ዋንግ ዪ ኤርትራ ገቡ።
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማምሻውን ኤርትራ ገብተዋል።
ዋንግ ዪን እና የልዑካን ቡድናቸው አስመራ ኤርፖርት ሲደርሱ በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዋንግ ዪ በኤርትራ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከአቻቸው (ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ) ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
Photo Credit : Yemane G. Meskel
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
ፌልትማን ምን አሉ ? " የአሜሪካ ፍላጎት ለ27 ዓመት በስልጣን ላይ የነበረውን ህወሓት መራሽ ኢህአዴግን ወደ ስልጣን መመለስ አይደለም " - አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከትናንት በስቲያ ከአ/አ ወደ ሀገራቸው አሜሪካ የሄዱት በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ስለቆይታቸው ከብዙሃን መገናኛዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። አምባሳደሩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት…
ፌልትማን ሀሙስ ኢትዮጵያ ይመጣሉ።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማ ሀሙስ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተነግሯል።
ፌልትማን ኢትዮጵያ የሚመጡት ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በሰላም ድርድር ጉዳይ ለመነጋገር እንደሆነ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ መናገራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።
አምባሳደር ፌልትማን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩ ቢገለፅም እነማንን እንደሚያገኙ አልተጠቀሰም።
አምባሳደር ፌልትማን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ወደ ትግራይ ክልል ይሄዱ እንደሆነ ፕራይስ ተጠይቀው ለአሁን መናገር የሚችሉት አምባሳደሩ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር እንደሆነ አመልክተዋል።
ቃል አቀባዩ ፥ በውይይቱ ዝርዝር ላይ መናገር የሚችሉት በማጠቃለያው እንደሆነ እና ዝርዝሩንም በፅሁፍ እንደሚያወጡ ገልፀዋል።
ፕራይስ ፥ አምባሳደር ፌልትማን ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር እንዲነጋገሩ አሁን ያለው ሁኔታ አመቺ መሆኑን ጠቁመው ሁለቱም ወገኖች ውጊያ እንዲያቆሙና ወደ ድርድር ጠረጴዛ እንዲቀርቡ ዕድል እንደሚሰጥ አመልክተዋል።
አምባሳደር ፌልትማን ኢትዮጵያ ሲገቡ የውይይቱ ይዘት ይኸው እንደሚሆን ገልፀዋል።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማ ከዚህ ቀደም የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት በሰላማዊ መንገድ ይፈታ ዘንድ ጥረት ለማድረግ በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወቃል።

#ቢላሉል_ሐበሺ_ሙዚየም
ቢላሉል ሐበሺ ሙዚየም ከታህሳስ 26 ቀን አስከ ጥር 06/2014 ዓ.ም ድረስ ልዩ የዲያስፖራዎች የጉብኝት መርሀግብር ማዘጋጁትን አሳውቋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይን ጥሪ ተከትሎ የገና በዓልን ሀገር ቤት ለማክበር የመጡ የዲያስፖራ አባላት በኢትዮጵያ ቆይታቸው ቢላል ኢስላማዊ ሙዚየምን በመጎብኘት ቆይታቸውን አስደሳችና አይረሴ እንዲያደርጉ ጋብዟል።
ሙዚየሙ ጠ/ሚኒስትሩን ጨምሮ በከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተጎብኝቶ አድናቆትን ያተረፈ ነው።
ከታህሳስ 26 ቀን አስከ ጥር 06/2014 ዓ.ም ድረስ በተዘጋጀው ልዩ የዲያስፖራዎች የጉብኝት ፕሮግራም ጎብኚዎች በሚመቻቸው ቀን በእነዚህ አድራሻዎች +251911132900 /
[email protected] ማሳወቅ እንደሚችሉ ሙዚየሙ ለቲክቫህ አሳውቋል።
አድራሻው ከአቦ ማዞሪያ አደባባይ ወደ ሣር ቤት በሚወስደው መንገድ አጋማሽ ላይ ጊብሰን ት/ቤትን አለፍ ብሎ ቢላሉል ሐበሺ ማዕከል ሕንፃ ውስጥ ነው የሚገኘው።

#AddisAbaba
የዲጂታል መታወቂያ ህትመትና ስርጭት ወደ ክፍለ ከተማ ማውረድ ቅድመ ዝግጅት ስራ እየሰራ መሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ገለጸ።
ኤጀንሲው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነዉን የአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት በማዕከል ደረጃ በማተም ለሁሉም ክፍል ከተማ ሲያሰራጭ መቆየቱን አስታውሷል።
አሰራሩ አንድ ነዋሪ አንድ የነዋሪነት መታወቂያ ብቻ እንዲኖረዉ የሚያደርግ በመሆኑ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር ለማድረግ ፋይዳዉ የጎላ ነው ብሏል።
ኤጀንሲው የፕሮጀክቱ የሙከራ ስራ በሁሉም ክፍለ ከተማ ለማስጀምር ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት ከሁሉም ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ የነዋሪዎች አገልግሎት ባለሙያዎች የመጀመሪያ ዙር ስልጠና መስጠቱን ገልጿል።
ህትመትና ስርጭት ወደ ክ/ከተማ መውረዱ ተገልጋዩ ህብረተሰብ የመታወቂያ ህትመት ለመውሰድ የሚፈግበትን ጊዜ እና ገንዘብ እንደሚያስቀር ፤ በማሽኖች ላይም የሚደርሰውን የስራ ጫና በመቀነስ የማሽን ብልሽትን እንደሚቀርፍ ኤጀንሲው አሳውቋል።
ምንጭ፦ ወ/ኩ/ም/መ/ኤጀንሲ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በ2014 ዓ.ም መታወቂያቸውን ማደስ ሲገባቸው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ያላደሱ ተገልጋዮች ከታገዱት አግልገሎቶች ውጭ ማለትም ከመሸኛ አገልግሎት፣ ከመታወቂያ አገልግሎት እና የነዋሪዎች ማረጋገጫ ውጭ የታደሰ መታወቂያ የሚጠይቁ ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ አሳውቋል።
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከተማ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ

#AliBira
አንጋፋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምና እየተከታትሉ ይገኛሉ።
የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ህክምና እየተከታተሉ በሚገኙበት ሆስፒታል በአካል በመገኘት እንደጠየቋቸው የጉሙሩክ ኮሚሽን አሳውቋል።
ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ለክቡር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ከህመማቸው ተፈውሰው የሚወዱትን ሙያ እንዲቀጥሉ እና ሀገራቸውን በኪነጥበብ መስክ እንዲያገለግሉ መልካም ምኞታቸውን እንደገለፁላቸው ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#Update ሶማሊ ክልል በሚገኙ 78 ወረዳዎች ላይ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በሁለት ወራት ተኩል ጊዜ ውስጥ ከ146 ሺ በላይ ከብት፣ ግመልና ፍየሎች መሞታቸውን የሶማሊ ክልል አደጋ ሥጋት አመራር ቢሮ አስታውቋል። በክልሉ ከሚገኙት 11 ዞኖች ውስጥ በዘጠኙ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎችና በሲቲ ዞን ውስጥ በሚገኙ 5 ወረዳዎች ውስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዕርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር ወደ…
#Update
" በድርቅ ምክንያት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል " - የሶማሊ ክልል መንግስት
በሶማሌ ክልል የተከሰተው ድርቅ ዜጎችን ለሞት እየዳረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።
የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አብዱልቃድር ረሺድ ለአሀዱ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
በጥቅምት መዝነብ የነበረበት ዝናብ ባለመዝነቡ በክልሉ የሚገኙ 9 ዞኖች ለድርቅ ተጋልጠው የነበረ ሲሆን አሁን ድርቁ ወደ 10ኛው ዞን መሸጋገሩን ኃላፊው ተናግረዋል።
በዚህም በተለይም በክልሉ 4 ዞኖች በዳዋ ፣ አፍዴራ፣ ሸበሌ እና ቆራሔ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት 1 መቶ 46 ሺሕ 8 መቶ 6 እንስሳት መሞታቸውን ገልፀዋል፡፡
በድርቁ የሚሞቱ እንስሳት ቁጥር በቅርብ ቀናት ሊጨምር እንደሚችል ስጋት መኖሩንም ጠቅሰው ፤ በድርቁ የተነሳ በክልሉ የሚገኙ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ሕዝብ ለችግር መጋለጡን አስረድተዋል፡፡
ሚያዚያ ወር ላይ የሚጠበቅ ዝናብ እንዳለ የገለፁ ሲሆን ዝናብ ካልዘነበ ድርቁ ከዚህም በላይ የከፋ እንደሚሆንና በርካታ ዜጎችን ሊያሳጣ እንደሚችል ስጋት መኖሩን ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ በሚኖሩበት ሀገር አሜሪካ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። በታጠቅ ጦር ሰፈር፣ ህፃናት አምባ ፣ ጀግኖች አምባ መቋቋም ላይ ድርሻ እንደነበራቸውና በኢሰፓ ውስጥ የጎላ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል። አምባሳደር ዶ/ር ካሳ በጄኔቫ የኢትዮጵያ አምባሳደር…
#Update
የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣን አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ ስርዓተ ቀብር ዛሬ ይፈፀማል።
የአምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ አስከሬን ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሲሆን የቀብር ስነስርዓታቸው ከሰዓታት በኃላ በቅድስት ስላሴ ካቴደራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ኢዜአ ዘግቧል።
አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን በታጠቅ ጦር ሰፈር፣ ህፃናት አምባ ፣ ጀግኖች አምባ መቋቋም ላይ ድርሻ እንደነበራቸው እንዲሁም በኢሰፓ ውስጥ የጎላ ሚና እንደነበራቸው ይነገራል።
በተለያዩ ሀገራትም የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሀገራቸውን አገልግለዋል።
በ80 ዓመታቸው በአሜሪካ ሀገር ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አምባሳደር ዶ/ር ካሳ ከበደ የአንድ ወንድ እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ።

2 ዓለም አቀፍ የእርዳታ ቡድኖች የኢትዮጵያ መንግስት በከፊል / በሙሉ ስራቸውን እንዳቋረጠባቸው እና የስራ ፍቃዳቸውን እንደነጠቃቸው ትላንት አሳወቁ። ቡድኖቹ የDoctors Without Borders - MSF (የደች ቅርንጫፍ) እና Norwegian Refugee Council (NRC) ሲሆኑ ሐምሌ 23/2013 ዓ/ም ጀምሮ መንግስት ስራ እንዳያከናውኑ እንዳገዳቸው ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግስት…
#Update
የኖርዌይ የስደተኞች ካውስል እገዳው እንደተነሳለት አሳወቀ።
የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል / NRC / በሰብአዊ ድጋፍ ስራው ላይ ለ5 ወራት ተጥሎበት የነበረው እገዳ እንደተነሳለት በኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንደተገለፀለት አሳውቋል።
እግዱ የተነሳለት ከታህሳስ 22/2014 ጀምሮ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህን አስመልክቶ ድርጅቱ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።