TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሰናበተች። ሀገራችን ከ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ውጭ ሆናለች። ብሄራዊ ቡድናችን ዛሬ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ እኩል ቢለያይም በአንድ ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል። በዛሬው ጨዋታ ጌታነህ ከበደ በፍጹም ቅጣት ምት ለሀገራችን ብቸኛዋን ጎል በ52ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡ @tikvahethiopia
ፎቶ : የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የልዑካን ቡድን ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ደርሷል።

ብሄራዊ ቡድኑ አዲስ አበባ ሲደርስ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ፣ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፣ ከፌዴሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች እና ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ አካላት አቀባበል አድርገዋል።

የብሄራዊ ቡድኑ አባላት ከቦሌ አየር ማረፍያ ወደ ጁፒተር ሆቴል ያመሩ ሲሆን በሆቴሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጎላቸው የተዘጋጀላቸውን ኬክ ቆርሰዋል ተብሏል።

More : @tikvahethsport
#ውበት

ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ?

0911607446 ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!              
ሙሉ ከወገብ በላይ (ቦዲ) - 950ብር
የቦርጭ ብቻ (ጉርድ) -650  ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ @wibet1
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ ቤዛ ህንፃ 2nd floor # webet
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቫይረሱ ቢቀያየርም መፍትሔው አልተቀየረም!

ስለክትባት እና ተያያዥ መረጃዎች የጤና ሚኒስቴር መመሪያዎችን ይከተሉ!!

#Lifebuoy #LifebuoyEthiopia #COVID19

@tikvahethiopia
#ወይብላ_ማርያም

የኢ.ኦ.ተ.ቤ. መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ፥ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ መቅደሷ ሳትገባ ወደ ኋላ ተመልሳ ቀራንዮ መድኃኔዓለም የቆየችውን ወይብላ ማርያም ታቦትን ለማስገባት ምእመናንንም ለማጽናናት በቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን መገኘታቸውን አሳውቋል።

ከእርሳቸው ጋር የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ ቆሞስ አባ ተክለሀይማኖት ወልዱ በስፍራው መገኘታቸውም ተገልጿል።

በክስተቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ ደግሞ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እና ሌሎች የቤተክርስቲያኗ ክፍሎች የሚሰጡት መረጃ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#EthiopianCoffee☕️

11 ሺህ ከረጢት የኢትዮጵያ 🇪🇹 ቡና በአምስት ሰከንድ ውስጥ ተሸጠ።

በቻይና በተካሄደ የቀጥታ ሽያጭ ስነስርዓት 11 ሺህ ከረጢት የኢትዮጵያ ቡና በአምስት ሰከንድ ውስጥ መሸጡን የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

በሚኒስቴሩ የአፍሪካ ጉዳይ ጀኔራል ዳይሬክተር ዉ ፔንግ በትዊተር ገጻቸው ፤ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በተገኙበት የተካሄደው የቀጥታ ሽያጭ ሂደት ውጤታማ ነበር ብለዋል።

የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ውስጥ ፍላጎቱ እያደገ መምጣቱን የገለጹት ዉ ፔንግ፤ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ከጥር እስከ ህዳር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ወደቻይና የገባው የኢትዮጵያ ቡና መጠን ቀደም ካለው ጊዜ አንጻር በ196 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል።

በመጪዎቹ ዓመታት ቻይና ከአፍሪካ የግብርና ምርቶችን በስፋት እንደምታስገባም ጠቁመዋል።

#ENA

@tikvahethiopia
#Gambella

" በጥቃቱ የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 5 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል " - ፖሊስ

በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ።

በጥቃቱ የ8 ሠዎች ህይወት ሲያልፍ በ5 ሠዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ተገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ ፥ በጋምቤላ በዚህ ሰዓት በጋ ስለሆነ እና ክልሉን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያጋራው ድንበር ሰፊና ክፍት ስለሆነ የታጣቂዎች የመግባትና የመውጣት አዝማሚያ አለ ብለዋል።

