TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስር ስለተፈቱ ግለሰቦች ምን አሉ ? ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦ " ... ትላንት ክስ የተቋረጠላቸው የተሸነፉ ኃይሎች ክስ እንዲቋረጥ እና ከእስር ቤት እንዲወጡ ሲደረግ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል። ይህ ቁጣ የተቀሰቀሰው በሁለት ቡድኖች ነው። አንደኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ጭር ሲል የማይወድ ፣ ሁል ጊዜ እያጋጨ በሰበር ዜና ብር የሚሰበስብ፣ የት እንዳለ የማይታወቅ ካለበት ሆኖ ስንዋጋ…
#ተጨማሪ

ከእስር ስለተፈቱት ግለሰቦች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን ተናገሩ ?

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ... ክስ የተቋረጠላችሁ ወገኖች ስላሸነፍን መበቀል እየቻልን ይቅር ማለትን ስለመረጥን ክስ አቋርጠን እናተን ሳይሆን ከእናተ ጀርባ ያለውን ህዝብ አክብረን የወሰን መሆናችንን አውቃችሁ ይህን እድል ሳታበላሹ እንድትጠቀሙበት ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ።

ክስ ማቋረጥ ማለት ምህርተ መስጠት ማለት አይደለም። ክስ የተቋረጠለት ሰው በአግባቡ መጠቀም ካልቻለ መልሶ የክስ መዝገቡን መምዘዝ የሚቻል ስለሆነ።

በዚህ ጉዳይ ያዘኑ፣ የተቆጡ፣ የኢትዮጵያ ቁርጥ ቀን ልጆች እንዲገነዘቡ የምፈልገው የወሰድነው መድሃኒት ማስታገሻ አይደለም የወሰድነው መድሃኒት ፈዋሽ በመሆኑ የጎንዮሽ ጉዳት አለው ፤ ይጎረብጣል ያማል ! ለማዳን ብቻ ሳይሆን በጎንም የመጎርበጥ ባህሪ አለው።

ለጊዜው የሚያስታግስ ሳይሆን ለልጆቻችንም የድልና የአሸናፊነት መንፈስ የሚያላብስ ስለሆነ እንደኛ ደጋግማችሁ ስታስቡት ጠቀሜታው ጎልቶ ይታያችኃል እናም ደግማችሁ ለማሰብ ልባችሁና አእምሯችሁ እንዲከፈት ዋናው አላማ የምትወዷትን ሀገር ኢትዮጵያን አንድ አድርገን ለማፅናት ካለን ፍላጎት አንፃር ብቻ የመነጨ መሆኑን እንድትገነዘቡ ቢያንስ ቢያንስ ጉቦ በልተን እንዳለቀቅናቸው እንድታስቡ ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ። "

@tikvahethiopia
#TPLF

ጠቅላይ ሚኒስትሩ TPLFን በተመለከተ ምንድነው ያሉት ?

ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፦

" ... አሁን ወደ ትግራይ ክልል ዘልቀን የማንገባበት በርካታ ምክንያቶች ያሉን ቢሆንም አንገባም ብለን ከቆምን በኃላ ነገሩን በተለየ መንገድ ለማየት ጥረት እያደረግን ባለንበት በዚህ ወቅት አሁንም TPLF አላረፈም። አሁንም TPLF በግራ በቀኝ ሊነካካን ይፈልጋል። 

ለ7ኛው ስህተት የሚጓዘው TPLF በፍፁም ድል ማግኘት የማይችል እንኳን ቢሆን በወጣቶች የትግራይ ልጆች ላይ በህይወት የመቀጠፍ የመቁሰል አደጋ የሚያስከትል ስለሆነ 7ኛው ስህተቱ መስመር ስቶ ሳይሄድ መማር የሚችልበት እድል መፍጠር የራሱ (TPLF) ቢሆንም እንኳ እንደባላንጣ አትንኩን ፤ እረፉ ለማለት እወዳለሁ።

የነካካችሁን እንደሆነ በተለመደው መንገድ የከፋ ቅጣት ይደርስባችኃልና።

ትላንትና እንኳን ክስ አቋርጠን እስረኞች ይውጡ ስንል የTPLF ጀሌዎች ከፊሉ የአማራ አካውንት ከፊሉ የኦሮሞ አካውንት አስመስሎ በመክፈት እኛን ለማባላት ሳይተኙ አድረዋል። አማራ መስለው ፣ኦሮሞ መስለው ብዙ ጥረት አድርገዋል። "

