#AddisAbaba
በግንባታ ላይ የሚገኘው የቦሌ ሚካኤል አደባባይ ተሸጋጋሪ ድልድይ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።
የቦሌ ሚካኤል ቡልቡላ የመንገድ ግንባታ አካል የሆነው ተሸጋጋሪ ድልድይ የግንባታ ስራው በከፊል ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን አሳውቋል።
የፕሮጀክቱ አማካሪ መሀንዲስ የሆኑት ኢንጅነር ምህረት አስፋው እንደገለጹት በዛሬው ዕለት ከሳሪስ አቦ ወደ ቦሌ የሚወስደው የድልድዩ አንድ ክፍል ለትራፊት ክፍት እንደሆነ ገልፀው፣ ይህም በአካባቢው የነበረውን ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
በቀን ከ50 ሺህ በላይ ተሽከርካሪ ያስተናግዳል ተብሎ የሚገመተው ይህ ድልድይ 600 ሜትር ርዝመትና 9.1 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ነው፡፡
ምንጭ፦ የአ/አ መንገዶች ባለሥልጣን
@tikvahethiopia

የወሎ ሰፈር - ኡራኤል የመንገድ ፕሮጀክት ከቀለም ቅብ እና ከእግረኛ መንገድ በስተቀር መጠናቀቁ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከወሎ ሰፈር ኡራኤል ቤተክርስቲያን ሲያስገነባ የቆየውን የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታውን አጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ማድረጉን ዛሬ አሳውቋል።
የመንገድ ፕሮጀክቱ ግንባታ አሁን ላይ ከቀለም ቅብ እና ከእግረኛ መንገድ ግንባታ በስተቀር ሌሎች የአስፓልትና መሰል ስራዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀዋል፡፡
ግንባታውን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በራሱ አቅም ያከናወነው ሲሆን አጠቃላይ 1.4 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 35 ሜትር የጎን ስፋት አለው፡፡
ለግንባታ ስራው ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል፡፡
የዚህ የመንገድ ፕሮጀክት ዲዛይን የብስክሌት መስመርና የመሀል አካፋዩ ላይ በቀለም ተለይቶ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን ያካተተ በመሆኑ ከተለመደው የመንገድ አሰራር የተለየ እንደሚያደርገው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿጻ።
የመንገድ ፕሮጀክቱ ከቦሌ እና ወሎ ሰፈር ለሚነሱ አሽከርካሪዎች መስቀል አደባባይ መሄድ ሳይጠበቃባቸው ወደ ኡራኤልና አትላስ አካባቢዎች በአቋራጭ ለመጓዝ ያስችላቸዋል፡፡
ምንጭ፦ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን

#ቅዱስ_ገብርኤል
የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም (ቤተመንግሥት ቅዱስ ገብርኤል) በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል።
በዓሉን በደማቅ መልኩ ለማክበር የገዳሙ አስተዳደር ጽ/ቤት ከፀጥታ አካላት ከአከባቢው ምዕመናን ጋር ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
ምእመናን ለበዓሉ ሲመጡ መታወቂያ ከእጃቸው ላይ እንዳይለይ መሳሰቢያ ተሰጥቷል።

• " ምንም የጸጥታ ስጋት አይኖርም " - የኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ
• " የሀዋሳ ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ ነው ያለው " - የሀዋሳ ፖሊስ መምሪያ
ነገ የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ እና የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አሳውቀዋል።
በዓሉ በተለይ በቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ በርካታ እንግዶች የሚታደሙበት እንደመሆኑ ያለምንም የጸጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የኦሮሚያ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው እንደ ክልል በቂ ዝግጅት በመደረጉ ምንም የጸጥታ ስጋት አይኖርም ብሏል።
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ በበኩኑ የቅዱስ ገብርኤል በዓል በከፍተኛ ድምቀት በሚከበርባት ሀዋሳ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተጠናቋል ሲል አሳውቋል።
የከተማው ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ መሆኑንም አረጋግጧል።
በአሁኑ ወቅት ኅብረተሰቡ አካባቢውን በመጠበቅ እና መረጃ በመለዋወጥ ትልቅ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
ከዚህ በተጨናሪ በጠ/ሚኒ ዐቢይ አሕመድ ጥሪ ከውጭ አገራት የሚመጡትን እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት መደረጉን ሀዋሳ ፖሊስ አሳውቋል።
የእንግዶችን ሰላም ለማስጠበቅ የጸጥታ ኃይሎች አስተማማኝ ዝግጅት ማድረጋቸው ተጠቁሟል። እንግዶች ምንም ዓይነት የጸጥታ ስጋት ሊኖራቸው አይገባም ተብሏል።
ነጋዴዎች በተለይ ሆቴሎች አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ጠንካራ ቁጥጥር እንደሚደረግ እና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ለእንግዶች መኪና ማቆሚያ እንደተዘጋጀ የሀዋሳ ፖሊስ አሳውቋል።
#Kulubi #Hawassa #EPA

TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የሱዳን ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ የስልጣን መልቀቂያ ለማስገባት የደረሱበትን የውሳኔ ሀሳብ ማጠፋቸው/ማንሳታቸው ተሰምቷል። ከሳዑዲ ጋዜጣ ላይ እንዳነበብነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ የደረሱበትን የውሳኔ ሀሳብ አንስተውታል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ሀሳባቸውን ያነሱት ከሌ/ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ውይይት ካደረጉ በኃላ መሆኑን ጋዜጣው ምንጮቹ እንደነገሩት…
ጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ ስልጣን ሊለቁ ነው ?
የቱርክ መንግስት ዜና ወኪል የሆነው አናዶሉ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን ሊለቁ መሆኑን ዘግቧል።
የዜና ወኪሉ መረጃውን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ዛሬ መስማቱን ገልጿል።
ለሚዲያ ማብራሪያ መስጠት ያልተፈቀደላቸው አንድ ምንጭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዳላ ሀምዶክ የቢሮ ሰራተኞቻቸውን አደራ እንዲያስረክቡ ማዘዛቸውን ፤ ሰራተኞቹም ይህን ከእሁድ ማታ ጀምሮ መተግበር መጀመራቸውን ለአናዱሉ ተናግረዋል።
እንደ ምንጩ ከሆነ ፥ አብደላ ሃምዶክ በሃገሪቱ ስላለው የፖለቲካ ቀውስ ከጦር ሀይሉ አዛዥ አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን እና ምክትላቸው መሀመድ ሃምዳን ዳግሎ ሄሜቲ ጋር ዝግ ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው የስራ መልቀቂያቸውን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ የተገለፀው።
ከሳምንት በፊት አብደላ ሀምዶክ ሥልጣን እንደሚለቁ ከውሳኔ ላይ መድረሳቸው በኃላም ከአልቡርሃን ጋር ውይይት አድርገው ውሳኔያቸውን ማጠፋቸው መዘገቡ አይዘነጋም።
ጠ/ሚር አብደላ ሀምዶክ ውሳኔያቸውን ማጠፋቸውን የሚገልፀው መረጃ በወጣበት ዕለት አሜሪካ ከጠ/ሚ አብደላ ሀምዶክ እና ከአል ቡርሃን ጋር ውይይት ማድረጓ ፤ የሱዳን መሪዎች የሱዳንን ህዝብ የነጻነት ፣ የሰላም እና የፍትህ ምኞት ለማሳካት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ማበረታቷን እንደምትቀጥል መግለጿ ይታወሳል።
በሱዳን ጥቅምት ወር ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የተነሳው የዜጎች ተቃውሞ አሁንም ድረስ ያልበረደ ሲሆን በሀገሪቱ መሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እየደረሰ ይገኛል።

አጫጭር መረጃዎች ፦
#Amhara, #Gashena
ጋሸና ከተማ ተቋርጦባት የቆየውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ማግኛቷን ተገልጿል። በአካባቢው ያሉ ሌሎች ከተሞችን የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር ጥገና እየተካሄደ ሲሆን በነገው እለት ፋላቂት፣ ገረገራ፣ ኮን እና በአካባቢው ያሉ ከተሞች የተቋረጠባቸውን ኃይል መልሰው ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#Afar
በአፋር በክልል በህወሓት ወረራ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ የመንግስት ስራ ከነገ ጀምሮ እንደሚጀመር የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
#Amhara
በአማራ ክልል በህልውና ዘመቻው ምክንያት ለአንድ ወር በላይ በከፊል ተዘግተው የቆዩት የአማራ ክልል ፍ/ቤቶች (ከጥቂቶቹ በስተቀር) ዛሬ መደበኛ ስራቸውን ጀምረዋል።
#AddisAbaba
በአ/አ ህገ ወጥ መሬት ወረራ በተሳተፉ 88 አመራሮች እና ሰራተኞች ላይ ፓለቲካዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአ/አ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል። ከ26 ሺ ካሬ ሜትር በላይ ስፋት ያላቸውና በህገ ወጥ የመሬት ወረራ የተያዙ 671 ይዞታዎች ካርታቸው እንዲመክን ተደርጎ ወደ መሬት ባንክ መመለሳቸው ሪፖርት ተደርጓል።
#DireDawa
በድሬዳዋ ኤርፖርት የጦር መሳሪያ ፍንዳታ ተከሰተ ተብሎ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተላለፈው መረጃ ሐሰት መሆኑ የድሬዳዋ ሲቪል አቪየሺን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አሳውቋል። ትላንት ከቀኑ 10:50 ላይ የአውሮፕላኑን አቅጣጫና የርቀት መለኪያ፣ የኃይል መቆጣጠሪያና የመገናኛ መሳሪያ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል መጨመር (high voltage) ምክንያት በተከሰተ ቃጠሎና ፍንዳታ የኃይል መቆጣጠሪያ ስርዓቱ ላይ አደጋ ደርሷል። በኃላ ችግሩን በማስተካከል ዛሬ ጥዋት 1፡00 ሰዓት ጀምሮ የአውሮፕላን በረራ እንዲካሄድ ተደርጓል።

#ALERT🚨
የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 6,262 የላብራቶሪ ምርመራ 1,864 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ6 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።
210 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Somalia አሜሪካ የሶማሊያ መሪዎች በ #ሞቃዲሾ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ፣ ከግጭት ቀስቃሽ ድርጊቶች እንዲታቀቡ እና ሁከትን ለማስወገድ እርምጃዎችን እንዲወስዱ አጥብቃ አሳስባለች። ሀገሪቱ ማሳሰቢያውን ያወጣችው በሶማሊያ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል ነው። @tikvahethiopia
" ምርጫ - አዎ ✅ ፤ መፈንቅለ መንግስት - አይሆንም ❌ " - የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ
የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ሀገሪቱን የመምራት ሃላፊነት ያለው ካቢኔያቸው መሆኑን ተናግሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱ ፀጥታ ኃይል አዛዦች ከፕሬዜዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ሳይሆን ከእሳቸው ትዕዛዝ እንዲቀበሉ አዘዋል።
ሮብሌ ፥ ፋርማጆ የወሰዱት እርምጃ " መንግስትን፣ ህገ መንግስትን እና ህጎችን ለመናድ የተደረገ ግልፅ ሙከራ ነው " ብለውታል።
" ምርጫ - አዎ! ይቻላል፤ መፈንቅለ መንግስት ግን አይሆንም ! አይቻልም " ሲሉም ተናግረዋል።
ፕሬዘዳንት መሀመድ ፋርማጆ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመሬት ወረራ ጋር በተያያዘ የሙስና ወንጀል ምርመራ ላይ ጣልቃ ገብተዋል በሚል ከስልጣናቸው እንዳገዷቸው ይታወቃል።
በመሪዎቹ መካከል ያለው አለመግባባት በሀገሪቱ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
#ቴሌግራም
በተለያዩ የዓለም ሀገራት ሚገኙ የቴሌግራም መተግበሪያ ተጠቃሚዎች በአገልግሎቱ ላይ ችግር እንዳጋጠማቸው በ " ዳውን ዲቴክተር " በኩል በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
አንዳንዶች ሙሉ በመሉ አገልግሎት መቋረጥ ፣ አንዳንዶች ፎቶ እና ቪድዮ አለመላክ፣ አንዳንዶች የሚላኩላቸውን መልዕክቶች በአግባቡ አለመድረስ ፣ የአገልግሎት ፍጥነት መቀነስ የመሳሰሉትን ሪፖርት እያደረጉ ናቸው።
የአገልግሎት ፍጥነት መቀነስ ባለፉት ቀናትም ያጋጠማቸው ችግር መሆኑን ሪፖርት ያደረጉ አሉ።
እስካሁን ድረስ ድርጅቱ በተገልጋዮች በኩል ስለሚቀርቡት ችግሮች ምላሽ አልሰጠም።
ውድ የቲክቫህ አባል እርሶ ባሉበት ሀገር ከላይ ከተጠቀሳት መካከል ያጋጠሞት ችግር አለ ?
✅ አዎ ! አለ
❌ የለም

" ሁሉም ነገር ወደነበረበት ተመልሷል " - ቴሌግራም
ቴሌግራም ከአገልግሎት መቆራረጥ ጋር በተያያዘ በተገልጋዮች ሲቀርቡ ለነበሩ አስተያየቶች ምላሽ ሰጥቷል።
ቴሌግራም " አንዳንድ ተጠቃሚዎች የግንኙነት ችግሮች አጋጥሟቸው ይሆናል ነገር ግን ሁሉም ነገር ወደነበረበት ተመልሷል " ብሏል። ለተፈጠረው ሁኔታም ይቅርታ ጠይቋል።
ድርጅቱ የተፈጠረውን ችግር በዝርዝር ባያስረዳም የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር ነገር ግን ሁሉንም ነገር ማስተካከል መቻሉን ገልጿል።
ዛሬ ምሽት በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች አንዳንዶቹ የሙሉ አገልግሎት መቋረጥ፣ አንዳንዶች ፎቶና ቪድዮ ለመላክ መቸገር፣ አንዳንዶች በፍጥነት መልዕክት አለመድረስ እንዲሁም የፍጥነት መቀነስ የመሳሰሉ ችግሮች እንዳጋጠሟቸው ሪፖርት ሲያደርጉ ነበር።

#UPDATE
የኮቪድ-19 ቀውስ ዓለም አቀፍ መረጃ፦
🇴🇲 ኦማን በመንግስት ሆነ በግል ዘርፍ ያሉ ሰራተኞች ሙሉ በሙሉ መከተባቸውን የሚያረጋግጥ የክትባት ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው ወደስራ ቦታቸው እንዲገቡ እንደማይፈቀድ አሳውቃለች።
🇫🇷 ፈረንሳይ በአዲስ አመት ዋዜማ ጥብቅ እርምጃዎችን እንደምትወስድ ነገር ግን የሰዓት እላፊ ገደብ እንደማትጥል አሳውቃለች። በሚቀጥሉት 3 ሳምንታት ሁሉም ህዝባዊ መሰባሰቦች ለቤት ውስጥ ዝግጅቶች በ2 ሺ እና ከቤት ውጭ ደግሞ በ5 ሺ ሰዎች እንደሚገደቡ እንደሚደረግ ታውቋል።
🇮🇹 በጣልያን ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል። ትላንት 142 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ እሁድ 81 ሰዎች መሞታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
🇩🇰 ዴንማርክ ከፍተኛ የኮቪድ-19 ኬዝ አስመዝግባለች። ባለፉት 24 ሰዓት 16,164 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ወረርሽኙ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ15ሺ ሲሻገር ይህ የመጀመሪያ ነው።
🏴 እንግሊዝ ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ተጨማሪ ገደቦች እንደማትጥል ቦሪስ ጆንሰን አሳውቀዋል። የምሽት ክለቦችና ሰዎች በብዛት የሚገኙባቸው ዝግጅቶች ይቀጥላሉ የተባለ ሲሆን ሁሉም ሰው ግን ተጋላጭ የሆኑትን ከማግኘቱ በፊት ሊመረመርና ማስክ ማድረግን ጨምሮ ሌሎች ጥንቃቄዎች ሊያደርግ ይገባል ተብሏል።
🇬🇷 ግሪክ በሀገሯን እየጨመረ የመጣውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመግታት ገደቦችን ጥላለች። በሱፐር ማርኬቶች፣ በህዝብ ትራንስፖርት፣ በመመገቢያ ቦታዎች ማስክ ማድረግ ግዴታ ነው ተብሏል። ባር እና ሬስቶራንቶች እኩለ ሌሊት ላይ መዘጋት አለባቸው የተባለ ሲሆን በመዝናኛ ስፍራዎች ላይ የሚቆሙ ደንበኞች እንደማይፈቀድና በ1 ጠረጴዛ ከፍተኛው የ6 ሰዎች ገደብ መሆኑ ተገልጿል።

#Ethiopia
አጫጭር መረጃዎች #1፦
- የደብረሲና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ ጀምሯል፤ ነገር ግን በተሟላ አቅሙ ወደ ስራ አልገባም። አሁን ላይ የድንገተኛ ህክምና ፣ የተኝቶ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው። ሆስፒታሉ የመብራት መቆራረጥ፣ የመድሃኒት እጥረትና የአምቡላንስ ችግር አለበት። የነበረው አንድ አምቡላንስ ለህልውና ዘመቻ ሄዶ እስካሁን ያልተመለሰ ሲሆን የአምቡላንስ አለመኖር በታካሚዎች ላይ ትልቅ ችግር ይፈጥራል ተብሏል። ሆስፒታሉ የጎደሉት እንዲሟሉለት ጥሪ ቀርቧል።
- ህወሓት በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ሳቢያ ከሰሜንና ደቡብ ወሎ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደብረብርሃን የቆዩ ወገኖች ወደ መኖሪያ ቀያቸው ሲመለሱ የደ/ብርሃን ህዝብና ሌሎች አካላት ስላደረጉላቸው መስተንግዶ አመስግነዋል። ደ/ብርሃን በጦርነት የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ያስጠለለች ከተማ ስትሆን አብዛኛው ተፈናቃዮች አሁን ወደቀያቸው ተመልሰዋል።
- በሰሜን ኢትዮጵያ የጤና ተቋማት ላይ የደረሰውን ውድመት ተከትሎ ዶ/ር ጥላሁን ጎሹ (Mihret Medical Supply) ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከነትራንስፖርታቸው 4.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎችን፣ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ ቪታሚኖችና አንድ ኮንቴነር ሙሉ መድሀኒቶችን በመርከብ ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል።
- በሰሜን ወሎ ዞን የመቄት ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ላይ በደረሰው ውድመት ምክንያት የረሀብ አደጋ ማንዣበቡን ገልፀዋል። ከመፈናቀል እየተመለሱ ያሉትን ለመደገፍ በወር 1.2 ሚልየን ኲንታል እህል እንደሚያስፈልገው የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ገልፆ ሁኔታው ከአቅሙ በላይ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እጆቻቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ አቅርባል።
#AMC #AmbFitsumArega #VOA

" አገሪቱ ያሉባትን ትላልቅ ተግዳሮቶች ለመፍታት አካታች አገራዊ ምክክሩ አስፈላጊ ነው " - አቶ አደም ፋራህ
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ፥ አገሪቱ ያሉባትን ትላልቅ ተግዳሮቶች ለመፍታት አካታች አገራዊ ምክክር በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ አደም ፥ አካታች አገራዊ ምክክርን አስፈላጊ የሚያደርጉ በርካታ ተግዳሮቶች አሉ ብለዋል።
በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የለም ያሉት ኃላፊው ፥ በህገ መንግስቱ፣ ሰንደቅ ዓላማ፣ አገር ግንባታ ላይ እና በሌሎችም መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የለም ነው ያሉት።
አገሪቱ እስካሁን ከግጭትና ከጦርነት አዙሪት ውስጥ መውጣት እንዳልቻለችና እንደ አገር ዴሞክራሲን ከመትከልና ከማጽናት አኳያ ሰፊ ክፍተት እንዳለ አንስተዋል።
የጋራ ማንነትንና ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን እንደ አገር ማረጋገጥ እንዳልተቻለም ነው አቶ አደም ያመለከቱት።
እነዚህን ትላልቅ ተግዳሮቶች ከመፍታት አኳያ አካታች አገራዊ ምክክር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ተብሎ እንደሚታመን መግለፃቸውን የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ኦቢኤን) ዘግቧል።

" ምርጫ - አዎ ✅ ፤ መፈንቅለ መንግስት - አይሆንም ❌ " - የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሁሴን ሮብሌ ሀገሪቱን የመምራት ሃላፊነት ያለው ካቢኔያቸው መሆኑን ተናግሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱ ፀጥታ ኃይል አዛዦች ከፕሬዜዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፈርማጆ ሳይሆን ከእሳቸው ትዕዛዝ እንዲቀበሉ አዘዋል። ሮብሌ ፥ ፋርማጆ የወሰዱት እርምጃ " መንግስትን፣…
#Somalia
አሜሪካ የሶማሊያን የሰላም መንገድ በሚያደናቅፉ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅቻለሁ አለች።
ሀገሪቱን ይህን ያለችው ትላንት ሶማሊያን በተመለከተ በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል ባወጣችው አጭር መግለጫ ነው።
አሜሪካ መሀመድ ሁሴን ሮብሌን ለማገድ የተደረገው ሙከራ በጣም አሳሳቢ ነው ፤ለፈጣን እና ተአማኒ ምርጫ የሚያደርጉትን ጥረት እንደግፋለን ብላለች።
ሁሉም ወገኖች ግጭት ከሚያባብሱ ድርጊቶች እና መግለጫዎች መራቅ እንዳለባቸው አሳስባለች።
ሀገሪቱ ፥ የሶማሊያ መሪዎች ውጥረቱን እንዲያረግቡና ከማንኛውም የግጭት ቀስቃሽ ድርጊት እና ኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡ ጠይቃለች።
አሜሪካ የምርጫውን ሂደት ለማፋጠን እና ለማሻሻል እንዲሁም ምርጫውን በተመለከተ ተአማኒነት ያለው መደምደሚያ ላይ ለመድረስ አስቸኳይ የNCC ስብሰባ ያስፈልጋል ስትልም ገልፃለች።
የአሜሪካን መግለጫ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ሲሆን መግለጫው ለአንድ ወገን ያደላ ፣ በግልፅ በሰው ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የመግባትና የበላይ ሆኖ የመታየ መኩራ ነው ያሉት በርካቶች ሲሆኑ አሜሪካ በሶማሊያ ውስጣዊ ጉዳዮች ከመግባት እንድትቆጠብም ጠይቀዋል።
ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ የአሜሪካን አቋም ደግፈው አስተያየት እየሰጡ ያሉ ወገኖችም አሉ።