TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

በትግራይ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ሕይወት አደጋ እንደተጋረጠበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) አስታወቀ።

በጦርነቱ ምክንያት የስደተኞቹ ኑሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ መሆኑንም ገልጿል።

በቅርቡ ማይ ዓይኒ እና አዲ ሐሩሽ በሚባሉ አካባቢዎች በሚገኝ የስደተኞች ጣብያ የሚኖሩ ስደተኞችን የመንግሥታቱ ድርጅት ሰራተኞች ጎብኝተዉ እንደነበር ድርጅቱ አስታውቋል።

ከ3 ሳምንት በፊት አካባቢዉ የአየር ድብደባ ከደረሰበት ወዲህ የድርጅቱ ሰራተኞች ስደተኞቹን መጎብኘት አልቻሉም ነበር።

ኤርትራዉያኑ ስደተኞች በቂ ምግብ፣ መድሐኒትና ንጹህ የመጠጥ ዉኃ የላቸዉም። ባለፉት 6 ሳምንታት ዉስጥ 20 ስደተኞች በመድሐኒት እጦት መሞታቸዉን ስፍራዉን የጎበኙት የUNHCR ሰራተኞች አስታዉቀዋል።

ትግራይ ዉስጥ የሚገኙ 25 ሺህ የኤርትራ ስደተኞን ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር ተኩስ አቁም እንዲደረግ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠይቋል።

በሌላ በኩል ፤ በጦርነት ለተጎዳዉ የትግራይ ሕዝብ የሚሰጠዉ የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ እየተሟጠጠ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ባወጣው ሪፖርት አሳውቋል።

ሙሉ ሪፖርት : https://reports.unocha.org/en/country/ethiopia/?s=09

ምንጭ፦ UNHCR , UN OCHA , DW

@tikvahethiopia
#Safaricom

" ሳፋሪኮም በፈረንጆቹ 2022 በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወጪ ያደርጋል " - አንዋር ሱሳ

የኬንያው የቴሌኮም ኩባንያ ሳፋሪኮም በፈረንጆቹ 2022 በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ 300 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ወጪ መዋዕለ ነዋይ እንደሚያፈስ ገልጿል።

የሳፋሪኮም የኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አንዋር ሱሳ ኩባንያው በተያዘው የፈረንጆቹ 2022 ወደ 300 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በኢትዮጵያ ፈሰስ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ስራውን ለመጀመር የኔትወርክ ዝርጋታ እያካሄደ መሆኑንና የመጀመሪያ የመረጃ ማዕከሉን በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ሳፋሪኮም በመጪዎቹ ጥቂት ወራት ውስጥ አገልግሎቱን በይፋ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
" በሃይማኖታዊ በዓላት የታደሙ ምእመናንን መግደል ሃይማኖቱ ብሎም ሀገር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ነው " - እናት ፓርቲ

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እናት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጥር 12 እንደ ሃይማኖታቸው የአምልኮ እና ቀኖና ሥርዓት ታቦተ ሕጉን ወደ መንበረ ክብሩ ለመመለስ በማኅደረ መለኮት ወይብላ ማርያም ቤተክርስቲያን በታደሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ላይ በጸጥታ ኃይሉ የተፈጸመው ግድያ ኢ ሕጋዊ፣ ኢ ሃይማኖታዊና የሞራል አልባነት ድርጊት ነው ብሎታል።

ጥንቱንም ላለፉት ዓመታት የመስቀልና የጥምቀት በዓላት በሚከበሩበት ጊዜ "ጠብ ያለሽ በዳቦ" ምክንያት እየፈለጉ ወከባ መፍጠር፣ ማሰር፣ መደብደብ ሕጋዊነት እስኪመስል ድረስ በተደጋጋሚ ሲፈጸም የቆየ ተግባር ቢሆንም በወይብላ ማርያም ያለፈውን ዓመት ጨምሮ መሰል ድርጊቶች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የጸጥታ አካላት እየተፈጸመ ነው ሲል ከሷል።

ፓርቲው ፥ " ሃይማኖት ለእኛ ለኢትዮጵያውያን እስትንፋሳችን መሆኑ እየታወቀ በየጊዜው ጸብ እየጫሩ ፓለቲካዊ ጉዳዮቻቸውን ሃይማኖታዊ ቀርጽ እንዲኖረው ለማስያዝ እየተሔደ ያለበት ርቀት በጊዜ ካልታረመ መዘዙ ከባድ ውጤቱም የከፋ መሆኑ የማይቀር ጉዳይ ነው " ሲል አሳስቧል።

እናት ፓርቲ ፥ የኦሮምያ ክልል መንግስት ሰለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ ሕዝብንም በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤ ድርጊቱን ባነሳሱ እና በፈጸሙ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ፣ የሕግ ውሳኔውም ለሕዝብ ይፋ እንዲደረግ፤ ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ለሃይማኖቱ ተከታዮች የሞራል ካሳ እንዲከፈል፤ ያለአግባብ የታሰሩ ምዕመናንም በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስቧል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
" መንግስት አጥፊዎችን ተከታትሎ ለህግ ማቅረብ ይገባዋል " - የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

በጥምቀት በዓል ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወይብላ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን ድርጊት እንደሚያወግዝ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታውቋል።

ጉባኤው ሃይማኖቶች የትህትና፣ የሰላምና የአንድነት፣ የፍቅርና መከባበር መሠረቶች ናቸው ብሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት የሰላም መሠረት ሆና ዘልቃለች ያለው የጉባኤው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ግጭት ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን አጥብቀን እንቃዎማለን ሲልም ገልጿል።

ጉባኤው ፤ ጥር 12/2014 ዓ.ም በቡራዩ ከተማ አስተዳደር በሕግ ማስከበር ሽፋን በቤተክርስቲያኗ ላይ የተቃጣው ድርጊት ፍጹም ሕገ ወጥ ነው ያለው መግለጫው መንግሥት አጥፊዎችን ተከታትሎ ለሕግ እንዲያቀርብም ጠይቋል።

መንግሥት የሃይማኖትን እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቀው ጉባኤው የሕይዎት፣ የአካልና የመንፈስ ስብራት በደረሰባቸው ወገኖች የተሠማንን ጥልቅ ሐዘንም በተሰበረ ልብ እንገልፃለን ብሏል።

#EPA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ኢትዮጵያ 📍

ሞሊ ፊ እና ዴቪድ ሳተርፊልድ ኢትዮጵያ ናቸው።

የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሀመት በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ የሆኑት ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሙሳ ፋኪ መሀመት ከሁለቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ቆይታ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ገልፀዋል።

ሁለቱ የአሜሪካ ባለስልጣናት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በተለይ ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት መፍትሄ ለማፈላለግ ነው።

@tikvahethiopia
#Kenya #Ethiopia

" ... ምንም እንኳን ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም ኢትዮጵያ ከስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል አቅም አላት" - ራይቼል ኦማሞ

ኬንያ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቀውስ መፍትሔ ያገኝ ዘንድ የምታደርገውን ጥረት ሁሉ በሰከነ ሁኔታ ተቀራርባ በመስራቷ እንደምትቀጥል አሳውቃለች።

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራይቼል ኦማሞ አገራቸው ኢትዮጵያን ችላ እንደማትላትና የሰከነና የተለሳለሰ ዲፕሎማሲን በመጠቀም በአገሪቱ የተከሰተው ችግር እንዲያበቃ አብራት መስራቷን ትቀጥላለች ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት ትላንት የኬንያን የውጭ ፖሊሲ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች በተመለከተ ናይሮቢ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ራይቼል ኦማሞ ፥ " ምንም እንኳን ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም ኢትዮጵያ ከስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል አቅም አላት " ብላ ኬንያ እንደምታምን ገልጸው፣ ለዚህም በቅርቡ የፖለቲካ እስረኞች የመለቀቃቸው እርምጃን እንደ በጎ ጅማሬ ጠቅሰዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም በአገሪቱ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አኳያ በብሔራዊ ውይይት ፣ በተኩስ አቁም እና ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ መንገድ ማመቻቸትን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ጋር ተቀራርበው ሲሰሩ እንደነበር መናገራቸውን ቢቢሲ በዘግባው አስፍሯል።

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚካኤል ደንፎርድ ጋር ተወያይተዋል።

አቶ ሙስጠፌ በውይይቱ ፤ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ሁኔታ ዙሪያ መክረዋል።

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የተመጣጠነ ምግብ እጥረትን ለመከላከል እና ህይወትን ለማዳን ለተጎዱ ወገኖች የሚደረገውን የምግብ እርዳታን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተውበታል።

ምንጭ፦ የአቶ ሙስጠፌ የተረጋገጠ የትዊተር አካውንት

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

እድሳት የተደረገለት የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ህንፃ በነገው እለት እንደሚመረቅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