ያንብቡ : https://telegra.ph/Dr-Abiy-Ahmed-01-09
#Amhara

ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከሐምሌ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከመኖሪያ ቀዬአቸው ከተፈናቀሉት ዜጎች ውስጥ፣ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑት ወደ ቀደመ መኖሪያቸው መመለሳቸቸው ተገልጿል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽነር አቶ ዘለዓለም ልጃለም ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል፥ በአሁኑ ወቅት ህወሓት በሰሜን ጎንደር አልፎ አልፎ በሚያደርገው ትንኮሳ ምክንያት በቅርቡ እንደሚመለሱ ከሚጠበቁትና በደባርቅ መጠለያ ውስጥ ከሚገኙት 200 ሺህ ተፈናቃዮች ውጪ፣ በሌሎች አካባቢዎች በመጠለያ የነበሩት ተፈናቃዮች ሙሉ በሙሉ ተመልሰዋል ብለዋል።

በጦርነቱ ከተፈናቀሉት በተጨማሪ ቀደም ሲል በአጣዬ ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት የተፈናቀሉ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቤንሻንጉል ነፃ አውጪ ነኝ እያለ በሚንቀሳቀሰው ኃይል የተፈናቀሉ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በኦነግ ሸኔ ጥቃት ደርሶባቻው ተፈናቅለው በመጠለያ የሚገኙ ዜጎች ቁጥር 900 ሺ መድረሱን ገልጸዋል፡፡

ህወሓት በከፈተው ጦርንት ምክንያት ተፈናቅለው ወደ ቀዬአቸው የተመለሱትን ጨምሮ ተወረው በነበሩ አካባቢዎች በደረሰው ዝርፊያ፣ ውድመትና የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር 11.4 ሚሊዮን መድረሱን አክለዋል፡፡

ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ ዜጎች ወደአምራችነት እስኪገቡና መቋቋም እስኪችሉ ለመመገብ በየወሩ 1.2 ሚሊዮን ኩንታል ምግብ የሚያስፈልግ ቢሆንም አሁን መቅረብ የቻለው 426 ሺ ኩንታል ምግብ ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ክልሉ የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ሥራ በማከናወን ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ባለሙያዎችና ጉዳት የደረሰባቸው ተቋማት መሪዎች የተካተቱበትና 6 ቡድን የያዘ የአጥኚዎች ስብስብ በአጠቃላይ በጦርነቱ የደረሰውን ጉዳት እያጠና ነው።

@tikvahethiopia
#ተጠናቋል

የሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሻን ጉራቻ የመንገድ ግንባታ ተጠናቋል።

35 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ ቢሻን ጉራቻ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ ሁለት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፥ የመጀመሪያው 14 ኪሎ ሜትር ከቢሻን ጉራቻ በመነሳት ወደ ሐዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ የሚሄድ ነው።

መንገዱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ የወሰደው 592 ሚሊየን 84 ሺህ ብር ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን፥ የመንገዱን ግንባታ አለም አቀፉ የስራ ተቋራጭ ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ኩባንያ አከናውኖታል።

በማማከርና በቁጥጥር ስራው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን መሳተፉን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

@tikvahethiopia
#Timket

የጥምቀት በዓል ሊከበር ቀናቶች ቀርተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የጥምቀት በዓል በድምቀት የሚከበርበት የጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ሥራ በመፋጠን ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ወቅታዊ የግንባታ ይዘቱ ከላይ በፎቶ ተያይዟል።

Photo Credit : EOTCTV

@tikvahethiopia
#Kenya

የኬንያ ፖሊስ አገሪቱ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ተገኝተዋል ያላቸውን ከ90 በላይ ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።

ፖሊስ ከጎረቤት አገራት በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞች ለመቆጣጠር እሁድ ምሽት አካሄድኩ ባለው አሰሳ 91 ኢትዮጵያውያን ከናይሮቢ ወጣ ብሎ በሚገኝ አንድ ቤት ውስጥ መያዙን ገልጿል።

የአገሪቱ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል እንዳለው ሁሉም ስደተኞች ወንዶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ነው። ጨምሮም እንዲቆዩ ከተደረጉበት ቤት ሰብረው ለመውጣት ሙከራ አድርገው እንደነበረም አመልክቷል።

በሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካይነት በጭነት መኪና ወደ ኬንያ መግባታቸውን ያመለከተው ፖሊስ፤ በተያዙበት ቤት ውስጥ በጊዜያዊነት ቆይተው ወደ ሌላ አገር ሊሸጋገሩ እንደነበር ተገልጿል።

ስደተኞቹን የሚያጓጉዙት ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር የገቡትን ከ90 በላይ ኢትዮጵያውንን በአንድ ቤት ያቆይዋቸው ቀጣይ ጉዟቸውን አስኪያመቻቹ ድረስ እንደሆነ ፖሊስ ተናግሯል።

አሁን በሕገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ገብተው የተያዙት ስደተኞች በቁጥር ከፍተኛ ተብሎ ከሚጠቀሱት መካከል ሲሆን ኢትዮጵያውያኑን ያመጧቸው የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ለመያዝ ክትትል እያደረገ ይገኛል።

ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ በሕገ-ወጥ መንግድ ወደ ኬንያ ገብተው ተገኝተዋል ያላቸውን 4 አዋቂዎችና 10 ልጆችን በአጠቃላይ 14 ኢትዮጵያውያንን ፖሊስ በቁጥጥር ማዋሉን አስታውቋል።

ስደተኞቹ ሊያዙ የቻሉት ማዕከላዊ ኬንያ ውስጥ የተከሰተን አደጋ ተከትሎ ሲሆን በተደረገ ፍተሻ ኬንያ ውስጥ ለመገኘት የሚያስችል ሕጋዊ ሰነድ እንደሌላቸው በመታወቁ ነበር።

14ቱን ኢትዮጵያውያን ከቦታ ቦታ ሲያጓጉዙ ነበር የተባሉ 2 ኬንያውያንም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#GoodayOn Mobile App

የፈለጉትን ባለሙያ ካሉበት ሆነው አማርጠው የሚያገኙበት መተግበሪያ!

አስጠኚ ፣ ሹፌር ፣ ቧንቧ ሰራተኛ ፣ ኤሌክትሪሺያን ፣ ዲሽ ጥገና ፣ መካኒክ ፣ የግንባታ ፊኒሺንግ ፣ ሽያጭ ፣ የሂሳብ ባለሞያ እና ...ሌሎችም

ከGoodayOn መተግበሪያ በተጨማሪ ፤ ወደ 9675 ጥሪ ማእከል በመደወል አገልግሎታችንን ማግኘት ይችላሉ።

GoodayOn መተግበሪያን ለማውረድ ፤ https://cutt.ly/JWR6vZb
ቴሌግራም ቻናል ፤ @goodayOn #ጉዳይ 9675
በሱዳን 2 ሰዎች ተገደሉ።

ጎረቤት ሀገር #ሱዳን በተቃውሞ መናጧን የቀጠለች ሲሆን ትላንት እሁድ በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉን ለማወቅ ተችሏል።

በኦምዱርማን እንዲሁም በካርቱም በሀገሪቱ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል።

የሱዳን የዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ በትላትናው ሰልፍ የሁለት ሰዎች ማለፉን ሪፖርት ያደረገ ሲሆን አንደኛው ሟች ትላንት አንዱ ደግሞ ዛሬ ነው የተገለፀው።

ተቃውሞ ከተነሳ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የተገደሉ ሰዎች 63 ደርሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas በትላንትናው ዕለት ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ ቀለብ (አስቴር) ስዩም በዋና ጽ/ቤት አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል። @tikvahethiopia
#Update

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ ዛሬ ጥር 2 ቀን 2014 ዓ/ም መደበኛ ሥራቸውን እንደጀመሩ በተረጋገጠ የትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።

ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 30 ቀን 2014 ዓ.ም በባልደራስ ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ከእስር ለተፈቱት ከፍተኛ አመራሮች፤ በአባላት አቀባበል እንደተደረገላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed #JoeBiden

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በተለይም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ጠቁመዋል።

ውይይቱ ሁለቱ አገራት በጋራ መከባበር ላይ የተመሰረተ ገንቢ ተሳትፎ በማድረግ ትብብራቸውን ለማጠናከር ትልቅ ጥቅም እንዳለው ሁለታችንም ተስማምተናል ብለዋል።

#DrAbiyAhmed #ENA

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 7,154
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 2,144
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 12
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 1,074

በሀገራችን ኢትዮጵያ ዛሬን ጨምሮ ትላንትና ከትላንት በስቲያ በአጠቃላይ 4,081 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 30 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
#WANTED #ተፈላጊ

በምስራቅ ጎጃም ዞን በ ' ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ' በቀራንዮ ንዑስ ከተማ ታህሳስ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 አካባቢ የፍቅር ጥያቄ አቅርቦ አለመግባባት በመፈጠሩ ምክንያት ተጠርጣሪው አቶ ይኸነው ፈንታ ይሁኔ የተባለ ግለሰብ የፍቅር ጥያቄ ባቀረበላት ወጣት ፊት እና ሌሎች የሰውነት ክፍሏ ላይ አሲድ በመድፋት ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት በማድረስ ከአካባቢው ተሰውሯል፡፡

የወረዳው ፖሊስም ወንጀሉ ከተፈፀመበት ሰዓት ጀምሮ ተጠረጣሪ ወንጀለኛውን ለመያዝ ክትትል እያደረገ የሚገኝ ቢሆንም አሁንም በቁጥጥር ሥር አልዋለም።

ስለሆነም ተጠረጣሪ ግልሰቡ ያለበትን አካባቢ ለፖሊስ ትብብርና ጥቆማ በመስጠት በህግ ቁጥጥር ሥር እንዲውል ህዝቡ እገዛ እንዲያደርግ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ስልክ ቁጥር ፡ 058 661 02 01

" ወንጀል ሠርቶ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም "

( በምስራቅ ጎጃም ዞን የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ፖሊሲ ጽህፈት ቤት )

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrAbiyAhmed #JoeBiden የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በተለይም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን…
#Update

የነጩ ቤተመንግስት (ዋይት ሀውስ) መግለጫ ፦

ዋይት ሀዋስ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ መወያየታቸውን አሳውቋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በኢትዮጵያ ስላለው ግጭት እና ሰላምና ዕርቅን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ላይ መክረዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደን በቅርቡ ስለተፈቱት በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምስጋና አቅርበዋል።

ሁለቱ መሪዎች በድርድር የተኩስ አቁም ስምምነትን ማፋጠን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፣በመላው ኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦትን በአስቸኳይ ስለማሻሻል ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስር ስለታሰሩ ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ሁሉም የተጎዱ ኢትዮጵያውያን የሰብአዊ መብት ጥያቄዎችን መፍታት በሚያስፈልግበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ጆ ባይደን በቅርቡ የተፈጸሙትን የአየር ድብደባዎች ጨምሮ እየቀጠለ ያለው ግጭት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳትና ስቃይ እያስከተለ እንደሚገኝና ይህም እንደሚያሳስባቸው ገልጸው አሜሪካ ከአፍሪካ ህብረት እና ከአካባቢው አጋሮች ጋር በመሆን ኢትዮጵያውያን ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ሁለቱም መሪዎች የአሜሪካ እና ኢትዮጵያ ግንኙነት አስፈላጊነት፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያለውን ትብብር ለማጠናከርና ግጭቱን ለመፍታት ተጨባጭ መሻሻሎች እንደሚያስፈልግ አስምረውበታል።

@tikvahethiopia
#Update

ከወራት በፊት በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተልከው ወደ አዲስ አበባ መጥተው የነበሩት ዴሞክራቱ ክሪስ ኩንስ የእስረኞችን መፈታት በደስታ እንደሚቀበሉ ገልፀዋል።

ኩንስ ፥ " የኢትዮጵያ መንግስት በርካታ ታዋቂ የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት እና የፖለቲካ እርቅ ሂደት ለመጀመር የወሰደውን እርምጃ በደስታ እቀበላለሁ " ነው ያሉት።

ኢትዮጵያን ወደፊት ለማራመድ ከTPLF ጋር የሚደረግ የሰላም ውይይትን ጨምሮ እውነተኛ ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ ውይይት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

ክሪስ ኩንስ ፤ ያልተቋረጠው የአየር ላይ ድብደባ (የሰሞኑን 56 ሰዎች የገደለውን በተፈናቃዮች ካምፕ ላይ የደረሰውን ጨምሮ) የተሳሳተ ምልክት ይሰጣሉ ፤ ልክ እንደሌሎች እርምጃዎች ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶችን ወደ ትግራይ እንዳይደርሱ ነው የሚከለክሉት ብለዋል።

ኩንስ ፥ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለሰላም የተደረጉት እርምጃዎችን ሲገነቡ ለማየት ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

@tikvahethiopia