#ችሎት
አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ 5 ተከሳሾች በህመም ምክንያት ዛሬ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ።
አሞናል በማለት ፦
- አቶ ስብሐት ነጋ ፣
- አቶ አባዲ ዘሙ፣
- አቶ ዘሚካኤል አንባዬ፣
- ዶ/ር ሙላት ይርጋ እና አቶ ቴድሮስ ሀጓስ ዛሬ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።
የማረሚያ ቤት ተወካይ 5ቱ ተከሳሾች አሞናል በማለታቸው ምክንያት እንዳላመጣቸው አስረድቷል።
ቀሪዎቹ ማለትም ፦
- ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ፣
- አንባሳደር አባይ ወልዱ ፣
- ዶ/ር አብርሐም ተከስተ ፣
- ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ፣
- አንባሳደር አዲስ አለም ባሌማ ፣
- ወ/ሮ ሙሉ ገ/ እግዛብሔርን ጨምሮ 16 ተከሳሾች ግን በችሎት ተገኝተዋል።
16 ቱ ተከሳሾች የቀረቡት በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ችሎቱ የተከሳሾች የክስ መቃወሚያ ውጤት ለመጠባበቅ እና " ሱር ኮንስትራክሽን " ን ጨምሮ በክሱ የተካተቱ ድርጅቶች መጥሪያ እንዲደርሳቸው የተሰጠውን ትዛዝ ማረጋገጫ ውጤት ለመጠባበቅ ነበር ዛሬ የተሰየመው።
በተጨማሪ በ44 ኛ ተከሳሽ ለምርመራ የተያዘብኝ ሰነዶች ይመለሱልኝ ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ትዛዝ ለመስጠት ነው።
የችሎት ውሎውን ንብቡ : https://telegra.ph/Trial-12-30-2
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

Telegraph
Trial
#ችሎት አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ 5 ተከሳሾች በህመም ምክንያት ዛሬ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ። አሞናል በማለት አቶ ስብሐት ነጋ ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ አቶ ዘሚካኤል አንባዬ፣ ዶ/ር ሙላት ይርጋ እና አቶ ቴድሮስ ሀጓስ ዛሬ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። የማረሚያ ቤት ተወካይ አምስቱ ተከሳሾች አሞናል በማለታቸው ምክንያት እንዳላመጣቸው አስረድቷል። ቀሪዎቹ ማለትም ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ፣ አንባሳደር አባይ ወልዱ…
አልሸባብ ?
ሶማሊያ ውስጥ ያለው ውጥረትና በፕሬዜዳንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል ያለው ቅራኔ ለአልሸባብ የሽብር ቡድን በር እንዳይከፍት ተሰግቷል።
ዛሬ ጥዋት ላይ የ #አልሸባብ ታጣቂዎች ከዋና ከተማይቱ ሞቃዲሾ በስተሰሜን በምትገኝ ከተማ ላይ ጥቃት ሰንዝረው ከተማውንም ለመቆጣጠር ሞክረው እንደነበር ተዘግቧል።
አልሸባብ ጥቃቱን የከፈተው ከሞቃዲሾ 30 ኪ.ሜ ያህል በምትርቀው ስትራቴጂክ ከተማ #ባላድ እንደሆነ የተሰማ ሲሆን በጥቃቱ ሰዎች ተገድለዋል።
እንደ ቪኦኤ ዘገባ ከሆነ ፥ የሶማሊያ ጦር ኃይል በወሰደው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የሽብር ቡድኑን ባላድን የመያዝ ሙከራውን አክሽፏል።
በአሁን ሰዓት ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በመንግስት እጅ ስር እንዳለችም ገልጿል።
በዛሬው ጥቃት 4 የመንግስት ወታደሮች እንደተገደሉ ቪኦኤ ሲዘግብ የሶማሊያ መንግስት ሚዲያ በበኩሉ በጥቃቱ 9 የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን እና በአሸባሪዎች በተተኮሰ ሞርታር 5 ንፁሀን ዜጎች መሞታቸውን ዘግቧል።
@tikvahethiopia

