TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ኢትዮጵያ 📍

ሞሊ ፊ እና ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ ናቸው።

የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሀመት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሙሳ ፋኪ መሀመት ከሁለቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ገልፀዋል።

ሁለቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በተለይ ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት መፍትሄ ለማፈላለግ ነው።

@tikvahethiopia
#Kenya #Ethiopia

" ... ምንም እንኳን ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም ኢትዮጵያ ከስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል አቅም አላት" - ራይቼል ኦማሞ

ኬንያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቀውስ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የምታደርገውን ጥረት ሁሉ በሰከነ ሁኔታ ተቀራርባ በመስራቷ እንደምትቀጥል አሳውቃለች።

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራይቼል ኦማሞ አገራቸው ኢትዮጵያን ችላ እንደማትላትና የሰከነና የተለሳለሰ ዲፕሎማሲን በመጠቀም በአገሪቱ የተከሰተው ችግር እንዲያበቃ አብራት መስራቷን ትቀጥላለች ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት ትላንት የኬንያን የውጭ ፖሊሲ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች በተመለከተ ናይሮቢ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ራይቼል ኦማሞ ፥ " ምንም እንኳን ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም ኢትዮጵያ ከስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል አቅም አላት " ብላ ኬንያ እንደምታምን ገልጸው፣ ለዚህም በቅርቡ የፖለቲካ እስረኞች የመለቀቃቸው እርምጃን እንደ በጎ ጅማሬ ጠቅሰዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም በአገሪቱ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ በብሔራዊ ውይይት ፣ በተኩስ አቁም እና ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ መንገድ ማመቻቸትን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ጋር ተቀራርበው ሲሰሩ እንደነበር መናገራቸውን ቢቢሲ በዘግባው አስፍሯል።

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚካኤል ደንፎርድ ጋር ተወያይተዋል።

አቶ ሙስጠፌ በውይይቱ ፤ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል።

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመከላከል እና ህይወትን ለማዳን ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገውን የምግብ እርዳታን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተውበታል።

ምንጭ፦ የአቶ ሙስጠፌ የተረጋገጠ የትዊተር አካውንት

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

እድሳት የተደረገለት የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ በነገው እለት እንደሚመረቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

ይህ ታሪካዊ እና የከተማዋ ምልክት የሆነ ህንፃ ከ57 ዓመት በኋላ ለእድሳት የበቃ መሆኑና የከተማዋ የዘመናት ጉዞ አሻራ የያዘ ታላቅ ቅርስ ጭምር መሆኑ ተገልጿል።

የከተማው አስተዳደር ፤ ህንፃውን እጀግ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲታደስ ማድረጉን ገልጾ ለተገልጋይ ምቹና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ሁሉ ባሟላ መንገድ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ መሰራቱን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

ጄነራል መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ አዲስ አበባ ሲደርሱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና የብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎና የልዑካን ቡድናቸው በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ ከተለያዩ የመንግሰት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በዉይይታቸው የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራ ፍላጎት ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ጉዳዮችን ማሳደግ እና መደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

ምንጭ ፦አል ዓይን ኒውስ ፣ ኢብኮ እና የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና)

@tikvahethiopia
#DStv

የዲኤስቲቪን ማህበራዊ ድረገፆች ይከታተሉ!
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀላሉ

Facebook: https://bit.ly/2ULhG8U
Telegram: https://bit.ly/3y59gYz
Instagram: https://bit.ly/3rwIOEM
Twitter: https://bit.ly/3yieDU8
ነገ በአዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ የታላቁ ሩጫ ይካሄዳል።

የ2014 ዓ/ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የሩጫ ውድድር የሚካሄድባቸው መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አመራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ተጠይቋል፡፡

የ2014 ታላቁ ሩጫ መነሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ የሚጀምር ሲሆን በአዲስ አበባ ስታዲዮም፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ በልደታ ቤተክርስቲያን በማድረግ ፣በዛጉዌ ህንፃ በመታጠፍ-በጌጃ ሰፈር ፣ጎማ ቁጠባ በፍልውሃ ፣በማድረግ በካዛንቺስ ፣በኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ ባንቢስ በመታጠፍ መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደርጋል፡፡

የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖርና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዲችሉ ለተሸከርካሪ ዝግ የሆኑ መንገዶች እንደሚኖሩ ፖሊስ ገልጿል።

በዚህም መሰረት ፦

• ኮቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ህንፃ፤

• ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍለጦር፤

• ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኬኬ ህንፃ ወይም ጨርቆስ ማዞሪያ፦

• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባበይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ገብርኤል መሳለሚያ፤

• ከሳር ቤቶች አደባባይ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ አፍሪካ ህብረት አደባባይ ፤

• ከካርል አደባባይ ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሚወስደው መንገድ ልደታ ፀበል፤

•ከጦር-ኃይሎች ወደ ሚክሲኮ ለሚመጡ ኮካ መገንጠያ ፤

• ከሜክሲኮ ልደታ ኮንደሚኒዬም መብራት፤

• ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ በርበሬ በረንዳ፤

• ከተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጎማ ቁጠባ የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር (ሼልድሬንስ)

• ከቸርቸር ጎዳና ወደ አምባሳደር ፣ ከሜክሲኮ እና ለገሃር ለሚመጡ አገር አስተዳደር/ኢምግሬሽን/ መብራት ፤

• ከአዋሬ ወደ ካዛንቺስ ለሚመጡ ሴቶች አደባባይ- ከመገናኛ ወደ 22 ለሚመጡ ዘሪሁን ህንፃ፤

• ከቦሌ መድሃኔዓለም የሚመጡ አትላስ ሆቴል አካባቢ፤

ከጠዋቱ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በተጨማሪም ፥ አሽከርካሪዎች የውድድሩ ተሳታፊዎች ወደ ሚያልፉባቸው መንገዶች ተሽከርካሪ ይዞ መውጣት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።

ማንኛውም አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም ሆነ ለፖሊስ መረጃ ለመስጠት 011-1-11-01 11 እና በ991 ነፃ የስልክ ቁጥሮች መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ ያሳውቋል።

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሀገር ቤት ጥሪን ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ማህበራት ተወካዮች እና አባላትን አግኝተዋል። በበርካታ ጉዳዮችም ላይ መወያየታቸውን የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ትግራይ ፣ አማራ ፣ አፋር 📍

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ :

የሕክምና አገልግሎት አቅራቢዎች መሠረታዊ ግብዓቶችን እያገኙ አይደለም፤ እንዲሁም በአንዳንድ መሠረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የመድኃኒት እና ሕክምና መስጫ መሳሪዎች እጥረት ከጤና መሠረተ ልማት ውድመቶች ጋር ተደማምሮ የጤና አገልግሎት አቅርቦትን እጅግ አስቸጋሪ አድርጎታል።

በአማራ እና አፋር ክልሎች የICRC ተወካይ ሚቻ ዌዲኪንደ 🗣

" በአማራ ክልል አንዳንድ ሆስፒታሎች በመድኃኒት እጥረት ምክንያት ተዘግተዋል። ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያለባቸው ሰዎች በየዕለቱ እየሞቱ ነው።

የጤና ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ ባለመሆናቸው፤ ውሃ ወይም መብራት ስለማይኖራቸው እናቶች በቤት ውስጥ እየወለዱ ነው።

...በአፋር በተመሳሳይ ከፍተኛ የሆነ መድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁሶች እጥረት አለ "

በኢትዮጵያ ICRC የጤና አስተባባሪ አፖሎ ባራሳ 🗣

" በትግራይ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ እንደ ጓንት፣ የቀዶ ሕክምና ቁሳቁሶች እና ሰውነት ውስጥ የሚገቡ የሕክምና ቱቦዎች ሳይቀሩ እየታጠቡ ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ ነው።

ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸውን የጤና መሳሪያዎችን ዳግም መጠቀም፤ ለኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልን ያሰፋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ታካሚዎች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ከመውሰዳቸውም በተጨማሪ ሐኪሞች የሰዎችን ቁስል ለማጽዳት ጨው ለመጠቀም ተገደዋል። "

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በጦርነቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት በፍጥነት የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ የበኩላቸውን እንዲወጡ በመግለጫው ጠይቋል።

ያንብቡ : www.icrc.org/en/document/dwindling-medical-supplies-in-northern-ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ምን አሉ ? • የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ "በተሳሳተ መንገድ ለእስር ተዳርገው" ላለፉት 18 ወራት በእስር መቆየታቸውን ገልፀዋል። • እስራቸው " ፖለቲካዊ " እንደነበር ገልፀዋል። ለእስር የተዳረግነው ገዢው ፓርቲ በምርጫ የተሻለ ድምጽ እንዲያገኝ ከፖለቲካዊው ምኅዳር ገለል እንድንል ታስቦ ነው ብለዋል። • በኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል…
#OFC

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራሮች እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎችም በአዲስ አበባ በሚገኘው የፓርቲው ፅ/ቤት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ኦፌኮ ፤ አሁንም በእስር ላይ ያሉ የቀሩ አባላቱ ከእስር እንዲፈቱ ፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮችና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በድጋሚ ጥሪውን አቅርቧል።

@tikvahethiopia