የሙርሌ ታጣቂዎች ትናትና ድንበር አቋርጠው በመግባት በኑዌር ዞን አኮቦ ወረዳ በካንካን ቀበሌ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት የ8 ሠዎች ህይወት ወዲያው ሲያልፍ 5 ሠዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል።

ኮሚሽነር አቡላ አክለውም ክልሉ በአሁኑ ሰዓት ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻ በመጠቀም ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ኮሚሽነሩ ፤ የአካባቢው ማህበረሰብ የታጣቂ ቡድኑን እንቅስቃሴ ነቅቶ በመጠበቅ ለመንግሥት ተገቢውን ጥቆማ ማድረግ እንደሚኖርበት አሳስበው በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገልጸዋል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከዓመታት በፊት፤ በኑዌር ዞን እና አኙዋ ዞኖች ገብተው በርካታ ሕፃናት አፍነው ሲወስዱ፣ ከአንድ መቶ ሰባ በላይ ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።

ከ2 ሺህ በላይ ከብቶች መውሰዳቸውንም ኮሚሽነሩ አስታውሰዋል።

በወቅቱ የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት ወደ ደቡብ ሱዳን በመግባትና ታጣቂዎቹ የሚኖሩበት አካባቢ ላይ ጥቃት በመፈፀም ታፍነው ከተወሰዱት ሕፃናት መካከል ከ100 ሕፃናት በላይ ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሱን አስረድተዋል።

ምንጭ፦ የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በህገመንግስቱ መሰረት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ማቋቋምያ አዋጅን ባለፈው ሳምንት መፈረማቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ፥ " መፈረም ኃላፊነቴ ቢሆንም እውነተኛና አካታች ብሄራዊ ምክክርን ቁልፍነት ስለማውቅ፣ ስለሰራሁበት ፣ ውጤቱንም ስላየሁ አምንበታለሁ " ብለዋል።

" እንደዚህ ያለ ምክክር በመሰረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት እንዲኖር ያደርጋል፤ ሀሳብን በግስ መጫን፣ ጦር መማዘዝን፣ ህዝብን ፣ አገርን አደጋ ላይ መጣልን ... ከመሳሰሉ አደጋዎች ያድናል። የንግግር የመደማመጥ፣ መከባበር አዲስ ባህል ይፈጥራል። እንደ እኛ ከአውዳሚ ጦርነት ማግስት ለሚገኝ አገር ጠቀሜታው ግልፅ ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን አባላት ጥቆማ ለአንድ ሳምንት ከተራዘመ በኃላ ጥር 13 (ዛሬ) እንደሚያበቃ የገለፁት ፕሬዜዳንቷ "ለኮሚሽነርነት የተጠቆሙ ሴቶች ቁጥር አነስተኛ ይሆናል ብዬ እሰጋለሁ" ብለዋል።

" ሴቶች መጠቆም አለባቸው። ያካሄድነው ጦርነት ያስከተለው ሰቆቃ የሴት መልክ ነው ያለው። በመቐለ እና በደሴ መጠለያ ጣቢያዎች ያነጋገርኳቸው ሴቶች ይህንኑ ያረጋግጣል። ይሁንና እያዘኑ፣ እያለቀሱ ቢያነጋግሩኝም እንባቸውን ጠርገው ጥያቄ አቅርበዋል። የመፍትሄ ሀሳብም ሰጥተዋል " ሲሉ ገልፀዋል።

ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ፤ " ጦርነታ በሴቶች ላይ ያስከተለው ሁኔታ ገና ብዙ የሚታይ ነው። ሴት ሰለባ ብቻ ሳትሆን የመፍትሄ አካል መሆንዋ ከግንዛቤ መወሰድ አለበት፤ የሴቶች ኮሚሽነሮች መኖር ካላቸው አጠቃላይ ኃላፊነት ጋር የእነዚህም ሴቶች ድምፅ ይሆናሉ " ብለዋል።

አክለው፥ " በቀረው ጠባብ ጊዜ የወጡትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሴቶችን ትጠቁሙ ዘንድ ለማበረታታት እፈልጋለሁ " ሲሉ ገልፀዋል።

* ሙሉ መልዕክቱ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ፓትርያርኩ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ። በዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና ህክምናቸውን በንቃት እየተከታተሉ እንደሚገኙ ታውቋል።…
#Update

ቅዱስ ፓትርያርኩ ህክምናቸውን ጨርሰው ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተመለሱ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሆስፒታል ሲደረግላቸው የነበረውን ህክምና ጨርሰው በሙሉ ጤንነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በሰላም ተመልሰዋል።

መረጃውን ከኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba 📍ቦሌ አትላስ አካባቢ የደረሰው አደጋ 9:20 አካባቢ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። ዛሬ ከሰዓት 8 ሰዓት አካባቢ ቦሌ አትላስ አካባቢ የሚገኙት የግንባታ ዕቃዎች መጋዘኖች ላይ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። የእሳት አደጋው በቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስትያን እና በአትላስ እንዲሁም በፀጋ ሆስፒታል መሃል ላይ በሚገኙት የንግድ ሱቆች መጋዘኖች ላይ የደረሰው።…
#Update

" በእሳት አደጋው 2.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል " - የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ አትላስ አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ 2.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አሳውቋል።

በአደጋው ከንብረት ውድመት በቀር በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ተከላካይ ሰራተኞች ባደረጉት ጥረት ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳን መቻሉም ተገልጿል።

8 ሰዓታትን በፈጀው እሳት የማጥፋት ሥራ 119 የአደጋ መከላከል ባለሙያዎች መሳተፋቸውንም ተናግሯል፡፡

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ፥የአደጋው መንስኤ አለመታወቁንና 400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መጋዘን ሙሉ በሙሉ መውደሙን ተናግረዋል፡፡

አደጋውን ለመቆጣጠር 14 የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች፣ 2 አምቡላንሶች፣ 142,000 ሊትር ውሃ እና 155 ሊትር ኬሚካል ጥቅም ላይ መዋሉንም አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ወይብላ_ማርያም የኢ.ኦ.ተ.ቤ. መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ፥ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ መቅደሷ ሳትገባ ወደ ኋላ ተመልሳ ቀራንዮ መድኃኔዓለም የቆየችውን ወይብላ ማርያም ታቦትን ለማስገባት ምእመናንንም ለማጽናናት በቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን መገኘታቸውን አሳውቋል። ከእርሳቸው ጋር የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ…
#UPDATE

" መንግሥት ማጣራት በማድረግ ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለሕግ ያቀርባል " - የመንግስት ኮሚኒኬሽን

የኢትዮጵያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ፤ የጥምቀት በዓል በመላ ኢትዮጵያ በደመቀና በሰላማዊ መንገድ ቢከበርም በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ እና በቡራዩ አዋሳኝ ወይብላ ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ በተፈጠረው ችግር በዓሉ መስተጓጎሉና በሰዎች ላይም ሞትና ከባድ ጉዳት መድረሱን አሳውቋል።

በዓሉ በተገቢው መንገድ ባለመከበሩ፣ እንዲሁም በደረሰው የሰው ሕይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት መንግሥት ጥልቅ ኀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

መንግሥት በስፍራው የተፈጠረውን ክሥተት በማጣራት ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለሕግ እንደሚያቀርብም አስታውቋል።

" ለዘመናት የኢትዮጵያዊነታችን መገለጫ እንዲሁም የጠንካራ ማኅበራዊ መስተጋብራችን ማሳያ በሆኑ እንደ ጥምቀት በዓል ያሉ ሀብቶቻችንን ለማደብዘዝ የሚደረግ ማንኛውም ጥረት በሁሉም ኢትዮጵያዊ ትብብር ይከሽፋል። " ብሏል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ወይብላ_ማርያም የኢ.ኦ.ተ.ቤ. መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ፥ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባ እና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ መቅደሷ ሳትገባ ወደ ኋላ ተመልሳ ቀራንዮ መድኃኔዓለም የቆየችውን ወይብላ ማርያም ታቦትን ለማስገባት ምእመናንንም ለማጽናናት በቀራንዮ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን መገኘታቸውን አሳውቋል። ከእርሳቸው ጋር የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ…
#Update

የማኅደረ ስብሀት ወይብላ ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ታቦታት ወደ መንበረ ክብራቸው ገቡ።

የማኅደረ ስብሐት ወይብላ ቅድስት ማርያምና የቅዱስ ሚካኤል ታቦታት ትላንት ካደሩበት ቀራንዮ መድኅኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በብጹእ አቡነ መልከጼዴቅ ፣ ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ፣በአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ በብዙ መቶ ሺዎች በሚቆጠሩ ምእመናን ታጅቦ ወደ መንበረ ክብሩ ገብቷል።

በትላንትናው ዕለት የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ ሊቀ ጉባኤ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ወልዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ መልአከ ህይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፉ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የካህናት አስተዳደር ክፍል ኃላፊ ፤ ከደብሩ ኃላፊ፣ ከወጣቶች ተወካዮች እንዲሁም ከምእመናን ተወካዮች ጋር ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ 6 ሰዓታትን የፈጀ ውይይት በማድረግ በቀጣይ ቀናት አሉ የተባሉ ጥያቄዎችን በተመለከተ በቤተ ክርስቲያን መዋቅር በኩል እንዲቀርብ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

የተፈጠረውን ችግር በተመለከተ ከካህናት ፣ ከሰንበት ትምህርት ቤትና ከምዕመናን ተወካዮች ተውጣጥቶ ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር በጋራ ለመስራትና ጥያቄዎቹ በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ ተቋማዊ የሆነ አሰራርን ተከትሎ በቅድሚያ ለአ/አ ሀገረ ስብከት እንዲቀርብ ስምምነት ላይ መደረሱ መታወቁን የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት ገልጿል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫው በትላንትናው ክስተት የሰው ህይወት መጥፋቱን በማረጋገጥ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ለድርጊቱ ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለህግ እንደሚያቀርብ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#twitter

ትዊተር ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ "ህግ የጣሱ " ያላቸዉን ተጠቃሚዎች ማገዱን ዛሬ አሳውቋል።

ትዊተር እንዳለው ብዙ አካዉንቶች ታግደዋል፤ ከታገዱት መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት የትግራይ ደጋፊ ተጠቃሚዎች ይመስላሉ ብሏል።

ይሁንና ትዊተር የታገደዉ አካዉንት መጠን ምን ያህል እንደሆን በውል አልገለፀም።

ትዊተር እርምጃዉ የተወሰደው "የትዊተርን ህግ በመጣስ፣ የተወሰኑ ሃሽታጎች እና የትዊተር ገፆች፤ በተለጠፈዉ መረጃ ላይ በተደጋጋሚ በአላስፈላጊ ሁኔታዎች በማካተታቸው ነው። በተጨማሪ ርምጃዉ " በኢትዮጵያ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተገናኘ በትዊተር ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ደኅንነታቸው በተጠበቀ መልኩ እንዲሄድ ከምናደርገው ጥረት ጋር የተገናኘ ነው " ብሏል።

እገዳዉን በተመለከተ " በተጨባጭ በአካውንቶቹና ይዘቶቹ ላይ ያተኮሩ " መሆኑን እና " ከፖለተካዊ ማንነት እና ርዕዮተ ዓለም ገለልተኞች ነን " ሲል ገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ / ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
ግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ ሊመረቅ ነው።

ባንኩ ፥ " ከምስራቅ አፍሪካ ረጅሙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ የዋና መ/ቤት ህንፃ ምርቃት ከባንኩ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ጋር ገጥሟል፡ " ብሏል።

በትክክል የሚመረቅበት ቀን ይፋ ይሆንም በቅርቡ ግን ህንፃው እንደሚመረቅ ተገልጿል።

@tikvahethiopia