#Afar #Abala #Tigray
• " ወደታች ከባድ መሳሪያ እየጣሉ ነው። እንኳን የእርዳታ መኪኖች እና እዛ ያሉ የሚሸሹ ማህበረሰብ አባላት በትራንስፖርት እንዳይሸሹ አድርጓቸዋል ፤ ... የፌዴራል መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል " - አቶ አብዶ አሊ
• " የኢትዮጵያ ጦር ከዚህ ቀደም በተወሰነው ውሳኔ ባለበት ፀንቶ ነው የሚገኘው። በአካባቢው ላይ ምንም አይነት የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ በሌለበት ነው የሽብር ቡድኑ ትንኮሳ እየፈፀመ ያለው " - ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ
• " ... ለህዝባችን ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ እንፈልጋለን ለጥቃቅን ጀብዱ ፍላጎት የለንም። ዓለምአቀፉ ማህበረሰብም ትኩረት ነፍጎናል " - አቶ ጌታቸው ረዳ
ለትግራይ ህዝብ እርዳታ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ በርካታ ተሽከርካሪዎች ወደኃላ ተመልሰዋል።
የህወሓት ቡድን የተለያዩ መሰረታዊ የእርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ዘልቀው እንዳይገቡ አፋር ክልል አብአላ ውስጥ ታግደው ተይዘዋል ብሏል።
ህወሓት ከሰመራ ታጅበው ወደ ትግራይ ሊገቡ ነበር የተባሉት 27 የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ መቐለ እንዳይገቡ ተደርገዋል የሚል ክስ አሰምቷል።
በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ የሰጠ ሲሆን ህወሓት የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ በሌለበት በአፋር ክልል አብአላ ላይ በከፍተው ጥቃት ለትግራይ ህዝብ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ሊገቡ የነበሩ ተሽከርካሪዎች ወደኃላ ለመመለስ ተገደዋል ብሏል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " ይሄ አካባቢ በዋናነት ወደ ትግራይ የእርዳታ ማስገቢያ መንገድ ነው። ይህንን አካባቢ ሆን ብሎ በማጥቃት አሁንም የትግራይን ህዝብ ለረሃብ ለማጥቃት እየሞከረ መሆኑን ነው የሽብር ቡድኑ ድርጊት የሚያሳየው። በዚህ ጥቃት በዓለም ምግብ ፕሮግራም በኩል ወደ ትግራይ ሊገቡ የነበሩ በርካታ የጭነት ተሽከርካሪዎች ህወሓት በከፈተው ጥቃት እንዲመለሱ ተገደዋል " ብለዋል።
ህወሓት አብአላ ላይ በከፈተው ጥቃት 50 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ነገር ግን ቁጥር ለማጣራት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገልፀዋል።
" የኢትዮጵያ ጦር ከዚህ ቀደም በተወሰነው ውሳኔ ባለበት ፀንቶ ነው የሚገኘው። በአካባቢው ላይ ምንም አይነት የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ የለም " ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት " ነገር ግን ጦሩ በሌለበት በሽብር ቡድኑ ምክንያት የተለያዩ ትንኮሳዎች እየተፈፀሙ ነው ፤ ይህን የሚያደርገው እና ጥቃት የሚፈፅመው ወደ ትግራይ የሚገባውን እርዳታ ለማስተጓጎል ነው " ብለዋል።
ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸው ከሠጡ የአፋር ክልል ነዋሪዎች መካከል አንደኛው ህወሓት በአብአላ ከተማ ላይ ብቻ በ6 ግንባር ጦርነት መክፈቱን ፣ በበርሀሌ በኩል አሰዳ ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ፣ከአብአላ ወደዚህ መጋሌላይም ጦርነት መክፈታቸውን አስረድተዋል።
እየተደረገ ያለው ከባድ ጦርነት ነው ያሉት ነዋሪው ከባድ መሳሪያ ስለታጠቁ ህዝብ በሚበዛበት አካባቢ እየተኮሱ ይገኛሉ ብለዋል። " ህፃናት ፣ ሴቶች ... በርካቶች ተፈናቅለዋል። አቅም የሌላቸው እዛው እያለቁ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።
ነዋሪው በጦርነቱ ምክንያት የህወሓት ታጣቂዎች አብአላን ገብተው ሙሉ በሙሉ መያዛቸውን ፣ መጋሌ 3 ቀበሌ መያዛቸውን መረጃ እንዳላቸው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።
የአፋር ክልል አደአር መንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ አብዶ አሊ ፥ ህወሓት ከአማራ እና አፋር አካባቢዎች በጦርነት እንዲወጣ ከተደረገ በኃላ አብአላ እና አካባቢው ላይ የከባድ መሳሪያ ጥቃት መሰንዘር ከጀመረ ወር እንዳለፈው ገልፀዋል።
" የአካባቢው ጥበቃ ሚሊሻዎች፣ የወረዳ ፖሊሶች ላይ ነው ጦርነት እያካሄደ ያለው " ያሉት አቶ አብዶ " በአካባቢው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የለም " ብለዋል።
በመድፍ እና በከባድ መሳሪያ ጥቃት እየፈፀመ ያለው ሲቪል ሰዎች ላይ ነው ሲሉ አክለዋል። ይህን የሚያደርገው ባጋጠመው ሽንፈት ለመበቀል እና ብቸኛድን የእርዳታ ማስተላለፊያ መንገድ ለመዝጋት ነው ብለዋል።
የህወሓት ታጣቂዎች ዘልቀው ስለገቡባቸው ቦታዎች በተመለከ አቶ አብዶ አሊ ፥ ትግራይ በሚያዋስኑ 5 ወረዳዎች በሙሉ ጦርነት ከፍተው እንደሚገኙና ጦርነቱ መቀጠሉን ገልፀው ፤ አብአላን በከፊል መቆጣጠራቸውን መረጃ እንዳላቸው ገልፀዋል።
ቡድኑ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጦርነት በተለየ መልኩ በተለያየ ግንባር የነበረ ኃይሉን በሙሉ እና ለዚህ ጦርነት ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ወታደሮቹን ከባድ መሳሪያዎቹን አሰልፎ በሁለተኛ ምዕራፍ ነው ጦርነት የከፈተው ብለዋል።
የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ፥ የአብአላው ጦርነት በአፋር ታጣቂዎች እና በኤርትራውያን አጋሮቻቸው ነው የተቀሰቀሰው ብለዋል። " እንደተነገረን ከሆነ ከሰመራ ታጅበው ወደ ትግራይ ሊገቡ የነበሩ 27 መኪናዎች ወደ ትግራይ መግባት ነበረባቸው ሆኖም እንደማስተባበያ የቀረበው የአፋር ክልል መንግስት በአካባቢው ጦርነት በመኖሩ ከለከለ የሚል ነው። ይህ መንግሥት ሳያውቀው ይፈፀማል የሚል እምነት የለኝም፤ ለህዝባችን ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ እንፈልጋለን ለጥቃቅን ጀብዱ ፍላጎት የለንም። ዓለምአቀፉ ማህበረሰብም ትኩረት ነፍጎናል " ብለዋል።
የአደአር ወረዳ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ አብዶ አሊ አቶ ጌታቸው የሰነዘሩትን አስተየት አጣጥለውታል።
ቡድኑ ከሁሉም ግንባሮች ሸሽቶ ወደ መቐለ ከከተተ በኃላ እንዳለ ወደ አብአላ እና አፋር ግንባር ነው ጦሩን ያዞረው የመጀመሪያውን ጥቃትም የከፈተው የእርዳታ ማስተላለፊያ በሆነው መንገድ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
" እስካሁን ድረስም ከተማውን በከባድ መሳሪያ እየደበደበ ነው ያለው። አብአላ ዝቅታ ቦታ ላይ ነው ያለችው እነሱ ከፍታ ቦታ ላይ ነው ያሉት ከከፍታው ነው ወደታች ከባድ መሳሪያ እየጣሉ ያሉት። እንኳን የእርዳታ መኪኖች እና እዛ ያለው የሚሸሹ ማህበረሰብ አባላት በትራንስፖርት እንዳይሸሹ አድርጓቸዋል። በእግራቸው ነው እየሸሹ ያሉት " ብለዋል።
ጉዳዩን በአፋር ክልል ብቻ የሚቀረፍ ባለመሆኑ የፌዴራል መንግስት ትኩረት እንዲሰጠው መልዕክት ተላልፏል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar #Abala #Tigray • " ወደታች ከባድ መሳሪያ እየጣሉ ነው። እንኳን የእርዳታ መኪኖች እና እዛ ያሉ የሚሸሹ ማህበረሰብ አባላት በትራንስፖርት እንዳይሸሹ አድርጓቸዋል ፤ ... የፌዴራል መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል " - አቶ አብዶ አሊ • " የኢትዮጵያ ጦር ከዚህ ቀደም በተወሰነው ውሳኔ ባለበት ፀንቶ ነው የሚገኘው። በአካባቢው ላይ ምንም አይነት የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ በሌለበት…
