንም " ሲሉ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ " ከወይብላ ማርያም ጋር የተከሰተው ክስተት አሳዛኝና መሆን ያልነበረበት ጉዳይ ነበር፡፡ እኛም ከልባችን አዝነናል። በምንም መንገድ ታቦት ውጪ ማደር አልነበረበትም፡፡ ጉዳዩ አሁን በህግ ተይዟል፡፡ እውነታውን አውቀን በህግ ተጠያቂ እስካላደረግን ድረስ ይቅርታ ብቻውን በቂ አይደለም " ብለዋል ።
" ከባንዲራ ጋር ተያይዞም የሚነሱ የተለያዩ ሃሳቦች አሉ፡፡ ይህ ጉዳይ የብሄራዊ ምክክር አጀንዳችን ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ጥልም ግጭትም በፍፁም አንፈልግም፡፡ ሰውም እንዲሞት አንፈልግም ጉዳዮችን ሁሉ ከፖለቲካ ዝንባሌ ጋር ማያያዝም ተገቢ አይደለም። " ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።
ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ።

ኣቡነ ኣንጦንዮስ ማረፋቸው ተሰማ። 3ኛው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የነበሩት ኣቡነ ኣንጦንዮስ ማረፋቸውን የቢቢሲ ትግርኛ አገልግሎት ዘግቧል። ኣቡነ ኣንጦንዮስ ለበርካታት አመታት በቁም እስር ላይ ነበሩ። የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን 3ኛው ፓትሪያርክ አቡነ ኣንጦኒዮስ እስከ 1998 ዓ.ም ድረስ ቤተክርስቲያኒቱን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ከሀይማኖቱ ተቃራኒ የሆነ አመለካከት…
የአቡነ እጦንኒዮስ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ።
ሶስተኛው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ እጦንኒዮስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ትላንት ሰፋአ በሚገኘው የትውልድ መንደራቸው እንድርያስ ገዳም መፈፀሙ ታውቋል።
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ በርካታ ህዝብ መሰብሰቡን፣ ብዙዎቹም ረጅም ርቀት በእግር ተጉዘው የመጡ መሆናቸውን የአካባቢውን ምንጮች ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ዘግቧል።
መንግሥት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይግባ በሚለው ጠንካራ አቋማቸው እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በመጠየቃቸው እኤአ በ2006 አንስቶ ከቤተክርስቲያኒቱ መሪነታቸው እንዲነሱ መደረጋቸውና እኤአ በ2017 ለአጭር ጊዜ ከተፈቀደላቸው እና ወዲያው ከተቋረጠው በስተቀር እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በቁም እስር እንዲቆዩ ተደርገዋል።
አስመራ ከተማ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባወጣው የሃዘን መግለጫ ከ15 ዓመታት በላይ የቁም እስር ላይ በቆዩት የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንጦንዮስ ማለፍ ከፍተኛ ሀዘን ተሰምቶናል ብሏል።

#Tigray , #Mekelle 📍
የዓለም ጤና ድርጅት ( #WHO_Ethiopia ) 33. 5 ሜትሪክ ቶን የሚገመት አስፈላጊ የሆኑ መድሃኒቶችን እና የህክምና ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ክልል ማጓጓዝ መጀመሩን አስታውቋል።
ድርጀቱ በቀን 10 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁስ ወደ ትግራይ ክልል ይገባል ብሏል።
በዛሬው ዕለትም 10 ሜትሪክ ቶን የህክምና ቁሳቁሶችን በአውሮፕን ወደ ትግራይ ክልል መግባቱን አስታውቋል።
ፎቶ፦ WHO Ethiopia

