#Ethiopia
አጫጭር መረጃዎች #1፦
- የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ ጀምሯል፤ ነገር ግን በተሟላ አቅሙ ወደ ስራ አልገባም። አሁን ላይ የድንገተኛ ህክምና ፣ የተኝቶ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው። ሆስፒታሉ የመብራት መቆራረጥ፣ የመድሃኒት እጥረትና የአምቡላንስ ችግር አለበት። የነበረው አንድ አምቡላንስ ለህልውና ዘመቻ ሄዶ እስካሁን ያልተመለሰ ሲሆን የአምቡላንስ አለመኖር በታካሚዎች ላይ ትልቅ ችግር ይፈጥራል ተብሏል። ሆስፒታሉ የጎደሉት እንዲሟሉለት ጥሪ ቀርቧል።
- ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ሳቢያ ከሰሜንና ደቡብ ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደብረብርሃን የቆዩ ወገኖች ወደ መኖሪያ ቀያቸው ሲመለሱ የደ/ብርሃን ህዝብና ሌሎች አካላት ስላደረጉላቸው መስተንግዶ አመስግነዋል። ደ/ብርሃን በጦርነት የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ያስጠለለች ከተማ ስትሆን አብዛኛው ተፈናቃዮች አሁን ወደቀያቸው ተመልሰዋል።
- በሰሜን ኢትዮጵያ የጤና ተቋማት ላይ የደረሰውን ውድመት ተከትሎ ዶ/ር ጥላሁን ጎሹ (Mihret Medical Supply) ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከነትራንስፖርታቸው 4.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎችን፣ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ ቪታሚኖችና አንድ ኮንቴነር ሙሉ መድሀኒቶችን በመርከብ ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል።
- በሰሜን ወሎ ዞን የመቄት ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ላይ በደረሰው ውድመት ምክንያት የረሀብ አደጋ ማንዣበቡን ገልፀዋል። ከመፈናቀል እየተመለሱ ያሉትን ለመደገፍ በወር 1.2 ሚልየን ኲንታል እህል እንደሚያስፈልገው የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ገልፆ ሁኔታው ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እጆቻቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርባል።
#AMC #AmbFitsumArega #VOA
@tikvahethiopia

December 28, 2021
" አገሪቱ ያሉባትን ትላልቅ ተግዳሮቶች ለመፍታት አካታች አገራዊ ምክክሩ አስፈላጊ ነው " - አቶ አደም ፋራህ
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ፥ አገሪቱ ያሉባትን ትላልቅ ተግዳሮቶች ለመፍታት አካታች አገራዊ ምክክር በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ አደም ፥ አካታች አገራዊ ምክክርን አስፈላጊ የሚያደርጉ በርካታ ተግዳሮቶች አሉ ብለዋል።
በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የለም ያሉት ኃላፊው ፥ በህገ መንግስቱ፣ ሰንደቅ ዓላማ፣ አገር ግንባታ ላይ እና በሌሎችም መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የለም ነው ያሉት።
አገሪቱ እስካሁን ከግጭትና ከጦርነት አዙሪት ውስጥ መውጣት እንዳልቻለችና እንደ አገር ዴሞክራሲን ከመትከልና ከማጽናት አኳያ ሰፊ ክፍተት እንዳለ አንስተዋል።
የጋራ ማንነትንና ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን እንደ አገር ማረጋገጥ እንዳልተቻለም ነው አቶ አደም ያመለከቱት።
እነዚህን ትላልቅ ተግዳሮቶች ከመፍታት አኳያ አካታች አገራዊ ምክክር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ተብሎ እንደሚታመን መግለፃቸውን የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) ዘግቧል።

TIKVAH-ETHIOPIA
" ምርጫ - አዎ ✅ ፤ መፈንቅለ መንግስት - አይሆንም ❌ " - የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ሀገሪቱን የመምራት ሃላፊነት ያለው ካቢኔያቸው መሆኑን ተናግሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱ ፀጥታ ኃይል አዛዦች ከፕሬዜዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ሳይሆን ከእሳቸው ትዕዛዝ እንዲቀበሉ አዘዋል። ሮብሌ ፥ ፋርማጆ የወሰዱት እርምጃ " መንግስትን፣…
#Somalia
አሜሪካ የሶማሊያን የሰላም መንገድ በሚያደናቅፉ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅቻለሁ አለች።
ሀገሪቱን ይህን ያለችው ትላንት ሶማሊያን በተመለከተ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ባወጣችው አጭር መግለጫ ነው።
አሜሪካ መሀመድ ሁሴን ሮብሌን ለማገድ የተደረገው ሙከራ በጣም አሳሳቢ ነው ፤ለፈጣን እና ተአማኒ ምርጫ የሚያደርጉትን ጥረት እንደግፋለን ብላለች።
ሁሉም ወገኖች ግጭት ከሚያባብሱ ድርጊቶች እና መግለጫዎች መራቅ እንዳለባቸው አሳስባለች።
ሀገሪቱ ፥ የሶማሊያ መሪዎች ውጥረቱን እንዲያረግቡና ከማንኛውም የግጭት ቀስቃሽ ድርጊት እና ኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡ ጠይቃለች።
አሜሪካ የምርጫውን ሂደት ለማፋጠን እና ለማሻሻል እንዲሁም ምርጫውን በተመለከተ ተአማኒነት ያለው መደምደሚያ ላይ ለመድረስ አስቸኳይ የNCC ስብሰባ ያስፈልጋል ስትልም ገልፃለች።
የአሜሪካን መግለጫ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ሲሆን መግለጫው ለአንድ ወገን ያደላ ፣ በግልፅ በሰው ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባትና የበላይ ሆኖ የመታየ መኩራ ነው ያሉት በርካቶች ሲሆኑ አሜሪካ በሶማሊያ ውስጣዊ ጉዳዮች ከመግባት እንድትቆጠብም ጠይቀዋል።
ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የአሜሪካን አቋም ደግፈው አስተያየት እየሰጡ ያሉ ወገኖችም አሉ።

#ቅዱስ_ገብርኤል • " ምንም የጸጥታ ስጋት አይኖርም " - የኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ • " የሀዋሳ ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ ነው ያለው " - የሀዋሳ ፖሊስ መምሪያ ነገ የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ እና የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አሳውቀዋል። በዓሉ በተለይ በቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ከተለያዩ…
#Update
ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል የእምነቱ ተከታዮች እና ጎብኚዎች በተገኙበት በቁልቢ እና ሀዋሳ በታላቅ ደምቀት በሰላም እየተከበረ ነው።
በንግስ በዓሉ ላይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ይገኛሉ።
በዓሉ ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ በየስፍራው የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች የተቀናጀ የፀጥታ ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
Photo Credit : ሀዋሳ ከተማ ኮሚኒኬሽን እና ኢዜአ

#DStv ...ከተማው
የአንድ ክ/ከተማ አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞች ከአለቆቻቸውና ወደ ቢሮው ከሚመጡት የተለያዩ የከተማው ነዋሪዎች ጋር የሚያሳልፉት ውጥረት የተሞላበትን ውሎና ገጠመኝ የሚያሳይ አዝናኝ ድራማ (ሲትኮም)
ማክሰኞ ከምሽቱ በ1፡30 በድጋሚ ቅዳሜ ከሰዓት 09:00 ሰዓት እንዲሁም እሁድ ከሰዓት 09:30 በአቦል ቻናል ቁጥር 146
#DStvየራሳችን

ፎቶ : ማራቶን ሞተርስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ አስመርቋል።
ማራቶን ሞተር ኢንጂነርሪግ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪካዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪን በመገጣጠም ፈር ቀዳጅ የሆነ ድርጅት ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ የመጀመሪያውን የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያና 2ኛውን ሞዴል ሃዩንዳይ KONA SUV የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አስመርቋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ፣ የድርጅቱ መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መልካሙ አሰፋ እንዲሁም ሌሎችም አካላት ተገኝተው ነበር።
Credit : CAPITAL & ENA

" ዋንጫውን ፤ ወይም በእናተ ላይ ኢንቨስት የተደረገውን ገንዘብ ትመልሳላችሁ " - ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ
ትላንትና የጊኒ ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ሽኝት ተደርጎለታል።
በዚህ የሽኝት ስነስርዓት ላይ ጊኒን እያስተዳደር ያለው የጁንታ መሪ ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ ለቡድኑ አባላት ያስተላለፉት መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል።
ኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ የሀገሪቱን ባንዲራ 🇬🇳 ለቡድኑ ካስረከቡ በኃላ ባስተላለፉት መልዕክት የቡድኑ አባላት ዋንጫውን ይዘው እንዲመጡ ካልሆነ ግን በእነሱ ላይ ኢንቨስት የተደረገውን ገንዘብ እንደሚመልሱ ተናግረዋል።
ኮሎኔሌ ማማዲ ዱምበያ " ዋንጫውን ፤ ወይም በእናተ ላይ ኢንቨስት የተደረገውን ገንዘብ ትመልሳላችሁ / ትተካላችሁ " ነው ያሏቸው ከAvenirguinee እና ከጋዜጠኛ ጁሊየት ባዋህ እንዳገኘነው መረጃ።
በኮሎኔል ማማዲ ዱምበያ የሚመራው ወታደራዊ ኃይል ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴን በመፈንቅለ መንግስት በማስነሳት ስልጣን መቆጣጠሩ ይታወሳል።
በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ለመፋለም የውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት ወደ ካሜሮን እያቀኑ ይገኛሉ።

#Assosa
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በሰሜን ሱዳን ብሉ ናይል ግዛት መካከል የሚደረግ የሰላምና የፀጥታ እንዲሁም የልማት ጉዳዮች ላይየሚደረገው ምክክር ዛሬ በአሶሳ ከተማ ይጀመራል።
የምክክር መድረኩን ተሳታፊዎች የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሰላም፣ በፀጥታ፣ በልማትና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ በሚመክረው መድረክ የሁለቱን አጎራባች ህዝቦች የጋራ ተጠቃሚነትን ይበልጥ ወደ ተሻለ ደረጃ የሚያሻግሩ ጉዳዮች ትኩረት ይደረግባቸዋል ተብሎም እንደሚጠበቅ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።