#Ethiopia_at_the_UN
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ፅህፈት ቤት ህወሃት በአፋር በኩል እየፈፀመ ባለው ጥቃት ለትግራይ ህዝብ የሰብዓዊ እርዳታ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል፣ መቐለ በመጓዝ ላይ የነበሩ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ተሽከርካሪዎች ከግማሽ መንገድ በኋላ ወደኋላ ለመመለስ መገደዳቸውን አሳውቋል።
በተከፈተው ጥቃትም በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ሰዎች መፈናቀላቸውን አመልክቷል።
የህወሃት መሪዎች ድርጊት ለአደገኛ የፖለቲካ ቁማር ሲሉ ሰላማዊ ህዝብን ለረሃብ እየዳረጉ መሆኑን የሚያሳይ ሁነኛ ማስረጃ ነውም ብሏል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ፅህፈት ቤት።

#AddisAbaba
በጊዜያዊነት ታግዶ የነበረው መሬት ነክ አገልግሎት አሁን እግዱ ተነስቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።
የከተማ አስተዳደሩ ከቀን 07/12/2013 ዓ.ም ጀምሮ መሬት ነክ አገልግሎትን አግዶ መቆየቱ ይታወቃል።
ጊዜያዊ እግዱ አሁን የተነሳ በመሆኑ አገልግሎቱን ከቀን 13/05/2014 ዓ.ም ጀምሮ በየክ/ከተማው ማግኘት ይቻላል።
ታግደው ከነበሩ አገልግሎቶች መካከል ጊዜያዊ እግድ የተነሳላቸው አገልግሎቶች ዝርዝር ከዚህ በታች የተገለጹት ናቸው ፦
1. ህጋዊ ሰነድ ላላቸው ይዞታዎች ብቻ ዋስትና እዳ መመዝገብ
2. የፍርድ ቤት እና የባንክ እግድ የመመዝገብና የመሰረዝ አገልግሎት
• የእዳና እገዳ የማጣራት አገልግሎት
3. የስመ ንብረት ዝውውር ስራ
• በባንክ ሐራጅ የተሸጠ
• በፍ/ቤት አፈፃፀም የተሸጠ
• የኮንዶሚኒየም ቤት የስም ዝውውር አገልግሎት
• በውርስ የተላለፈ ንብረት
• በReal estates አልሚ የተፈፀመ የቤት ሽያጭ
4. ለነባር ይዞታዎች የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ተመን
5. የንብረት ግመታ
6. በይዞታ ይገባኛል ክርክር በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማስረጃ መስጠት
7. የወሰን ይመላከትልኝ /የወሰን ችካል/
8. በከተማ አስተዳደር የሚታወቅ እና ቅድሚያ የሚሰጥ የልማት ተነሺ አገልግሎት
• ካሣ ክፍያ
• ምትክ ቤት
• ምትክ ቦታ አሰጣጥ አገልግሎቶች
9. የቦታ ዝግጅት
10. የወሰን ማስከበር ተግባራት
11. በሊዝ በተላለፈ ቦታ ላይ የግንባታ ክትትል
12. የለማ መሬት በምደባ ወይም በጨረታ ማስተላለፍ
13. አዲስ ካርታ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
• የምትክ ኮንዶሚኒየም ቤት ለተወሰነላቸው
• ለአመራር የሚሰጡ ኮንዶሚኒየም ቤቶች፣
• የReal estates ተጠቃሚዎች /ቤት ገዥዎች የተናጠል ካርታ

#Update በስልክ በትግረኛ ቋንቋ ለማውራት እና ማስታወሻ ደብተር እንድንይዝ ይፈቀድልን ሲሉ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ማረሚያ ቤቱ መልስ ሰጥቷል። በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ለዛሬ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በ6 ተከሳሾች በተነሱ አቤቱታዎች ላይ መልስ እንዲሰጥ በያዘው ቀጠሮ ችሎቱ የተሰየመ ሲሆን አቤቱታ…
#ችሎት
ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ሚዲያዎች ወደ ፍ/ቤት እንዳይገቡ ይታዘዝልን ሲሉ አመለከቱ።