#ETHIOPIA
#Amazon እና #eBay ላይ በርካሽ ለሽያጭ ስለቀረቡት ቅርሶች የዘርፉ ባለሞያዎች ምን አሉ ? የኢትዮጵያ መንግስት ስለጉዳዩ የማያውቀው ነገር አለ ?
በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች እንደ ebayና Amazon ባሉ የመገበያያ ገጾች ላይ በርካሽ ዋጋ ለሽያጭ ቀርበው ታይተዋል።
ከኢትዮጵያ የተወሰዱ እንደሆኑ የተገመቱ ቅርሶች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢንተርኔት የመገበያያ መድረኮች ለሽያጭ መቅረባቸውን ከሰሞኑን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘግቡት ነበር።
ቅርሶቹ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት ከትግራይ ክልል ተሰርቀው ሳይሆን አይቀርም የሚል ጥርጣሬን አጭሯል።
🗣 ከቢቢሲ ኒውስዴይ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረጉት የቋንቋ ታሪክ ተመራማሪ እና በሐምቡርግ ዩኒቨርስቲ የድኅረ ዶክትሬት ተማሪ የሆኑት ዶክተር ሐጎስ አብረሃ ተከታዩን ብለዋል ፦
" በጦርነቱ ወቅት ከበርካታ የትግራይ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናትን ቅርሶች መዘረፋቸውን አረጋግጫለሁ።
በወቅቱ ከተዘረፉት ቅርሶች አንዳንዶቹ ጥንታዊና እጅግ ብርቅዬ የነበሩ ናቸው።
ከኢትዮጵያ የተዘረፉት ቅርሶች በብዛት እየተሸጡ ያሉበት ዋጋ እጅግ ርካሽ የሚባል ነው።
በዚህ ወቅት እንዴት ተዘርፈው ከአገር ሊወጡ እንደቻሉ ማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ በሱዳንና ኬንያ በኩል ሊሆን ይችላል "
🗣 የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ የተናገሩት ፦
" ቅርሶቹ ያለምንም ጥያቄ የኢትዮጵያ ቅርስ ናቸው። ቅርሶቹ የወጡት ቀድሞ ነው ወይንስ አሁን በጦርነቱ ምክንያት የሚለውን ግን በአሁኑ ወቅት ለመመለስ አስቸጋሪ ነው።
የዓለም ቅርሶችን የሚጠብቀውና ፓሪስ የሚገኘው የተመድ የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) ቅርሶቹ የኢትዮጵያ ስለሆኑ ለሽያጭ እንዳይውሉ እና ወደ አገር ቤት መመለስ እንዲችሉ አዲስ አበባ ከሚገኘው የድርጅቱ ኃላፊ ጋር ዛሬ ጥዋት ተነጋግረናል።
በጦርነት ወቅት በርካታ ቅርሶች ለውድመት፣ ለስርቆት፣ ለዝርፊያ ይጋለጣሉ።
ቅርሶች በጎብኝዎችና ሌሎች እንዳይወጡ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ጠንካራ ቁጥጥር ይደረጋል። ይሁንና በእንዲህ ያለው የጦርነት ጊዜ ሰዎች በድንበር በኩል መውጣታቸው ስለማይቀር ይዘዋቸው የሚወጡ ቅርሶች ይኖራሉ።
አጠቃላይ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት ውድመት የደረሰባቸው ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ቅርሶች ምን ያህል እንደሆኑ ጥናት ሲደረግ እንደቆየ እና የጥናቱ ውጤት በቅርቡ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል "
ያንብቡ : https://telegra.ph/ETHIOPIA-02-11

Telegraph
ETHIOPIA
#ETHIOPIA Amzon እና eBay ላይ በርካሽ ለሽያጭ ስለቀረቡት ቅርሶች የዘርፉ ባለሞያዎች ምን አሉ ? የኢትዮጵያ መንግስት ስለጉዳዩ የማያውቀው ነገር አለ ? በርካታ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች እንደ ebay እና Amazon ባሉ የመገበያያ ገጾች ላይ በርካሽ ዋጋ ለሽያጭ ቀርበው ታይተዋል። ከኢትዮጵያ የተወሰዱ እንደሆኑ የተገመቱ ቅርሶች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በኢንተርኔት ለሽያጭ መቅረባቸውን የዓለም…
" ማለቂያ የሌለውን የዜጎቻችንን ሰቆቃ መስማት ራሱ ያሳቅቃል " - ኦፌኮ
ሳውዲ ዓረቢያ ውስጥ እየተሰቃዩ ስለሚገኙ ዜጎቻችንን አስመልክቶ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) መግለጫ አውጥቷል።
ኦፌኮ በመግለጫው ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በጅምላ እስር ቤት ታጉረው ያሉ ዜጎቻችን ያሉበት ሰቆቃ እጅግ ያሰቅቃል ብሏል።
ፓርቲው ፥ " ብዙ ነገሮች ለተወሰኑ ጊዜያት ቀርተውብን መንግስት የእነዚህን ወገኖቻችንን ሕይወት ቢታደግ የተሻለ ነው የሚሉ ወገኖች ቁጥር ቀላል አይደለም " ያለ ሲሆን ይህንን ሐሳብ እንደሚደግፍ ገልጿል።
ኦፌኮ እስካሁን ብዙዎችን በሞት ተነጥቀናል መንግስት የቀሪ ወገኖቻችንን ሕይወት ለማትረፍ አስቸኳይ ዕርምጃ እንዲወስድ እንማፀናለን ብሏል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አባል የሆነበት " ስታር አሊያንስ " የአየር መንገዶች ሕብረት በ 2022 የአየር ትራንስፖርት ሽልማት ላይ ለ 4ኛ ጊዜ የ “ምርጥ የአየር መንገዶች ሕብረት” ሽልማትን ተቀዳጅቷል።
" ስታር አሊያንስ " 26 አየር መንገዶችን በአባልነት የያዘ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን የአየር መንገዶች ሕብረት ከተቀላቀለ አስር አመታትን አስቆጥሯል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

#GERD #ItsMyDam 🇪🇹
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለአል-አረቢያ ሚዲያ የተናገሩት ፦
" ... ሀገራችን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን በፍጥነት እንድታጠናቅቅ ግብፅ ማበረታታት አለባት።
ግድቡ ግብፅን በድርቅ ወቅት እንኳ የውሃ ቋት ሆኖ የሚያገለግል እንደመሆኑ ፕሮጀክቱን ልትደግፈው ይገባል።
ሱዳን በአነስተኛ ግድቦቿ ላይ ይደርስብኛል ብላ የምታነሳውን የደህንነት ስጋት በሚመለከት መደበኛ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ ኢትዮጵያ ዝግጁ እንደሆነች አቋሟን አስርድታለች።
ሀገሪቱ ግን አሁን ላይ የራሷን ብሄራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ይልቅ የሶስተኛ ወገን ጉዳይ አስፈፃሚ አየሆነች መጥታለች።
ኢትዮጵያ አንድ ወገን ብቻ ከአባይ ሀብት ተጠቃሚ ሲሆን ዘላለም አለሟን መጠበቅ አትችልም። በመሆኑም ሱዳን እና ግብፅ አሁን ላይ ከያዙት ግትር አቋም መላቀቅ አለባቸው።
ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ በሚመለከት ብዙ አዎንታዊ የሆኑ እድሎችን አቅርባ ነበር። ግብፅና ሱዳን ባለመቀበላቸው ምክንያት ግን ሳይሳኩ ቀርተዋል።
የህዳሴ ግድብ ከጭቅጭቅ ይልቅ የቀጠናዊ ህብረትና አንድነት ማሳያ ነው። ኢትዮጵያ በታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ላይ ምንም አይነት የጎላ ጉዳት ሳታደረስ የራሷን ሀብት መጠቀም ትችላለች "
(ኤፍቢሲ)

Photo
የአዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ መኪና ማቆሚያ ፦
ነገ እንደሚመረቅ የሚጠበቀው አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ ከምድር በታች 4 ወለል የመኪና ማቆሚያ እንዳለው እና እስከ 1500 መኪና ማቆም እንደሚችል ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ባንኩ እንደገለፀው ፥ በሁለተኛው ምድር ቤት የሚገኘው የመኪና ማቆሚያ በዓይነቱ ለየት ያለና ዘመናዊ ሜካኒካል መኪና ማቆሚያ ነው።
ይህም በአንድ ጊዜ 541 መካከለኛ መኪኖችን ደራርቦ ማቆም እና በካርድ መኪኖችን መጥራት የሚያስችል መሳሪያ የተገጠመለት መሆኑ ተብራርቷል።
አውቶማቲክ መሳሪያው ብልሽት ሲኖር የሚጠቁም እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመጠገን የሚያስችል ሲስተም እንዳለውም ተገልጿል።
የታዋቂው የቻይናው " ዳያንግ ፓርኪንግ " ስሪት የሆነ መሳሪያ እንደተገጠመለት የተገለፀው ይህ መካኒካል መኪና ማቆሚያ በጥቂት ቦታ ብዙ መኪኖችን ማቆም የሚያስችል የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤት መሆኑን ባንኩ ይፋ ያደረገው መረጃ ያሳያል።