#ETHIOPIA #SUDAN
ዛሬ #ኢትዮጵያ ሀገራችን ከጎረቤት ሀገር #ሱዳን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታዋን እያደረገች ትገኛለች።
ይህ ጨዋታ እየተካሄደ የሚገኘው የሁለቱም ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች በአፍሪካ ዋንጫ ለመካፈል ባቀኑባት ካሜሮን ሀገር ነው።
የሀገራችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቀናት በፊት በትልቁ የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ከውድድሩ ቀደም ብሎ ወደ ካሜሮን አቅንቷል።
ቡድናችን ካሜሮን ከደረሰ በኃላ በየዕለት ልምምድ እየሰራ ውድድሩ እስኪጀመር እየተጠባበቀ ይገኛል። ዛሬ አቋሙን የሚፈትሽበት ጨዋታ እያደረገ ነው።
ሀገራችን በተወከለችበት ትልቁ የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር መድረክ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም ወደ ስፍራው ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ያቀኑ ሲሆን በስፖርት ገፃችን ላይ መረጃዎችን ያካፍላሉ።
የቲክቫህ ስፖርት ገፅ ፦ https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x
@tikvahethsport

TIKVAH-ETHIOPIA
" የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ ይመረጣሉ " - የህግ ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ እንደሚመረጡና ሹመታቸውም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደሚጸድቅ የህግ ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ናቸው። በጋዜጣዊ መግለጫው…
#ጠቁሙ
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265 /2014 ማጽደቁ ይታወሳል፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 1 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የዕጩ ኮሚሽን አባላትን ከህዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች ና ከሲቪል ማህበራት እንደሚቀበል ተደንግጓል፡፡
በዚህም መሰረት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቀበያ ጽ/ቤት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቋቁሟል፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 13 መሰረት ለኮሚሽነርነት የሚያበቁ መሥፈርቶችም፡-
1/ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ፤
2/ ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ የተለያዩ ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችን እና ሕዝቦችን በእኩል ዓይን የሚያይ፤
3/ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ፤
4/ ለአገራዊ መግባባት ጉልህ አስተዋፅዖ ሊያበረክት የሚችል ፤
5/ መልካም ሥነ-ምግባርና ስብዕና ያለው፤
6/ በሕዝብ ዘንድ ዓመኔታ ያለው፣
7/ በከባድ ወንጀል ተከሶ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተላለፈበት ፤
8/ የኮሚሽኑን ሥራ በአግባቡ ለመሥራት የሚያስችል የተሟላ ብቃት ያለው፤
9/ ሙሉ ጊዜውን ለኮሚሽኑ ስራ ለማዋል ፍቃደኛ የሆነ።
የሚሉ ናቸው፡፡
የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ፡-
• በቀጥታ ስልክ 0111300340 ወይም 9988
• በፋክስ ቁጥር 0111233007
• በኢ-ሜል [email protected] ወይም
• በ [email protected] ወይም
• በአካል በም/ቤቱ መረጃ ማአከል መስጠት ይቻላል።
በቀጣይ ሶስት ቀናት ውስጥ ጠቆማ የሚሰጥበትን ቅጽ www.hopr.gov.et እንደሚጭን የህ/ተ/ምክር ቤት አሳውቋል።

#LALIBELA
ከፊታችን ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ታሪካዊቷ ከተማ ላሊበላ እለታዊ የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
ከፊታችን ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ታሪካዊቷ ከተማ ላሊበላ እለታዊ የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ አሳውቋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #SUDAN ዛሬ #ኢትዮጵያ ሀገራችን ከጎረቤት ሀገር #ሱዳን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታዋን እያደረገች ትገኛለች። ይህ ጨዋታ እየተካሄደ የሚገኘው የሁለቱም ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች በአፍሪካ ዋንጫ ለመካፈል ባቀኑባት ካሜሮን ሀገር ነው። የሀገራችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቀናት በፊት በትልቁ የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ከውድድሩ ቀደም ብሎ ወደ ካሜሮን…
#ETHIOPIA
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሱዳንን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
አማኑኤል ገብረ ሚካኤል 2 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን አንዱን ጎል ሽመልስ በቀለ አስቆጥሯል።
የብሄራዊ ቡድናችን ከአፍሪካ ዋንጫ መጀመር አስቀድሞ ካሜሮን በመግባት ለውድድሩ አስፈላጊውን ዝግጅት ሁሉ እያደረገ ይገኛል።
More : @tikvahethsport

#ALERT🚨
የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 14,035 የላብራቶሪ ምርመራ 4,998 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ10 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።
260 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#MoH
አዳዲስ ምሩቃን ሃኪሞችን ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።
የጤና ሚኒስቴር አዳዲስ ምሩቃን ሃኪሞችን በቅጥር ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል የፕሮጀክት ስምምነት ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች ጋር ተፈራረመ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ፕሮክጀቱ በብዙ ልፋት ተመርቀው ስራ ላይ ያልተሰማሩ ሃኪሞችን ወደ ስራ የሚያሰማራ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ ትልቅ እምርታ ነው ብለዋል፡፡
ከተያዘው አመት ጀምሮ የሚተገበረው ይህ ፕሮጀክት የሶስት ዓመት ቆይታ እንደሚኖረው ገልፀዋል።
በመጀመሪያው ዓመት 2 ሺ 898 ሃኪሞችን ወደ ስራ ለማሰማራት መታቀዱን ተናግረዋል።
ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው በጀትም የመጀመሪያው ዓመት ከፌዴራል መንግሥት እና ከአጋር ድርጅቶች በተገኘ ገንዘብ የሚሸፈን ሲሆን፥ ሁለተኛው እና ሶስተኛው ዓመት ከፌዴራል፣ ከክልልና ከከተማ አስተዳደሮች እና ከአጋር የልማት ድርጅቶች ድጋፍ በተገኘ ገንዘብ የሚተገበር ይሆናል።
ከአራተኛው ዓመት በኋላ ሙሉ በሙሉ በክልሎች አቅም እንደሚተገበርም ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
ምንጭ፦ ጤና ሚኒስቴር

#MoH አዳዲስ ምሩቃን ሃኪሞችን ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ። የጤና ሚኒስቴር አዳዲስ ምሩቃን ሃኪሞችን በቅጥር ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችል የፕሮጀክት ስምምነት ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች ጋር ተፈራረመ። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ፕሮክጀቱ በብዙ ልፋት ተመርቀው ስራ ላይ ያልተሰማሩ ሃኪሞችን ወደ ስራ የሚያሰማራ በመሆኑ በጤናው ዘርፍ ትልቅ እምርታ ነው…
#ProfessorSenaitFisseha
ዛሬ የጤና ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞችን በቅጥር ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ፕሮጀክት ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች ጋር ተፈራርሟል።
ፕሮጀክቱ ዘንድሮ ጀምሮ ለ3 ዓመት ይቆያል። በመጀመሪያ አመት 2,898 ሃኪሞች ወደስራ ለማስገባት ታቅዷል።
ለዚሁ ለመጀመሪያው ዓመት ስራ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከፌዴራል እና ከልማት አጋር ድርጅቶች በሚደረግ ድጋፍ የሚሞላ ነው።
ፕሮጀክቱ እንዲጀምር የበፌት ፋውንዴሽን የመጀመሪያውን ዓመት 175 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የፋውንዴሽኑ የዓለም አቀፍ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ሰናይት ፍሰሃ ዛሬ በተካሄደው የፊርም ስነ-ስርዓት ላይ በበይነ መረብ ንግግር አድርገዋል።
ፕሮፌሰር ሰናይት የተደረገው ድጋፍ በተለይ ጤና ሚኒስቴር የእናቶችን ሞት 50 በመቶ ለመቀነስ ያስቀመጠውን ግብ እንዲያሳካ እንደሚያግዝ ገልፀዋል።
በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ሃኪሞችን ወደ ስራ በማስማራት የባለሙያዎችን እጥረት ለመቅረፍና ኮቪድ-19 በእናቶችና ስነ-ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ ላይ ሰፊ ተጽዕኖ እንዳያሳድር ወረርሽኙን ለመከላከል ከሚደረግ ሰፊ እንቅስቃሴ ጎን ለጎን የጤና ተቋማት ፤ የእናቶች ጤና እና የቤተሰብ ዕቅድ ጨምሮ ሌሎችም መሰረታዊ የስነ-ተዋልዶ አገልግሎቶችን አጠናክረው መስጠት እንዲችሉ ሰፊ እገዛ እንደሚያደርግ ፕሮፌሰር ሰናይት ተናግረዋል።

#UPDATE😷
የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ፦
🇫🇷 በፈረንሳይ ለ2ኛ ተከታታይ ቀን ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሪፖርት ተደረገ። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 206,243 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
🇲🇽 በሜክሲኮ የሟቾች ቁጥር ወደ 300 ሺህ እየተጠጋ ይገኛል፤ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 153 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ሟቾች 299,285 ደርሰዋል።
🇷🇺 በሩሲያ በኦሚክሮን የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን እስካሁን 106 ሰዎች መያዛቸው ተረጋግጧል። ተጋላጭ ናቸው ከተባሉ ሀገራት የሚገቡ ተጋዦች ላይ ጠንካራ ምርመራ እየተደርገ ነው።
🇮🇱 እስራኤል የመጀመሪያውን የPfizer ፀረ-ኮቪድ ክኒን ተቀብላለች።
🇵🇹 ፖርቹጋል ለኮቪድ-19 ተጋላጫ የሆኑ ሰዎች እራሳቸውን ለይተው እንዲቀመጡ የሚያስገድደውን መመሪያ ከ10 ቀን ወደ 7 ቀን አሻሽላለች። የጤና ባለሞያዎች ውሳኔውን አደገኛ ብለውታል፤መንግስት ድጋሚ እንዲያስብበት አሳስበዋል።
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ በኦሚክሮን ምክንያት ጥላው የነበረውን ሰዓት እላፊ ገደብ አንስታለች። ባለሥልጣናት አገሪቱ 4ኛውን የኮቪድ-19 ማዕበል ጫፍን እንዳለፈች ገልፀዋል። የኦሚክሮን ዝርያ በከፍተኛ ፍጥነት የሚዛመት ቢሆንም ከቀደሙት ዝርያዎች ሲነጻጻር ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ዝቅተኛ ነው ተብሏል። በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ደግሞ በመጠኑ መጨመሩን ጠቅሰዋል።
🇺🇸 CDC አሜሪካ ውስጥ የኦሚክሮን ቫይረስ በከፍተኛ መጠን እየተስፋፋ ቢሆንም ወደ ሆስፒታል የሚገቡ እና በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥር በአንጻራዊነት ሲታይ ዝቅተኛ ነው ብሏል። ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ኦሚክሮን በመላ አገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት የተስፋፋ ሲሆን በተከታታይ ሳምንታትም በዚሁ መልኩ ይቀጥላል ሲል CDC አሳውቋል።

ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ማን ነው ? - ነሐሴ 22/1960 ዓ.ም ከኤርትራውያን ቤተሰቦቹ ቢሾፍቱ ከተማ ነበር ተወልዶ ያደገው። - በደርግ ዘመን ማብቂያ አካባቢ ላይ ወደ ጦር ሠራዊቱ ተመልምሎ ሥልጠና ከወሰደ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ወታደራዊው መንግሥት ወድቆ ከኢህአዴግ ጋር ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ በጋዜጠኝነት ሲያገለግል ቆይቷል። - ዕለታዊ የመንግሥት ጋዜጦችን የሚያሳትመው የኢትዮጵያ ፕሬስ…
#Asmera
ባለፈው ሳምንት ታህሳስ 15 ቀን 2014 ዓ/ም በኬንያ ናይሮቢ በ53 ዓመቱ ህይወቱ ያለፈው ደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገብረአብ ስርዓተ ቀብር ተፈፅሟል።
የጋዜጠኛና ደራሲ ተስፍዬ ስርዓተ ቀብር የተፈፀመው ትላንት አስመራ ውስጥ ዃዝ ዃዝ በተባለ መካነ መቃብር ነው።
በቀብር ስነስርዓቱ ላይ ቤተሰቦቹ፣ የጥበበ አድናቂዎች እና ወዳጆቹ ተገኝተው ነበር።
ጋዜጠኛ እና ደራሲ ተስፋዬ በኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የፕሬስ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የእፎይታ መጽሄትና ጋዜጦች ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሰርቷል፡፡
ተከታታይ ጽሆፍችንና በርካታ መጽሀፍትን ፅፏል።
ከፃፋቸው መፅሀፍት መካከል ፦
- የቡርቃ ዝምታ
- ያልተመለሰው ባቡር
- የቢሾፍቱ ቆሪጦች
- የጋዜጠኛው ማስታወሻ
- የደራሲው ማስታወሻ
- የስደተኛው ማስታወሻ
- የቅድሜ ማስታወሻ
- የጀሚላ እናት
- የኑረነቢ ማህደር
- የትራቮሎ ዋሻ የሚሉት የሚገኙበት ሲሆን ህይወቱ ከማለፉ በፊት ደግሞ ወደ ህትመት የገባ " ቀይ ዘመን " የተባለ መጽሐፍን ጨምሮ ሌሎችም ጅምር ሥራዎች እንደነበሩት ቪኦኤ ዘግቧል።

#ATTENTION
የደብረ ብርሃን ከተማ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በደብረ ብርሃን ከተማ ኮቪድ መሰል ወረርሽኝ በስፋት እየታየ ስለሆነ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አስገነዘበ።
የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ናደው ወንድማገኝ ፥ በከተማው በሁሉም ቀበሌዎች የኮቪድ ወረርሽኝ በሽታ የሚመስል ምልክት የሚታይባቸው ብዙ ሰዎች መታመማቸውን አስረድተዋል፡፡
አሁን ተከሰተ የተባለው ኮቪድ መሰል በሽታ ፦ ሳል፣ ከፍተኛ ትኩሳት እና የማንቀጥቀጥ ስሜት ያለው ነው ያሉት ኃላፊው ምልክቶቹ ከኮቪድ ጋር ይመሳሰላሉ ብለዋል።
ማስክ በማድረግ ፣ ርቀትን በመጠበቅ ፣ የእጅን ንፅህና በመጠበቅ እና ሰው ከተሰበሰበበት ቦታ በመራቅ ህብረተሰቡ ከወረርሽኙ ራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
መረጃው የደ/ብርሃን ከተማ ኮሚኒኬሽን ነው።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SUDAN
በሱዳን ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት እንዲሁም የሱዳንን ወታደራዊ ክንፍ በመቃወም እና ሙሉ በሙሉ ሲቪል አስተዳደር በመጠየቅ የሚካሄደው ሰልፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ትላንት በተካሄደ ህዝባዊ ሰልፍ 4 ሰዎች በሱዳን የፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል፤ በርካቶች ቆስለዋል።
እንደ ሱዳን የዶክተሮች ቡድን መረጃ አራቱ የተገደሉት ዜጎች ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ ነው።
የሱዳን መንግስት ተቃውሞውን ለመግታት ከፍተኛ የፀጥታ ኃይሎች አሰማርቶ ፤ የስልክ እና ኢንተርኔት ግንኙነትንም አቋርጦ ነበር።
አሜሪካ ካርቱም በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል በትላንትናው ሰልፍ በትንሹ 4 ሰዎች መገደላቸው እና በደርዘን የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን ገልፃ ድርጊቱን አጥብቃ እንደምታወግዝ አሳውቃለች።
በሱዳን ጸጥታ አገልግሎት በሚዲያ ተቋማትና በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰው የሃይል ጥቃት እንዳሳዘናት የገለፀችው አሜሪካ ባለስልጣናት የፕሬስ ነፃነትን እንዲያስጠብቁ አሳስባለች።
በተመሳሳይ የአውሮፓ ህብረት የትላንቱን ግድያ እንዲሁም በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን እንደሚያወግዝ አሳውቋል።
Video Credit : Thomas Linge