#AFAR
የአፋር ክልል የትምህርት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አሊ ጃፓን ፥ " በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወህት ምክንያት 65 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል " ሲሉ አሳወቁ።
የቢሮው ሀላፊ ይህን ያሳወቁት ለኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ነው።
አቶ አሊ ፥ በክልሉ በ21 ወረዳዎች ውስጥ የነበሩ 759 የትምህርት ተቋማት ላይ ጉዳት መደረሱንና ከዚህ ወስጥ 65ቱ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ የወደሙ መሆኑን ገልፀዋል።
በተጨማሪ የትምህርት ዘርፍ ሰራተኞችን ሳይጨምር ከ150 ሺህ በላይ በወደሙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የነበሩ ተማሪዎች ከትምህርታቸው ውጭ እንደሆኑ ተናግረዋል።
እነዚህን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስና የመማር የማስተማሩን ስራ ለመጀመር መላው ኢትዮጵያዊ ከአፋር ክልል ጎን እንዲሆኑ አቶ አሊ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን /ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው /
@tikvahethiopia

👍6❤5😢1
#ETHIOPIA
" ይሄ የምዕራቡ ሀገር ኤምባሲ የሚለው ምንድነው ? የሚለውን ልጠይቅም ጭምር ነው የመጣነው ። " - ዮሃንስ
ዳያስፖራዎች የተደረገላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ይገኛሉ።
ጥሪውን ተቀብለው ወደሀገር እየገቡ ካሉት መካከከል 10 እና 20 ዓመት ከዛም በላይ በሰው ሀገር በስደት የኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል።
ወደሀገር ከገቡ መካከል በኤርፖርት ሆኖ ለብሄራዊ የቴሌቪዥን ቃሉን የሰጠ ዮሃንስ የተባለ ዳያስፖራ ላለፉት 10 ዓመታት ሀገሩን አይቷት እንደማያውቅ ተናግሯል።
ዮሃንስ ፥ " ኢትዮጵያዊነት ምንም የማይቀየር ነው ፤ ካሊፎርኒያ ያለው ህዝብ ተነሳስቶ ኢትዮጵያን ለመርዳት ነው ሀሳቡ፤ በሚሊዮኖች ደረጃ የሚላከውም ሀገራችንን አንድ አድርጎ ለማቆየት ነው፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ አንድ ሆና እንደምትቆይ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ጠላቶቿ ይፈርሳሉ እሷ ግን ትቆማለች በዚህ አምንነን ነው ወደሀገራችን የገባነው " ብሏል።
" እስቲ ይሄ ወሬው ምንድነው ? የምዕራቡ ኤምባሲ የሚለው ምንድነው ? የሚለውን ልንጠይቅም ጭምር ነው የመጣነው " ሲልም ገልጿል።
ወደ ሀገር እየገቡ ያሉት ዳያስፖራዎች ባዶ እጃቸውን ሳይሆን በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እንዲሁም ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት የተለያዩ አስፈላጊ ድጋፎችን በመያዝም ጭምር ነው።

👍13❤1🕊1
" ዴልታ እና ኦሚክሮን አደገኛ ማዕበል እያመጡ ነው " - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
የኮሮና ቫይረስ #ዴልታ እና #ኦሚክሮን ልውጥ ዝርያዎች በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን በማበራከት አደገኛ ማዕበል እያመጣ ነው ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገለፁ።
ዶ/ር ቴድሮስ፥ ይህንን ያሉት በአሜሪካና በመላው አውሮፓ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እየተመዘገቡ መሆኑን እየተገለፀ ባለበት በአሁን ሰዓት ነው።
ዶ/ር ቴድሮስ ፥ ለወረርሽኙ መበራከት የሁለቱ ዝርያዎች " ጥምር " ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
አክለውም ሁኔታው " በተዳከሙ የጤና ባለሙያዎች ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር እና የጤና ስርአቶችን ሊያናጋው ይችላል" ብለዋል።
ከክትባት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ሃብታም ሀገራት 3ኛውን ዙር ክትባት ወይም ማጠናከሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
ዶ/ር ቴድሮስ ፥ የበለፀጉ አገራት መጠነ ሰፊ የማጠናከሪያ ክትባት ዘመቻዎች " ወረርሽኙን እንዲራዘም " ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለዋል።
ለዚህ ምክንያትም የክትባት አቅርቦቶችን ከድሃ ሀገራት በማዘዋወሩ ቫይረሱ " እንዲሰራጭ እና አዳዲስ ዝርያ እንዲፈጥር የበለጠ እድል ይሰጠዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
እ.ኤ.አ. በ2022 አጋማሽ 70 በመቶ የሚሆነውን የዓለም ህዝብ ክትባት እንዲያገኝ የተጀመረው ዘመቻ እንዲሳካ ሁሉም ሰው መከተብን የአዲስ አመት ዕቅድ እንዲያደርገው ዶ/ር ቴድሮስ መጠየቃቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

👍20👎2
TIKVAH-ETHIOPIA
#Assosa የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በሰሜን ሱዳን ብሉ ናይል ግዛት መካከል የሚደረግ የሰላምና የፀጥታ እንዲሁም የልማት ጉዳዮች ላይየሚደረገው ምክክር ዛሬ በአሶሳ ከተማ ይጀመራል። የምክክር መድረኩን ተሳታፊዎች የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። በሰላም፣ በፀጥታ፣ በልማትና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በሚመክረው መድረክ የሁለቱን አጎራባች ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትን…
#Update
ለ2 ቀናት በአሶሳ ከተማ ሲካሄድ የነበረው በኢትዮጵያ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በሱዳን የብሉናይል ግዛት የጋራ የድንበር ልማት ትብብር ውይይት በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና የብሉናይል ግዛት ከዚህ ቀደም የነበራቸውን ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እና የብሉናይል ግዛት ፕሬዚዳንት ጀነራል አህመድ አልዑምዳ ናቸው የፈረሙት።
ስምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት በልማት ፣ በሕዝብ ግንኙነት በሠላም እና ሕዝቦችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ በሌሎች መሠል ጉዳዮች በጋራ ከመስራት ባለፈ፣ አፈጻጸሙን በየጊዜው እየተገናኙ እንደሚገመግሙም ገልፀዋል፡፡
መረጃው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።

👍15
TIKVAH-ETHIOPIA
#Kenya #USA #Somlia #Ethiopia የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እና የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ያለውን ሁኔታ ጨምሮ በቀጠናዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል። በውይይታቸው ኢትዮጵያ ያለው ጦርነት እንዲቆም አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና ረገጣ እንዲቆም እንዲሁም…
" በእኛ ጉዳይ ከእኛ ጋር መወያየት አለባቸው " - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው አሜሪካ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከእኛ ጋር በቀጥታ ከመወያየት ይልቅ ከሌሎች ሀገራት ጋር መወያየትን መርጣለች ብለዋል።
ለአብነትም በኢትዮጵያ ጉዳይ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር መወያየታቸው ገልጸዋል፡፡
ከ2 ሳምንት በፊት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጀፍሪ ፊልትማን በኢትዮጵያ ጉዳይ ከቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬት እና ግብጽ ጋር መክረዋል ሲሉ ጠቅሰዋል።
አምባሳደር ዲና " አሜሪካ በኢትዮጵያ ጉዳይ መወያየት ከፈለለገች እኛ ሁሌም ዝግጁ ነን ፤ በእኛ ጉዳይ ከእኛ ጋር መወያየት አለባቸው " ብለዋል።
በተጠናቀቀው የፈረንጆች 2021 ዓመት ኢትዮጵያ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ በተነዙ ሀሰተኛ መረጃዎች ምክንያት ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብለው የተለያዩ አቋም የያዙ አገራት እና ተቋማት የታዩበት ዓመት እንደነበር አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው ላይ ገልጸዋል።
በአዲሱ 2022 ዓመት ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ በአዲስ መንገድ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እንደምትሰራ ተናግረዋል።
ምንጭ፦ አል ዓይን