ይህ ታሪካዊ እና የከተማዋ ምልክት የሆነ ህንፃ ከ57 ዓመት በኋላ ለእድሳት የበቃ መሆኑና የከተማዋ የዘመናት ጉዞ አሻራ የያዘ ታላቅ ቅርስ ጭምር መሆኑ ተገልጿል።

የከተማው አስተዳደር ፤ ህንፃውን እጀግ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንዲታደስ ማድረጉን ገልጾ ለተገልጋይ ምቹና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ሁሉ ባሟላ መንገድ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን ታስቦ መሰራቱን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

ጄነራል መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ አዲስ አበባ ሲደርሱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ እና የብሄራዊ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎና የልዑካን ቡድናቸው በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ ከተለያዩ የመንግሰት የስራ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በዉይይታቸው የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብር ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራ ፍላጎት ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ጉዳዮችን ማሳደግ እና መደገፍ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

ምንጭ ፦አል ዓይን ኒውስ ፣ ኢብኮ እና የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና)

@tikvahethiopia
#DStv

የዲኤስቲቪን ማህበራዊ ድረገፆች ይከታተሉ!
ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀላሉ

Facebook: https://bit.ly/2ULhG8U
Telegram: https://bit.ly/3y59gYz
Instagram: https://bit.ly/3rwIOEM
Twitter: https://bit.ly/3yieDU8
ነገ በአዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ የታላቁ ሩጫ ይካሄዳል።

የ2014 ዓ/ም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

የሩጫ ውድድር የሚካሄድባቸው መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አመራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ተጠይቋል፡፡

የ2014 ታላቁ ሩጫ መነሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ የሚጀምር ሲሆን በአዲስ አበባ ስታዲዮም፣ ሜክሲኮ አደባባይ፣ በልደታ ቤተክርስቲያን በማድረግ ፣በዛጉዌ ህንፃ በመታጠፍ-በጌጃ ሰፈር ፣ጎማ ቁጠባ በፍልውሃ ፣በማድረግ በካዛንቺስ ፣በኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ ባንቢስ በመታጠፍ መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደርጋል፡፡

የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖርና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንዲችሉ ለተሸከርካሪ ዝግ የሆኑ መንገዶች እንደሚኖሩ ፖሊስ ገልጿል።

በዚህም መሰረት ፦

• ኮቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ህንፃ፤

• ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍለጦር፤

• ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኬኬ ህንፃ ወይም ጨርቆስ ማዞሪያ፦

• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባበይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ገብርኤል መሳለሚያ፤

• ከሳር ቤቶች አደባባይ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ አፍሪካ ህብረት አደባባይ ፤

• ከካርል አደባባይ ወደ ከፍተኛ ፍ/ቤት የሚወስደው መንገድ ልደታ ፀበል፤

•ከጦር-ኃይሎች ወደ ሚክሲኮ ለሚመጡ ኮካ መገንጠያ ፤

• ከሜክሲኮ ልደታ ኮንደሚኒዬም መብራት፤

• ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ በርበሬ በረንዳ፤

• ከተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጎማ ቁጠባ የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር (ሼልድሬንስ)

• ከቸርቸር ጎዳና ወደ አምባሳደር ፣ ከሜክሲኮ እና ለገሃር ለሚመጡ አገር አስተዳደር/ኢምግሬሽን/ መብራት ፤

• ከአዋሬ ወደ ካዛንቺስ ለሚመጡ ሴቶች አደባባይ- ከመገናኛ ወደ 22 ለሚመጡ ዘሪሁን ህንፃ፤

• ከቦሌ መድሃኔዓለም የሚመጡ አትላስ ሆቴል አካባቢ፤

ከጠዋቱ 11፡30 ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በተጨማሪም ፥ አሽከርካሪዎች የውድድሩ ተሳታፊዎች ወደ ሚያልፉባቸው መንገዶች ተሽከርካሪ ይዞ መውጣት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።

ማንኛውም አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም ሆነ ለፖሊስ መረጃ ለመስጠት 011-1-11-01 11 እና በ991 ነፃ የስልክ ቁጥሮች መጠቀም እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ ያሳውቋል።

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሀገር ቤት ጥሪን ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ማህበራት ተወካዮች እና አባላትን አግኝተዋል። በበርካታ ጉዳዮችም ላይ መወያየታቸውን የጠ/ሚ ፅ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia