TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ጋር ትናንት ሃሙስ መነጋገራቸው ተገልጿል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና አምባሳደር ፌልትማን መነጋገራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ትናንት ሃሙስ እንደተነጋገሩ ከመግለጽ ውጪ በምን ዐይነት መንገድ ተነጋገሩ በስልክ ወይስ በአካል ስለሚለው የገለጸው ነገር የለም፡፡

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ሆነ ጽህፈት ቤታቸው ስለጉዳዩ ያሉት ነገር የለም፡፡

ንግግሩን ተከትሎ በተለይ ዓመት ያስቆጠረውን ጦርነት በተመለከተ የሚገኙ አዎንታዊ ነገሮች ይኖራሉ በሚል አሜሪካ ተስፋ ማድረጓን ሮይተርስ ሚኒስቴሩን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው ይለቃሉ።

ምንጭ፦ አል ዓይን / ሮይተርስ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ “ ጀግና ሕዝብ - በቀኝ እጁ ድልን የሚጨብጥ፣ በግራ እጁ ይቅርታና ምህረትን የሚቸር ነው! ” በሚል መልዕክት አስታላልፈዋል።

በዚህ መልዕክታቸው ከድላችን ማግስት 4 ነገሮችን መርሖቻችን አድርገን እንድሄድባቸዋለን ብለዋል።

እነዚህም ፦

1ኛ. ድላችንን እንዳይቀለበስ አድርገን በሁለንተናዊ መስክ እናጠብቀዋለን።

2ኛ. ድላችን ዘላቂ እንዲሆን በፖለቲካዊና ሰላማዊ መንገዶች እንዲቋጭ እናደርገዋለን።

3ኛ. ድላችንን ለመጠበቅና ድላችን ዘላቂ ለማድረግ እንድንችል በአሸናፊ ምሕረት ግጭቱ የፈጠረውን ውጥረት እናረግባለን።

4ኛ. ያጠፋ እንዲቀጣ፣ የበደለ እንዲክስ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ ፍትህ በሽግርር እና በተሀድሶ ፍትህ እይታ ፣ ሀገራዊ ባህሎቻችን እና እሴቶቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ፍትህ እናሰፍናለን ፤ ሲሉ ገልፀዋል።

እነዚህ 4ቱ መርሖች አንዱ ሌላውን ሳይተካ ሁላችንንም አሸናፊ በሚያደርግ መልኩ እንደ አስፈላጊነታቸው ሁሉ እንተገብራለን ሲሉም አሳውቀዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በመልዕክታቸው በድል ፣ በምህረትና ትህትና ኢትዮጵያን ዘላቂና የፀናች አሸናፊ እንደርጋታለንም ብለዋል።

* ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ከእስር መፈታታቸውን ፓርቲው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ከእስር መፈታታቸውን ፓርቲው አሳውቋል። @tikvahethiopia
ፎቶ : አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከቂሊንጦ መፈታታቸውን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Update

በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱት ግለሰቦች ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ እንደተነገራቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

የእነ አቶ ጃዋር ጠበቃ የሆኑት አቶ ቱሊ ባይሳ ፥እነ አቶ ጃዋር ከማረሚያ ቤት እንዲወጡ እንደተነገራቸው እና ዛሬ በመምሸቱ አንወጣም ማለታቸውን ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#BREAKING

ከእስር በምሕረት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ፦

1. አቶ ስብሐት ነጋ

2. ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ

3. አቶ ዓባይ ወልዱ

4. አቶ አባዲ ዘሙ

5. ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር

6. አቶ ኪሮስ ሐጎስ

7. አቶ ጃዋር መሐመድና በእርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ

8. አቶ እስክንድር ነጋና በእርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ ሁሉ

@tikvahethiopia
የፍትሕ ሚኒስቴር ፦

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሕገ-መንግስት እና የሽብር ችሎት እየታየ ከነበሩት ተከሳሾች መካከል በነጃዋር ሲራጅ መሃመድ እና በእነ እስክንድር ነጋ ፈንታ መዝገብ ያሉ ተከሳሾች ክሳቸው በአዋጅ ቁጥር 943/2008 መሰረት እንዲነሳ ተደርጓል።

ክሱ እንዲነሳ የተደረገው በቀጣይ የሚደረገውን ሃገራዊ የምክክር መድረክ ሂደት ውጤታማነት እና አካታችነት ከፍ ለማድረግ በማሰብ መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዐሾ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ውስጥ የጤና እና የዕድሜ ሁኔታን ከግምት በማስገባት የስድስት ግለሰቦች ክስ እንዲነሳ መደረጉን ፍትሕ ሚኒስቴር ዛሬ ምሽት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Update

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ከእስር ተፈቱ።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሀምዛ አዳነ ከእስር ተፈተዋል።

ከሰዓታት በፊት ከጠበቃቸው መካከል ከሆኑት አቶ ቱሊ ባይሳ እነአቶ ጃዋር መሀመድ ስለመሸ እንደማይወጡ እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ቢገልፁም ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከማረሚያ ቤት ወጥተዋል።

ሶስቱን እስረኞች የጫነ ተሽከርካሪ የቃሊቲ ማረሚያ ቤትን ለቅቆ የወጣው ከምሽቱ አራት ሰዓት ተኩል ገደማ እንደነበር ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

እስረኞቹን የያዘው ተሽከርካሪ፤ የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ አባላትን በጫኑ ሶስት ፒክ አፕ መኪናዎች ታጅቦ ወደ ቦሌ አቅጣጫ ሲጓዙም እንደነበር ተገልጿል።

እነ ጃዋር ከእስር ሲለቀቁ አቀባበል ለማድረግ በርካታ ደጋፊዎቻቸው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቅራቢያ ሆነው ለሰዓታት ሲጠብቁ ቆይተዋል።

ከእነ አቶ ጃዋር ቀደም ብሎ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ ሸምሰዲን ጣሃ ሌሎችም በአቶ ጃዋር መዝገብ ስር ያሉ እስረኞች ተፈተዋል።

@tikvahethiopia
#Update

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፥ በኢትዮጵያ ቁልፍ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ በርካታ እስረኞች ከእስር መፈታታቸውን በደስታ እቀበላለሁ ብለዋል።

ዋና ፀሀፊው ፥ ሁሉም ወገኖች ግጭት እንዲቆምና ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት በማድረግ ፣ እንዲሁም ተአማኒና ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይትና የእርቅ ሂደት እንዲጀመር በመስማማት ይህን ትልቅ የመተማመን ግንባታ ሂደት እንዲያጎለብቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

ጉተሬዝ ፥ በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም እና ሰላምና መረጋጋትን ወደነበረበት ለመመለስ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በንቃት እሰራለሁ ሲሉም አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ : የኦሮሞ ፌዴራሊት ኮንግረስ / #ኦፌኮ / ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።

Credit : Boontuu Baqqalaa

@tikvahethiopia
" ወደቤታቸው አትሂዱ "

የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን ፥ የኦፌኮ አመራር የሆኑት አቶ ጃዋር መሀመድ በአሁን ሰዓት ባለው የደህንነት ሁኔታ ሊጠይቋቸው የሚመጡ ሰዎችን ሊቀበሉ እንደማይችሉ አሳውቋል።

የጠበቆች ቡድኑ ፥ የአቶ ጃዋር ጠያቂዎች ወደ መኖሪያ ቤታቸው ቢሄዱ ሊገቡ እንደማይችሉ በማወቅ ወደ ቤታቸው እንዳይሄዱ መልዕክት አስተላልፏል።

ሁኔታዎች ሲመቻቹና እሳቸው ጠያቂዎቻቸውን መቀበል ሲችሉ እንደሚያሳውቅ የኦሮሞ የፖለቲካ እስረኞች ጠበቆች ቡድን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Balderas

በትላንትናው ዕለት ከእስር የተፈቱት የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ ቀለብ (አስቴር) ስዩም በዋና ጽ/ቤት አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

መከላከያ ሰራዊት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የማዕረግ ምልክቶች ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

በምልክቶቹ ውስጥ ጋሻና አንበሳን ጥቅም ላይ ማዋሉን ነው የተገለጸው።

ማሻሻያ ያስፈለገው የሠራዊቱ ማዕረግ አገራዊ ይሁን ወታደራዊ ታሪካዊ ይዘት ያለውና የሠራዊቱንም ባህሪ ሊገልፅ የሚችል ሆኖ እንዲዘጋጅ በማስፈለጉ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia