TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን በአብለጫ ድምፅ አጽድቋል፡፡ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ በ13 ተቃውሞ እና በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የጸደቀው። @tikvahethiopia
#ETHIOPIA
የፀደቀው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ማሻሻያዎች ተደረገበት ?
የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚ አዋጅ በዛሬው ዕለት በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።
የኮሚሽኑን መሪዎች በመሰየሙ ሂደት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ በሙሉ እጃቸው እንዳይገባ ሆኖ ነው የኮሚሽኑ የማቋቋሚያ አዋጅ የፀደቀው።
አገራዊ መግባባትን ለማምጣት ተከታታይ ምክክሮችን በማዘጋጀት እንዲሰራ ስልጣን የተሰጠውን ኮሚሽን የሚመሩ ኮሚሽነሮችን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መርጠው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው እንዲያሾሙ በረቂቅ አዋጁ ተደንግጎ ነበር፡፡
ይህም የኮሚሽነሮችን #ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባል የሚል ተደጋጋሚ ትችት ሲዘነዘር ቆይቷል፡፡
በዚህም ምክንያት ረቂቅ አዋጁን ሲመረምር የቆየው ቋሚ ኮሚቴ ማሻሻያ እንደተደረገበት ተገልጿል።
በፀደቀው አዋጅ መሰረት እጩ ኮሚሽነሮችን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ከሕዝብ፣ ከፖለቲካ ድርጅቶች እና ከሲቪክ ማህበራት ጥቆማ ይቀበላል ይላል፡፡
ጽኅፈት ቤቱ ጥቆማውን ከሰበሰበ በኋላ 14 የእጩዎች ዝርዝር ለይቶ ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል።
ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ፣ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ እጩ ኮሚሽነሮችን በተመለከተ ውይይት ካደረጉ በኋላ ከ14ቱ 11ዱን መርጠው ለምክር ቤቱ አቅርበው ያፀድቃሉ ተብሏል።
ለኮሚሽኑ ደንብ እንዲያወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በረቂቅ አዋጁ ስልጣን ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም፣ ይህ ተሰርዞ ደንቡን የማውጣት ሥልጣን የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር እንዲሆን መደረጉም ታውቋል።
ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤፍም 102.1 ሬድዮ
@tikvahethiopia

ከኤሊ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በዓል አክብሮ የሚመለስ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከሪካሪ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ። ዛሬ ዓመታዊውን የኤሊ ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ አክብረው ወደ ገረሴ ወረዳ በመመለስ ላይ የነበሩ አንጋሾችን ያሳፈረ ኤፍ ኤስ አር የሕዝብ ማመላለሻ አዉቶቢስ ' ሞርካ ቀበሌ ' ላይ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ሕይወት አልፏል። በአደጋው ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለሕክምና ተልከዋል።…
#Update
ትናንት በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል።
በትላንትና ታህሳስ 19 ዓመታዊውን የቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ አክብረው የሚመለሱ ምዕመናንን አሳፍሮ ወደ ገረሴ ወረዳ በመመለስ ላይ የነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 ደ/ህ 19406 ኤፍ ኤስ አር የሕዝብ ማመላለሻ አዉቶቢስ በማዜ ብሔራዊ ፓርክ አካባቢ ተገልብጦ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉ መግለፁ ይታወሳል።
ዛሬ የጋሞ ዞን ፖሊስ በሰጠው መረጃ የሟቾች ቁጥር 6 የደረሰ ሲሆን ሟቾቹ 3 ሴቶችና 3 ወንዶች ናቸው። 18 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ ይገኛሉ።
ጉዳት የደረሰባቸው ምዕመናን በሰላምበር ፣ ወላይታ እና ሳውላ ሆስፒታሎች በህክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
የአደጋዉ መንስኤ ከወንበር በላይ መጫን እና ጠጥቶ ማሽከርከር መሆኑን የጋሞ ዞን ፖሊስ አሳውቋል።

ዛሬ 3ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን ምክር ቤቱ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
(ውሳኔዎቹ ከላይ ተያይዘዋል - ያንብቡ)
@tikvahethiopoa

#DebreMarkos
በደብረ ማርቆስ ሠርግ፣ ተስካርና መሠል ፕሮግራሞች በግዚያዊነት ታገደ።
ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ሠርግ ፣ ተስካር እና መሠል የድግስ ፕሮግራሞች በግዚያዊነት የታገደ መሆኑን የኮማንድ ፖስት አባል እና የደብረ ማርቆስ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ኮማንደር ባንተአምላክ ካሳሁን ገልጸዋል።
" አሁን ካለንበት ሀገራዊ እና ክልላዊ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር አንገብጋቢ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ችግር አኳያ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በአለበት ሁኔታና ለሐገራቸው ሲሉ መስዋትነትን የሚከፍሉ ወንድሞቻችን እንዲሁም በሚሊየን የሚቆጠር የንበረት ውድመት አኳያ ሰርግ እና ሌሎች ፕሮግራሞችን ማካሄድ ለከፋ ርሀብ እና ችግር እንዳንጋለጥ በማሰብ እንዲሁም ያላስፈላጊ የሀብት ብክነትን ለመከላከል ታስቦ በጊዚያዊነት ሰርግ ፣ ተስካር እና መሠል ፕሮግራሞች ታግዷል " ሲሉ ኮማንደር ባንተአምላክ ካሳሁን አስረድተዋል።
በሌላ በኩል በርካታ ህዝብ ተፈናቅሎ እያለ የተትረፈረፈ ድግስ ደግሶ መዝፈን እና መደለቅ ለሞራልም ፤ ለሐይማኖትም ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ሰርግ ለመሠረግ እና ተያያዥ ፕሮግራሞች ለማድረግ ያሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎች በክልሉ ለተፈናቀሉ እና ለጥምር ሀይሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
ምንአልባት በልዩ ሁኔታ መጋባት ያለባቸው ለኮማንድ ፖስቱ ጥያቄ አቅርበው በማስፈቀድ ጋብቻው ከሰርግ ዝግጅት ውጭ እንዲፈፀም የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።
ክልከላው ተላልፎ ጋብቻም ሆነ ተስካር እንዲወጣ የሚፈጽም እና የሚያስፈፅም የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አስፈፃሚ ግብረሀይሉ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ሁሉም የከተማው ነዋሪ ለተግባራዊነቱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ አሳስበዋል።
ምንጭ፦ የደ/ማርቆስ ከተማ ፖሊስ ፌስቡክ ገፅ

ቪድዮ : ቡጢ የተሰናዘሩት የጆርዳን ፓርላማ አባላት ! የጆርዳን የፓርላማ አባላት በቀጥታ ስርጭት ላይ እየተላለፈ በነበረ ስብሰባ ላይ ክርክራቸው እና የቃላት ምልልሳቸው ወደከፍተኛ ፍጥጫ ተቀይሮ ወደ ድብድብና ቡጢ መሰናዘር ሲገቡ ታይተዋል። ይህም ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። አባላቱ የሁሉንም ዜጎች የእኩልነት መብት በሚያረጋግጥ የሕገ መንግሥቱ ክፍል ላይ የሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች እንዲደረጉ (የሴቶች…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : ድብድብ በኬንያ 🇰🇪 ፓርላማ !
ዛሬ ከሰአት #በኬንያ የፓርላማ አባላት አወዛጋቢ ነው በተባለው የፖለቲካ ፓርቲዎች (ማሻሻያ) ረቂቅ ህግ ላይ ሲያደርጉት የነበረው ጠንከር ያለ ክርክር ተካሮ የፓርላማው አባላት ሲደባደቡ ታይተዋል።
ከሰሞኑን ብቻ ፓርላማ ውስጥ የተከሰቱ መሰል ክስተቶችን ስናጋራችሁ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ዛሬ ጥዋት የጆርንዳን ፓርላማ አባላት እንዲሁም ከቀናት በፊት በጋና የፓርላማ አባላት ክርክራቸው ጦፎ ወደ ድብደብ እና ቡጢ መሰናዘር ሲገቡ የሚታዩበትን ቪድዮ እንዳጋራናችሁ ይታወሳል።
Video Credit : TheStarKenya

" የኢንተርኔት አገልግሎት ለማስጀመር ከጸጥታ አካላት ጋር ንግግር እየተደረገ ነው " - ኢትዮ ቴሌኮም
ኢትዮ ቴሌኮም በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት በተቋረጠባቸው አካባቢዎች ዳግም አገልግሎት ለማስጀመር ከጸጥታ አካላት ጋር ንግግር መጀመሩን አሳውቋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ የኮሙኒኬሽን ኤክስፐርት አቶ መሳይ ለአል ዐይን አማርኛ ክፍል በሰጡት ቃል ፤ የተቋረጠውን አገልግሎት ዳግም ለማስጀመር ንግግር ተጀምሯል ብለዋል።
አቶ መሳይ ፥ አገልግሎት በተቋረጠባቸው አካባቢዎቹ በቅርቡ አገልግሎቱን እንደሚያገኙ ያሳወቁ ሲሆን ትክክለኛውን ቀን ግን ለመናገር እንደማይቻል መግለፃቸውን አል ዓይን በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

#UPDATE😷
የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ ፦
🇮🇹 በጣልያን በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ሲሆን በትላንትናው ዕለት 98,030 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 148 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
🇫🇷 ፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 208,000 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች። በሀገሪቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው።
🇧🇦 ቦሲኒያ #የመጀመሪያውን የኦሚክሮን ልውጥ ቫይረስ ኬዝ ሪፖርት አድርጋለች። 10 ሰዎች በኦሚክሮን መያዛቸው ሲረጋገጥ ምናልባትም ብዙ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ ተብሎ ተሰግቷል።
🏴 የስኮትላንድ ጠ/ሚ ስኮት ሞሪሰን አስቸኳይ ብሄራዊ የካቢኔ ስብሰባ ጠርተዋል። በሀገሪቱ የኮቪድ-19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እተባባሰ ነው ተብሏል።
🇵🇱 ፖላንድ በ4ኛው የኮሮና ቫይረስ ማዕበል እየተፈተነች ሲሆን በ1 ቀን 794 ዜጎቿ እንደሞቱባት የሀገሪቱ ምክትል የጤና ሚኒስትር አሳውቀዋል።
🇪🇸 በስፔን በአንድ ቀን ብቻ 100,760 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ወረርሽኙ ከጀመረ አንስቶ በቀን ከ100,000 በላይ ኬዝ ሲመዘገብ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። ለወረርሽኙ በዚህ ደረጃ መጨመር የኦሚክሮን ዝርያ መስፋፋት አንዱ ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል።
🇪🇹 በኢትዮጵያ ሀገራችን ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ 11,749 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
🇺🇸 CDC በአሜሪካ በሚቀጥሉት 4 ሳምንታት ከ44 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ምክንያት ሊሞቱ እንደሚችሉ ተንብይዋል።
🌍 በዓለም አቀፍ ደረጃ እኤአ ከታህሳስ 22 እስከ ታህሳስ 28 ድረስ ባሉት ቀናት በየዕለቱ በአማካኝ 935,863 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የነበረ ሲሆን በአጠቃላይ 6,550,000 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

#Ethiopia : አጫጭር መረጃዎች ፦
- የዳሸን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ከታህሳስ 12 ጀምሮ አቶ ዱላ መኮንንን የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ ሰይሟል። አቶ ዱላ የሊቀመንበርነቱን ቦታ የተረከቡት በግል ምክንያት ከኃላፊነታቸው በለቀቁት አቶ ነዋይ በየነ ምትክ መሆኑን ዳሸን ባንክ አሳውቆናል።
- በ2 ወር ውስጥ በ 'አይዞን ኢትዮጵያ' በጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሰብስቧል። በውጭ አገራት ከሚኖሩ ከ23 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ነው ገንዘቡ የተሰበሰበው።
- የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከዛሬ ታህሳስ 21 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል።
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ጥር ወር ጀምሮ ወደ በርበራ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል።
- ገቢዎች ሚኒስቴር በ5 ወር በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በመቐለ ገቢዎች ሚኒስቴርና ጉምሩክ ኮምሽን ቅርንጫፎች 1.8 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቢያቅድም ምንም ገቢ እንዳልሰበሰብ፤ በኮምቦልቻ ገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮምሽን ቅርንጫፎች 2.3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 1.9 ቢሊየን ብር ብቻ ለመሰብሰብ እንደተቻለ አሳውቋል። በዚህም ከመቐለ እና ኮምቦልቻ 4 ቅርንጫፎች ይሰበሰባል ተብሎ ከታቀደው 3.3 ቢሊየን ብር ውስጥ 1.9 ቢሊየን ብቻ ሲሰበሰብ ቀሪው 2.3 ቢሊየን ብር ሳይሰበሰብ ቀርቷል።
- በሶማሊ ክልል በጨረቲ ወረዳ ውስጥ የሚኖሩ አርብቶ አደር ወገኖቻችን በአካባቢያቸው በተከሰተ #አስከፊ ድርቅ እና በበሽታ ምክንያት ግመሎቻቸው እና ከብቶቻቸው እየሞቱ መሆኑን በመግለፅ መንግስት ይደርስላቸው ዘንድ ተማፅነዋል። በርካቶች አካባቢያቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል። ውሃና የምግብ ሬሽን በአስቸኳይ ካልደረሰላቸው ከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚወድቁ ለSRTV ተናግረዋል።

#AFAR
የአፋር ክልል የትምህርት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አሊ ጃፓን ፥ " በአፋር ክልል በአሸባሪው ህወህት ምክንያት 65 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል " ሲሉ አሳወቁ።
የቢሮው ሀላፊ ይህን ያሳወቁት ለኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ነው።
አቶ አሊ ፥ በክልሉ በ21 ወረዳዎች ውስጥ የነበሩ 759 የትምህርት ተቋማት ላይ ጉዳት መደረሱንና ከዚህ ወስጥ 65ቱ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ የወደሙ መሆኑን ገልፀዋል።
በተጨማሪ የትምህርት ዘርፍ ሰራተኞችን ሳይጨምር ከ150 ሺህ በላይ በወደሙ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የነበሩ ተማሪዎች ከትምህርታቸው ውጭ እንደሆኑ ተናግረዋል።
እነዚህን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስና የመማር የማስተማሩን ስራ ለመጀመር መላው ኢትዮጵያዊ ከአፋር ክልል ጎን እንዲሆኑ አቶ አሊ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን /ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው /

" ይሄ የምዕራቡ ሀገር ኤምባሲ የሚለው ምንድነው ? የሚለውን ልጠይቅም ጭምር ነው የመጣነው ። " - ዮሃንስ
ዳያስፖራዎች የተደረገላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ይገኛሉ።
ጥሪውን ተቀብለው ወደሀገር እየገቡ ካሉት መካከከል 10 እና 20 ዓመት ከዛም በላይ በሰው ሀገር በስደት የኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል።
ወደሀገር ከገቡ መካከል በኤርፖርት ሆኖ ለብሄራዊ የቴሌቪዥን ቃሉን የሰጠ ዮሃንስ የተባለ ዳያስፖራ ላለፉት 10 ዓመታት ሀገሩን አይቷት እንደማያውቅ ተናግሯል።
ዮሃንስ ፥ " ኢትዮጵያዊነት ምንም የማይቀየር ነው ፤ ካሊፎርኒያ ያለው ህዝብ ተነሳስቶ ኢትዮጵያን ለመርዳት ነው ሀሳቡ፤ በሚሊዮኖች ደረጃ የሚላከውም ሀገራችንን አንድ አድርጎ ለማቆየት ነው፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ አንድ ሆና እንደምትቆይ ምንም ጥያቄ የለውም፤ ጠላቶቿ ይፈርሳሉ እሷ ግን ትቆማለች በዚህ አምንነን ነው ወደሀገራችን የገባነው " ብሏል።
" እስቲ ይሄ ወሬው ምንድነው ? የምዕራቡ ኤምባሲ የሚለው ምንድነው ? የሚለውን ልንጠይቅም ጭምር ነው የመጣነው " ሲልም ገልጿል።
ወደ ሀገር እየገቡ ያሉት ዳያስፖራዎች ባዶ እጃቸውን ሳይሆን በጦርነት ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እንዲሁም ለኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት የተለያዩ አስፈላጊ ድጋፎችን በመያዝም ጭምር ነው።