የአሜሪካ መግለጫ ፦
አሜሪካ በአፋር እና ትግራይ ክልል አዋሣኝ አካባቢዎች አዲስ የተቀሰቀሰው ጦርነት ያሳስበኛል አለች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት ሐሙስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "በአፋር ክልል ጦርነት እንደ አዲስ መቀስቀሱ እጅግ አሳሳቢ ነው" ብለዋል።
ፕራይስ ከቀናት በፊት አዲሱ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ጦርነቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ደኅንነት እና ፀጥታ ስጋት መሆኑን በመጥቀስ፣ በግጭቱ አካባቢ ላሉ ሰዎች ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት እንዲመቻች እና ግጭቱ በድርድር እንዲጠናቀቅ የመንግሥታቸው ፍላጎት መሆኑን አመልክተዋል።
ኔድ ፕራይስ በትላንትናው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከቀናት በፊት በመላው አገሪቱ ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ውሳኔ ማሳለፉ የአሜሪካ መንግሥት በበጎ እንደሚመለከተው ገልጸዋል።
"ይህ ውሳኔ [የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ መወሰኑን] በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይጸድቃል ብለን ተስፋ እንዳርጋለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ፕራይስ ፤ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ሰዎች እንዲፈቱም ጠይቀዋል።
ቃል አቀባዩ ፤ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ማስቆም የሚቻለው በድርድር ግጭት ሲቆም፣ የታሰሩ ሰዎች ሲፈቱ፣ የሰብዓዊ እርዳታ ሲፈቀድ እና ሁሉን አካታች የሆነ ብሔራዊ ምክክር ለማድረግ መሠረት ሲጣል ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

#NewsAlert
መንግስት የህወሃት ቡድን ለሚፈፅመው ትንኮሳ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የክልል ጸጥታ ሃይሎች በጥናት ላይ ተመስርተው እርምጃ የሚወስዱበትን አቅጣጫ ማስቀመጡን ዛሬ አስታወቀ።
ይህ የተሰማው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተመራው የፌደራል ጸጥታ ም/ቤትና የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች በሀገራዊ ጸጥታ ሁኔታ ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው።
በውይይቱ ላይ የህወሃት ቡድን የሚያደርገውን ትንኮሳን ተከትሎ እርምጃዎች የሚወሰድበት አግባብ አቅጣጫ ተቀምጦለታል ተብሏል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ፥ " የአሸባሪ ቡድኖችን እንቅስቃሴ በመገምግም እርምጃ መውስድ የሚቻልበት ሁኔታን ከመመልከት ባለፈ አሸባሪዎች ላይ እርምጃ መውሰድን የተመለከተ አቅጣጫ ተቀምጧል " ብለዋል።
በሌላ በኩል በምክክሩ ላይ ሀገሪቱ አሁን ያለችበት አንጻራዊ ሰላምና ጸጥታን አጠናክሮ ማስቀጠል፣ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን ማስቆምና በጦርነቱ ምክንያት የተፈጠሩ ኢመደበኛ አደረጃጀቶችን ቅርጽ ማስያዝ እንደሚገባ ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።
የተቀመጡ አቅጣጫዎችም ሆነ የተደረሰባቸው ስምምነቶችን የፌደራልም ሆነ የክልል የጸጥታ አካላትና አስተዳደሮች በየደረጃው ተግባራዊ እንደሚያደርጉት እንደሚጠበቅ ኤፍቢሲ ዘግቧል።

#HPR
በዛሬው ዕለት የሕዝብ ተወካዮች ምክርት ባካሄደው ሶስተኛ ልዩ ስብሰባ የቀረበለትን የ120 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል።
የተጨማሪ በጀት ውሳኔው በዘጠኝ ተቃውሞ በሰባት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።
በምክር ቤቱ ከጸደቀው በጀት ውስጥ 90 ቢሊየኑ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ስንቅና ትጥቅ እንደሚውል ተነግሯል።
ለዕለት ደራሽ ዕርዳታ 8 ቢሊየን ብር፣ ለመጠባበቂያ በጀት 5 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ 7 ቢሊዮን ብር እና ለታክስ ገቢ ጉድለት ማካካሻ 9 ቢሊዮን ብር ፀድቋል።
ተጨማሪ በጀቱ የተቋረጡ እና በጅምር ላይ ያሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለማስቀጠል እንዲሁም በጦርነቱና በኮቪድ 19 ምክንያት በቂ ያለተሰበሰበውን ታክስ ጉድልት ለመሙላት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ቀደም ሲል ለ2014 በጀት አመት 561 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የፌደራል መንግስቱ በጀት ሆኖ በምክር ቤቱ መፅደቁ ይታወሳል።

#France #Ethiopia
በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያ በፈረንሳይ መንግስት የተለገሰ 6.7 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባት ዶዝ በኮቫክስ አማካኝነት መረከቧን በአዲስ አበባ የሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ዛሬ አሳውቋል።
ኤምባሲው፤ ኢትዮጵያን ከፈረንሳይ ለአፍሪካ በክትባት ልገሳ ቀዳሚ ኢትዮጵያን ተጠቃሚ አድርጓታል ብሏል።
ይህ አቅርቦት ከዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ግሪክ፣ ጣሊያንና ስዊድን ጋር በዩኒሴፍ ድጋፍ 13 ሚሊዮን የክትባቶች ዓለም አቀፍ ልገሳ አካል መሆኑ ተገልጿል።
በአዲስ አበባ የፈረንሳይ ኤምባሲ ፥ " እንደ ቡድን አውሮፓ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ለውጥ ማምጣት እንችላለን " ብሏል።

#Woldia
ከደሴ ወደ ወልድያ ከተማ የሚገባው የኤሌክትሪኮ ኃይል እክል እንዳጋጠመው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስታወቁን የወልዲያ ኮሚኒኬሽን ገልጿል።
ተቋሙ ከደሴ ወልድያ ከተማ የሚገባው 66 ኬቪኤ የትራንስሚሽን መስመር ባልታወቀ ምክንያት በሀብሩ ወረዳ ቀበሌ " ቀርጨም በር " አካባቢ ባለ 4 ቋሚ ምሰሶ በእሳት በመቃጠሉ ምክንያትና የደረሰውንም ጉዳት የአካባቢው ነዋሪ (ማኅበረሰብ) አደጋው መድረሱን ለሚመለከታቸው አካላት ባለማሳወቁ በፍላጋ ማግኘቱን አስታውቋል።
ተቋሙ የደረሰውን ጉዳት በመጠገን አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ መሆኑን አስታውቆ ኅብረተሰቡ በትእግስት እንዲጠብቅ አሳስቧል።
ምንጭ ፦ የወልዲያ ከተማ ኮሚኒኬሽን

" ለ36 ሺ 800 ተማሪዎች ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ፤ በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያልተፈተኑ ተማሪዎችን በሙሉ እንደሚያስፈትን አሳውቋል።
ክልሉ አሁንም ድረስ በሰሜን ጎንደር እና በዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አንዳንድ ስፍራዎች አሳሳቢ የፀጥታ ስጋት ቢኖርም ከዞኖቹ ማስፈተን አንችልም የሚል ሪፖርት ስላልደረሰው ለ36 ሺ 800 ተማሪዎች ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።
ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 በተሰጠው የብሔራዊ ፈተና በክልሉ 133 ትምህርት ቤቶች በፀጥታ ችግር ማስፈተን አልቻሉም።
አሁን ላይ ምን አልባት እንኳን ነገሮች ከአቅም በላይ የሚሆኑበት አጋጣሚ ከተፈጠረ እንኳን ተማሪዎችን ሰላማዊ ወደ ሆኑ ሌሎች ዞኖች በመውሰድ ፈተናው እንደሚሰጥ ቢሮው ገልጿል።
በመጀመሪያው ዙር ፈተናውን ለመውሰድ በክልሉ ከ127 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ተመዝገበው ነበር።
የሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከጥር 24 እስከ 27 ለተከታታይ አራት ቀናት ይሰጣል፡፡
መረጃ ምንጭ አሐዱ ቴሌቪዥን ነው።