የሰሞኑ ጉንፋን!
የሰሞኑ ጉንፋን ለየት የሚያረገው ግን ከፍተኛ ትኩሳት እና ጠንከር ያለ ሳል አለው በተጨማሪም እነዝህ ምልክቶች ይታዩበታል፡፡
• ብርድ ብርድ ማለት
• የመገጣጠሚያ ህመም
• የጀርባ ህመም
• የጡንቻ ህመም
• ምግብ ፍላጎት መቀነስ
• ኃይለኛ ራስ ምታት
• ፍዝዝ ማለት
ምክንያቱ ምን ሊሆን ይችላል ?
ጉንፋን ዋና መንስኤዎቹ በትንፋሽ በሳል እና በማስነጠስ የሚተላለፉ ቫይረሶች ናቸው። ለምሳሌ÷ ኮሮና ቫይረስ ፣ራይኖ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ አዴኖ ቫይረስ እና የመሳሰሉት ጉንፋንን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የሰሞኑ ጉንፋን ኮሮና ይሁን አይሁን የሚታወቀው በምርመራ ብቻ ነው። ስለዚህ ምን እናድርግ?
• የመከላከያ መንገዶቹን ይተግብሩ
• ሁሌም የአፍ እና አፍንጫዎን ይሽፍኑ
• የእጅ እና አካል ንክኪ ይቀንሱ
• ሰዉ የሚሰበብበት ቦታ አይገኙ
• ስያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን በክንድዎ/በጨርቅ ይሸፍኑ
• መንግስት በነፃ ያቀረበውን የኮሮና ክትባትን ይውሰዱ
ለልጆች እና ህፃናት የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው?
• ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ ትንሽ ጨው አርጎ አፍንጫቸው ቀዳዳ ዉስጥ 2 ጠብታ ማድረግ በመቀጠልየአፍንጫ ቀዳዳዎችን በመምጠጫ ማጽዳት
• ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት መጠቀም ፣
• ትኩስ ትኩስ ነገሮችን ማጠጣት
• ተጨማሪ ምግቦችን በደንብ መመገብ
• የሕፃኑን ክፍል በደንብ ማፅዳት ማናፈስ
• ቤቱን በውሀ እንፋሎት ማጠን
• ንፍጥ እና ትኩሳት በጣም አስፈላጊ ፈሳሾችን እና ንጥረ ነገሮችን ይዘው ስለሚወጡ ተጨማሪ ፈሳሽ ነገሮችን ማግኘት ይኖርባቸዋል።
ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎችስ የቤት ዉስጥ ሕክምናው ምንድነው ?
• ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ራስን በአንድ ክፍል ማግለል
• ትኩስ ፈሳሽ ነገሮችን ደጋግሞ መውሰድ
• ነጭ ሽንኩርት ማር እና ዝንጅብል መጠቀም
• በቂ እረፍት ማድረግ
• የትኩሳት እና ራስ ምታት ማስታገሻ መውሰድ
• እነዚህን መፍትሄዎ እያረጋችሁ ምንም ለውጥ ከሌለው እና ሳሉ የመባስ ትኩሳቱ የመጨመር ባህሪ ካለው ወይም ትንፋሽ የማጠር ምልክት በህፃንም ሆነ በአዋቂ ላይ ካለ በአፋጣኝ ሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል፡፡
ዶ/ር ፋሲል መንበረ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም
Credit : ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ

#Update ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል የእምነቱ ተከታዮች እና ጎብኚዎች በተገኙበት በቁልቢ እና ሀዋሳ በታላቅ ደምቀት በሰላም እየተከበረ ነው። በንግስ በዓሉ ላይ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ይገኛሉ። በዓሉ ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ በየስፍራው የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች የተቀናጀ የፀጥታ ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው ኃላፊነታቸውን…
የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል እንዴት አለፈ ?
የቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግስ ያለምንም የፀጥታ ችግር በደማቅ ሀይማኖታዊ ስነስርዓት በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን ፖሊስ ሪፖርት አድርጓል።
ለበአለ ንግሱ በሰላም መከበር ምዕመኑ፣ መላው ነዋሪና የፀጥታ ሀይሉ ለነበረው አስተዋፆ እና እገዛ ብሎም ውጤታማ ድርሻ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።
በሌላ በኩል አመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በሐዋሳ በደማቅ ሁኔታ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር ተከብሮ ነው የተጠናቀቀው።
የዛሬው በዓል ከወትሮው በተለየ መልኩ በርካታ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ የእምነቱ ተከታዮች እና ጎብኚዎች የታደሙበት እንደነበር ተገልጿል።
በበዓሉ ለመታደም የመጡ እንግዶች በከተማዋ በሚገኙ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትና የቱሪስት መስህቦች ቆይታቸውን እያደረጉ ይገኛል።
ለዚህ ስኬታማ ሀይማኖታዊ የንግስ በዓል የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ የሲዳማ ክልል እና የሐዋሳ ከተማ የፀጥታ መዋቅር እንዲሁም የቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ የከተማዋ ነዋሪ የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንደቻለ ተገልጿል።
ምንጭ፦ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ፣ ድሬ ፖሊስ እና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር