#Dessie #Hayq
ትምህርት ሚኒስቴር በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች በህወሓት የሽብር ቡድን ወረራ ምክንያት ከ2 ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት በድጋሚ እንደጀመረ አሳውቋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን (ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው)
@tikvahethiopia

#DStv
የMyDStv መተግበሪያን በመጠቀም የዲኤስቲቪ አካውንትዎን በማንኛውም ጊዜ፣ በየትኛውም ቦታ ይቆጣጠሩ።
ሂሳብዎን ይክፈሉ፣ የE-16 እና ሌሎች የቴክኒክ ችግሮችን በቀላሉ ያስተካክሉ!!!
የ MyDStv መተግበሪያን ለማውረድ ይህን ሊንክ ይጫኑ👇
https://bit.ly/theMyDStvApp
#DStvSelfServiceET #DStvየራሳችን

TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ለቀቁ። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ስልጣን መልቀቃቸውን በይፋ አሳውቀዋል። አብደላ ሀምዶክ ከጦር ኃይሉ ጋር በተደረገው የፖለቲካ ስምምነት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸው ከተመለሱ ከ6 ሳምንታት በኋላ ነው ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት። ከጥቂት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ሊለቁ መሆኑን የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው…
#SUDAN
በሱዳን የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬም ቀጥሏል።
ዛሬ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ወታደራዊውን አስተዳደር በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።
የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች በሀገሪቱ የተደረገውን መፈንቅለ መንግሥት በመቃወም በካርቱም ከተማ በፕሬዝደንቱ መኖሪያ አካባቢ የተሰባሰቡ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ መጠቀማቸውን እማኞች መገልፃቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።
ዛሬ ከካርቱም በተጨማሪ በኦምዱርማን ከተማ ሱዳናውያን አደባባይ ወጥተው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቱን አውግዘዋል።
በሌሎች ከተሞችም ፖርት ሱዳንን ጨምሮ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፎች መኖራቸውን አሶሴትድ ፕረስ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ከሥልጣናቸው መልቀቃቸውን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ካሳወቁ በኋላ የሱዳን የፖለቲካ ቀውስ ተባብሷል።
መረጃው የዶቼቨለ እና አሶሼትድ ፕሬስ ነው።

#ለኢትዮጵያ
የፊታችን ጥር 1 ከቀኑ 9:00 ላይ በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ " ለኢትዮጵያ " በሚል የምልጃና የአምልኮ ጊዜ መዘጋጀቱ ተገለፀ።
ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በዘጸአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን ሲሆን ስለኢትዮጵያ የጸሎት እና አምልኮ ጊዜ እንደሚሆን ቤተክርስትያኗ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቃለች።
በዕለቱ በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖቻችን የገቢ ማሰባሰቢያ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ከደህንነት አንፃር ከመንግስት ጋር አስፈላጊው ሁሉ ዝግጅት መጠናቀቁና ምንም አይነት የሚያሰጋ ነገር ባለመኖሩ ከአዲስ አበባ ሆነ ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ እንዲታደሙ ጥሪ ቀርቧል።
ዝግጅቱ የኮቪድ-19 ጥንቃቄ በሚተገበርበት መልኩ እንደሚሆንም ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የስያሜ ለውጥ አድርጓል ?
ከኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ስያሜ ጋር የተያያዙ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል። በጉዳዩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት መኩሪያ ንጋቱ ለ @tikvahuniversity ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የቀድሞው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመቋቋሚያ አዋጁ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ደረጃና ስያሜ የመስጠት መብት ነበረው።
በዚህም የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረውን የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት ወደ ዩኒቨርሲቲ የማደግ ጥያቄ ምላሽ ሰጧል። በየካቲት 2013 ዓ.ም ለኢንስቲትዩቱ "የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ" የሚል ስያሜም ሰጥቷል።
ይሁን እንጂ የስያሜ ለውጡ ኢንስቲትዩቱ ሲቋቋም የተሰጠው ተልዕኮ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ተሻሽሎ፣ በነጋሪት ጋዜጣ መታወጅ እንደነበረበት ኃላፊው ገልጸዋል።
ይህ ሕጋዊ ሂደት ሳይጠናቀቅ በመስከረም 2014 ዓ.ም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ሚኒስቴር ስር መጠቃለሉን አስታውሰዋል።
የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲም አዲስ በተደራጀው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ስር የተካተተ ሲሆን ''የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት" የሚል ስያሜ እንዲሰጠውም ተወስኗል።
ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት ''የስያሜ ለውጥ ውሳኔው በድጋሜ ሊታይ እንደሚገባ ለመንግስት ጥያቄ ማቅረባቸውን'' ኃላፊው ገልጸዋል።
"ጥያቄው በተለያዩ ደረጃዎች እየታየና የመንግስት ምላሽ እየተጠበቀ እንደሆነ" ኃላፊው አስረድተዋል።
ከመንግስት ምስረታው በኋላ በአዋጅ ለተቋቋሙ እና የደንብ ክለሳ ለሚያስፈልጋቸው ከ50 ያላነሱ ተቋማት የሚኒስትሮች ም/ቤት በቅርቡ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።
More : @tikvahuniversity

#Lalibela
የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የደብረ ሮሀ ቅዱስ ላልይበላ ገዳም ዋና አስተዳዳሪ መምህር አባ ፅጌሥላሴ መዝገብ አሳውቀዋል።
ሁሉም ምዕመን በዓሉን በአካል በመገኘት እንዲታደም ጥሪ አቅርበዋል።
መምህር አባ ፅጌሥላሴ መዝገብ ለአሚኮ በሰጡት ቃል ለበዓሉ እንኳን አደረሳችሁ ያሉ ሲሆን " ሁላችሁም መጥታችሁ በዓሉን በደስታ አብረን እንድናከብር መልዕክታችን ነው፤ ሁሉም አስፈላጊ የሆነ ዝግጅት ተድረጓል " ብለዋል።
በተጨማሪም ወቅቱን ታሳቢ ያደረገ የፀጥታ ፣ የደህንነት ጥበቃ እንዲሚደረግና የየብስም የአየርም የትራንስፖርት አማራጭ መመቻቸቱን ገልፀዋል።
የገዳሙ ዋና አስተዳዳሪ ፥ " ሁላችሁም የተዘጋጃችሁ በሙሉ ልብ እግዚአብሔርን በማመን እንድትመጡ መልዕክታችን ነው " ብለዋል።
በሌላ በኩል ለአካባቢው ምዕመናን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ምዕመናን የተለመደው አገልግሎታቸውን እንዲቀጥሉ እና ጊዜው በሚፈቅደው መልኩ እንግዶችን መቀበል እንዳለባቸው ተናግረዋል።
መምህር አባ ፅጌሥላሴ መዝገብ ፥ " ወቅቱ ፈታና ያለበት ነው ሰውን ማመን የማይቻልበት ፤ የማያውቀው ሰው ሲመጣ ፀጉረ ልውጥ የሚባልበት ነው ሆኖም ግን በሀይማኖት እይታ በማየት መጠርጠሩ እንዳለ ሆኖ እንደእባብ ልባሞች እንደእርግብ የዋሆች ሆነን ከቅርሳችን ደህንነት ከአካባቢያችን ደህንነት አኳያ የሚመጡ ሰዎችን መታወቂያቸውን በማያት የመጡበትን በመጠየቅ ማረፊያ መስጠት ፤ እግራቸውን አጥቦ የተለመደውን አብርሃማዊ አገልግሎት እድትሰጡ አደራ እንላለን " ብለዋል።

#Ethio_Sudan
ለስድስት ወራት የተዘጋው በመተማ - ጋላባት በኩል ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው መንገድ ነገ ክፍት ይሆናል ተብሏል።
ዛሬ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ወታደራዊ አመራሮች እና የሁለቱ ሀገራት አጎራባቸው አስተዳደሮች ማለትም የምዕራብ ጎንደርና በሱዳን በኩል ደግሞ የጋላባት አካባቢ አስተዳደር ተወካዮች በመተማ ተወያይተዋል፡፡
ይህን በተመለከተ የመተማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሀብቴ አዲሱ ለአል ዐይን አማርኛ ክፍል በሰጡት ቃል ሐምሌ17 ቀን 2013 ዓ.ም የመተማ-ጋላባት መንገድ በሱዳን በኩል ተዘግቶ ነበር ሲሉ አስታውሰዋል።
የሱዳን መንግስት መንገዱን የዘጋው አንድ ወታደራዊ አመራር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ተገድሎብኛል ብሎ በማሰቡ መሆኑን አቶ ሀብቴ ተናግረዋል፡፡
ከንቲባው እንዳሉት መንገዱ አለምአቀፍ መስመር ስለሆነ እንዲከፈት በአካባቢው አስተዳደር እና በሀገር ሽማግሌዎች ለማስከፈት ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡
በስብሰባው ላይ መንገዱ ተክፍቶ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንዲቀጥል መግባባት ላይ መደረሱን የገለጹት አቶ ሀብቴ ከዚህ በተጨማሪም ለሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮችም ተነስተዋል ብለዋል፡፡
በሱዳን ግዛት ውስጥ ሚንቀሳቀሱ የህወሓት ኃይሎች መኖራቸውንና ያሉበትን ቦታ ጭምር በመጥቀስ እና ትክክል እንዳልሆነ ለሱዳን ወታደራዊ አመራር እንደተነገራቸው ከንቲባው ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
ፎቶ ፦ የምዕራብ ጎንደር ዞን

#Harari
በፖሊስ የአምቡላንስ መኪና የኮንትሮባንድ እቃ ሲያዘዋውሩ የተገኙ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።
የክልሉ ፖሊስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በፖሊስ ኮሚሽን የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ አምቡላንስ በቀን 24/ 4/ 2014 ዓ.ም በህገወጥ መንገድ በርካታ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ጭኖ ሲንቀሳቀስ አወዳይ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ገልጿል።
አምቡላንሱ የኮንትሮባንድ እቃ የጫነ ቢሆንም ታማሚ የያዘ በመምሰልና የአምቡላንስ ድምፅ በማሰማት ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር የዋለው።
ተሽከርካሪው እና አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን አሽከርካሪው ለጊዜው መሰወሩና በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም የተከሰተውን ህገወጥ ድርጊት በወቅቱ ለበላይ አካል ማሳወቅ ሲገባቸው ያላሳወቁ አባላትም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አሽከርካሪው አምቡላንሱን ከኮሚሽኑ ቅጥር ጊቢ ጎማ ለማሰራት በሚል በህገ ወጥ መንገድ ያለ መውጫ ይዞ እንዳወጣ ፖሊስ አሳውቋል።
ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን

#US #Eritrea
አሜሪካ በኤርትራ ያሉ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ አሳሰበች።
አሜሪካ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና መንግስታቸው የህሊና እስረኞችን እንዲፈቱ አሳስባለች።
አስመራ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፥ " ፕሬዜዳንት ኢሳያስ እና መንግስታቸው በግእዝ የገና በዓል መንፈስ እና በክርስትናውም ሆነ በእስልምናው እምነት ውስጥ ይቅርታ ያለውን ትልቅ ሚና በመገንዘብ የኤርትራ የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ አሜሪካ ታሳስባለች ። " ብሏል።
በአስመራ የሚገኘው አሜሪካ ኤምባሲ ስላሰራጨው መልዕክት በኤርትራ መንግስት ሆነ ባለስጣናት በኩል የተሰጠ ምላሽ/አስተያየት የለም።

ዋንግ ዪ ኤርትራ ገቡ።
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማምሻውን ኤርትራ ገብተዋል።
ዋንግ ዪን እና የልዑካን ቡድናቸው አስመራ ኤርፖርት ሲደርሱ በኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ዋንግ ዪ በኤርትራ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ከአቻቸው (ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ) ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
Photo Credit : Yemane G. Meskel