" ለጋሾች ርዳታ ለማድረስ በእግር መጓዝ ጀምረዋል " - UN OCHA
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ እና ሊተነበይ የማይችል መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (UNOCHA) ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።
በአፋር በኩል በመጋሌ፣ ኢረብቲ፣ በራህሌ፣ ዳሎል እና አባላ ግጭት መኖሩን ፤ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር በኩል፣ በዋግ ኽምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ከትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት መኖሩን ሪፖርት አድርጓል።
በተቀረው የአማራ ክልል ሁኔታው የተረጋጋ እና ለሰብአዊ ምላሽ ተደራሽ መሆኑን ገልጿል።
UNOCHA በትግራይ ክልል ባለው የነዳጅ እጥረት ሳቢያ የውጭ ሃገራት ርዳታ ድርጅቶች በምግብ እጦት የተጎዱ ሴቶች እና ህጻናትን ለመርዳት በእግራቸው መጓዝ ጀምረዋል ሲል አሳውቋል።
UNOCHA ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ የሰብአዊ አቅርቦት ወቅታዊ ሁኔታ በሚመለከት ባወጣው ሪፖርቱ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የርዳታ ድርጅቶች በአጠቃላይ ካለፉት አራት ቀናት አንስቶ ነዳጃቸው መሟጠጡን ገልጿል።
ያም ቢሆን ግን ድርጅቶቹ " ሠራተኞቻቸው የቀሯቸውን ጥቂት የርዳታ አቅርቦቶች ለማዳረስ እስከ ቻሉት ድረስ በእግር መጓዝ ጀምረዋል " ብሏል።
UN OCHA ትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሀገር በቀል የርዳታ ድርጅቶችም ቢሆኑ በነዳጅ እጥረት " ሙሉ ለሙሉ እንቅስቃሴያቸውን የማቆም ስጋት " ተጋርጦባቸዋል ብሏል።
ከነዳጁ በተጨማሪ የገንዘብ እጥረት መከሰቱም ተገልጿል።
ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/

#ማሳሰቢያ
በአዲስ አበባ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት በትራንስፖርት ዘርፍ የወጡ የመከላከያ መንገዶች በአግባቡ እንዲተገበሩ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ አሳስቧል።
ቢሮው ዛሬ በትራንስፖርት ዘርፍ የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የቫረሱን ስርጭት ለመቀነስ በትራንስፖርት ዘርፍ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርጉ አሽከርካሪዎች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተገልጿል።
የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት፦
- የተሽከርካሪዎችን ንጽህና መጠበቅ፣
- አሽከርካሪዎችና ረዳቶች ማስክ መጠቀም
- ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪዎች አገልግሎት እንዳያገኙ ማድረግ እንደሚገባም ተብራርቷል፡፡
የኮቪድ ስርጭት ለመግታት በወጣው መመሪያ መሰረት ማስክ ያላደረጉ አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ከተገኙ ብር 1 ሺህ የሚያስቀጣ ሲሆን፥ ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪ በሚጭኑበት ወቅት በአንድ ሰው 500 ብር የሚያስቀጣ ይሆናል፡፡
ምንጭ፦ የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ

TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba አዲስ የስምሪት መስመር 👉 አራት ኪሎ - ሽሮሜዳ - ቁስቋም - እንጦጦ ማርያም ! አዲስ የስምሪት መስመር በመክፈት የህብረተሰቡን ተደጋጋሚ ጥያቄ መልስ መሰጠቱን የሸጎሌ ዴፖ ሰራ አስኪያጅ አቶ ኢሳያሰ አለማየሁ ዛሬ አሳውቀዋል። ስራ አስኪያጁ ፥ " የዚህ መስመር መከፈት ሸገር የህብረተሰብ ጥያቄን መልስ መስጠት ተቀዳሚ ዓላማዉ መሆኑን ያሳያል " ያሉ ሲሆን " አዲሱ የሰምሪት መሰመርም…
#AddisAbaba
ከ 4 ኪሎ በሽሮ ሜዳ በቁስቋም አድርጎ እንጦጦ ማርያም የሚደርስ የአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት የጉዞ መስመር በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
የተከፈተው አዲሱ መስመር ‹‹መስመር ቁጥር 122 ልዩ ›› የሚል መጠርያ ሲኖርው 10.3 ገደማ ኪ.ሜ ርቀት የሚገመትና እና የ 4 ብር ታሪፍ ተመን የተደረገለት መሆኑን አንበሳየ ከተማ አውቶብስ ድርጅት አስታውቋል።
በ6 አውቶብሶች አገልግሎት መስጠት የጀመረው ይህ መስመር በተለመደው የአውቶብስ አገልግሎት ሰዓት ተሳፋሪዎችን የሚያስተናግድ ይሆናል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጋራ በመቀናጀት ባደረጉት ኦፕሬሽን አንድ ስናይፐር ጠብመንጃ ፣ ከ20ሺ በላይ የክላሽ እና 260 የብሬን ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ መያዛቸውን አስታወቁ፡፡
የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 62651 በሆነ ኤፍ ኤስ አር አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ አካል ላይ መሸሸጊያ (ሻግ) በማሰራት ከወሊሶ ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ የነበረ አንድ ስናይፐር ጠበመንጃ፣ 20 ሺህ 630 የክላሽን -ኮቭ ጠበመንጃ እና 260 የብሬን ጥይት ጥር 20 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው እህል በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተይዟል።
ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ የመኪናው ሾፌርና የጦር መሳሪያውን ያስጫነው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#Woldia ከደሴ ወደ ወልድያ ከተማ የሚገባው የኤሌክትሪኮ ኃይል እክል እንዳጋጠመው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስታወቁን የወልዲያ ኮሚኒኬሽን ገልጿል። ተቋሙ ከደሴ ወልድያ ከተማ የሚገባው 66 ኬቪኤ የትራንስሚሽን መስመር ባልታወቀ ምክንያት በሀብሩ ወረዳ ቀበሌ " ቀርጨም በር " አካባቢ ባለ 4 ቋሚ ምሰሶ በእሳት በመቃጠሉ ምክንያትና የደረሰውንም ጉዳት የአካባቢው ነዋሪ (ማኅበረሰብ) አደጋው…
#Update
የወልድያ ከተማና አካባቢያው ዳግም ኤሌክትሪክ አገኘ።
ከደሴ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ እስከ ወልድያ ማከፋፋያ ጣቢያ በተዘረጋው የ66 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶዎች ላይ በደረሰ ቃጠሎ የተነሳ የተቋረጠው ኤሌክትሪክ የወልዲያ ከተማና አካባቢው ዳግም ኤሌክትሪክ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።
ትናንት የደረሰውን የኤሌክትሪክ ምሰሶ ቃጠሎ በሌላ በመተካት ወልድያ፣ መርሳ፣ ውጫሌ እና አካባቢያቸ ዳግም ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ርብርብ ሲደረግ ቆይቶ ወልዲያ ከደቂቃዎች በፊት ኤሌክትሪክ ማግኘት ችላለች።
በየደረጃው ሌሎች ከተሞችም ኤሌክትሪክ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

የWFP ሪፖርት ምን ይላል?
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ የከፋ ረሃብ ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል።
#ትግራይ
በትግራይ ክልል ውስጥ 40 በመቶ የሚጠጉ ሰዎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት ውስጥ ናቸው።
በትግራይ ክልል በተደረገው አስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዋስትና ግምገማ 83% የሚሆነው ሕዝብ የምግብ ዋስትና ችግር አጋጥሞታል።
በዚህ ሳቢያ የተለያዩ ቤተሰቦች ያላቸውን ምግብ ሁሉ አሟጠው በመጨረሳቸው ጥራጥሬ ብቻ መመገብና የሚመገቡትን የምግብ መጠን ለመቀነስ ተገደዋል።
ከተመጣጣነ ምግብ አንጻር ግምገማው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ትግራይ ውስጥ ከሚገኙ ልጆች መካከል 13% እና ከነፍሰጡር ሴቶች ግማሽ ያህሉ እንዲሁም ጡት የሚያጠቡ እናቶች ለተለያዩ ችግሮች በሚያጋልጥ ሁኔታ የተመጣጠነ ምግብ ችግር ገጥሟቸዋል።
#አማራ
በአማራ ክልል በቅርቡ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ባለፉት 5 ወራት የረሃብ ሁኔታ ከእጥፍ በላይ ጨምሯል።
በዚህ ሳቢያ ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ህጻናት መካከል 14%ና አንድ ሦስተኛ የሚሆኑ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች የተመጣጣነ ምግብ ችግር አጋጥሟቸዋል።
#አፋር
በአፋር ክልል በጦርነት በተከሰቱ መፈናቀሎች ምክንያት ረሃብና የተመጣጠነ ምግብ ችግር መጠን ከፍ ብሏል።
በቅርቡ የተሰበሰበ መረጃ በክልሉ ከ5 ዓመት በታች ከሆኑ ህጻናት መካከል 28 በመቶው የተመጣጠነ ምግብ ችግር አጋጥሟቸዋል።
#ሰሜንኢትዮጵያ- WFP በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ ከ9 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች እርዳታ ማቅረብ ያስፈልጋል ብሏል።
በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች የእርዳታ አቅርቦት እንዲጓጓዝ እንዲፈቅዱ ጠይቋል፥።
ሙሉ ሪፖርት www.wfp.org/news/severe-hunger-tightens-grip-northern-ethiopia?s=09

#NewsAlert መንግስት የህወሃት ቡድን ለሚፈፅመው ትንኮሳ የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የክልል ጸጥታ ሃይሎች በጥናት ላይ ተመስርተው እርምጃ የሚወስዱበትን አቅጣጫ ማስቀመጡን ዛሬ አስታወቀ። ይህ የተሰማው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተመራው የፌደራል ጸጥታ ም/ቤትና የክልል ርእሳነ መስተዳደሮች በሀገራዊ ጸጥታ ሁኔታ ላይ በተወያዩበት ወቅት ነው። በውይይቱ ላይ የህወሃት ቡድን የሚያደርገውን…
"ኢመደበኛ አደረጃጀት"
የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ስለ " ኢ-መደበኛ አደረጃጀት " ምንድነው ያሉት ?
አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፦
" ... ኢመደበኛ አደረጃጀት ያልናቸው አንዳንዶች በጦርነቱ ወቅት በጣም ከፍተኛ የሆነ ድርሻ የነበራቸው አሉ። አንዳንዶች ግን ጦርነቱን የሆነ ከተማ ውስጥ ሆነው በፌስቡክ፣ በዩትዩብ፣ ልክ እዛ ሆነው ምሽግ እንደሰበሩ የሚያሳዩ።
አሁንም ደግሞ ልክ ትላልቅ እጀባዎች የሚመስል ሰራዊት እያስከተሉ የሚንቀሳቀሱ አካላት አሉ። ነገር ግን በጦርነቱም በውጊያውም ምንም አይነት ተፅእኖና ይሄን አደረጉ ብሎ ለመናገርም ሚያሳፍሩ ብድኖች፣ ግለሰቦች እየተፈጠሩ ነው ያሉት።
እነዚህ ማህበረሰቡ አስታግሱልን የሚል እና ቀስ በቀስ በወደዝርፊያም ወደሌላም ጉዳዮች የሚሄዱ ናቸው ከውጭም ከውስጥም እነዚህን በገንዘብ የሚደግፍ ኃይል አለ፤ ልክ እንደተገዳዳሪ ነገር ለመቁጠር የመፈለግ ነገር አለ።
ኢመደበኛ አደረጃጀት መንግስት ተዳከመ በሚል እሳቤ የሚፈጠሩ ናቸው በብዛት።
እናም በእነዚህን ጉዳዮች ህብረተሰቡም ያነሳው ጥያቄ አለ አስታግሱልን የሚል ስለዚህ እነዚህ ስርዓት እንዲይዙ ይሰራል።
እነዚህ ኃይሎች መንግስትን በማጥላላት እና እንገዳደራለን በሚል ብቻ ሳይሆን ከመጋረጃ ጀርባ ደግሞ በመሳሪያ ንግድ ፣ በተተኳሽ ንግድ በጣም ከፍተኛ የሆነ ስራ የሚሰሩ ፣ ገንዘብ ለማከማቸት የሚፈልጉ ፣ ያለ አግባብ ግብር በነጋዴዎች ላይ የሚጥሉና ህብረተሰቡን የሚያስቸግሩ አካላት ናቸው።
በጥናት ላይ ተመስርቶ የክልል የፀጥታ ኃይሎች ፣ የክልል የፀጥታ አስተዳደር መዋቅሮች እነዚህን ኃይሎች መከላከል እና ስርዓት ማስያዝ አለባቸው የሚል ተነጋግረናል ፤ አቅጣጫም ተቀምጧል "