👍11❤1
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የፀደቀው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ማሻሻያዎች ተደረገበት ? የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚ አዋጅ በዛሬው ዕለት በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል። የኮሚሽኑን መሪዎች በመሰየሙ ሂደት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ በሙሉ እጃቸው እንዳይገባ ሆኖ ነው የኮሚሽኑ የማቋቋሚያ አዋጅ የፀደቀው። አገራዊ መግባባትን ለማምጣት ተከታታይ ምክክሮችን በማዘጋጀት እንዲሰራ ስልጣን የተሰጠውን ኮሚሽን…
" የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ ይመረጣሉ " - የህግ ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ እንደሚመረጡና ሹመታቸውም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደሚጸድቅ የህግ ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ናቸው።
በጋዜጣዊ መግለጫው ምን ምን ነጥቦች ተነሱ ?
• የኮሚሽነሮች ጥቆማ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያካተተ ነው። ከተጠቆሙት 14 እጩዎች መካከል 11 ተመልምለው በአፈ ጉባኤው አቅራቢነት በም/ቤቱ ይሾማሉ።
• ኮሚሽነሮቹ በም/ቤቱ ከተሰየሙበት እለት ጀምሮ ለ3 ዓመታት የሚቆይ የስራ ጊዜ ይኖራቸዋል። እንደ አስፈላጊነቱ ቆይታቸው ሊራዘም ይችላል።
• በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ስለ #ድርድር የሚገልጽ ምንም አይነት ይዘት አልተካተተም፤ የአዋጁ ዋና አላማ እስካሁን መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸውና የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተኑ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያካተተ ውይይት በማድረግ ችግሮችን መፍታት ነው።
• የሚቋቋመው ኮሚሽን ከምክክር መድረኮቹ የሚያገኘውን ምክረ ሀሳብ በመቀመር ተግባራዊ እንዲደረጉ ይሰራል። ም/ቤቱን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት ወስደው እንደሚያስፈጽሙና ለስኬታማነቱም ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል።
#HPR

👍16❤4😢1
#BankofAbyssinia
ባንካችን ለመጪው የገና በዓል አምስት (5) ቴክኖ ካሞን 17ፒ ስልኮችንና በርካታ የሥጦታ ካርድ ሽልማቶችን አዘጋጅቷል፡፡
በውድድሩ ለመሳተፍ ከታች የተዘረዘሩትን ቀላል ቅደም ተከተሎችን ይከተሉ።
1. የአቢሲንያ ባንክ የኢንስታግራም ገፅን (abyssinia_bank) follow ያድርጉ
2. በባንካችን ከሚሰጡት አገልግሎቶች ለእርስኦ ይበልጥ የጠቀምዎትን ወይም የተደሰቱበትን አገልግሎት በኮሜንት መስጫው ላይ ያጋሩን
3. ከላይ ያለውን ፖስት ወደ ራስዎ የኢንስታግራም ስቶሪ (Instagram Story) በማጋራት የባንካችንን የኢንስታግራም ገፅ abyssinia_bank Tag ያድርጉ
ውድድሩ አስከ ታህሳስ 26፣ 2014 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል!
መልካም ዕድል!
#አቢሲኒያ_ባንክ

👍31❤6🎉5
#MinistryofFinance
የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ተዘጋጀ።
በገንዘብ ሚኒስቴር የተዘጋጀ የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡
ተጨማሪ በጀቱ ፦
• ለሀገር ደህንነት ማስጠበቂያ፣
• ለሰብአዊ እርዳታ፣
• በጦርነትና ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ የመንግስት ስራዎች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው፡፡
ተጨማሪ በጀቱን ማዘጋጀት ያስፈለገው ፦
• በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ወጪ በማስፈለጉ፣
• መንግስት በሚሰበስበው ገቢ አሁን ያለውን የክፍያ ጥያቄ መመለስ አስቸጋሪ በመሆኑ
• የተጨማሪ ወጪ ፍላጎትን በበጀት ሽግሽግ ማስተናገድ አዳጋች በመሆኑ ነው።
የተጨማሪ በጀት ጥያቄው በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት እንደ ጸደቀ በቀጥታ ስራ ላይ እንደሚውል ታውቋል፡፡
ምንጭ፦ የገንዘብ ሚኒስቴር

👍16
#ችሎት
አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ 5 ተከሳሾች በህመም ምክንያት ዛሬ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ።
አሞናል በማለት ፦
- አቶ ስብሐት ነጋ ፣
- አቶ አባዲ ዘሙ፣
- አቶ ዘሚካኤል አንባዬ፣
- ዶ/ር ሙላት ይርጋ እና አቶ ቴድሮስ ሀጓስ ዛሬ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።
የማረሚያ ቤት ተወካይ 5ቱ ተከሳሾች አሞናል በማለታቸው ምክንያት እንዳላመጣቸው አስረድቷል።
ቀሪዎቹ ማለትም ፦
- ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ፣
- አንባሳደር አባይ ወልዱ ፣
- ዶ/ር አብርሐም ተከስተ ፣
- ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ፣
- አንባሳደር አዲስ አለም ባሌማ ፣
- ወ/ሮ ሙሉ ገ/ እግዛብሔርን ጨምሮ 16 ተከሳሾች ግን በችሎት ተገኝተዋል።
16 ቱ ተከሳሾች የቀረቡት በፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ችሎቱ የተከሳሾች የክስ መቃወሚያ ውጤት ለመጠባበቅ እና " ሱር ኮንስትራክሽን " ን ጨምሮ በክሱ የተካተቱ ድርጅቶች መጥሪያ እንዲደርሳቸው የተሰጠውን ትዛዝ ማረጋገጫ ውጤት ለመጠባበቅ ነበር ዛሬ የተሰየመው።
በተጨማሪ በ44 ኛ ተከሳሽ ለምርመራ የተያዘብኝ ሰነዶች ይመለሱልኝ ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ትዛዝ ለመስጠት ነው።
የችሎት ውሎውን ንብቡ : https://telegra.ph/Trial-12-30-2
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

Telegraph
Trial
#ችሎት አቶ ስብሐት ነጋን ጨምሮ 5 ተከሳሾች በህመም ምክንያት ዛሬ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ። አሞናል በማለት አቶ ስብሐት ነጋ ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ አቶ ዘሚካኤል አንባዬ፣ ዶ/ር ሙላት ይርጋ እና አቶ ቴድሮስ ሀጓስ ዛሬ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። የማረሚያ ቤት ተወካይ አምስቱ ተከሳሾች አሞናል በማለታቸው ምክንያት እንዳላመጣቸው አስረድቷል። ቀሪዎቹ ማለትም ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ፣ አንባሳደር አባይ ወልዱ…
👍19❤3
አልሸባብ ?
ሶማሊያ ውስጥ ያለው ውጥረትና በፕሬዜዳንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ መካከል ያለው ቅራኔ ለአልሸባብ የሽብር ቡድን በር እንዳይከፍት ተሰግቷል።
ዛሬ ጥዋት ላይ የ #አልሸባብ ታጣቂዎች ከዋና ከተማይቱ ሞቃዲሾ በስተሰሜን በምትገኝ ከተማ ላይ ጥቃት ሰንዝረው ከተማውንም ለመቆጣጠር ሞክረው እንደነበር ተዘግቧል።
አልሸባብ ጥቃቱን የከፈተው ከሞቃዲሾ 30 ኪ.ሜ ያህል በምትርቀው ስትራቴጂክ ከተማ #ባላድ እንደሆነ የተሰማ ሲሆን በጥቃቱ ሰዎች ተገድለዋል።
እንደ ቪኦኤ ዘገባ ከሆነ ፥ የሶማሊያ ጦር ኃይል በወሰደው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ የሽብር ቡድኑን ባላድን የመያዝ ሙከራውን አክሽፏል።
በአሁን ሰዓት ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በመንግስት እጅ ስር እንዳለችም ገልጿል።
በዛሬው ጥቃት 4 የመንግስት ወታደሮች እንደተገደሉ ቪኦኤ ሲዘግብ የሶማሊያ መንግስት ሚዲያ በበኩሉ በጥቃቱ 9 የአልሸባብ ታጣቂዎች መገደላቸውን እና በአሸባሪዎች በተተኮሰ ሞርታር 5 ንፁሀን ዜጎች መሞታቸውን ዘግቧል።

👍12👎2
#ETHIOPIA #SUDAN
ዛሬ #ኢትዮጵያ ሀገራችን ከጎረቤት ሀገር #ሱዳን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታዋን እያደረገች ትገኛለች።
ይህ ጨዋታ እየተካሄደ የሚገኘው የሁለቱም ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች በአፍሪካ ዋንጫ ለመካፈል ባቀኑባት ካሜሮን ሀገር ነው።
የሀገራችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቀናት በፊት በትልቁ የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ከውድድሩ ቀደም ብሎ ወደ ካሜሮን አቅንቷል።
ቡድናችን ካሜሮን ከደረሰ በኃላ በየዕለት ልምምድ እየሰራ ውድድሩ እስኪጀመር እየተጠባበቀ ይገኛል። ዛሬ አቋሙን የሚፈትሽበት ጨዋታ እያደረገ ነው።
ሀገራችን በተወከለችበት ትልቁ የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር መድረክ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትም ወደ ስፍራው ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ያቀኑ ሲሆን በስፖርት ገፃችን ላይ መረጃዎችን ያካፍላሉ።
የቲክቫህ ስፖርት ገፅ ፦ https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x
@tikvahethsport

👍13🤩1
TIKVAH-ETHIOPIA
" የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ ይመረጣሉ " - የህግ ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ እንደሚመረጡና ሹመታቸውም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደሚጸድቅ የህግ ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ናቸው። በጋዜጣዊ መግለጫው…
#ጠቁሙ
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው 2ኛ ልዩ ስብሰባው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265 /2014 ማጽደቁ ይታወሳል፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 1 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የዕጩ ኮሚሽን አባላትን ከህዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች ና ከሲቪል ማህበራት እንደሚቀበል ተደንግጓል፡፡
በዚህም መሰረት የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቀበያ ጽ/ቤት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተቋቁሟል፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 13 መሰረት ለኮሚሽነርነት የሚያበቁ መሥፈርቶችም፡-
1/ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ፤
2/ ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ የተለያዩ ብሔሮችን፣ ብሔረሰቦችን እና ሕዝቦችን በእኩል ዓይን የሚያይ፤
3/ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ፤
4/ ለአገራዊ መግባባት ጉልህ አስተዋፅዖ ሊያበረክት የሚችል ፤
5/ መልካም ሥነ-ምግባርና ስብዕና ያለው፤
6/ በሕዝብ ዘንድ ዓመኔታ ያለው፣
7/ በከባድ ወንጀል ተከሶ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተላለፈበት ፤
8/ የኮሚሽኑን ሥራ በአግባቡ ለመሥራት የሚያስችል የተሟላ ብቃት ያለው፤
9/ ሙሉ ጊዜውን ለኮሚሽኑ ስራ ለማዋል ፍቃደኛ የሆነ።
የሚሉ ናቸው፡፡
የዕጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ ፡-
• በቀጥታ ስልክ 0111300340 ወይም 9988
• በፋክስ ቁጥር 0111233007
• በኢ-ሜል [email protected] ወይም
• በ [email protected] ወይም
• በአካል በም/ቤቱ መረጃ ማአከል መስጠት ይቻላል።
በቀጣይ ሶስት ቀናት ውስጥ ጠቆማ የሚሰጥበትን ቅጽ www.hopr.gov.et እንደሚጭን የህ/ተ/ምክር ቤት አሳውቋል።

👍19
#LALIBELA
ከፊታችን ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ታሪካዊቷ ከተማ ላሊበላ እለታዊ የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ አሳውቋል።

❤9👍6🤩2👎1
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA #SUDAN ዛሬ #ኢትዮጵያ ሀገራችን ከጎረቤት ሀገር #ሱዳን ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታዋን እያደረገች ትገኛለች። ይህ ጨዋታ እየተካሄደ የሚገኘው የሁለቱም ሀገራት ብሄራዊ ቡድኖች በአፍሪካ ዋንጫ ለመካፈል ባቀኑባት ካሜሮን ሀገር ነው። የሀገራችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከቀናት በፊት በትልቁ የአፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ ከውድድሩ ቀደም ብሎ ወደ ካሜሮን…
#ETHIOPIA
ሀገራችን ኢትዮጵያ በአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሱዳንን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።
አማኑኤል ገብረ ሚካኤል 2 ግቦችን ያስቆጠረ ሲሆን አንዱን ጎል ሽመልስ በቀለ አስቆጥሯል።
የብሄራዊ ቡድናችን ከአፍሪካ ዋንጫ መጀመር አስቀድሞ ካሜሮን በመግባት ለውድድሩ አስፈላጊውን ዝግጅት ሁሉ እያደረገ ይገኛል።
More : @tikvahethsport

👍14❤5🎉5🔥1