ይህን አቤቱታ ያቀረቡት ዶ/ር ሰለሞን በባለፈው ቀጠሮ ላይ ታመን ችሎት አለመቅረባችንን ተከትሎ ትግራይ የሚገኙ ቤተሰቦቻችን በሚዳያ ሰምተው ስለተጨነቁ ሚዲያዎች ታመን ስንቀር መታመማችንን እንዳይዘግቡ ችሎት እንዳይገቡ ይደረግልን ሲሉ ነው አቤቱታ አቅርበዋል።
በዛሬው ቀጠሮ የቀድሞ ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዬ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ የቀድሞ የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ፣ የቀድሞ የትግራይ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ አሰፉ ሊላይን ጨምሮ አምስት ተከሳሾች በችሎት ተገኝተዋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ተከሳሾች ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ትዛዝ ለመስጠት ተሰይሞ ነበር።
በታሳስ 21 ቀን በነበረ ቀጠሮ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ በማረሚያ ቤት በተለያየ ቦታ የታሰርን ታራሚዎች እንዲሁም ከጠበቃ ጋር ተገናኝተን ለመወያየት ይፈቀድልን ሲል አቅርቦ የነበረው አቤቱታን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ መርምሮ በዚህ አቤቱታ ላይ ብቻ ቅድሚያ ትዛዝ መሰጠት አለበት ሲል ተከሳሾቹ ተገናኝተው እንዲወያዩ ትዛዝ ሰቷል።
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ባቀረቡት የማስታወሻ ደብተር እንድንይዝ እና ስልክ በትግረኛ ቋንቋ እንዳናወራ ይታዘዝልን አቤቱታን እንዲሁም ሌሎች አቤቱታዎችን በተመለከተ ግን ችሎቱ አጠቃሎ ትዛዝ ለመስጠት ለጥር 25 ቀን ቀጥሯል።
በዛሬው ቀጠሮ ላይ 20ኛ ተከሳሽ የትግራይ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ የነበሩት ወ/ር አሰፉ ሊላይ ወደፍርድ ቤት ስመጣ ሽፉን ጫማ ለመጠቀም ስለተከለከልኩ እንዲፈቀድልኝ ሲሉ አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ሽፍን ጫማ እንዲጫሙ ፈቅዶላቸዋል።
Credit : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

#SomaliRegion
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሶማሌ ክልል የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል አንዱ የሚገኝበትን ቀብሪበያን ዛሬ ማለዳ መጎብኘታቸውን አሳውቀዋል።
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ " በጊዜያዊነት የውኃ አቅራቢ ተሽከርካሪዎችን ፣ የምግብ፣ የእንስሳት መኖ እና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን አቅርቦት እናሳድጋለን " ብለዋል።
" ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የጀመርናቸውን የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን " ሲሉም ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅ ከተከሰተባቸው ክልሎች አንዱ የሶማሌ ክልል ሲሆን ድርቅ በተከሰተባቸው የክልሉ ዞኖች አስከፊ ሁኔታ መኖሩ በተደጋጋሚ መገለፁ አይዘነጋም።

#Update
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካሪ ኮሚቴ ሁለት አጀንዳዎችን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
አጀንዳዎቹ ፦
• የማሕበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ረቂቅ አዋጅ
• የ2014 በጀት አመት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ ናቸው።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በማሕበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ረቂቅ አዋጅ ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ረቂቅ አዋጁ መታከም የማይችለው የሕብረሰተብ ክፍል ፍትሃዊ ፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው የጤና ሽፋን በመስጠት እንዲታከም ለማድረግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።
በሌላ በኩል በ2014 በጀት አመት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ አስፈላጊነት ላይም ወ/ሮ ሎሚ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ፣ ረቂቅ አዋጁ የተቋረጡ እና በጅምር ላይ ያሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለማስቀጠል እንዲሁም በኮሮና እና በጦርነቱ ምክንያት የወጡ ወጪዎችን ለመሸፈን እንደሚውል ጠቅሰው ለዚህም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት እንደቀረበ ነው የገለጹት።
#HPR

#AliBira #NuhoGobena
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አንጋፋውን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራን በመኖሪያ ቤታቸው ተገኝተው መጠየቃቸውን ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና ሲከታተሉበት በነበረው ሆስፒታል ተገኝተው መጠየቃቸው ይታወሳል።
በሌላ መረጃ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦፌኮ ከፍተኛ አመራሮቹ አቶ ጃዋር መሐመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም ሀምዛ ቦረና በአዳማ ተገኝተው በቅርቡ ከዚህ ዓለም ሞት የተለዩት አርቲስት ኑሆ ጎበና ቤተሰቦችን አጽናንተዋል።
በተጨማሪ በክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ መኖሪያ ቤት በመገኘት አርቲስቱን ጠይቀዋል።
Photo Credit : AA Mayor Adanech Abiebie & Meseret Daba

#ProfessorAsratWeldeyes
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ " ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ " በዛሬው ዕለት ይመረቃል፡፡
የምረቃ ስነስርዓቱ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እንደሚካሄድ ከዩኒቨርስቲው የተገኘው መረጃ ይመለክታል፡፡
Credit : የደብረ ብርሃን ኮሚኒኬሽን

#Benishangul
በዛሬው ዕለት የበርታ ብሔረሰብ ምክር ቤት 8ኛ መደበኛ ጉበዔውን በኩርሙክ ወረዳ አካሂዶ ነበር።
በዚህ ጉባዔው የብሔረሰቡ መጠሪያ ሥያሜ 👉ቤኒሻንጉል እንዲሆን መወሰኑ ተሰምቷል።
ሥያሜውን ለመቀየር የተጠናዉ ጥናት በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት ተገልጿል።
በጥናቱ ዙሪያ ከተደረገው ሰፊ ዉይይት በኃላ ምክር ቤቱ የብሔረሰቡን መጠሪያ ሥያሜ ቤኒሻንጉል እንዲሆን ወስኗል ነው የተባለው።

Photo
#Update
በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካምፓስ እንዲሁም የሐኪም ግዛው ማስተማሪያ ሆስፒታል ምረቃ ፕሮግራም ተካሂዷል።
በምርቃት ስነስርአቱ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ ስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።
ፎቶ : የደብረ ብርሃን ኮሚኒኬሽን