TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር) ፦ • የፈተና መሰረቅ ከግለሰብ ይልቅ ተቋማዊ እየሆነ በመምጣቱ ፤ በአጠቃላይ የደረሰብን የሞራል ክስረት ከፍተኛ ነው። • የእኔ ክልል ተማሪዎች ማለፍ አለባቸው በሚል በተቋም ደረጃ የፈተና ወረቀቶችን በመስረቅና መልስ በመስጠት ጭምር ተባባሪ የሆኑ አመራሮች መኖራቸው የትምህርት ሲስተሙ ጥራት ተዓማኒነት ከፍተኛ ጥያቄ ዉስጥ ገብቷል። • ግማሹ ለፍቶ…
የብሄራዊ ፈተና ጉዳይ ?
በትምህርት ሚኒስቴር የዕቅድ እና ሀብት ማፈላለግ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ግርማ ፦
" የአገር አቀፍ ፈተናው በቴክኖሎጂ ተደግፎ በኦንላይን ሥርዓት ታግዞ ካልተሰጠ የምዘናው ሥርዓት አደጋ ውስጥ ነው "
የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ፦
" የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዘና ጉዳይ የሚመለከታቸው ተቋማትን ብቻ ሳይሆን መንግሥትንም የፈተነ ነው።
የፀጥታ ችግር ፈተናውን ለመስጠት አዳጋች ካደረጉት ጉዳዮች ተጠቃሹ ሲሆን፣ ከሰሞኑ በሁለተኛ ዙር በተሰጠው የ2013 ዓ.ም. አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና እንኳን 150 የሚደርሱ ተማሪዎችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ወስዶ ለመፈተን ከ100 በላይ የፀጥታ ኃይል ባልደረባ እጀባ አስፈልጎ ነበር።
በዚህ የተነሳ አገር አቀፍ ሁለተኛ ደረጃ ፈተናን የመስጠት ሥራ ከኤጀንሲው አቅም በላይ ለመንግሥትም ፈተና ሆኗል።
አገራዊ ፈተናው የሚሰጥበት ዋና ዓላማ፣ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ አንዱ መሣሪያና የብቁ ዜጋ ማፍሪያ መለኪያነቱን ታሳቢ በማድረግ ቢሆንም፣ በዚህ ወቅት ከዚህ ዓላማ ውጪ መስመሩን ስቶ ራሱን የቻለ ትልቅ ፈተና ሆኗል።
በሌላ በኩል ፈተናው ፖለቲካዊ ይዘትን እየተላበሰ መጥቷል። አገርን በሚገነባ ዕሳቤ ሳይሆን፣ " ከእኔ ክልል ይህን ያህል አለፈ " ወደሚል ጤናማ ያልሆነ ውድድር ውስጥ እንደተገባ ነው።
ከኤጀንሲው አቅም በላይ የሆነውን ይህንን ችግር መንግሥት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። በተለይ ከላይ የተነሱትን ችግሮች ለመፍታት ብቸኛው መንገድ፣ ፈተናውን በዲጂታል መንገድ በኦንላይን መስጠት ነው "
[ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተናግሩት - ሪፖርተር ]
@tikvahethiopia

#AnbesaCityBus
አንበሳ የከተማ አውቶብስ እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጀ እንደሚገኝ አስታወቀ።
ድርጅቱ እስከ የለሊት አገልግሎትን ለመስጠት ተገልጋዮች የሚበዙባቸውን የአዲስ አበባ አካባቢዎች የመለየት ስራ እያከናወነ ሲሆን ጥናቱ ሲጠባቀቅ እስከ ምሽት 3 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡት አውቶብሶች እስከ ለሊት 6 ሰዓት ወደ ስራ እንደሚያስገባ ገልጿል።
የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ምስክር ማንደፍሮ፥ " አሁን እስከ 3 ሰዓት ብቻ ነው አገልግሎት የሚሰጡት ከዚህ በኃላ በምንጀምረው አዲስ አገልግሎት እስከ ለሊት አጋማሽ ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ የትኞቹ መስመሮች ለእንደዚህ አይነት ስራ ተጋላጭ ናቸው / የትኞቹ መስመሮች አምሽተው የሚሰሩ በዛ በምናስበው ሰዓት ከስራቸው የሚወጡ ማህበረሰቦች አሉ የሚለውን ጥናት እያደረግን ነው፤ ጥናቱን ከጨረስን በኃላ የተወሰኑ እንደ ዲሞንስትሬሽን የምንጀምረው አሰራር ይኖራል " ብለዋል።
አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት የቀኑን የትራንስፖርት እጥረት ለመፍታት የአዲስ አበባ አስተዳደር ይገዛቸዋል የተባሉትን 3 ሺህ አውቶብሶች እየጠበቀ እንደሚገኝ እና አውቶብሶቹን እንደተረከበ በመጠሉ ችግሩን ለማቃለል እንሞክራለን ሲል አሳውቋል።
አሁን ላይ አምበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት 630 አውቶብሶች ያሉት ሲሆን በ125 መስመሮች በቀን ውስጥ እስከ 600 ሺ ያህል ሰዎችን እንደሚያጓጉዝ ገልጿል።
ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

#SafaricomEthiopia
ሳፋሪኮም - ኢትዮጵያ በሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ ሥራ እንደሚጀመር አሳውቋል።
የድርጅቱ የቁጥጥር እና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ማቲው ሃሪሰን ሃርቬይ ከመንግስት ጋር ያላቸው ስምምነት እንደሚያሳየው ፍቃድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በዘጠኝ ወር ወደ ስራ መግባት እንደሚኖርባቸው ገልፀው ከመጪው ሚያዝያ ወር ጀምሮ በይፋ የንግድ ሥራ ለመጀመር እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።
ኃላፊው ይህን የገለፁት ለካፒታል ጋዜጣ ነው።
እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 9፣ 2021 ጀምሮ የሚቆጠር የመሥሪያ ፍቃድ ያገኘው ሳፋሪኮም ቴሌኮሙኒኬሽን ኢትዮጵያ በሀገሪቱ የቴሌኮም ማስፋፊያ ስራዎችን ጀምሯል።
ባለፈው ወር የኩባንያው የመጀመሪያ የመረጃ ማዕከል ስራ የጀመረ ሲሆን ኩባንያው የኔትወርክ ዝርጋታውን እየሰራ ነው።
ማቲው ሃሪሰን ሃርቬይ ሳፋሪኮም ከ2 የኔትወርክ አቅራቢዎች ኖኪያ እና ሂዋዌ ጋር እየሰራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በአዲስ አበባ እና አካባቢው ያለውን የኮር ኔትወርክ መሠረተ ልማት በኖኪያ ኩባንያ እንደሚሰራ ሁዋዌ ቀሪውን የአገሪቱን ክፍል እንደሚሸፍን አስረድተዋል።
" የመሰረተ ልማት መጋራት በተመለከተም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እስካሁን በድርድር ደረጃ ላይ ነን " ሲሉም አክለዋል።
ከመሰረተ ልማት ጎን ለጎን የሳፋሪኮም ደንበኞች እና የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች እንዲገናኙ ለማድረግ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑን ገልፀዋል።
#Capital_Newspaper

#Tigray #Afar #Amhara
" ለሰላም ተስፋ አለ "
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድ ዛሬ ስለኢትዮጵያ ጉብኝታቸው መግለጫ ሰጥተዋል።
በጦርነቱ የተጎዱትን ትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎችን ከጎበኙ በኋላ ለሰላም ተስፋ እንዳለ የገለጹ ሲሆን " በእርግጥ የሚስተዋለው ከጥቂት ወራት በፊት ከነበሩ ግጭቶች ያነሰ ነው " ብለዋል።
ከትግራይ ክልል አመራሮች፣ ከአማራ ክልል እንዲሁም ከፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደረጉት አሚና መሐመድ ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ምክትል ዋና ፀሐፊዋ "በአሁኑ ወቅት በእርግጠኛነት የተሻለ ቦታ ላይ ነን። ተጨማሪ ውይይቶችም አሉ" ብለዋል።
አሚና መሐመድ በኢትዮጵያ ጦርነት ትልቁ ተጎጂዎች ህጻናትና ሴቶች ናቸው ያሉ ሲሆን በህብረተሰቡ ላይ እየደረሰ ያለውን አስከፊ ችግር ለመከላከል ሁሉን አቀፍ አገራዊ ምክክር ያስፈልጋል ብለዋል።
ለውጤቱም ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ውይይት ያደርጋሉ ብዬ እጠብቃለሁ ሲሉም ተናግረዋል።
አሚና መሀመድ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ፦ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣ ከፕሬዜዳንት ሳህለወቅር ዘውዴ ፣ ከም/ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
ዛሬ ደግሞ ከአፋር ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አወል አርባ ጋር ከቀናት በፊት ደግሞ ከአማራ ክልል ምክትል ፕሬዜዳንት ዶክተር ጌታቸው ጀንበር ጋር ተወያይተዋል።
አሚና ወደ ትግራይ ክልልም በመሄድ ከዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል ጋር ውይይት አድርገው ነበር።
በሌላ በኩልም ፤ በሶማሊ ክልል ስላለው የድርቅ ሁኔታ ወደ ክልሉ ተጉዘው ከፕሬዜዳንት ሙስጠፌ ሙሁመድ ጋር ተወያይተዋል።
ፎቶ ፦ ENA

" ... ታጣቂዎች የአንድ ከባድ መኪና አሽከርካሪን ተኩሰው በመግደላቸው መንገዱ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሠዓት ተዘግቶ አድሯል ፤ ዛሬ ግን መንገዱ ተከፍቷል " - ኮማንደር ቢምረው አሰፋ
በአማራ ክልል የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ ቤት ከአዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ጎሐጺዮን ወደ አማራ ክልል የሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ታጣቂዎች 1 የጭነት መኪና አሽከርካሪን በመግደላቸው ለ12 ሰዓታት ከተዘጋ በኋላ ዛሬ ጠዋት ላይ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን አስታውቋል።
ፖሊስ ይህን ያሳውቀው ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ በሰጠው ቃል ነው።
የጽ/ቤት ኃላፊ ኮማንደር ቢምረው አሰፋ " ትናንት አመሻሹ ላይ በኦሮሚያ ክልል አባይ በረሀ ውስጥ ፍልቅልቅ ከተባለች አነስተኛ ከተማ አቅራቢያ ልዩ ስሟ "አዝዋ ሜዳ" ታጣቂዎች የአንድ ከባድ መኪና አሽከርካሪን ተኩሰው በመግደላቸው መንገዱ ከምሽቱ አንድ ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሠዓት ተዘግቶ አድሯል " ብለዋል።
ዛሬ ግን ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መንገዱ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን ኃላፊው አመልክተዋል።
የደረሰውን ጉዳት መንስኤ መነሻ በተመለከተ ግን ክስተቱ የተፈፀመው በኦሮሚያ ክልል በኩል በመሆኑ ዝርዝር ጉዳዩ በዚያ በኩል እንደሚታይ መናገራቸውን ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

" ... ታጣቂዎች የአንድ ከባድ መኪና አሽከርካሪን ተኩሰው በመግደላቸው መንገዱ ከምሽቱ 1 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሠዓት ተዘግቶ አድሯል ፤ ዛሬ ግን መንገዱ ተከፍቷል " - ኮማንደር ቢምረው አሰፋ በአማራ ክልል የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ ቤት ከአዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ጎሐጺዮን ወደ አማራ ክልል የሚወስደው ዋና መንገድ ላይ ታጣቂዎች 1 የጭነት መኪና አሽከርካሪን በመግደላቸው ለ12 ሰዓታት ከተዘጋ…
#Update
ከኦሮሚያ ክልል በኩል ምን ተባለ ?
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር የተናግሩት ፦
" ... አባይ ድልድይ ከመደረሱ በፊት ባለው “ኮቲቻ” በሚባል አካባቢ ጥቃት የተሰነዘረው ትላንት ማክሰኞ የካቲት 1 ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው።
ጥቃቱን የሰነዘሩት የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው።
በጥቃቱ ኮንቲኔየር የጫነ ሎቤድ የጭነት መኪና አሽከርካሪ ተገድሏል።
ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም አቅጣጫ በማሽከርከር ላይ በነበረው በዚሁ ግለሰብ ላይ የእሩምታ ተኩስ መከፈቱን ተከትሎ የወረዳው ፖሊሶች ምላሽ ሰጥተዋል።
እነሱ ተኩስ እንደጀመሩ የእኛም ልጆች ተኩስ ጀመሩ። ከዚያ በኋላ ወደ ጫካቸው ተመለሱ።
... በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ስጋት ለመቅረፍ በአቅማችን የምንችለውን እያደረግን ነው። ትላንት አመሻሽ ላይ ጥቃት በደረሰበት አካባቢም ተጨማሪ የጸጥታ ኃይሎች ተመድበዋል።
ለአባይ ድልድይ ጥበቃ ከሚያደርጉት የፌደራል ፖሊስ አባላት በተጨማሪ የወረዳው ፖሊስ አባላት እና የአካባቢው ሚሊሺያዎች በአሁኑ ወቅት በቦታው ላይ ይገኛሉ።
አሁንም አካባቢው ከስጋት ነጻ ባለመሆኑ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ ሊያሰርጉ ይገባል። ጠላት አድፍጦ ሰዓት ጠብቆ ሰለሚመጣ፤ የትኛው ጋር ተደብቆ ጉዳት እንደሚያደርስ ስለማይታወቅ አሽከርካሪዎች ማታ ባይጓዙ የተመረጠ ይሆናል "

#Update የፈተና ውጤታችሁን ከነገ ጀምሮ መመልከት ትችላላችሁ። በህክምና /Medicine/ ሙያ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች የፈተናው ውጤት ከነገ ጀምሮ መመልከት ይቻላል። ከታህሳስ 21-27/2014 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ የህክምና /Medicine/ ተመዛኞች ከየካቲት 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥር…
#MoH
በህክምና /Medicine/ ሙያ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች የፈተናው ውጤት ትላንት የካቲት 1 ይፋ ሆኗል።
ተመዛኞች ከትላንት ማክሰኞ ጀምሮ በ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እንዲሁም የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታቸውን እየተመለከቱ ነው።
በሌሎችም የሙያ ዘርፎች ፈተና የወሰዱ ተመዛኞች ውጤት በቅርብ ቀን ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በሌላ መረጃ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዱ የ2014 የሕክምና ሳይንስ /Medicine/ ተመራቂዎች #በሙሉ ማለፋቸውን ገልጿል።
ውድ ቤተሰቦቻችን የተለያዩ የ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልዕክቶች በ @tikvahuniversity በኩል ማግኘት ትችላላችሁ።

ኣቡነ ኣንጦንዮስ ማረፋቸው ተሰማ።
3ኛው የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የነበሩት ኣቡነ ኣንጦንዮስ ማረፋቸውን የቢቢሲ ትግርኛ አገልግሎት ዘግቧል።
ኣቡነ ኣንጦንዮስ ለበርካታት አመታት በቁም እስር ላይ ነበሩ።
የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን 3ኛው ፓትሪያርክ አቡነ ኣንጦኒዮስ እስከ 1998 ዓ.ም ድረስ ቤተክርስቲያኒቱን ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ከሀይማኖቱ ተቃራኒ የሆነ አመለካከት ያራምዳሉ ተብለው ሲከሰሱ ነበር።
ኣቡነ ኣንጦንዮስ ለረጅም ጊዜ የአገሪቱ መንግሥትን ሲተቹ የቆዩ ሲሆን፤ በዚህም ለ15 ዓመታት ከመንበራቸው ተነስተው በቁም አስር ላይ መቆየታቸው ይነገራል።
ከዓመታት በፊት የኤርትራ ቤተክርስቲያን ጳጳሳት ፓትሪያርኩን አውግዘው ከመንበራቸው በማንሳት የእምነቱ ተከታዮች "እውቅና እንዳይሰጧቸውና ስማቸውንም እንዳያነሱ" አዘው ነበር።
ፓትሪያርኩ ከቤተክርስቲያኗ አባልነት የተገለሉ ቢሆንም በቤተክርስቲያኗ ባለቤትነት ስር በሆነ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ ተፈቅዶላቸዋል ነበር።
ኣቡነ ኣንጦንዮስ አስመራ ውስጥ ህይወታቸው እንዳለፈ ነው ዛሬ የተሰማው።

#NEAEA
" ... አሁን የመቁረጫ ነጥቡ ( የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ) ይለያል አይለይም የሚለውን ኤጀንሲው ሊወስን አይችልም፤ የኤጀንሲውም ስልጣን አይደለም " - አቶ ተፈራ ፈይሳ
በሁለተኛው ዙር የሀገር አቀፍ ፈተና በፀጥታ ችግር ምክንያት ፈተና ላይ መቀመጥ ያልቻሉ ተማሪዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ፈተናቸውን ወስደዋል።
በአጠቃላይ በአማራ፣ አፋር፣ኦሮሙያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከ60 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና ወስደዋል።
ፈተናውም የወሰዱ ተማሪዎች እና የትምህርት ባለሙያዎች " ተፈታኞች ያሳለፉትን የስነልቦ ጫና እና አስቸጋሪ ሁኔታ ከግምት ያስገባ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ሊኖር " ይገባል እያሉ ይገኛሉ።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክታ ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል ይህንን የመወሰን ስልጣን የኤጀንሲው እንዳልሆነ ገልፀዋል።
አቶ ተፈራ ፈይሳ ፥ " ... ያሉ ጥያቄዎች አሉ፤ ይሄን ኤጀንሲው አሁን ላይ የሚለውም ምንም ነገር የለም። በዚህ ደረጃ ኤጀንሲው አይወስንም ፤ ይህ ትልቅ ጉዳይ ስለሆነ። ዞሮ ዞሮ ችግሩ እንዳለ እንረዳለን። ችግሩን ለመፍታት እኛ የተወሰነ ጊዜ ከመስጠት ባሻገር አሁን የመቁረጫ ነጥቡ ይለያል አይለይም የሚለውን ኤጀንሲው ሊወስን አይችልም የኤጀንሲውም ስልጣን አይደለም። ...ይሄን የሚወስነው መንግስት ነው "
በሌላ በኩል ፤ ኤጀንሲው በትግራይ ክልል ካሉ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ የታሰበ ነገር ያለ እንደሆነ ከሬድዮ ጣቢያው የተጠየቁት አቶ ተፈራ ፥ " በእኛ በኩል የሚፈታ አይደለም። ከአጠቃላይ ከሀገራዊ ፀጥታ ጋር የሚታይ ስለሆነ ሀገራዊ ፀጥታው ሲረጋገጥ ፣ ትግራይም እንደማንኛውም ክልል ሰላም ሲሆን ፈተና የምንፈትነው " ሲሉ መልሰዋል።
#MesfinArageVOA

#እናት_ፓርቲ
" ንጹሓን የትግራይ ተወላጅ ወገኖቻችን ወደሥራ ገበታቸው መመለስ ችሮታ ሳይሆን ግዴታ መሆኑ ይታወቅ " - እናት ፓርቲ
እናት ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ልኮልናል።
ፓርቲው ኢትዮጵያ ከገባችበት የህልውና ጦርነት ጋር በተያያዘ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የትግራይ ተወላጅ ወገኖች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር እና ሂደቱ ህግ እና ህግን ብቻ መከተል እንዳለበት በተደጋጋሚ አበክሮ ሲያሳስብ መቆየቱን አስታውሷል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንዶች እየተለቀቁ መሆኑን ገልጿል።
በሕግ ጥላ ሥር የነበሩ እና በቁጥጥር ሥር ሳይውሉ ከሥራ ገበታ ታግደው በቤት እንዲቆዩ የተደረጉ ንጹሓን ወደየሚሠሩባቸው መሥሪያ ቤቶች ሲመለሱ በአግባቡ እንዳልተስተናገዱ፣ ደመወዛቸው እንደተቋረጠ እና አንዳንድ ቦታዎች ይባስ ብሎ “በእናንተ ቦታ ሌላ ሰው ተተክቶበታል” በሚል ማን አለብኝነት ለተጨማሪ እንግልት እንደተዳረጉ መረጃዎች እንደደረሱት ፓርቲው ገልጿል።
እንዲህ ያለውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ዘመድ አዝማድ እና ተወላጅ ለመሰብሰብ፣ ለማሸማቀቅ፣ ኪስ ለማደለብ የሚሯሯጡ አካላት ተግባር ርካሽና ትሕነግ (TPLF) ካደረሰው በደል ያልተናነሰ ነገር እንደፈጸሙ ሊያውቁት ይገባልም ብሏል።
ፓርቲው ምንም አይነት ወንጀል ሳይፈጽሙ በትውልድ ሥፍራቸው ምክንያት ብቻ ከሥራ እንዲሁም ከሥራና ደመወዝ ታግደው ያሉ የትግራይ ተወላጅ ወገኖች ወደ ሥራ ገበታቸው እንዲመለሱ አጥብቆ ጠይቋል።
ይህንን በዜጎች ላይ በሰበብ አስባብ የሚደርስ እንግልት ማስወገድ ችሮታ ሳይሆን የዜጎች መብት የመንግስት ደግሞ ግዴታ መሆኑን እናት ፓርቲ በጽኑ እንደሚያምን ገልጿል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#AmharaRegion
የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ የተለያዩ የህክምና እና ሆስፒታል ግብዓቶችን እና ቁሳቁስ በአማራ ክልል ለሚገኙ ከተሞች በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
ድርጅቱ በላሊበላ ፣ መቄት እና ዋድላ ለሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እንደ ጓንት፣ ፋሻ እና መድሀኒት ያሉ የህክምና ቁሳቁሶች አበርክቷል።
በደብረ ታቦር ፣ ጎንደር እንዲሁም ባህር ዳር ለሚገኙ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል አምቡላንሶች የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ዕቃዎችን ማስረከቡን ዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አሳውቋል።

#Gambella " በጥቃቱ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 5 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል " - ፖሊስ በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ። በጥቃቱ የ8 ሠዎች ህይወት ሲያልፍ በ5 ሠዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ተገልጿል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ ፥ በጋምቤላ…
#Gambella
ትላንትና በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት በዲማ ስደተኛ ካምፕና በጎግ ወረዳ ጥቃት ማድረሳቸውን የጋምቤላ ክልል አስታውቋል።
በጥቃቱ የአንድ ሠው ህይወትሲያልፍ ሁለት ሠዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና ሶስት ህፃናት ታፍነው ተወስደዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በጎግ ወረዳ ከፑኝዶ ከተማ ወደ ቴዶ ቀበሌ የሚሄድ ሞተር ሳይክል ላይ ባደረሱት ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ተገልጿል።
በቅርቡም መነሻውን ከጋምቤላ ከተማ አድርጎ ወደ ኑዌር ዞን በመጓዝ ላይ ባለ የጭነት መኪና ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ባደረሱት ጥቃት የመኪናው አሽከርካሪ እና ረዳቱ ህይወታቸው እንዳለፈ የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።
ጥቃት ያደረሱትን ግለሰቦች በክልሉ ልዩ ሀይልና ሚሊሻዎች አማካኝነት ተከታትሎ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ጠንካራ ስራ እየተከናወነ እንደሆነ ክልሉ ገልጿል።
ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።
በአሁኑ ሰዓት ክልሉ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በመጠቀም ጥቃት በደረሰባቸው አካባቢዎች ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑንና የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በየቦታው ሾልከው ሊገቡ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በቅርቡ፤ በኑዌር ዞን እና አኙዋ ዞኖች ገብተው 4 ሕፃናት አፍነው በመውሰድ፣ የከብት ዝርፊያ በማካሄድ አስራ አንድ ሰዎችም ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።
መረጃው የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው።

#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር እና ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚረዳ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር በይፋ አስጀምረዋል፡፡
ለዚሁ ተግባር በተዘጋጁት በአጭር መልዕክት 9222፣ በቴሌብር የመለገሻ ቁጥር 9222 ፣ በውጪ ሃገራት የሚኖሩ ድጋፍ ሰጪዎች በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሃዋላ መላኪያ 993161616 ገንዘብ በመላክ ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠይቋል።
ፎቶ ፦ ኢትዮ ቴሌኮም

#ችሎት እነ አቶ አብዲ ኢሌ ተቃውሞ አሰሙ። ዛሬ ፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረ-ሽብር እና የህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀረቡት የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ጨምሮ 17 ተከሳሾች ተቃውሞ አሰምተዋል። እነ አቶ አብዲ ኢሌ ከኛ ጋር ታስረው የነበሩት እስረኞች ተፈተው እኛ የምንታሰርበት ምክንያት የለም ሲሉ ነው ተቃውሞ ያሰሙት። …
#ችሎት
የቀድሞ የሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የነአቶ አብዲ መሀመድ ኡመር አቤቱታ ውድቅ ተደርጓል።
አቶ አብዲ ጨምሮ 17 ተከሳሾች " ከኛ ጋር ተከሰው የነበሩ እስረኞች ክስ ተቋርጦ እኛ ብቻ የምንታሰርበት ምንም ምክንያት የለም። በህገ መንግስቱ የተሰጠንን በእኩል የመታየት መብታችን የተነፈገ በመሆኑ ፍርድ ቤት አንቀርብም " ሲሉ ተከሳሾቹ ማክሰኞ አቤቱታ ማሰማታቸው ይታወሳል።
በአቤቱታው ላይ ፍ/ቤቱ መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለዛሬ በተያዘው ቀጠሮ ችሎቱ ተሰይሟል።
ሆኖም ዛሬ አቶ አብዲ መሀመድን ጨምሮ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙ 14 ተከሳሾች ችሎት አንቀርብም በማለት ሳይቀርቡ ቀርተዋል።
በዛሬው ችሎት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኙ 3 ተከሳሾች በችሎት ቀርበው በአስገዳኝ ሁኔታ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ፍ/ቤት እንዳመጣቸው አቤቱታ አቅርበዋል። ከሌሎች ታራሚዎች ጋር ቃሊቲ እንዲዛወሩ እና አንድ ላይ ጉዳያቸው እንዲታይላቸው ጠይቀዋል።
ፍርድ ቤቱ የደረሰባቸው የመብት ጥሰት ካለ በጽሁፍ እንዲያቀርቡ ብሏል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ አብዲ ኢሌን ጨምሮን አጠቃላይ ተከሳሾች ሌሎች እስረኞች ተፈተው እኛ ፍርድ ቤት የምንቀርብበት ምክንያት የለም ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ በተመለከተ መርምሮ አቤቱታውን ማቅረብ ያለባቸው ክስ ላቋረጠው መንግስታዊ አካል እንጂ ለዚህ ችሎት አደለም፤ ጥያቄው የህግ መሰረት የሌለው ነው ሲል አቤቱታቸውን ውድቅ አድርጓል።
በዚህም ፍርድ ቤቱ በያዘው ቀጠሮ የምስክር አሰማም ሂደት ይቀጥላል ሲል የዓቃቢ ህግ ቀሪ ምስክርን ለመስማት ለየካቲት 14 /2014 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዛሬ ያልቀረቡ 14 ተከሳሾችን በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርብ አዟል።
#ታሪክ_አዱኛ

H.R. 6600
የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት የፕሬዜዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ፣ ኤርትራና ከግጭት ጋር ተያይዞ ለደረሱ በደሎች ተጠያቂ ናቸው በተባሉ ግለሶች ላይ ማዕቀብ መጣል የሚያስችል ረቂቅ ሕግ አስተዋውቀዋል።
ረቂቅ ሕጉ ተፈጻሚ ቢሆን የጦርነቱ ተሳታፊዎች ተገደውም ቢሆን ወደ ድርድር እንዲመጡ ያስችላል የሚሉ እንዳሉት ሁሉ፤ በረቂቅ ሕጉ ላይ የፕሬዜዳንት ባይደን ፊርማ ቢያርፍ ፤ ተራው ዜጋ ሰርቶ እንዳይገባና በልቶ እንዳይደር ከፍተኛ ጫና ያሳድራል የሚሉ አሉ።
የረቂቅ ህጉ ምን ይዘት አለው ?
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት አጥብቀው የተቃወሙት ይህ ረቂቅ ሕግ በፕሬዝደንት ባይደን የሚጸድቅ ከሆነ አሜሪካ በደኅንነት፣ በፋይናንስ/በኢንቨስትመንት እና በኢሚግሬሽን ጉዳዮች ላይ በሁለቱ አገራት ላይ አዲስ ማዕቀብ ትጥላለች።
'የኢትዮጵያ የመረጋጋት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ሕግ' በሚል ርዕስ የቀረበው ረቂቅ ሕግ፤ አሜሪካ ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ በደኅንነት እና ፀጥታ ላይ የምታደርገው ድጋፍ ላይ ገደብ ይጥላል።
ይህ ረቂቅ ሕግ ተፈጻሚ ከሆነ አሜሪካ ተሰሚነቷን እና ድምጽ የመስጠት መብቷን ተጠቅማ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ብድሮች ወይም የብድር ማራዘሚያዎች እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፎች እንዳያገኙ እንድትሰራ ይጠይቃል።
ይህ ብቻ አይደለም፤ በኢትዮጵያ መረጋጋት እና የዲሞክራሲ ሥርዓት እንዳይኖር ምክንያት ናቸው በተባሉ ግለሰቦች ላይ የንብረት እግድ እና የቪዛ ማዕቀቦች ይጣላሉ።

#ይበቃል
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ያሉ ዜጎቻችን ፍትህን እንዲያገኙ የሚጠይቅ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ ነው።
ዘመቻው ሳዑዲ ያሉ ዜጎቻችን እምነበረድ ላይ ለብሰው የሚተኙትን ጥቁር ፌስታል በመልበስ አጋርነት የሚገለፅበት ነው።
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በርካታ ዜጎቻችን እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ይታወቃል።
የሳኡዲ አረቢያ መንግስት መሰረታዊ የእስረኛ አያያዝ ህግን እንዲተገብር፣ ፍትሃዊ የሆነ ምላሽም እንዲሰጥ የሚጠየቅበት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ነው እየተካሄደ ያለው።
ዘመቻው ከተጀመረ ሳምንታት ተቆጥረዋል።
በሳዑዲ አረቢያ ስላሉት ወገኖች የሰማነው ተስፋ ሰጪ ዜና እስካሁን የውሀ ሽታ እንደሆነ ነው።
የማህበራዊ ሚዲያው ዘመቻው በሳዑዲ አረቢያ ላሉት ወገኖች ድምፅ የሚኮንበት፣ ዜጎቻችን ወደሀገራቸው እንዲመለሱ ድምፅ የሚኮንበት ፣ በሳዑዲ መንግስት ላይ ጫና ለማሳደር / መሰረታዊ የሆነው የእስረኞች አያያዝን ተግባራዊ እንዲያደርግም ግፊት የሚደረግበት ነው።
የአረብኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆናችሁ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በይበልጥ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሳዑዲ አረቢያ ባለልስጣናት እና የዓለም መንግስታት የዜጎቻችንን ስቃይ እንዲያውቁ መልዕክቶችን በማጋራት ድምፅ ሁኑ።
#ይበቃል
#ጥቁር_ፌስታል
#الحرية_للسجناء_الاثيوبيين
#العدالة_للسجناء_الاثيوبيين
ፎቶ፦ ሶሻል ሚዲያ