TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATTENTION

በ 'ሰሞኑ ጉንፋን መሰል' ወረርሽኝ ላይ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ማብራሪያ ሰጥቷል።

በማብራሪያው ህብረተሰቡ አሁን በየቤቱ ፣ በየጎረቤትና በየመስሪያ ቤቱ የሚታየው እንደ ንፍጥ መዝረብረብ ፣ የራስ ምታት፣ የድካም ስሜት ፣ የመገጣጠሚያና የጀርባ ህመም ፣ ሳል እና የመሳሰሉት ምልክቶች የኮቪድ-19 ሊሆን ስለሚችል " የሰሞኑ/አዲሱ ጉንፋን " በሚል መዘናጋት አስፈላጊ አለመሆኑን አሳስቧል።

* ሙሉ ማብራሪያው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 13,409 የላብራቶሪ ምርመራ 4,899 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ11 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የውጭ አገራት ገንዘብ በሕገወጥ አሠራር ሲመነዘርባቸው ይታዩ የነበሩ ወይም በጥቁር ገበያ ይሳተፉ የነበሩ በዛ ያሉ ሱቆች መታሸጋቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

በተለይ በብሔራዊ ቴአትር እና አካባቢው ፣ ስታዲየምና ዙሪያ ገባው ፣ ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ፊት ለፊት እንዲሁም ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢዎች በሚገኙ ልዩ ልዩ አነስተኛ ሱቆች ውስጥ በሚሰሩ ሰዎች አላፊ አግዳሚው ምንዛሪ ይፈልግ እንደሆን በግላጭ ይጠየቅ ነበር።

በእነዚህ አካባቢዎች በተለይ ደግሞ ወጣቶች በብዛት ሲሳተፉበት በሚስተዋለው ይህን መሰል ሕገ ወጥ ተግባር የአሜሪካ ዶላርን ፣ የአውሮፓ መገበያያ ገንዘብ ዩሮን፣ ፓውንድንና እና ሌሎች የውጭ አገራት ገንዘቦችን ብሔራዊ ባንክ በየዕለቱ ከሚያወጣው የውጭ አገራት ገንዘብ የምንዛሪ ተመን ከፍ ባለ የተጋነነ ልዩነት ሕገ ወጥ የገንዘብ ምንዛሪ ተግባር ሲፈፅሙ ማየት የተለመደ ዕለታዊ ክስተት ነበር።

ሬድዮ ጣቢያው ዛሬ በአካባቢው አደረኩት ባለው ቅኝት አብዛኞቹ ሱቆች በመደዳ በራቸው ላይ #ታሽጓል የሚል ማኅተም ያረፈበት ወረቀት ተለጥፎባቸው ተዘግተውና ለወትሮው በርከት ብለው ይህንኑ ተግባር በመፈጸም ይታዩ ከነበሩ ሰዎች መንገዶቹ ጭር ብለው ታዝቤያለሁ ብሏል።

እነዚህ ሱቆች ሲታሸጉ በአካባቢው የነበረውን ሁኔታ የተመለከቱ ሰዎች የማሸግ እርምጃው ' ቀይ ቀለም ያለው ወታደራዊ መለዮ ባጠለቁ ወታደሮች ' ታኅሣሥ 20/2014 ዓ.ም (ረቡዕ) በድንገት እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል።

በወቅቱ ይሄንኑ ሕገወጥ ሥራ ሲያከናውኑ የነበሩና የተገኙ ሰዎችም እርምጃው ድንገተኛ ስለነበር በእነዚሁ የፀጥታ አካላት ተይዘው እንደተወሰዱ ለጀርመን ሬድዮ ጣቢያ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#Telegram

ቴሌግራም በተጠናቀቀው 2021 / እ.አ.አ. / ድንቅ የሚባል አመትን እንዳሳለፈ የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ ዛሬ ምሽት አሳውቀዋል።

ጥር ወር ላይ በመላው ዓለም ላይ በብዛት ዳውንሎድ የተደረገ መተግበሪያ ፣ በጥቅምት ወር በአንድ ቀን ብቻ ከ70 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተጠቃሚዎችን መቀበል የቻለ እንዲሁም በታህሳስ ወር በፍጥነት እያደገ ያለ መተግበሪያ ተብሎ መታወጁ ተገልጿል።

የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፥ " የእድገቱ ሁሉ ባለቤቶች ተጠቃሚዎቹ እንደሆኑ እናውቃለን " ያሉ ሲሆን በተጠቃሚዎች የሚሰጡትን አስተያየቶች በጥሞና በማድመጥ አመቱን ሙሉ ቴሌግራም ለተጠቃሚዎቹ የተሻለ እንዲሆን አድርገናል ብለዋል።

ቴሌግራም በተጠቃሚዎች ጥያቄ መሰረት በቻናሎች፣ ግሩፖች እንዲሁም የአንድ ለአንድ መልዕክ ልውውጥ ወቅት ሪአክሽን መስጫ (👍👎❤️😢...) እንዲሁም የመልዕክት መተርጎሚያ የተካተተበት በዓመቱ 12ኛ ዋና ማሻሻያ ተደርጎበት ተለቋል።

አዲሱ የሪአክሽን ማሻሻያ የሚሰራው የቻናሉ ወይም የግሩፑ ባለቤቶች ክፍት ሲያደርጉ ነው። እንዴት ? (ወደ ቻናሉ /ግሩፕ በመግባት Edit የሚለውን መጫን ፣ በመቀጠል Enable Reactions የሚለውን ON ማድረግ እና የሚሰጡትን Reaction መምረጥ)

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ዋናውን የቴሌግራም መተግበሪያችሁን (ባለ ሰማያዊ ምልክቱን) Update በማድረግ ማሻሻያዎቹን እንድትመለከቷቸው መልዕክት እናስተላልፋለን።

የቴሌግራም መተግበሪያችሁን Update ለማድረግ👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger

@tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ፦

🇨🇳 ሙሉ በመሉ የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለባት የቻይናዋ ዢያን ከተማ በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች እየጨመሩ መሆኑ ተነግሯል። ባለፉት 24 ሰዓት 174 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል፤ከዚህ አንድ ቀን በፊት 161 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸድ ሪፖርት ተደርጎ ነበር። ዢያን 13 ሚሊዮን ነዋሪዎቿ ከቤት እንዳይወጡ ካዘዘች ዛሬ 11ኛ ቀኗን ይዛለች።

🇺🇬 ዩጋንዳ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ዘግታ የነበረውን ኢኮኖሚ ከ2 ዓመት በኃላ ክፍት ልታደርግ መሆኑ ተነግሯል። በህዝብ ትራንስፖርት ላይ የተጣለው ገደብ የተነሳ ሲሆን፣ ትምህርት ቤቶች ጥር 10 ይከፈታሉ፤ትምህርት ቤቶች ከተከፈቱ ከ2 ሳምንት በኃላ አርቲስቶች ዝግጅት ማቅረብ እንደሚችሉ፣ ባሮች፣ ሲኒማ ቤቶች ክፍት እንደሚደረጉ እንዲሁም ት/ቤቶች ከተከፈቱ በኃላ የሰዓት እላፊ ገደብ እንደሚነሳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አሳውቀዋል።

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 በእንግሊዝ በኮቪድ-19 ምክንያት ከስራ ገበታቸው የራቁ የሆስፒታል ሰራተኞች በአንድ ወር ውስጥ በእጥፍ ጨምሯል። የታመሙ / እራሳቸውን ያገለሉ የሆስፒታል ሰራተኞች ቁጥር እኤአ ህዳር 29 ከነበረው 11,375 በታህሳስ 26 ላይ 24,362 ደርሷል እንደ NHS ሪፖርት።

🇹🇷 ቱርክ በአንድ ቀን ከ40 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት አድርጋለች በዚህ ቁጥር ሪፖርት ሲደረግ ከ8 ወር በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 40,786 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 163 ሰዎች ሞተዋል።

🇪🇹 የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር በኢትዮጵያ አዲስ የኮቪድ-19 ወጀብ መከሰቱን አሳውቋል። ከባለፉት 2 ሳምንታት ጀምሮ በኮቪድ 19 ቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በተከታታይ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ከ2 ሳምንት በፊት ከነበረበት 5% ከትላንት በስቲያ ወደ36% አድጓል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዴዝሞንድ ቱቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የደቡብ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ዴዝሞንድ ቱቱ በደቡብ አፍሪካ የጨቋኙን አፓርታይድ ስርዓት እንዲወገድ የታገሉና የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ነበሩ። የሊቀ ጳጳሱን ከዚህ አለም በሞት መለየት ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ አረጋግጠው መግለጫ አውጥተዋል። በመግለጫቸው የእሳቸው ማረፍ " ነፃ የወጣች…
#Update

የሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱ አስክሬን በውሃ እንዲሟሟ ሊደረግ ነው።

የነጻነት ትግል ቁንጮው ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ከባቢ አየርን በማይጎዳ ሁኔታ አስክሬናቸው በውሃ እንዲሟሟ እንደሚደረግ መገለፁን ቢቢሲ አስነብቧል።

ዴዝሞንድ ቱቱ የአካባቢ መብት ተቆርቋሪ ስለነበሩ አስክሬናቸው በውሃ እንዲሟሟ ተናዘዋል ተብሏል።

የነጻነት ታጋዩ አስክሬን በውሃ የሚሟሟበት ሂደት አኳሜሽን (Aquamation) ተብሎ ይጠራል።

የሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ አስክሬን በኬፕ ታውን በሚገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ውስጥ ተቀምጦ በሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ አፍሪካውያን እየተሰናበቱት ነው።

ከመሞታቸው በፊት በተናዘዙት መሠረት "ቅንጡ የቀብር ሥነ ሥርዓት" አይፈልጉም።

አስከሬናቸው በጣም ርካሽ በሆነ ሬሳ ሳጥን እንዲቆይ እና በሬሳ ሳጥናቸው ላይ የሚቀመጠው አበባ ከቤተ ክርስቲያን የተገኘ እንዲሆን ተናዘዋል።

የአስክሬናቸው ቅሪትም በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይቀበራል።

አስክሬን በውሃ የሚሟሟው እንዴት ነው?

አኳሜሽን የሚባለው ሂደት የሚከናወነው የአንድን ሰው አስክሬን በውሃ እና ሀይድሮክሳይድ ውህድ ውስጥ በማሟሟት ነው።

መጀመሪያ የግለሰቡ አስክሬን ይመዘናል። ከዚያም የውሃ እና ሀይድሮክሳይድ ውህዱ በ150 ሴንቲ ግሬድ እንዲፈላ ይደረጋል። ከዚያም አስክሬኑ ይሟሟል።

ይህ ሂደት ሳይንሳዊ መጠሪያው አልካሊን ሀይድሮሊስስ (alkaline hydrolysis) ይባላል።

ለ90 ደቂቃ ያህል አስክሬኑ ከቆየ በኋላ የግለሰቡ ሰውነት ሲሟሟ፣ አጥንቱ ይቀራል።

የሟሟውን አስክሬን ለማድረቅ 120 ሴንቲ ግሬድ ሙቀት ይለቀቃል።

የግለሰቡ አስክሬን በዚህ መንገድ ሟምቶ አመድ ከወጣው በኋላ አስክሬኑን መቅበር ወይም በሟች ኑዛዜ መሠረት በሚመርጡት አካባቢ መበተንም ይቻላል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
አብዱልዋሀብ መሐድ ከአሶሳ ማረሚያ ቤት አመለጠ።

የቤንሻጉል ሕዝቦች ነጻ አውጭ ንቅናቄ (ቤሕነን) የቀድሞ ሠራዊት መሪ አብዱልዋሀብ መሐድ ታሥሮ ከነበረበት አሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት ማምለጡን አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ እንደነገሩት አዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስነበበ።

የ9 ዓመት ዕሥር የተፈረደበት አብዱልዋሀብ ያመለጠው ታኅሣሥ 18/2014 መሆኑ ተገልጿል።

ግለሰቡ ከዚህ በፊትም እንዲሁ 2001 ዓ/ም የዕድሜ ልክ ዕሥራት ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን፣ 2002 ላይ ከማረሚያ ቤት አምልጦ ወደ ኤርትራ በመግባት ኢትዮጵያን ከሚወጉ ኃይሎች ጋር ሲሠራ እንደነበር ተገልጿል።

ከዚያ በመቀጠል 2009 ዓ/ም ላይ የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግሥት ግለሰቡ ከሚመራው ቡድን ጋር ባደረጉት የሠላም ድርድር ተስማምቶ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ሠላማዊ ኑሮ መምራት ጀምሮ ነበር።

ግለሰቡ ይመራቸው የነበሩ ታጣቂዎች ከመንግሥት 20 ሚሊዮን ብር መቋቋሚያ ተቀብለው ተበታትነው ከቆዩ በኋላ፣ ሰኔ 2010 ዳግም አሶሳ ላይ ጥቃት በፈጸሙበት ወቅት መሪው ራሱ ተሳታፊ በመሆን የሰው ነፍስ አጥፍቷል ተብሏል።

በዚህም ግለሰቡ ተከሶ ሲከራከር ከቆዬ በኋላ፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ16 ዓመት ከስድስት ወር ዕሥራት ተፈርዶበት እንደነበር ታወቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ፍርደኛው ለፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ አቅርቦ ቅጣቱ ወደ ዘጠኝ ዓመት ዕሥር ዝቅ ተደርጎለት የነበረ ቢሆንም፣ ዐቃቤ ሕግ በቅጣት ውሳኔው ባለመስማማቱ በፍርድ ክርክር ሒደት ላይ ሳለ ግለሰቡ አምልጦ መጥፋቱ ነው የተነገረው።

ግለሰቡ ፍርድ የተሠጠው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ሆኖ ለቤተሰብ እንዲቀርብ በሚል ወደ አዲስ አበባ ሌሎች ፌዴራል ማ/ ቤቶች እንዳልተወሠደ ነው የተጠቆመው።

ታሳሪው በፌዴራልና በክልሉ መንግሥት በጥብቅ ሲፈለግ እና ከፍተኛ ክትትል ሲደረግብት የነበረ ከመሆኑም አንጻር፣ በርካታ ዕሥረኞች ካሉበት ማረሚያ ቤት ቀን ላይ በግልጽ ለኹለተኛ ጊዜ ማምለጡ፣ ሴራ ሳይኖርበት እንዳልቀረ ያመላክታል ሲሉ ስማቸው ያልተሀለፀድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊው ጠቁመዋል።

በአሁን ሰዓት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታ ኃይሎች እሥረኛውን እየፈለጉት ቢሆንም ቦታው ለሱዳን ካለው ቅርበት እንዲሁም ሰውዬው መውጫ እና መግቢያውን የሚያውቅ፣ በትግልም ለ20 ዓመት ገደማ የቆዬበት በመሆኑ በቀላሉ ሊገኝ ይችላል ተብሎ እንደማይታሰብ ነው የሥራ ኃላፊው የገለጹት።

ግለሰቡ ሱዳን ከገባ በኋላም እንደከዚህ ቀደሙ ወጣቶችን መልምሎ በማሠልጠን፣ በመተከልና አሶሳ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች ላይ ተመሳሳይ የሆነ የሽብር ድርጊቱን ሊቀጥል እንደሚችል ነው የተመላከተው።

የአብዱልዋህብ አጋር የነበሩ ሰዎች ሱዳን ውስጥ በርካታ ወጣቶችን በማሰልጠን ክልሉ ውስጥ ረብሻ ሲፈጥሩ ቆይተዋል ያሉት ኃላፊ ፥ በዚህ የሰውዬው ከእስር ማምለጥ ለአካባቢው ሠላምና ደኅንነት አደገኛ ነው ብለውታል።

የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ሐሩን አብዱራማን ፥ አብዱልዋህብ ከተፈረደበት ከስድስት ወር በኋላ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተጣለበት ቅጣት ላይ ጥያቄ ማቅረቡ ስሜታዊ እንዳደረገው እና ለልማት ሥራ በሚል ከማረሚያ ቤት ሲወጣ በነበረበት ወቅት ላይ እንዳመለጠ ለጋዜጣው ተናግረዋል።

ከአብዱልዋህብ መሐድ ውጭ ከማረሚያ ቤቱ ያመለጠ ሌላ ታራሚ እንደሌለ የተናግሩት ኃላፊው ፣ እሱም በቅርብ ቀን በቁጥጥር ሥር ይውላል የሚል ግምት እንዳለቸው ተናገረዋል።

ግለሰቡ ወደ ሱዳን እንዳይወጣ ሁሉም ቦታዎች በፀጥታ ኃይሎች መዘጋታቸውን ገልጸው፣ እሥረኛው ወደ ሱዳን ከመሸሽ ይልቅ ተጸጽቶ ተመልሶ ይመጣል የሚል ዕምነት እንዳለቸው ተናግረዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Addis-Maleda-01-01

ምንጭ፦ #አዲስ_ማለዳ_ጋዜጣ
#አብርሆት

ከአንድ ነጥብ አንድ (1.15) ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ወጥቶበታል የተባለው የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ዛሬ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቋል።

አብርሆት በ19ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነባ እጅግ ዘመናዊ ቤተ-መጽሐፍት ሲሆን ዓለም አቀፍ ደረጃዉን ጠብቆ የተገነባ እንደሆነ ተገልጿል።

በውስጡ በ4 ወለሎች 1.5 ኪሜ እርዝመት ያለውና 1.4 ሚሊዮን መፃህፍትን መያዝ የሚችል መደርደሪያ አለው።

ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ የወረቅት አልባ መጽሐፍትና 300 ሺህ ጥናታዊ ፅሁፎችን የያዘ መሆኑም የተገለፀ ሲሆን ወላጆች ከልጆቻቸዉ ጋር ማንበብ የሚችሉበትም ነው ተብሏል።

ቤተ መጽሐፍቱ የህፃናት ማንበቢያና ማረፊያ ስፍራን ይዟል። ማየት ለተሳነቸው አንባቢዎች በቂ የብሬይል መጽሐፍት አቅርቦት እንዳለው ተገልፃል።

በተጨማሪ ዘመናዊ የካፍቴሪያና የመሰብሰቢያ አዳራሾችን፣ ስምንት የመፅሃፍትና ተጓዳኝ አገልግሎት መስጫ ሱቆችን፣ አምፊ ትያትርና መጫወቻ ቦታዎችን እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ በአንዴ 115 መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል የመኪና ማቆሚያ ስፍራን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
#AFAR

" ዲያስፖራዎች እና ባለሀብቶች አፋርን በመጎብኘት በሙሉ አቅማቸውም ኢንቨስት ቢያደርጉ ተጠቃሚ ይሆናሉ " - ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴ

የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ዛሬ አፋር ሰመራ ተገኝተው ድርጅቱ ለአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ያደረገውን ድጋፍ አስረክበዋል።

በኋላም የክልሉን የቆላማ ሰንዴ ልማት እና ሌሎች የመስኖ ልማት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው የታዘቡትን ሲናገሩ " እዚህ በረሃ ላይ እንደዚህ እያየኸው ለማመን የሚከብድ ግን እውነት የሆነ ነገር ስመለከት ለካ የአእምሮ በረሃ እንጂ የመሬት በረሃ የለውም፣ ካለሙት መልማት ይችላል" በማለት ገልፀዋል።

ሻለቃ ሀይሌ ባዩት ነገር በጣም መደመማቸውን ገልፀው በዚሁ ቦታ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉና ይህንንም በቀጣይ 2 እና 3 አመታት ውስጥ ምርት በማምረት ወደ ውጭ ለመላክ እውን ለማድረግ ለራሳቸው ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል።

ሻለቃ ሀይሌ ዲያስፖራዎች እና ባለሀብቶች አፋርን በመጎብኘት በሙሉ አቅማቸው ኢንቨስት ቢያደርጉ የውሀ፣ የመሬት እና የአየር ንብረት ችግር የለም በተጨባጭ ያየሁትን ነው የምመሰክረው ብለዋል።

በም/ርዕሠ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት አቶ አሊ ሁሴን ዌኢሳ በበኩላቸው በአፋር ክልል ካሉ በርካታ ወንዞች ውስጥ ትልቁ የአዋሽ ወንዝ መሆኑን አውስተው ይህን ወንዝ በጣም በትንሹ ነው እየተጠቀምን ያለነውና ገና ብዙ መስራት እንደሚጠበቅና ዲያስፖራዎችና ባለሀብቶች ወደ ክልሉ በመምጣት ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ የአፋር ብዙሀን መገናኛ ድርጅት

@tikvahethiopia
#Update

የ12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናውን የሚወስዱበት ቀን ይፋ ተደረገ።

በ2013 የጸጥታ ችግር በተከሰተባቸው አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ከጥር 24 እስከ ጥር 27 ቀን 2014 ዓ.ም ፈተናው እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

በሁለተኛ ዙር የሚሰጠውን ፈተና 58 ሺህ 936 ተማሪዎች እንደሚወስዱም የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ተናግረዋል። 

በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎች በፀጥታ ምክንያት ፈተና መወሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ አቶ ተፈራ አብራርተዋል።

የመጀመሪያው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ያስታወሱት ዳይሬክተሩ ሁለተኛ ዙርም በሰላም እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ህብረተሰቡና የሚመለከታቸው አካላት ፈተናው በሰላም መጠናቀቅ እንዲችል የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ዳይሬክተሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia